Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Thursday 12 April 2012

የሰሜን ሱዳን ፓርላማ አገሪቱ ደቡብ ሱዳንን ለመውጋት ሙሉ ዝግጅት እንድታደርግ ወሰነ

ሚያዚያ ፫ (ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የሰሜን ሱዳን ፓርላማ አገሪቱ ደቡብ ሱዳንን ለመውጋት ሙሉ ዝግጅት እንድታደርግ ወሰነ የኢትዮጵያ ጦር እጣ ፋንታ አልታወቀም

ደቡብ ሱዳን ሰሞኑን ሄግሊግ እየተባለ የሚጠራውን ዋነኛ የነዳጅ ጉድጓዶችን ከሰሜን ሱዳን ማስለቀቁዋን፣ የሱዳን መንግስት ጦርም  ተሽንፎ አካባቢውን መልቀቁን የመገናኛ ብዙሀን ሲዘገቡ ሰንብተዋል።

የሱዳን የመካላከያ ሚኒስትር የሆኑት አብደል ራሂም ሁሴን ለፓርላማው ያቀረቡትን ሪፖርት ተከትሎ ነው አገሪቱ ለሙሉ ጦርነት እንድትዘጋጅ ውሳኔ የተላለፈው። ፓርላመው በአፍሪካ ህብረት አደራዳሪነት በአዲስ አበባ ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው የሰላም ድርድርም እንዲቋረጥ ወስኖአል።

በሁለቱ አገሮች የሰላም ማስጠበቅ ተልእኮ የተሰጠው የኢትዮጵያ ጦር ሁለቱ አገሮች ወደ ጦርነት ሲያመሩ ምንም አይነት እርምጃ አለመውሰዱ የተባበሩት መንግስታትን ግራ አጋብቷል። ከዲፕሎማቶች ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየው በወር 10 ሺ ዶላር ገደማ የሚከፈላቸው የህወሀት ጄኔራሎች በሁለቱ አገሮች መካከል የተፈጠረውን ችግር ለተመድ ባለስልጣናት በበቂ ሁኔታ ሊያስረዱ አልቻሉም። በህወሀት ጄኔራሎቹ ውስጥ የሚታየው የቋንቋ እጥረት እንዲሁም አብዛኞቹ በቅርቡ ጡረታ መውጣታቸው የማይቀር መሆኑን አውቀው በንግድ ስራ ላይ መሰማራታቸው የተመድ ባለስልጣናትን ማበሳጨቱን ዲፐሎማቱ ለኢሳት ገልጠዋል።

ሁለቱ አገሮች ወደ ጦርነት ከገቡ የኢትዮጵያ ጦር  ሱዳንን ውስጥ የትኛውን ሰላም ለመጠበቅ ይቆያል በማለት ጥያቄ ያቀረቡት ዲፐሎማቱ ምናልባትም የሰሜን ሱዳን መንግስት የኢትዮጵያ ጦር አገሪቱን ለቆ እንዲወጣ ሊጠይቅ ይችላል  ሲሉ አስተያየታቸውን አክለዋል።

ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ደግሞ በሱዳን የሚገኙት 200 መቶ ወታደራዊ ታዛቢዎችና ወታደራዊ አዛዞች በቀን 130 ዶላር ይከፈላቸዋል። 4 ሺ የሚሆኑት  ወታደሮች በአንጻሩ ከተባባሩት መንግስታት ድርጅት ምንም አይነት ክፍያ አያገኙም። እንደመረጃዎች ከሆነ በአቤይ ግዛት የሚገኙት 200 ወታደራዊ ባለስልጣናት 98 በመቶው  የህወሀት አባላት እና የአንድ ብሄር ተወላጆች ናቸው።

No comments:

Post a Comment