Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Saturday 22 September 2012

እነ አንዱዓለም አራጌ የታሰሩበት 1ኛ ዓመት በሻማ ምሽት ታሰበ…………..ከፍኖተ ዘመቻ ነጻነት “እናሸንፋለን” we will win (www)




         - የፖለቲካና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ ጥሪ ቀረበ
         - የሻማ ምሽት ዕለት ጥቁር ልብስ እንዲለበስ ተጠየቀ

የአንድነት ፓርቲ /ሊቀመንበርና ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበሩት አቶ አንዱዓለም አራጌ፣ ጋዜጠኛና ፖለቲካ ተንታኝ እስክንድር ነጋ፣ የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት አባል አቶ ናትናኤል መኮንንን ጨምሮ ሌሎች የታሰሩበት 1 ዓመት በሻማ ማብራት ዝግጅት ታስቧል፡፡ መስከረም 3 ቀን 2005 . በአንድነት
በፓርቲው ዋና /ቤት በተከናወነ ዝግጅት ላይ የታሳሪ ቤተሰቦች፣ የአንድነት ፓርቲ አመራሮች፣ የፓርቲው አባላትና የሌሎች ፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች በዝግጅቱ ላይ ታድመዋል፡፡ መድረኩን ያስተባበሩት የአንድነት ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት አባል የሆኑት አቶ ፍቃዱ ሰጠኝ የሻማ ዝግጅቱ ዓላማ በኢትዮጵ ውስጥ ስለመብትና
ነፃነት በሠላማዊና በህጋዊ መንገድ ሲታገሉ ለእስር ለበቁ የፖለቲካና የህሊና እስረኞችን ለማሰብ መሆኑን አስረድተው የዕለቱን ዝግጅት የሚያወድሱ አጫጭር ግጥሞችን በማቅረብ የተለያዩ እንግዶችን በተናጋሪነት ጋብዘዋል፡፡

በቅድሚያ ለታዳሚው ንግግር ያደረጉት የአንድነት ፓርቲ ብሄራዊ /ቤት ዋና ፀሐፊ የሆኑት አቶ ትግስቱ አወሉ ሲሆኑፖለቲካ አገርን የመምራት ጥበብ እንጂ የህዝብ መጨቆኛ መሣሪያ አይደለምካሉ በኋላዴሞክራሲያዊና ፍትሐዊ ሥርዓት ባልሰፈነበት አገር የሚከሰተው ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀውሶች እጅግ አስከፊ ናቸውብለዋል፡፡ በዚህ ምክንያት በአገራችን በተንሰራፋው -ዴሞክራሲያዊና -ፍትሐዊ ሥርዓት ህዝብ በአፈና ውስጥ ህዝቡም ዝምታን መርጧል፣ ዛሬ የምናበራው ሻማ ነፃ ሻማ አይደለም፤ በአጥር ሽቦ የተከበበ ሻማ ነው፤ እስረኞቻችን የትግላችን አርአያ እንጂ የእኛ ማስፈራሪያዎች አይደሉም፤ ዛሬ በአገራችን ባለው የፖለቲካ ሁኔታ ሁላችንም ነፃ ሰዎች አይደለንም፤ ቀድሞ ማንን እንደሚያስር የሚያውቀው ኢህአዴግ ነው፤ እነ አንዱዓለም፣ እስክንድር፣ ናትናኤል ውብሸት፣ ርዮት፣ በቀለ ገርባና ኦልባና የድርሻቸውን እየተወጡ ናቸው እኛስ?” ሲሉ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል፡፡ አቶ ትግስቱ በርካታ ነጥቦችን በማንሳት ለታዳሚው ንግግራቸውን ቋጭተዋል፡፡ በዕለቱ የሰማያዊ ፓርቲ ተወካይ አቶ ይልቃል ጌትነትም ንግግር አድርገዋል፡፡

አቶ ይልቃል እንዳሉትአንዱዓለም እና ርዕዮት ጓደኞቼ ናቸው፡፡ አንዱዓለም ከመታሰሩ ከሁለት ቀን በፊት ለዓመት በዓል ተቀጣጥረን ተገባብዘን ነበር፡፡ካሉ በኋላበዚህ የሻማ ምሽት ላይ የተገኘው የሰው ቁጥር ይህ ብቻ መሆን አልነበረበትም፡፡ ፓርቲዎች ተሰባስበን ትግላችንን ማጠናከር ይገባናል፡፡ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ የዕለቱ ሻማ የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት የነበሩት የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር / ነጋሶ የለኮሱ ሲሆን የመዝጊያውን ንግግር የአንድነት ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካርያስ የማነብርሃን አድርገዋል፡፡ አቶ ዘካሪያስ ሲናገሩየሠላም አርበኞቻችን ከታሰሩ ዛሬ 365 ቀን ሆኗቸዋል፡፡ እነሱ የዜግነት ግዳጃቸውን እየተወጡ ናቸው፡፡ እኛስ ምን እየሰራን ነው?” አድርገዋል፡፡ አቶ ይልቃል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ አቶ ዘካሪያስ በመቀጠልምዛሬ በእስር እየማቀቁ የሚገኙ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች ናቸው፡፡ እናከብራቸዋለን፡፡ እንዘክርላቸዋለን፡፡ ዛሬ እንደምታዩት ሙሉ በሙሉ ጥቁር ልብስ ለብሼአለሁ፡፡

ብዙዎቹ ለማነው ያዘንከው? ምን ችግር ገጠመህ እያሉ ጠይቀውኛል፤ እኔ ዛሬ ጥቁር የለበስኩበት ምክንያት ስለአለኝ ነው፡፡ ወር በገባ በሦስት ኢትዮጵያ ውስጥ በአመለካከታቸው ምክንያት በእስር በመማቀቅ ላይ ለሚገኙ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች የሻማ ምሽት የምናደርግበት ዕለት ነው፡፡ በአገሪቱ ውስጥ ያሉ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች በሙሉ እስኪለቀቁ ድረስ ዘወትር ወር በገባ በሦስት የሐዘን ቀን ሆኖ ጥቁር መለበስ አለበት ብዬ አምናለሁ፡፡ ስለዚህ ሁሉም ሰው በየወሩ ጥቁር በመልበስ እንዲያስታውሰው ጥሪዬን አቀርባለሁብለዋል፡፡ በመጨረሻም አቶ ዘካሪያስ ሐሳባቸውን ሲያጠቃልሉዛሬ በአገራችን የመናገር፣ የመጽሐፍ፣ በነፃነት የማሰብ መብት ሞቷል፡፡ የኦሮሞ፣ የአማራና ሌሎችም ቋንቋ ተናጋሪ ልጆች በእስር ቤት እየማቀቁ ናቸው፡፡

አባት ያላቸው የስዊዲን ጋዜጠኞች ሲፈቱ አባት የሌላቸው ኢትዮጵያዊያን ጋዜጠኞች ሊፈቱ አልቻሉም፡፡ ስለዚህ በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞች እስክንድር ነጋ፣ ውብሸት ታዬ፣ ርዕዮት ዓለሙና የሱፍ ጌታቸውና በእስር ላይ የሚገኙ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ እጠይቃለሁብለዋል፡፡ በዕለቱ በርካታ ግጥሞችና መጣጥፎች ቀርበዋል፡፡

No comments:

Post a Comment