Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Thursday 12 April 2012

የአማራ ተወላጆች ከቤንች ማጂ ዞን እንዲወጡ ማዘዛቸው ኢህአዴግ ደቡቡንና አማራውን ለማጋጨት የቀየሰው ሴራ ነው ተባለ


ሚያዚያ ፬ (አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የአማራ ተወላጆች ከቤንች ማጂ ዞን እንዲወጡ ማዘዛቸው ኢህአዴግ ደቡቡንና አማራውን ለማጋጨት የቀየሰው ሴራ ነው ሲሉ የአንድነት ፓርቲ የደቡብ ተወካይ ገለጡ
የአንድነት ፓርቲ የምክር ቤት አባልና የደቡብ ተወካይ የሆኑት አቶ ዳንኤል ሺበሺ ለኢሳት እንደተናገሩት በአቶ ሽፈራው ሽጉጤ የተጻፈው መመሪያ አንድን ብሄር ነጥሎ ለማጥቃት ያለመ ነው
ኢህአዴግ ከዚህ ቀደም ሲያደርግ እንደነበረው ሁሉ የአሁኑ እርምጃውም ደቡቡን ከአማራው ህዝብ ጋር ለማጋጨት የቀየሰው ሴራ ነው። የዚህ ሁሉ ችግር መነሻው ኢህአዴግ የሚከተለው የብሄር ፖለቲካ መሆኑን አቶ ዳንኤል አስምረውበታል ።
ሰፋሪዎች ስርአቱን ተከትለው አልሰፈሩም ከተባለ ለምን አስቀድሞ ለመከላከል አልተሞከረም ሲሉ የሚጠይቁት አቶ ዳንኤል ፣ ሰዎች ቋሚ ንብረት ካፈሩና ቤተሰብ ከመሰረቱ በሁዋላ እየተደበደቡ ከክልሉ እንዲወጡ የተደረገው አሰራር አሳዛኝ ነው
በቅርቡ የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከክልሉ የተባረሩት ሰዎች በቁጥር 800 የአማራ ተወላጆች ብቻ ናቸው በማለት ለሰጡት አስተያየት ደግሞ አቶ ዳንኤል የሚከተለውን ብለዋል
በክልሉ ከማዳበሪያ እዳ እና ከፍትህ እጦት ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ራሳቸውን እያጠፉ ነው እየተባለ ነው፣ ይህንንስ ድርጅታችሁ ያውቃል ወይ ተብለው የተጠየቁት አቶ ዳንኤል ፣ ማዳበሪያ በክልሉ ትልቅ አደጋ እያመጣ መሆኑን ገልጠዋል
በዳውሮ ዞን አቶ አባተ አየለ የተባሉት  ሰው ፍትህ ካልተሰጠኝ ራሳቸውን ከዛፍ ላይ ፈጥፍጠው እንደሚገድሉ በመዛታቸው ከመንግስት ባለስልጣናት በተደረገላቸው ድለላ ከዛፍ ላይ እንዲወርዱ መደረጉን መዘገባችን ይታወሳል።

No comments:

Post a Comment