Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Tuesday 11 September 2012

አንድነት ፓርቲ ብርሃንና ሰላም በህገ ወጥ መንገድ ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣን አላትምም ማለቱ ሕገ ወጥ ነው አለ

ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት
ከነብዩ ኃይሉ የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ፡-
የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ልሳን የሆነችው እና በተጨማሪም በኢትዮጵያ ውስጥ የነፃ ጋዜጦችን መታፈን፣ መመናመን እና ድፍረት ማጣት ተከትሎ ዘወትር ማክሰኞ ጠንካራ የፖለቲካ ትንታኔዎችንና ዜናዎችን በመያዝ ለህትመት የምትበቃው ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ብርሃንና ሰላም የህግ አግባብ በሌለው ውሳኔ አላትምም ማለቱ ህገ ወጥ በመሆኑ በአስቸኩዋይ ይታረም ሲል የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት አስታወቀ፡፡
ለህትመት ከበቃችበት ጊዜ ጀምሮ በህዝብ ዘንድ ተወዳጅነትን በማትረፍ ተናፋቂ ለመሆን የበቃችው ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ እንዳትታተም በብርሃንና ሰላም የታገደችበት ሁኔታ ከጠ/ሚ መለስ ሞት ጋር የሚያያዝ ሲሆን ጋዜጣዋ የፖቲካ ፓርቲ ልሳን እንደመሆንዋና ፓርቲው ደግሞ ያለበትን ሃገራዊ ሃላፊነት ለመወጣት የጠቅላይ ሚንስትሩን ሞት ተከትሎ በሃገሪቱ የፖለቲካ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች ምን መልክ እንደሚኖራቸው የሚያሳይ የፖለቲካ አመራሮች፣ ታዋቂ ግለሰቦችና የጋዜጣዋ ክፍል ባልደረቦች የፃፉዋቸውን ትንታኔዎች በልዩ ዕትም ዓርብ ነሐሴ 18 ቀን 2004 ዓ.ም ለንባብ ማብቃቱ የሚታወስ ነው፡፡ በመቀጠልም ማክሰኞ በመደበኛ ቀንዋ ጋዜጣዋ ለአንባቢያን የደረሰች ሲሆን፡፡ በሀገሪቱ ያለውን ወቅታዊ ሁኔታ ተከትሎ ጠንካራ ሃሳብ ያላቸውን ኢትዮጵያውያን ለማስተናገድ እንደገና ዓርብ ነሐሴ 25 ቀን 2004 ዓ.ም  የጋዜጣ ክፍሉ በመረባረብ ስራውን አጠናቆ ነበር፡፡ ይሁን እንጅ እንደተለመደው ገንዘብ ለመክፈል የህትመት ክትትል ሰራኛው ሲሄድ እንዳይታተም ታግዷል በማለት መልሰውታል፡፡
የህዝብ ግንኙነትቱ አያይዞ እንደገለፀው አቶ መኮንን አበራ የተባሉትን የማርኬቲንግ ማናጀርና ከአገዱት የማኔጅመንት አባል አንዱ የሆኑትን ጠይቆ እንደተረዳው ‹‹ጋዜጣው የጠ/ሚ መለስን ሞት ተከትሎ የወጡ ፅሁፎች ጥሩ አልነበሩም ህዝቡም አስተያየት ሰጥቶናል››  ከማለት ውጭ የትኛው ዘገባ ጥሩ እናዳልነበር የገለፁት ነገር የለም፡፡ እገዳውም በወረቀት ሳይሆን በቃል ነው፡፡ እገዳውን የፈፀሙትም የማተሚያ ቤቱ የማኔጅመንት አባላት ከህግ አግባብ ውጭ ነው፡፡
የህዝብ ግንኙነት ም/ኃላፊ የሆኑት አቶ ዳንኤል ተፈራ ስለጉዳዩ ሲገልፁ ‹‹እኛ በህጋዊ መንገድ የምንንቀሳቀስ የፖለቲካ ፓርቲዎች ነን፡፡ የሃገራችን ጉዳይ ያሳስበናል፣ የህዝቡ ጉዳይ ያሳስበናል፣ የሉዓላዊነታችን ጉዳይ ያሳስበናል እንዲሁም የአቶ መለስ ድንገተኛ ሞትና ተከታዩ ጊዜ ያሳስበናል ስለዚህ ያወጣናቸው ዘገባዎች አግባብነት ያላቸውና ወቅታዊ ነበሩ፡፡ አቶ መለስ መሞታቸውን እንደሰማንም የሃዘን መግለጫ በማውጣት የተሰማንን ሀዘን ገልጠናል፡፡ ከዚህ በላይ ግን የሚያሳስበን የሀገራችን ዱዳይ ነው›› በማለት ተናግረዋል፡፡
በቀጣይም አገዱ የተባሉትን የማኔጅመንት አካላት ለማነጋገር የአንድነት ከፍተኛ አመራሮች ቀጠሮ የያዙ ሲሆን እገዳው ህገ-ወጥ በመሆኑ እስከ መጨረሻው የምንታገለው ይሆናል፡፡ ከህዝብ ጋር የመገናኛ በራችንን ሲዘጉ ዝም ብለን አንመለከትም፡፡ ከዚያ በፊት ግን የማተሚያ ቤቱ ኃላፊዎች ስህተታቸውን ያርማሉ ብለን ተስፋ እናደርጋለን፡፡ በማለት የአንድነት  የህዝብ ግንኙነት ያደረሰን መረጃ ያመለክታል

No comments:

Post a Comment