ነሀሴ ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-አቶ በረከት ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “በሀይወት ዘመናቸው አቶ መለስ የያዙት ዓላማ የጥቂቶች ዓላማ ከሆነ ሞት ነበር ” ብለዋል ።
የመንግስትና
የኢህአዴግ አመራርም የህዝቡን መልዕክት ተቀብለን ጠቅላይ ሚኒስትሩን አርዓያ አደርገን ለመከተል ወስነናል የሚሉት
አቶ በረከት፤ ሌሎች ባለስልጣኖችና የኢህአዴግ አመራር አካላት፣ ህዝቡ እና የአለማቀፉ ማህበረሰብ ከጎናቸው እንዲቆም
ተማጽነዋል።
ኢሳት በትንናት ዘገባው አንድ የብአዴን ከፍተኛ ባለስልጣንን በምንጭነት በመጠቀም ፣
የኢህአዴግ ባለስልጣናት በአቶ መለስ ሞት የህዝብ ድጋፍ ለማግኘት ስትራቴጂ መንደፉቸውን መግለጻችን ይታወሳል።
የኢህአዴግ ስልት ህዝቡ በየወረዳዎች በተዘረጋው ድንኳን እየወጣ ለአቶ መለስና ለኢህአዴግ ያለውን ድጋፍ
እንዲገልጽና ስሜታቸው የተዳከመውን የመንግስት ባለስልጣናት እና የኢህአዴግ ካድሬዎችን እንዲያበረታታ ማድረግ ነው።
አቶ በረከት “በ መለስ አጥንት” በማለት ዛሬ ለባለስልጣኖቹና ለህዝቡ ያቀረቡት ጥሪ በኢህአዴግ ውስጥ የተፈጠረውን መከፋፈል እና ውጥረት እንደሚያሳይ ነው ታዛቢዎች የሚናገሩት።
ኢሳት
ዜና:-ኢሳት ከሳምንታት በፊት ከዓለማቀፉ ግጭት ተንታኝ ቡድን ውስጥ ያሉ ምንጮቹን በመጥቀስ ጠቅላይ ሚኒስትር
መለስ ዜናዊ ማረፋቸውን ይፋ ቢያደርግም፤ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትሩን አቶ በረከት ስምዖንን ጨምሮ የተለያዩ
የመንግስት ባለስልጣናትና በአገር ቤት የሚታተሙ አንዳንድ ጋዜጦች አቶ መለስ በቅርቡ ሥራ ለመጀመር በሚያስላቸው
ጥሩ የጤንነት ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ሲገልፁ ቆይተዋል።