Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Wednesday 11 April 2012

የኢሕአዴግ መንግሥት በመቶ ሚሊዮኖች በሚሰላ ብር እስር ቤቶች ሊያሰራ ነው!

በካሣሁን ለማ

የወያኔ ኢህአዴግ መንግሥት አራት መቶ ሰባ ሰባት ሚሊዮን ብር ወጪ በመመደብ አራት ተጨማሪ እሥር ቤቶችን ሊያሰራ ውሳኔ ላይ እንደደረሰ ከሀገር ቤት የተሠራጨው ዜና ያመለክታል።የተጨማሪ እሥር ቤቶች ግንባታ የሚካሄድባቸው ሥፍራዎች አዲስ አበባ፣ ድሬደዋ፣ሸዋሮቢትና ዝዋይ ከተሞች መሆናቸው ታውቋል። ቃሊቲ እሥር ቤት የመሠረት ድንጋይ የተጣለ ሲሆን፣ይህ ማለት ደግሞ የአዲስ አበባው 'አዲስ እሥር' ቤት ግንባታ እዛው ቃሊቲ ይደረጋል፣ወይም ሊስፋፋ እንደሚችል ይጠበቃል።ሁሉም እሥር ቤቶች አንድ በፌዴራል ደረጃ የተወከለ ሪፈራል ሆስፒታል እንደሚሰራ የተጠቀሰ ሲሆን ፣ መቀመጫውም አዲስ አበባ እንደሆነ ተመልክቷል።
የራሣቸው እንጂ የሕዝብ ጩኸት የማይሰማቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ባለስልጣናት እዚህ ውሣኔ ላይ የደረሱት በአሁኑ ወቅት ከሰባ ሺ በላይ አማራዎች መጠለያ አጥተው ''የመንግሥት ያለህ!'' በሚሉበት ሰዓት መሆኑ ሁኔታው ሳያስገርም እንዳልቀረ ይታመናል።
በአሁኑ ወቅት በመላው ሀገሪቱ ተንሰራፍቶ አደገኛ ደረጃ ላይ የደረሠው የኑሮ ውድነት በመጠኑም ቢሆን ለመቀነስ ጥረት የማይታይበት የወያኔ አስተዳደር ለህዝብ ያለው ንቀት፣አምባ ገነናዊነትና ማንአልሆኝነት በስፋት እያራመደ መምጣቱ ፤ ወያኔ ኢሕህአግ እየወሰደ ያለው ፍፁም ወቅታዊና አንገብጋቢ ርምጃ ያለመሆኑ የማንነቱ ዓይነተኛ ገላጭ ሊሆን እንደሚችል ቡዙዎቹን ሊያነጋር እንደሚችል ይጠበቃል።
የመለስ ዜናዊ አስተዳደር ከፊት ለፊቱ መጠነ ብዙ ጋሬጣዎች እንደተደቀኑበት የሚገልፁ የቅርብ ሰዎች እንደሚሉት በአንድ ፓርቲ እና በአንድ ሰው ሥር የሚተዳደር መንግሥት ምን ጊዜም ቢሆን ዕድሜዉ አጭር መሆኑን ገልጸው ፣ በሰበብ አስባቡ ምክንያት በማበጀት አስጊ ናቸው የተባሉትን እሥር ቤት መወርወር መሆኑን ይገልጻሉ። ከዚህ አንፃር የመለስ መንግሥት ተጨማሪ እስር ቤቶችን ለማሰራት እያወጣ ያለው በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ አይስገርማቸውም።
ከልማት ተቋማት ግንባታ ይልቅ የእሥር ቤቶችን ግንባታ የመረጠው የወያኔ መንግሥት አደገኛ የፖለቲካ አጣብቂኝ ውስጥ መግባቱን የሚያምኑ በርካታ ገለልተኛ የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት፣ የመለስ መንግሥት ዕድሜውን በአንድ ቀን ለማራዘም ማድረግ ያለበትን ከማድረግ የሚያግደው የለም ይላሉ።እንደነዚህ የፖለቲካ አዋቂዎች መለስ ለቀጣዩ ምርጫ በዕጩነት ለማቅረብ አይኑን በጨው አጥቦ በኢትዮጵያና በዓለም ኅብረተሰብ ፊት መውጣቱ እንደማይቀር ግምታቸውን ከገለጹ በኋላ ፣ ከዚሁ ጋር ተያይዞ ከህወሃት ሊያፈነግጡ የሚጠበቁና ከተቃዋሚ ጎራ ሆነው የሚቃወማቸውና በጹሑፍ የሚተቿቸውን እሥር ቤት ለመወርወር የአዲሶቹ እስር ቤቶች መገንባት ለዚሁ ዓላማ ሊሆን እንደሚችል እምነታቸውን አስፍረዋል።
በአሁኑ ወቅት በርካታ የአማራ ተወላጆች ዕትብታቸው በተቀበረበትና ወልደው በሳሙበት መሬት ላይ እንዲሠደዱና እንደ ሁለተኛ ዜጋ በመሠቃየት ላይ መሆናቸውን ያስታወሱት ተጠቃሽ ገለልተኛ ሙሑራን እንደሚሉት ወያኔ ኢሕአዴግ ከ ምርጫ ተምሪያለሁ ቢልም ፤ ከቅንጅት ወዲህ የተማረው ቢኖር በተንኮልና በመከፋፈል ሕዝቦችን መበደል ነው ይላሉ ። ለዚህም የአማራን ከቀዬው ማፈናቀልና ጉዳዩን ከደቡብ ሕዝቦች ጋር የማገናኘቱ ጊዜው ያለፈበት የቂል አቀራረብ ኮንነዋል።
እንደ አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች ከሆነ የመለስ ዜናዊ መንግሥት ከምርጫ ዘጠና ሰባት ምርጫና መዘዙ ወዲህ ለሕዝቡ ቅን አሳቢ በመምሰል በተቃራኒው መንቀሳቀስ ነው።ለምሣሌ የፀረ ሽብሩ አዋጅ ጠንካራ ተፎካካሪዎችን ፣ ጋዜጠኞችንና የሰበዓዊ መብት ተሟጋቾችን ሆን ብሎ ለማፈን እንጂ ፤ በእውነቱ ቦንብ በመታጠቅ የመንግሥትን ተቋማት የሚያወድም ወይም አጥፍቶ የሚያጠፋ ኢትዮጵያዊ ኖሮ አይደለም ህጉ የወጣው በማለት አጥብቀው ይተቻሉ።
በአሁኑ ወቅት ከሰባት መቶ ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ሆኖ እንዲገነባ እንቅስቃሴ የተጀመረለት የተጨማሪ እሥር ቤቶች ግንባታ ገንዘብ ለልማት ቢውል የሺዎች ኢትዮጵያውያን ኑሮ ሊታደግ እንደሚችል ጥርጥር የለውም።ወይም በሺዎች የሚሰሉ ኢትዮጵያዊያን ተፈናቃዮችን የመጠለያ ችግር መፍትሄ በመስጠት ባቃለለ ነበር የሚሉ ወገኖች ፤ አሁን ወያኔ ሊያሠራ የወሰነውን የእሥር ቤቶች ግንባታ ሂደት አንድ አንድምታ እንዳለው በጋራ ይስማሙበታል።ይህውም መንግሥት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንን ፊት ለፊት ከሚጠብቀው የፖለቲካ ቀውስና ምርጫ ጋር በተየያዘ እሥር ቤት ለመማገድ ውሳኔ ላይ ደርሷል።
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
April 6, 2012

No comments:

Post a Comment