Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Saturday 12 January 2013

TPLF and the Culture of Violence

by Yilma Bekele
According to ESAT the FBI has foiled an attempt by the Ethiopian government to assassinate Ato Abebe Gellaw.
According to ESAT the FBI has foiled an attempt by the Ethiopian government to assassinate Ato Abebe Gelaw. Goosh Abera and his accomplices are under custody. Please note here I said the Ethiopian government since there seems to be no thin line between the TPLF party and the government. Why am I not surprised? I am not surprised because for the TPLF violence is sanctioned by the party leaders as a legitimate tool to achieve political, economic and military dominance.

The following weeks as we look closely at Goosh Abera and his criminal friends and the FBI presents a psychological profile of the alleged conspirators we are sure to find out certain telltale signs about TPLF and their bizarre psychopathic behavior. Individuals like Goosh are most probably equipped with basic rudimentary education if any and survive by their wit and ethnic fueled bravado. In Ethiopia they are known for carrying weapons conspicuously, brandishing them at will and revealing in their thuggish behavior. They are the kind that administers summary judgment on street corners, bars and clubs.

Friday 11 January 2013

የተቃዋሚዎቻችን አበሳ ከፋሲል አያሌው

09/01/2013

የአንድ ሃገር ህዝብ በራሱ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዊ ፣ተፈጥሮዋዊም ሆነ በሌሎች አዊዎቹ ላይ የተሰማውን፣ የታየውን፣
ቅር ያለውን፣ እንዲሁም ያደነቀውን ነገር ያለምንም ተጽዕኖና ፍራቻ መግለጽ ካልቻለ ሰው በመሆኑ ብቻ የተፈቀደለትን በነጻነት
የማሰብ፣ የመጻፍና የመናገር ተፈጥሮዋዊ መብቶቹ የተነፈጉት ብቻ ሳይሆን በተለይም በዚህ በሃያ አንደኛው ክ/ዘመን የሰው ልጆች
ከደረሱበት ዲሞክራሲያዊ መብቶች አንጻር ሲምዘን በከፍተኛ የነጻነት እጦት ከሚሰቃዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ውስጥ እንዲመደብ
ያደርገዋል:: ኢትዮጵያ በዲሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብቶች መከበር ዙርያ (ደረጃው በተለያየ መልኩ ይገለጽ ይሆናል) ለረጅም ጊዜ
ያደረገችው ሙከራና አሁን ያለችበትን የዲሞክራሲና የሰብአዊ መብቶች ነጻነት ላስተዋለ ሲደረጉ የነበሩ ሙከራዎች ሁሉ በተለይም
ሲፈራረቁባት የኖሩት ገዢዎቿ ሲተገብሩት የኖሩት ድንጋጌዎችና መመሪያዎች በርግጥም ለህዝቦቿ ዘለቄታዊ የዲሞክራሲያዊ ጥቅም
የቆሙ ሳይሆኑ ለገዚዎቿ የስልጣን ጥቅም ማስጠበቂያ መሳሪያ ሆነው ሲያገለግሉ የኖሩ ናቸው::

አሁን በስልጣን የሚገኘው የወያኔው ስርአት ላለፉት 21 አመታት የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታ እያለ ጆሮአችንን ቢያደነቁረውም
እሱ የሚለው የዲሞክራሲ ስርዓትና ትክክለኛው ዲሞክራሲያዊ ስርአት አራምባና ቆቦ መሆናቸው ብቻ ሳይሆን ዲሞክራሲያዊ
ስርአትን በገመድ ለክቶና መጥኖ የናንተ መብትና ነጻነት እስከመጨፈር እንጂ የኔን ስልጣንና ጥቅም የሚነካ ከሆነ ቢላ ባንገቴ ካለን
ሰነባበተ:: ለዚህም ይመስላል በተለይም ህገ መንግስታዊ መብታቸውን ተጠቅመው የተቃውሞ ድምጻቸውን ለሚያሰሙ
ጋዜጠኞችም ሆነ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ምንም አይነት መፈናፈኛ እንዳያገኙ ሌት ተቀን ደፋ ቀና የሚለው::

ከዚህም የነጻነት እጦት እና ፍጹም አምባገነናዊ አፈናዎች መካከል እንደ አንድ ማሳያ የሚሆነው በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ
የሚያደርሰው ቅጥ ያጣ አፈናና በደል ሲሆን ዛሬ በወያኔው ስርዓት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚታዩት እንደ ተፎካካሪ ፓርቲ ሳይሆን
ሃገርን ለማፍረስ እንደተዘጋጁ አሸባሪዎች ተደርገው ነው:: በጣም የሚያሳዝነውነና አደገኛው አካሄዱ ደግሞ ይህን እምነቱን ቀሪው
የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያምንና እንዲቀበል ፍጹም ህገወጥ በሆነና ከዕውነት በራቀ ውንጀላ ተቃዋሚዎችን ለማጠልሸት
የሚያደርገው እልህ አስጨራሽ ትግሉ ነው::