Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Monday, 28 May 2012

ትናንት በፒያሳ አትክልት ተራ ነጋዴዎች ከፖሊሶች ጋር ተጋጩ - በግጭቱ ነጋዴዎች፣ ገዢዎችና ፖሊሶች ተጎድተዋል



በአራዳ ክፍለ ከተማ በአዲሱ ቀበሌ 02 በተለምዶ ‹‹ፒያሳ አትክልት ተራ›› ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ትናንት በአከራይና ተከራይ ውል ምክንያት
በሻጮችና በፖሊሶች መካከል በተፈጠረ አለመግባባትና ግጭት ሳቢያ ሰዎች መታሰራቸውንና መጐዳታቸውን ምንጮች ለፍትሕ ገለፁ። ትናንት ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት ገደማ ላይ የቀበሌው መስተዳድሮች ፖሊሶችን ይዘው በስፍራው በመምጣት በመደባቸው ላይ ይሰሩ ከነበሩት አትክልት ሻጮች መካከል ቁጥራቸው 15 ያህል የሚገመቱትን ‹‹ቦታችሁን ለቃችሁ ውጡ›› የሚል ትእዛዝ እንዳቀረቡላቸው ምንጮች ለፍትሕ አስረድተዋል። ‹‹መንግስት ከወራቶች በፊት አውጥቶት በነበረው የአከራይ ተከራይ ውል ምክንያት ለሰባት ወራት ያህል ከአከራዮች ጋር ውል አቋርጠን ነበር። ቀበሌውም ‹በእናንተ ምክንያት ውሳኔ እስኪሰጥ ድረስ ለአከራዮች ምንም እንዳትከፍሉ› የሚል ሀሳብ ሰጥቶን ነበር›› የሚሉት እነዚህ ሻጮች ‹‹የቀበሌው መስተዳድር ኃላፊነት ወስዶ በሕጋዊ መንገድ ሕጋዊ ወረቀት የሚሰጠንና የሚረከበን ከሆነ እንለቃለን›› ማለታቸውን ምንጮች ይናገራሉ። በወቅቱ የቀበሌው መስተዳድር ‹‹መጀመሪያ እዚህ ስትገቡ ወረቀት ማን ሰጣችሁ? ለእናንተ ወረቀት አያስፈልጋችሁም›› ካላቸው በኋላ በመሀል ፖሊሶች አንዱን አትክልት ሻጭ በጉልበት ጎትተው መደብደብ እንደጀመሩ የዓይን እማኞች ለፍትሕ ተናግረዋል። ከዚያም ሰኢድ ሹመካ የተባለውን ልጅ ፖሊሶች ጎትተው ሲደበደቡት በስፍራው የነበረ ሕዝብ እንደጮኸባቸውና ከፖሊሶች ጋርም ሻጮች በዱላ ወደ መደባደብ እንዳመሩ እነኚህ የዓይን እማኞች ገልፀዋል።
ሰኢድም ‹‹ወደ ፖሊስ ጣቢያ አልሄድም›› በማለቱ ፖሊሶች በጋራ ጐትተው እየደበደቡት ቀበቶውን ፈትተው ሁለት እጆቹን በካቴና በማሰር የፖሊስ
መኪና ላይ እንደጫኑት ምንጮች አስረድተዋል። በዚህ ወቅትም በአካባቢ የሚገኘው የአፍሪካ አንድነት ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች በጩኸት አካባቢውን መረበሻቸውን የፍትሕ እማኞች ተናግረዋል። ከረፋዱ 5፡30 ሰዓት የጀመረው ረብሻ ከቀኑ 7፡30 ገደማ ማቆሙን የሚገልፁት ምንጮች ሶስት አትክልት ሻጮች፣ የተወሰኑ ገበያተኞችና ፖሊሶች ላይ ጉዳት መድረሱን፣ እንዲሁም 15 ያህል ሰዎች በአቅራቢያው በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸውን አስረድተዋል። ፍትህ ጋዜጣም ፒያሳ አካባቢ የማህበረሰብ አቀፍ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ የሆኑትን ኮማንደር መስፍን አያሌው ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጡ ጥያቄ አቅርባ ነበር። ሆኖም ኮማንደሩ የአራዳ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ የሆኑትን ኮሚሽነር እሸቱ አበበን መረጃ ለማግኘት ማስፈቀድ እንደሚኖርብን በመጥቀስ ምላሽ ሰጥተውናል፡፡ ኮሚሽነር እሸቱን ስለጉዳዩ በስልክ ካነጋገርናቸው በኋላ ‹‹ፖሊስ በአከራይ ተከራይ መመሪያ መሰረት የተወሰነውን ውሳኔ ፈፅሟል፡፡… ብለውናል።

Sunday, 27 May 2012

Tension within TPLF inner circle is mounting-Meles redculed for nepotism



Tension within TPLF inner circle is mounting-Meles redculed for nepotism











There has been a spreading whisper among TPLF big wigs about the recent tension within TPLF central committee members. In their informal meeting in Meles’ zenawi’s office to assess the rising protests by Ethiopian Moslems and other segments of the society, few members of the TPLF political bureau members were irritated by Meles' recent remarks in regard to the mounting corruption within his government. Meles has been calling people within the government as "thieves in the government” and he blamed them as the main elements that are taking the corruption to stratospheric level. However, few members of the political bureau led by Abay Tsehaye voiced their concern that nepotism and corruption started from the top-citing Meles' nomination of his wife to lead the front's business empire and also coerce members to elect Azeb to be the sole female member of TPLF’s political bureau member. Sources said Abay told Meles that “ Ye-Asa Gematu Ke Chenqlatu” and Meles got very infuriated by Abay’s remarks and attempted to respond in kind by saying that everybody is riding on his back and without his diplomatic skills TPLF would cease to lead the country and all of its leaders would fall prey to “Amahra’s sword”. It is also now becoming an open secret that there is a rising tension between the TPLF generals and “civilian” leaders in the government-the main reason for the tension is that the generals thinks that they have been short changed in sharing spoils of TPLF victory over Ethiopia for the last 20 years. Many members of TPLF political bureau are believed that they are fleeing their capital to foreign banks given the uncertain future of TPLF in Ethiopia’s political landscape. The coming couple years will determine the fate of TPLF as we know it.

የአርቲስት ሐመልማል አባተ ቪላ በእሳት ቃጠሎ ወደመ

አዲስ አበባ- በኢትዮ-ሳውዲው ባለሀብት ሼክ መሀመድ አላሙዲን የገንዘብ ድጋፍ እንደተገነባ የሚነገርለትና በመካኒሳ መንገድ አቦ ተብሎ በሚታወቀው አካባቢ የሚገኘው የአርቲስት ሐመልማል አባተ ቪላ ቤት ግንቦት 13 ቀን 2004 ዓ.ም. በእሳት ቃጠሎ የወደመ መሆኑ ታወቀ፡፡ ቃጠሎው የደረሰው ከሁለት ወራት በላይ ሲያጋጥማት በነበረው ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል መዋዠቅ መሆኑንና እንዲስተካከል ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን ስታመለክት ብትቆይም፣ መፍትሔ የሚሰጣት በመጥፋቱ መሆኑን ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡
አርቲስት ሐመልማል አባተ
አርቲስቷ ለጋዜጣው እንደገለጸችው፣ በቤቱ መቃጠል እጅግ አስፈላጊዋ የነበሩ ንብረቶችና መተኪያ የሌላቸው ሰነዶች ወድመውባታል፡፡ ‹‹እንኳን የሰው ሕይወት አልጠፋ፤›› በማለት መናገሯንም ሪፖርተር ጨምሮ ዘግቧል፡፡
ለኮርፖሬሽኑ ከሁለት ወራት በላይ ደጋግማ ብታመለክትም ምንም መፍትሔ ማጣቷን ለጋዜጣው የገለጸችው አርቲስቷ፣ ቤቱ በራሱ ጊዜ በመጋል የቧንቧ ውኃ ሳይቀር እያፈላ ሲያስቸግራት ቆይቶ ድንገት በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ሊነድ መቻሉን አስታውሳ፣ ቤቱ በእሳት መያያዙ የማያስገርምና ቀድሞም ቢሆን መቃጠሉ እንደማይቀር በስጋት ይጠበቅ እንደነበር ለጋዜጣው ገልጻለች፡፡
ኮርፖሬሽኑ ከደንበኞቹ የሚፈልገውን እንደሚያገኘው ሁሉ በምላሹ ደንበኞቹን ለመርዳት አለመቻሉና ለአደጋ መንስዔ የሆኑ አጋጣሚዎችን እንዲያስተካክል ጥሪ ሲደረግለት ዝምታን መምረጡ እንዳሳዘናት ተናግራለች፡፡
በ500 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው ቪላ በእሳት ሲያያዝ ጎረቤቶችና የአካባቢ ሰዎች ከእሳት አደጋ መከላከያ ድርጅት ጋር በመሆን ሊያጠፉት ሞክረዋል፡፡ በኤሌክትሪክ ኃይል ምክንያት የተነሳውን ቃጠሎ ከመስመር አለያይተው ለማጥፋት የሞከሩት የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች ሠራተኞች፣ የኤሌክትሪክ መስመሩን ቆርጠናል ባሉበት አፍታ ከባድ እሳት መልሶ መንበልበሉ እንዳደናገጣቸው በመግለጽ ክስተቱን ታስታውሳለች፡፡ በዚህም ሳቢያ ቪላው ሙሉ ለሙሉ ከጥቅም ውጪ ሊሆን ችሏል ብላለች፡፡
በአርቲስቷ ቤት ላይ የደረሰውን ቃጠሎ በሚመለከት ሪፖርተር ጋዜጣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ምስክር ነጋሽን አነጋግሯል፤ ‹‹ቃጠሎ መድረሱን የሰማነው ቆይቶ ነው፡፡ አደጋው የደረሰው በኮርፖሬሽኑ ስህተት መሆን አለመሆኑን በማጣራት ላይ ነን፡፡ አርቲስቷ ቃጠሎ በደረሰ በ24 ሰዓታት ውስጥ አመልክታ ከሆነና ችግሩ የተከሰተው በኮርፖሬሽኑ ስህተት መሆኑ ከተረጋገጠ ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት ካሳ ይከፈላታል፤›› ማለታቸውን ሪፖርተር ጨምሮ ዘግቧል፡፡

መልእክተ ፍትህ-ለኢህአዴግ

ከሁለት ቀን በኋላ ኢህአዴግ ስልጣን የያዘበት 21ኛ አመት የግንቦት ሃያ በዓል ይከበራል። እናም በአለፉት 21 አመታት በሀገሪቱ የታዩ ለውጦች እንዳሉ ሆነው ዋና ዋና የሚባሉ ጉዳዮች ላይ ግን የነበሩ ተስፋዎች ከመምከንም አልፈው ፍፁም እየጠፉ በመሆናቸው በዚህ ርዕስ አንቀፅ ለኢህአዴግ መልእክት ማስተላለፍ አስፈላጊ ሆኖ አግኝተነዋል።
1ኛ የፕሬስ ነፃነት
በየትኛውም ሀገር አስፈላጊ እና ወሳኝ ከሚባሉት የሚመደበው አንዱ የፕሬስ ህልውና ነው። የፕሬስ አስፈላጊነት ከሕግ አውጭው፣ ከሕግ ተርጓሚው እና ከሕግ አስፈፃሚው ቀጥሎ እንደ አራተኛ የመንግስት አካል ተደርጎ እስከመወሰድ ይደርሳል። ይሁንና ኢህአዴግ የፕሬሱን ህልውና በተሻለ ደረጃ እንዲኖር የፈቀደው ላለፉት አስራ አምስት አመታት ብቻ ነው። ምክንያቱም ከምርጫ 97 በኋላ በርካታ የግል ጋዜጦች እና መጽሔቶች ከመዘጋታቸውም ባሻገር በመቶዎች የሚቆጠሩ
ጋዜጠኞች ለስደት ተዳርገዋል። ከዚህም በኋላ ቢሆን ወደ ህትመት የመጡት አዳዲስ ጋዜጦች ለህልውናቸው አደገኛ በሆኑት የፕሬስ እና የፀረ ሽብር አዋጆች መዳፍ ስር እንዲወድቁ ተደርገዋል። ይህንንም ተከትሎ አዲስ ነገር እና አውራምባ ታይምስ የተባሉ ጋዜጦች የመዘጋት ዕጣ ሲገጥማቸው ጋዜጠኞቹም የነፍስ አውጭኝ ሽሽት እንዲያደርጉ ተገድደዋል። የተቀሩት ጥቂት ጋዜጦች ደግሞ በሚታይ እና በማይታይ መንግስታዊ ጫና ውስጥ ሆነው እንዲሰሩ ለመደረጋቸው ፍትህ ያለችበት ወቅታዊ ሁኔታ ዋነኛ ምስክር ነው።
2ኛ በሀገሪቱ የነበረው ደካማ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ከ19 አመት በኋላ ሙሉ በሙሉ እንዲጠፋ ተደርጓል። እናም ሀገሪቱ ራሱን አውራ ፓርቲ ብሎ በሚጠራ በአንድ ጉልበተኛ ፓርቲ እና በአንድ ሃሳብ ስር ወድቃለች። እናም ከገዢው ፓርቲ አካሄድ አንፃር የፖለቲካው ምህዳር መጥበቡ ሰላማዊ ትግሉን ይበልጥ አቀጭጮታል።
3ኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሀገር በቀል ድርጅቶችን ጨምሮ በርካታ አለም አቀፍ ድርጅቶች ሲወተውቱ እና ሲመክሩ ቢቆዩም አንዳች ለውጥ ሳይታይ የዘንድሮ ግንቦት 20 ላይ ደርሰናል።
4ኛ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት መጎልበትም ሆነ ለሁለንተናዊ የሀገር እድገት የማይተካ ሚና እንዳላቸው የሚታወቀው የሲቪል ማህበረሰብ /መያድ/ ተቋማት በፓርቲው የአፈና አዋጅ የተነሳ የሚረባ እንቅስቃሴ ማድረግ ተስኗቸዋል። ቁጥራቸውም ሆነ ተቋማዊ አቋማቸውም በእጅጉ አሽቆልቁሏል።
5ኛ ኢህአዴግ ዘላቂ ሰላም አስፍኛለሁ ቢልም በሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ቁጥራቸው የበዛ ብሄር ተኮር ግጭቶች እየተባባሱ መጥተዋል።
6ኛ ኢትዮጵያን እንደሚመራ ፓርቲ የኢህአዴግ ውስጣዊ የኃይል መስተጋብር ወሳኝ ከመሆኑ አንጻር፣ የአመራሩን የመተካካት ሂደት ተከትሎ አደገኛ ሁኔታዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ እየተነገረ ነው። ለሃያ አመታት ሀገሪቱን በብቸኝነት የመራ ፓርቲ ለመፈራረስ እየቀረበ መምጣቱ መንግስታዊ ስርዓቱ ላይ የሚያደርሰውን አደጋ ከፍተኛ ያደርገዋል።
7ኛ ባለፉት ሃያ አንድ ዓመታት ዴሞክራሲያዊ ስርዓት በሚገባ ባለመተግበሩ የማዕከላዊ መንግስቱን ህልውና ጥያቄ ውስጥ የሚከቱ እንቅስቃሴዎች በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች እየተሞከሩ ነው። ከዚህ በተጨማሪ የድህነቱ መባባስ እና ስርዓቱ መንግስታዊ ሀላፊነቱን ያለመወጣቱ ሀገሪቱን ወደ ክስመት እያመራት ነው።
8ኛ.ከውጭ ግንኙነት ፖሊሲ አንፃር ያለፉትን አመታት በተለያየ መልኩ የተሳኩ ናቸው ለማለት አያስደፍርም። መንግስት በውጭ ግንኙነት ፖሊሲና ስትራቴጂ ላይ እስከዛሬ የተጓዘባቸው መንገዶች በብዙ መልኩ ወጥነት የጐደላቸው ከመሆናቸውም በተጨማሪ የወደፊቷን ኢትዮጵያ መልክ በተሻለ መልኩ የማየት እድል አለው ብለን ደፍረን ለመናገር አንችልም። ለዚህ ማሳያ የሚሆነን በተለያዩ ጊዜያት በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ለተነሱ ግጭቶች መንግስት እየሰጠ ያለው ትኩረት አንዱ ነው። በድንበር የሚዋሰኑን የቀንዱ አባል አገራትን በተመለከተ ይህ ነው የሚባል ጥረት ያለ አቋም ሲንፀባረቅ አይስተዋልም። ከአብዛኞቹ ግጭቶችና አለመግባባቶች ጀርባ የውጭ ኃይል ተፅዕኖ በእጅጉ ይንፀባረቃል። በሶማሊያ እና ኤርትራ ላይ የተወሰደው የመንግስት አቋም የግጭቱን ምክንያቶች ከስሩ እልባት የሚሰጥ ሳይሆን በተደጋጋሚ ለሚነሱ አለመግባባቶች ጊዜያዊ መፍትሄ ብቻ እየሰጠ የሚያልፍ ሆኗል። ይህ ደግሞ በሀገር ሀብትና ንብረት ከመቀለድ እና የዜጐቻችንን ህይወት ከመገበር ውጭ በዘላቂነት ያመጣቸው ለውጦች አለመኖራቸውን መታዘብ እንችላለን።
የኢህአዴግ መንግስት ቀድሞ ከምዕራባውያን ጋር ከነበረው ጥብቅ ግንኙነት ተላቆ ሙሉ ለሙሉ ፊቱን ወደምስራቁ የአለማችን ክፍል ማድረጉ ብዙ ፖለቲካዊ እንድምታዎች እንዳሉት እውን ነው። የቻይና መንግስት የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ መሰረት የሚያደርግ በአገራት የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ አለመግባት የሚለውን ነው። ይህ ደግሞ የአምባገነን መሪዎችን ማን አህሎኝነት በእጅጉ የሚደግፍ በመሆኑ ቻይናን ተመራጭ ያደርጋታል። ከዴሞክራሲና ሰብዓዊ መብት አያያዝ አንፃር ቻይና ለማንም አገር ተምሳሌት የሚያደርጋት ተሞክሮ የላትም። ስለዚህ ነው የኢህአዴግ ሃያ አመታት የቻይና ውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ዴሞክራሲ ከመገንባት አንፃር ያለው ፋይዳ ከዛም አይደለም ብለን የምናምነው።
ስለዚህም በፍትህ እምነት ኢህአዴግ ሰሞኑን የሚያከብረውን ሃያ አንደኛ የድል በዓል መሰረት በማድረግ ብሄራዊ እርቅ እንዲፈጠር አመቻችቶ፣ በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ሀገር ላሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥሪ በማድረግ እና በማሳተፍ ጊዜያዊ የሽግግር መንግስት መስርቶ አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ በማድረግ ሀገሪቷን ከመበታተን አደጋ የማደን ታሪካዊ ግዴታ ተጥሎበታል፡፡ ይህንን ታላቅ ሀገራዊ አደራም ግንባሩ ይወጣ ዘንድ ፍትህ ትጠይቃለች፡፡