Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Tuesday, 5 June 2012

በጐንደር ፖሊስ የሟቾችን አስክሬን በመኪና መሬት ለመሬት አስጐተተ


- ከቀኑ 11 ሰዓት እስከ ንጋቱ ተዘቅዝቀው ዛፍ ላይ ተሰቅለው ነበር
- ቤተክርስቲያን አይቀበሩም ተብለው ሜዳ ላይ ተቀብረዋል
- የአካባቢው ህብረተሰብ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሮበታል
- በጐንደር ተቃዋሚዎች እየታሰሩ ነው

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሰሜን ጐንደር ዞን ታች አርማጭሆ ሳንጃ ከተማ በተኩስ ልውውጥ የተገደሉ ሁለት ሰዎች አስከሬን በመኪና ላይ ታስረው ከተማ ውስጥ መሬት ለመሬት መጐተቱን የዜና ምንጮቻችን ለዝግጅት ክፍላችን አስታወቁ፡፡ የዜና
ምንጮቻችን እንደሚሉት “አቶ ሽንኩ ከፍያለውና አቶ ዳኛቸው አያሌው የተባሉ ሁለት ግለሰቦች ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርገው ከተገደሉ በኋላ አስከሬናቸው መሬት ለመሬት ሲጐተት ውሏል” ብለዋል፡፡
ምንጮች እንደሚሉት “አቶ ዳኛቸው አያሌው ከአንድ ግለሰብ ጋር በመጋጨቱ አካባቢውን ለቆ ሄዷል፡፡ ከመንግስት ጋር ፀብ አልነበረውም፡፡ ከዚያም ታጣቂዎች ሸፍተዋል በማለት ይገኛሉ የተባለበትን አካባቢ በመክበብ ተኩስ ከፈቱ፡፡ ሟቹም የተኩስ ልውውጥ እያደረጉ ሞቱ፡፡ በመቀጠልም አስክሬናቸውን በመኪና ላይ አስረው በከተማ ውስጥ ከ8-11 መሬት ለመሬት ከጐተታቸው በኋላ መሐል አራዳ ላይ ጣሏቸው፡፡ ህዝብ እንዲመለከታቸው አደረጉ፡፡ አስክሬኑን ሲመለከቱ የመንፈስ ጭንቀት ተፈጥሮባቸው የጮሁ ያለቀሱ ሰዎች በፖሊስ ቆመጥ ተደብድበዋል” ይላሉ፡፡ በማያያዝም ሲናገሩ “የአቶ ዳኛቸው አያሌው አባት፣ እናትና አያትም በሥፍራው ነበሩ፡፡ አስከሬኑን ወስደው ለመቅበር ቢጠይቁ ተከልክለዋል፡፡ በ11 ሰዓት ላይ እግራቸው ላይ ገመድ አስረው ከፖሊስ ጣቢያ ጀርባ ዛፍ ላይ ሰቅለው ዘቅዝቀው አሳደሯቸው፡፡ በማግስቱ እንዲቀበሩ ሲወሰን ቤተሰብና የአካባቢው ህብረተሰብ ቤተክርስቲያን ለመቅበር ቢጠየቅ የአካባቢው ኃላፊዎችና ፖሊሶች ቤተክርስቲያን አይቀበሩም ብለው ከልክለው ሌላ ቦታ እንዲቀበሩ አድርገዋል፡፡” በማለት በቅሬታ ይገልፃሉ፡፡ ምንጮች በመጨረሻም ሲናገሩ “የአካባቢው ህብረተሰብ እጅግ አዝኗል፡፡ በተለይ ከግድያው
በኋላ ፖሊሶች በአስከሬኖቹ ላይ የፈፀሙት ድርጊት ከባህልና ወግ ያፈነገጠ ከሰብአዊ አስተሳሰብ የወጣ በመሆኑ እናዝናለን፡፡ ማንም ሰው በሠራው ወንጀል በሞትም ሊቀጣ ይችላል፡፡ አስክሬን ግን ክብር አለው፡፡ የቀብር ቦታም መከልከል ህገወጥ ተግባር ነው፡፡ አስክሬን ዘቅዝቆ ሰቅሎ ማሳደርስ ምን ማለት ነው? ይህንን ድርጊት የፈፀሙም ያስፈፀሙም በህግ ሊጠየቁ ይገባል” ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የሳንጃ ከተማ ፖሊስ በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥበት በተደጋጋሚ ስልክ ብንደውልም ስልካቸውን ስለማይነሳ ዜናውን ለጊዜው ሚዛናዊ ማድረግ አልቻልንም፡፡ በተያያዘ ዜና በዚሁ በሰሜን ጐንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ አብረሃ ጅራ ከተማ ዙሪያ “ለረጂም ዓመታት የቆየው የመሬት ግጭት አሁን በተባባሰ ሁኔታ ፍጥጫ መፍጠሩን” ምንጮች ገልፀዋል፡፡ ምንጮቻችን እንደሚሉት “አካባቢው ከሱዳን ጋር ድንበር ነው፡፡ መንግስት የአካባቢውን መሬት ለሱዳኖች ማስረከብ ይፈልጋል፡፡ የአካባቢውን ህብረተሰብ ድንበሩን ለማስከበር ከሱዳኖች መሬቱን ሲከለከል የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት ለሱዳን ወግኖ የራሱን ዜጋ ይወጋል፡፡ በአካባቢው ያለው የመከላከያ ሠራዊት ሙሉ በሙሉ ለሱዳን ቆሞ ኢትዮጵያኖች ምንም ዓይነት የመከላከል ሥራ እንዳይሰሩ እያደረገ ነው፡፡” በማለት በአግርሞት ይገልጹታል፡፡
ምንጮች በመቀጠልም ሲገልጹ “ሰሞኑን መንግስት በተጨማሪ ለውጪ ዜጐችና ለባለሀብቶች ለመስጠት እቅድ ይዟል፡፡ ለእያንዳንዱ ገበሬ አንድ ሄክታር መሬት ብቻ ለመስጠት በማቀድ መሬት እያሸጋሸገ ነው፡፡ አንዱ ለፍቶ ያለሰለሰውን እርሻ ለሌላው ይመድባል፡፡ ገበሬው ግን አንዱ የአንዱን እርሻ ላለማረስ ቃል ተገባብቷል፡፡ የአካቢው ኃላፊዎች ግን እንዲያርስ እያስገደዱት ነው፡፡ በዚሁ ምክንያት ከሁለት ቀን በፊት ለሊት ማንነታቸው ያልታወቁ ሰዎች ፖሊስ ጣቢያውንና ቀበሌ መስተዳደሩን ጽ/ቤት አቃጥለውታል፡፡ በዚህ የተነሳ የአካባቢውን ህብረተሰብ እየሰበሰቡ እያሰሩና እየደበደቡ ናቸው፡፡ የአካባቢውን ህዝብ ወደ መጥፎ ድርጊት እየገፋፋት ነው፡፡ ህዝቡ በኩርፊያ ሥራቸውን በተጠንቀቅ ቆሞ እየተከታተለ ነው፡፡” ሲሉ ያብራራሉ፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ “ፖሊስ ጣቢያውንና የቀበሌውን መስተዳድር ያቃጠሉት ምናልባትም ከመሬት ጋር በተያያዘ በሙስና የተነካኩ ግለሰቦች መረጃ ለማጥፋት የሠሩት ሥራ ነው፡፡” በማለት ጥርጣሬአቸውን ይገልፃሉ፡፡ ከመሬት ድልድሉ ጋር ተያይዞ የአካባቢውን መሬት ከሌላ ቦታ ለመቱ ሰዎች እየተሰጠ በመሆኑ የአካባቢው ሊቀመንበርና ቅሬታ ሰሚ በጉዳዩ ባለመስማማት አካባቢውን ለቀው ወደ ሌላ ቦታ ሄደዋል” ይላሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ መሬቱን የሚሸነሽኑት የመሬት አስተዳደሩና የወረዳው ፀጥታ ኃላፊውች ናቸው በማለት ይናገራሉ፡፡ በዚህ ምክንያት ግንቦት 20 ህዝቡ ከወጣ አይመለስም ተብሎ እንዳይከበር ሰሞኑን በደረሰን ዜና በዚሁ በሰሜን ጐንደር ተቃዋሚዎች በህገወጥ መንገድ እየታሰሩ መሆናቸው ተጠቁሞአል፡፡ ምንጮች እንደሚሉት “በምርጫ 2002 መኢአድን ወክለው ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የተወዳዳሩ እየታሰሩ ናቸው፡፡ ከታሰሩት ውስጥ ታደለ ተፈራ የሰሜን ጐንደር የመኢአድ ም/ቤት ድርጅት ጉዳይ ኃላፊ፣ ስለሺ ጥጋቤ የጀናሞራ ወረዳ መኢአድ ኮሚቴ ሰብሳቢ መለስ አስሬ የጭልጋ ወረዳ መኢአድ ሰብሳቢ ሆነው ሲታገሉ የቆዩ ሲሆን ባለፈው ሐሙስና ዐርብ ምሽት በእያንዳንዱ ሰው ቤት ከአስር በላይ ፖሊሶች ተገኝተው ቤታቸውን እየበረበሩ አስረዋቸዋል፡፡” ሲሉ ገልፀዋል፡፡ የእስረኞቹ ቤተሰቦች እንደሚሉት “ፖሊሶቹ የፍ/ቤት ትዕዛዝ እንዳላሳዮቸውና ድርጊቱ ከመደበኛ የሥራ ሰዓት ውጪ በምሽት መከናወኑና እስረኞቹ የታሰሩበት ቦታ አለመታወቅ እንዳሳሰባቸው” ለዝግጅት ክፍላችን ገልፀዋል፡፡ እስረኞቹ ይገኙበታል ተብሎ የነበረው ደርጊ ፖሊስ ጣቢያና ጐንደር ፖሊስ ደውለን ለመጠየቅ ጥረት ብናደርግም ዜናውን ሚዛናዊ ማድረግ አልተቻለም፡፡

ኦብነግ ጅጅጋ አጠገብ “ከ50 በላይ የወያኔ ወታደሮችን ገደልኩ” አለ

VOA | June 4th, 2012 at 4:37 pm, posted by Dawit Wasihun
(VOA) — ግንባሩ ጥቃቱን የፈፀመው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት ደበች ሕሪሶ በተባለ አካባቢ ባለፈው ዕሁድ ግንቦት 19 አድርሰውታል ላለው ጥቃት በወሰደው የበቀል እርምጃ ነው፡፡
ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር በጠቅላላው ስድስት መኮንኖችን ጨምሮ 168 ወታደሮችን መግደሉን መግለጫው አክሎ ጠቁሟል፡፡
ባለፈው ዕሁድ የመከላከያ ሠራዊቱ አድርሶታል ሲል ኦብነግ በሚያሰማው ክስ 18 ሠላማዊ ሰዎችን መግደሉንና ከ15 በላይ ደግሞ ጉዳት እንደደረሰባቸው የግንባሩ የውጭ ጉዳይ ኮሚቴ አባልና የኢትዮጵያ ጉዳይ ኃላፊ አቶ ሃሰን አብዱላሂ ገልፀዋል፡፡
ተዋጊዎቻቸው እንደወሰዱት በተናገሩት የበቀልና እስረኞችንም የማስፈታት እርምጃ ሁለት መኪኖችን ማቃጠላቸውን፣ የተለያዩ መሣሪያዎችና የመገናኛ ሬዲዮኖችን መማረካቸውን፣ ብርቆት ከተማንም ለ15 ሰዓታት ተቆጣጥረው መቆየታቸውንና ለወታደራዊ ስትራተጂ ሲባል ለቅቀው መውጣታቸውን አመልክተዋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በተጠቀሰው ውጊያ ውስጥ መሣተፋቸውን የተናገሩትና “ለሕዝቡ አገልግሎት የተሠራ የውኃ መሣቢያ ሊያወድሙ የመጡ ወንበዴዎችን ከአካባቢው አባርረናል” ያሉት ሻለቃ ሙክታር ሼኽ ሞሐመድ የሚባሉ የክልሉ ልዩ ፖሊስ አዛዥ በግጭቱ ወቅት 35 የኦብነግ ተዋጊዎችን መግደላቸውንና አሥር መማረካቸውን ለሶማሊኛ ቋንቋ አገልግሎት ክፍላችን አስታውቀዋል፡፡
ቀደም ሲልም የክልሉ ልዩ ፖሊስ አሥር ሲቪሎችን ራቅዳ በተባለች ቀበሌና በአካባቢዋ ገድሏል፤ ዘፈፋ አካሂዷል፤ የከፉ የሰብዓዊ መብቶች ረገጣዎችንም ፈፅሟል ሲሉ ሂዩማን ራይትስ ዋች የሚባለው የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ቡድን የአፍሪካ ጉዳዮች ምክትል ዳይሬክተር ሌስሊ ሌፍኮው ስለሰጡት መግለጫ የተጠየቁት ሻለቃ ሙኽታር ሼክ ሞሐመድ መግለጫው “አንዳችም መሠረት የሌለውና የተለመደ የሂዩማን ራይትስ ዋች ፕሮፓጋንዳ ነው” ብለውታል፡፡

Human Rights Violations Being intensified In afar region of Ethiopia!!!!

Human Rights Violations Being intensified In afar region of Ethiopia!!!!
Press Release June 4, 2012 
posted by Dawit Wasihun
The conflict between Afars the Tigray People’s Liberation Front (TPLF) led government has been intensified during the last few months. The core issue of this disagreement is related to forced eviction of the pastoralists and the aggressive land grabbing investment policy.The regime has continued its military repression, harassment and intimidation of the civilians as they refuse to submit and leave their homes to sugarcane plantation project owned by an Indian company. Hence, in many part of the Afar region a well-orchestrated and systematic human rights abuse has become a daily pattern. The recent strategy used by the regime is to instigate internal and external conflict in the Afar region and thereby use its military to silence the civilian resistance against the illegal land grabbing policy.
In the north of the Afar Region, resource potential has been a serious issue at stake. Among others a huge Salt source of Amole, Salt block of Assale area, has been a well-known commercial item between Afars and Tigray peoples. This has been also a huge tax revenue source for the administration in the region. Throughout the history the Assale area is administratively situated within Brahle. However, lately the increasing economic significance of the Assale attracted much attention of the TPLF affiliated investors, who are effectively lobbying to control the area. Currently, the regime is being diverting the Salt rich area of Assale to Afdera district – another Salt rich area currently solely exploited by those Tigrean investors. The Barahle district administration has rejected the arbitrary decision of diversion of the Salt rich area to Afdera. However, the regime deployed its Military on the border area of Afdera and Barahle in order to implementits diversion plan. The Barahle district called for elders and mass meeting of 750 people to divert the conflict. These elders led meeting is repelled by the regime and over 6 district leaders including the Head, Ali Osman, removed from their position in administration of Barahle and are kept at house arrest in Mekele.The local community is fretful about that this deadlock gradually could lead to army-led confrontation, where the Afars the two districts are positioned to fight each other. The conflict concerns about 70 000 inhabitants combined into two districts.
The other serious confrontation is taking place along the Awash Valley in Rumaytoabout 3 km west of Aysaita. The regime arbitrarily assigned this area for a Sugarcane plantationproject. Local population is removed by force and forests are cleared by over 20 bulldozers day and night. The local community called for a self-defense to protect the forest and the land, because they have no other place to go. The regime has placed a huge army around the Rumayto people and nobody is allowed to move in or out of the area. The ecological and forest destruction is clear where the rain forest is destroyed. The armyof the regime threatens to clear the forest by force but the confrontation is at sight. The confrontation concerns about 50 000 inhabitants in the localities.
In search of land for investment along the Awash Valley, the regime is allowing the neighboring Issa contrabandist not only to claim part of Afar Regional territory but also to inspire their claim and oversee their recurrent raids against the Afars along the Middle Awash Valley. As late as yesterday, June 2nd these raided was carried on a feeder road project at a place called BaareytainAmibara district at Zone three. The project wasimplemented by Afar Regional government. In this confrontation more than 10 Afarswere killed and some more injuries were reported. The raid said to have supported by Issa Special Forces and also in turn backed by Djibouti government. Both the Regional and Federal governments are watching the incidents without any preventive action.
Finally, the Awash River which is a life line of the southern Afar for water sources is being curtailed by Dam and diversion so that people have no alternative water sources.
Afar Human Rights Organisation is concerned about both the short- and long term consequences of the ill planned and non-inclusive economic policy of the regime, and the Afar civilians are already paying the heavy toll. Therefore,we call:
  • On international community to give a serious attention to the suffering of Afar people.
  • On the regime in Addis Ababa to stop harassing and killing of civilians
  • On to observe and investigate the case of those who are affected and lost their lives
  • On to sendthe Red Cross and other relief agencies to visit the area.
  • To investigate the human rights violations inside these areas!
For further information, e-mail: ahro2006@hotmail.com