Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Friday 26 October 2012

ኢቲቪ እስከ ዶቃ ማሰሪያው ድረስ ተነገረው! .....አቤ ቶክቻው


በመላው ሀገሪቱ ለአረፋ በዓል የተሰባሰቡ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ዛሬም ተቃውሟቸውን አሰሙ።
ሙስሊም ኢትዮጵያውያኑ መንግስት በሃይማኖታችን ጣልቃ መግባቱን ያቁም (ነጠላ ሰረዝ) ኮሚቴዎቻችን እና ሌሎች ንፁሐን ይፈቱ (ነጠላ ሰረዝ) ምርጫው ህገወጥ ነው (ነጣላ ሰረዝ) ግድያው ይቁም (አራት ነጥብ) እና በሌላ ነጠላ ሰረዝ ደግሞ ሌሎች በርካታ ጥያቄዎችን ዎችን ከቢጫ ካርድ ጋር አንግበው ለመንግስት አበርክተውለታል!
በተለይ ኢቲቪ በገዛ ደጃፉ እስከ ዶቃ ማሰሪያው ድረስ ተነግሮታል። ኢቲቪ በእኔ ቁጥር የመገመት ችሎታ የማይደፈሩ በርካታ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጮክ ብለው ልክ ልኩን ሲነግሩት ህንፃው በሀፍረት ሽምቅቅ ብሎ አለመስመጡ እንዴት ያለ ግንበኛ ቢሰራው ነው ብለን እንድንደነቅ አድርጎናል።
“ኢቲቪ አሸባሪ” “ኢቲቪ ውሸት አውሪ” “ኢቲቪ የማታፍሪ” “ኢቲቪ ነሽ ደባሪ” “ኢቲቪ ወዲያ ቅሪ” ብለው መፈክር አሰምተዋል። (በቅንፍም መፈክሩን በግጥም ለማድረግ በማሰብ የራሴን የፈጠራ መፈክሮች መጠቀሜን እገልፃለሁ!) ከቅንፍ ውጪ በቅርቡ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የሚለቁ ተጨማሪ ሰራተኞችን እንደምናይ እናስባለን! ከእንዲህ ያለ ተቃውሞ ጋር ያለ እንከን ከሰሩ የጤና እንከን አለ ማለት ብለንም እንጠረጥራለን!
በአዲስ መስመርም መንግስት በመላው ሀገሪቱ የተሰማውን ተቃውሞ እየሰማ እንዳልሰማ ከሆነ የገዢው ፓርቲ አባላት ራሳቸው የመንግስት ተቃዋሚ ናቸው ማለት ነው ብለን እናስባለን!

ESAT DC Daily News 25 October 2012.


Wednesday 24 October 2012

ከኦሮሞ ህዝብ ጀርባ...(ከተመስገን ደሳለኝ)

እንደ መግቢያ

1975 ዓ.ም.፡፡ በመሀል ሀገር የነበረው የፖለቲካ ግለት ከብዙ ደም መፋሰስ በኋላ ወደ ጠረፍ እና የገጠር ከተሞች አፈገፈገ፡፡ በ‹‹ምርጥ መኮንኖች›› የተመሰረተው መንግስትም አንፃራዊ ሰላም ያገኘ መሰለ፡፡ አስቀድሞ ‹‹ወታደራዊ ክንፍ›› አቋቁሞ የነበረው የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) በሀገሪቱ ዋና ዋና ከተሞች ለማቀጣጠል ሞክሮት የነበረው አብዮት ከፍተኛ ዋጋ አስከፍሎት ከሸፈ፡፡ ለክፉ ቀን ‹‹አማራጬ›› ያለው ወታደራዊ ክንፉም ቢሆን ለሶስት በመከፈሉ በእጅጉ ተዳከመ (ትግል በቃን ብለው ወደ ምዕራብ ሀገራት ለመሰደድ በወሰኑ፣ ኢህአፓን ይዘን እስከመጨረሻው እንፋለማለን ባሉና ‹‹ኢህአፓ ዴሞክራት አይደለም›› በሚል ተገንጥለው ‹‹ኢህዴን›› የተባለ አዲስ ድርጅት በመሰረቱ) ከዚህ በተቃራኒው በመገንጠል እና በብሄር ጥያቄ ዙሪያ የተሰባሰቡት ሻዕቢያ፣ ህወሓት እና በሽብርተኝነት የተፈረጀው ኦነግ የተሻለ ድርጅታዊ አቅም መፍጠር ቻሉ፡፡

…በሁለት ወጣት ታጋዮች የሚመራ ከህወሓት የጦር ሰፈር (ደደቢት) የተነሳ አንድ ልኡክ ከኢትዮጵያ መንግስት የመረጃ ሰራተኞች እና የገጠር ካድሬዎች አይን ተሸሽጎ በከፍተኛ ጥንቃቄ ጉዞ ጀምሯል፡፡ መድረሻ ነጥቡ ‹‹ደባዜን›› የተሰኘች ከተማ ነች፡፡ ልኡኩ ከብዙ ቀናት በኋላ የኦሮሚያ ገጠር ከተማ በሆነችው ደባዜን ደረሰ፡፡ በወቅቱ ደባዜን የኦሮሞ ነፃ አውጪ ግንባር /ኦነግ/ ወታደራዊ ቤዝ ስትሆን ትግረኛ ተናጋሪ ታጋዮቹ ወደ አካባቢው የመጡት በድርጅታቸው ህወሓት እና ኦነግ መካከል በተፈረመ ስምምነት መሰረት ነው፤ የስምምነቱ ይዘት ‹‹የህወሓት ታጋዮች ለኦነግ ታጋዮች ወታደራዊ ስልጠና እንዲሰጡ፣ ካድሬዎችን እንዲያነቁ እና ሁለቱ ድርጅቶች በትጥቅ ትግሉም ሆነ ከትጥቅ ትግሉ በኋላ በጋራ እንዲሰሩ›› የሚል ነው፡፡ ሆኖም በሁለት የህወሓት አመራር አባል የተመራው ልዑክ ደባዜን ከደረሰ በኋላ ከኦነግ የጠበቀው አቀባበል የስምምነቱ ተቃራኒ ሆነ፡፡

ኦነግ በግልፅ ከህወሓት የተላኩትን ‹‹መርሲነሪዎች›› (ቅጥረኛ ነፍሰ ገዳዮች) ሲል አውግዞ ከወታደራዊ ሰፈሩ በፍጥነት እንዲወጡ አደረገ፡፡ በሁለቱ የአመራር አባላት የተመራው ቡድንም ወደ ትግራይ ተመለሰ፡፡ የቡድኑ መሪዎችም መላው የህወሓት የአመራር አባላት በተገኙበት ሪፖርታቻውን አቀረቡ፡፡ ሁለቱ የአመራር አባላት ክንፈ ገ/መድህን እና ሙሉጌታ ጫልቱ ነበሩ፡፡ ከዚህ ሪፖርት በኋላም ህወሓት ከኦነግ ጋር ለመስራት የነበረው ተስፋ መከነ፡፡

መለስ እና የባነር ላይ ታሪኮቹ....... ፀሐፊ፦ ጥበበ አቢዮት

የኢትዮጵያ ብዕሮች ህብረት

አዲስ አበባ አዲሱን ዓመትና መስቀልን የተቀበለቸው በአበቦች አጊጣና በችቦ ደምቃ ሳይሆን የአቶ መለስን ፎቶዎች በያዙ ሰፋፊ ባነሮች ተከፍና ነው፡፡ በመሆኑም 2005 ዓ.ምን ዘመነ ባነር ብየዋለሁ፡፡
ሁሉም የመንግስት መስሪያ ቤቶች ከአቶ መለስ ፎቶ ስር ልዩ ልዩ ጥቅሶች የሰፈሩባቸው ባነሮችን ከየመግቢያና መውጫ በሮቻቸው ላይ ማንጠልጠላቸው ግዴታ የተጣለባቸው ይመስላል፡፡ አንዳንዶቹማ የብረት አጥሮችን በሙሉ ባነር ዘርረውባቸው መስሪያ ቤታቸውን የልብስ ማስጫ አስመስለውታል፡፡ ሌሎቹ ደግሞ በህንፃዎቹ ግድግዳ ፖስተሮችን ለጣጥፈው ጭራሽ ፎቶ ቤት ለመሆን ጥቂት ቀርቷቸዋል፡፡ ኧረ ጋለሪ ሆነዋል ብል ይቀላል፡፡ ስለዚህ ጉዳይ አንስተን ከአንድ ጓደኛዬ ጋር ስንወያይ “አንደ አጀማመራቸው ከሆነ ከምንበላው እንጀራ ላይም ሳይለጥፉበት አይቀሩም!” ብሎኛል እየተንገሸገሸ፡፡
በዚህ ዘመን የፕሮፓጋንዳ ዛር ከላዩ ላይ ተሰቅሎ እየጋለበው የሚይዘውንና የሚጨብጠውን ያሳጣው የወያኔ-ኢህአዴግ አይነት የፖለቲካ ድርጅት የለም፡፡ ወያኔ-ኢህአዴግ ኢትዮጵያን በወሬ ብቻ ለማበልፀግ ፖሊሲና ስትራቴጅ ነድፎ የተነሳ ድርጅት ነው፡፡ የበሬ ወለደ ወሬዎችን በመፈብረክ በዓለም ላይ የሚስተካከለው አልተገኘም፡፡ በየጊዜው ቃላትን በማምረትም እንዲሁ፡፡ ኪራይ ሰብሳቢነት፣ ጠባቂነት፣ ኢንተርሃሞይ፣ ነፍጠኛ፣ ሽብርተኛ፣ ፀረ-ሰላም ኃይል፣ አኬልዳማ፣ ሙስና፣ ልማታዊ ምንትስ፣ ጠባብ፣ ትምክህተኛ… መች ተዘርዝሮ ያልቅና፡፡
ታድያ ይህንን ሁሉ ፕሮፓጋንዳውን የሚጠቀምበት ‘ተው ታገስ! ከጥፋትህ ተመለስ!’ የሚሉትን የአገርና የወገን ተቆርቋሪ የሆኑትን ሰላማዊ ዜጎች ለማጥቃት ነው፡፡ የፕሮፓጋንዳውን እሳት ለማራገብ የሚጠቀምበት ወናፉ ኢቲቪ ሲሆን ወናፉን በሁለት እጆቹ ጨብጦ የሚነፋው ደግሞ “የሁለት ምርጫዎች ወግ” መፅሃፍ ደራሲ ኮሚኩ በረከት ስምኦን ነው፡፡ “የኮሚኬሽን” ጉዳዮች ሚኒስትር እሱ አይደል በቃ ስራው ይህን ገራገር ህዝብ መኮመክ ብቻ ነው፡፡ ዓይኖቹን እያስጨፈነ ማሞኘት፡፡
እናም አዲስ አበባችን ከዋና ከተማነት ወደ አቶ መለስ የፎቶ አልበምነት ተቀይራ አሸብርቃ አምሮባት ከረመቻታ፡፡ ስለሆነም በዋና ዋና ጎዳናዎቿ ዳርና በህዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋሞቿ አጥር ላይ ከተሰቀሉት የመለስን ፎቶ ከያዙ ግዙፍ ግዙፍ ባነሮች ላይ ተፅፈው ካነበብኳቸው ህልቆ መሳፍርት ጥቅሶች መካከል እጅግ በጣም ጥቂቶችን በማንሳት እውነታነታቸውን ለመመርመር ፈለግሁ፡፡

ኦህዴድ ለአራት ለመሰንጠቅ ጫፍ ላይ ደርሷል ........ ፍኖተ ነጻነት



ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በኋላ በተደጋጋሚ ተሰብስቦ መግባባት ያልቻለው ኦሮሞ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት /ኦህዴድ/ በአራት ቡድን ተከፍሎ ውዝግብ ውስጥ እንደገባ የውስጥ አዋቂ ምንጮች ገለፁ፡፡ ለፓርቲው ቅርበት ያላቸው የፍኖተ ነፃነት ታማኝ የዜና ምንጮች እንደሚያረጋግጡት ኦህዴድ በአሁኑ ጊዜ በግልጽ ለአራት ቡድኖች ተከፍሏል፡፡ ቡድኖቹ 1 ኦህዴድ- መለስ 2 ኦህዴድ-አባዱላ 3 ኦህዴድ- ኦሮሚያ 4 ኦህዴድ- አድፋጭ በሚል የሚታወቁ ሲሆን፣ የተካረረ ፍጥጫ ውስጥ የመግባት አዝማሚያ ታይቶባቸዋል፡፡ ምንጮቻችን እንደሚያስረዱት ኦህዴድ- ለመለስየሚባለው ቡድን ከህውሓት ጋር
የቀረበ ግንኙነት ያለውና ከመለስ ራዕይ ውጪ ምንም ዓይነት ሐሳብና እንቅስቃሴ ማድረግ የለብንምየሚል ክርክር በማንሳት ኦህዴድ ውስጥ የተጀመረውን የስልጣን ይገባኛል ጥያቄ እንዲጠፋ ጥረት የሚያደርግ ነው፡፡ የመለስ እቅድሳንሸራርፍ መተግበር አለብን ብለው ራሳቸውን ያሳመኑት የዚህ ቡድን አባላት
ከዚህ ሐሳብ ውጪ የሚያስቡትን እንደ ከሐዲ የሚፈርጁ ናቸው፡፡ በዚህ ቡድን ውስጥ ሙክታር ከዲር፣ ኩማ ደመቅሳ፣ አስቴር ማሞና ዘላለም ጀማነህ እንደሚገኙበት የዜናው ምንጮች ተቁመዋል፡፡ ሁለተኛው ቡድን ኦህዴድ -አባዱላየሚባል ሲሆን የአባዱላን ወደ ክልሉ ፕሬዝዳንትነት ለመመለስ ከመጣር ውጪ ከመጀመሪያው ቡድን ጋር መሰረታዊ የሀሳብ ልዩነት የለውም፡፡ ኦህዴድ ከዚህ ቀደም እንደነበረው ከኢህአዴግ/ ህውሓት የሚሰጠውን መመሪያ እየተቀበለና እያስፈፀመ መቀጠል አለበት፡፡ በድርጅት ስምና በኦሮሞ ህዝብ ስም የፌደራል ስልጣን መጠየቅ ከድርጅቱ ዓላማ መውጣት ነው፡፡ ክልላችንን እስካስተዳደርን ድረስ ለፌዴራል ሥልጣን መጨነቅ የለብንም፡፡ ከህውሓት ጋር ግጭት ውስጥ መግባት የለብንምየሚሉት የቡድኑ አባላት ውስጥ ውስጡን ግን ኦህዴድ በፌደራል ደረጃ ተገቢውን ውክልና ባለማግኘቱ የተነሳውን ተዋውሞ በተወሰነ ደረጃ የመቀበል አዝማሚያ ይታይባቸዋል፡፡ በዚህ ቡድን ውስጥ አፈጉባኤ
አባዱላ ገመዳና የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር አለማየሁ ተገኑ እንደሚገኙበት ምንጮቻችን አስረድተዋል፡፡ ኦህዴድ- ኦሮሚያ የሚባለው ቡድን ኦህዴድ የኦሮሞን ህዝብ መብትና ጥቅም ማስከበር አለበት፡፡ ድርጅቱ ከህውሃት ጥገኝነት መላቀቅ ያለበት ሰዓት ላይ ደርሷል፡፡ ድርጅቱ በአማራ ህዝብ ላይ እንዲከተል የሚደረገው የጥላቻና የብቀላ ፖለቲካ ማቆም አለበት፡፡የሚል ሀሳብ ይዞ የሚሟገት ሲሆን የኦህዴድ ተጠሪነትም ሆነ አገልግሎት ለአሮሞ ህዝብ ብቻ መሆን ይጠበቅበታል፡ በድርጅቱ ውስጥ የህውሓት ተላላኪ የሆኑትን ግለሰቦች ከአመራርነት ማስወጣት አለብን፡፡ የሚል ጠንካራ አቋም የሚያራምድ ቡድን ነው፡፡ የኦሮሞ ህዝብ በፌዴራል ደረጃ ተገቢውን ውክልና ማግኘት አለበት፡፡የሚሉት የቡድኑ አባላት መካከለኛውንና ወጣት አመራሮችን ድጋፍ ማግኘት የቻሉ ሲሆን የድርጅቱን መካከለኛ ካድሬዎች ሀሳብ ወደ አመራሩ እዳመጡ ምንጮቻችን አስረድተዋል፡፡ ከመካከለኛውና ወጣት አመራሩ ውጭ አቶ አለማየሁ አቶምሳና አቶ ጁኔዲን ሳዶን ጨምሮ ሌሎች የድርጅቱ ጠንካራ አመራሮች በዚህ ቡድን ውስጥ እየተሰባሰቡ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል ፡፡ አራተኛው ቡድን ኦህዴድ- አድፋጭ

ሐሙስን ከሚኒስትሩ ጋር!

ዕለቱ ሐሙስ ነው፡፡ ቀኑ ደግሞ ‘08’፡፡ ወርሃ ጥቅምት፡፡ የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የኢህአዴግ ግንባር ቀደሞች ተሰብስበናል፡፡ በታሪካዊው የ”FBE” አዳራሽ፡፡ ታሪካዊ ማለቴ ቆራጡ መንጌ የፖለቲከ ርዮት ያጠጣበት የነበረ አዳራሽ በመሆኑ ነው፡፡ ካለመናችሁ ወንበሮቹን እዩአቸው፡፡ መደገፊያዎቹ ላይ “ፖ/ት ይላሉ፡፡ ፖለቲካ ት/ቤት እንደማለት፡፡
በቀኝ እጃቸው ሴ
ቷ ማጭድ ወንዱ መዶሻ ይዘው ግራ እጃቸውን “የሁሉም ሐገር ሠራተኞች ተባበሩ!” የሚል መፈከር ያነገቡ የሚመስል ቅርፅም መግቢያው ላይ አለ፡፡ እናስ ታሪካዊ አይደለም ትላላችሁ?! እኛም ግንባር ቀደሞቹ በዚህ ታሪካዊ አዳራሽ ታሪካዊ ስብሰባ እያደረግን ነው፡፡ ሰብሳቢዎቻችን ደግሞ የፌዴራል ጉዳዮች ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ሽፈራው ተክለማርያም እና የ ዩኒቨርስቲያችን ፕሬዝዳንት ዶ/ር አድማሱ ፀጋዬ ናቸው፡፡
ከጠዋቱ 3፡00 ከአራቱ የኢህአዴግ ብሔራዊ ድርጅቶች የተውጣጣን ግንባር ቀደሞች አዳራሹን ሞላነው፡፡ የመሰረታዊ አደረጃጀት አመራሮች በር ላይ ሆነው ግንባር ቀደም ያልሆነውን ግንባሩን አዙሮ እንዲሄድ ለማድረግ በጥንቃቄ እየለቀሙ ያስገባሉ፡፡ አዳራሹ ከአፍ እስከ ገደፉ ሞላ፡፡ ስብሰባው ለታላቁ መሪያችን ጸሎት በማድረግ ተጀመረ፡፡ ክቡር ሚንስትሩ አጀንዳውን አስተዋወቁ፡፡ ስለ ‘አክራሪነት’ ነው፡፡ አቶ አምባዬ የተባሉ ሰው (ይቅርታ ማዕረጋቸው ስላልተነገረን) ያዘጋጁትን ጽሑፍ “በፕሮጀክተር” ዘረገፉት፡፡ የቀረ የለም፡፡ ሁለም በአክራሪነት ተፈርጇል፡፡ አንዳንድ ዋሃቢያዎች… አንዳንድ ሰለፊዎች… አንዳንድ ካዋርጃዎች… አንዳንድ ማኅበረ ቅዱሳኖች… አንዳንድ…፡፡ አክራሪዎች ናቸው ተባለ፡፡ ከንጉሡ ጀምሮ እስከ አምባ ገነኑ ደርግ ድረስ የሃይማኖት እኩልነትና ነፃነት እንዳልነበር አስተጋቡ ፤ የዛሬውንም መንግሥት ቸርነት ሰበኩ፡፡ አቶ አምባዬ ረጅሙን ትንተናቸውን ሲጨርሱ ክቡር ሚንስተሩ ተተኩ፡፡ ትንሽ ላጠናክረው ብለው አንዳንድ ነገሮችን አንስተው በአንዳንዶች ላይ ዙሩን አከረሩት፡፡ እኝህ ክቡር ሚኒስትር ንግግራቸው ጠንካራ ነው ፤ ልክ እንደ ጓዳችን፡፡ ትንሽ የሚለዩት በአማርኛቸው ነው፡፡ ያዝ! ያደርጋቸዋል፡፡ የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ 90/2/ን ተነተኑት፡፡ “ትምህርት ከፖለቲካ ፤ ከሃይማኖት እና ባህላዊ ተፅዕኖ ነፃ በሆነ መንገድ መካሄድ አለበት” ይላል አሉ፡፡ በእርግጥ እሳቸው ከ‘ሃይማኖት’ የሚለው ላይ ነው ጠበቅ ያሉት፡፡ ይሄኔ ከጎኔ የተቀመጠው ግንባር ቀደም ጓደኛዬ “what about this” አለኝ፡፡ በዩኒቨርስቲ ግቢ ውስጥ ፖለቲካ እየሰበኩ እንዴት ነው አንቀጹ የሚነሳው ማለቱ ነው፡፡ የአይኖቼን ቅንድቦች ብቻ ከፍና ዝቅ በማድረግ “እኔም አልገባኝ!” አልኩት፡፡ ክቡር ምኒስትሩ ማጠናከሪያቸውን እስኪበቃው ድረስ እንደ ብረት ካጠነከሩት በኋላ መድረኩ ለውይይት ክፍት ሆነ፡፡
የመጀመሪያው ተናጋሪ ‘ማይኩን’ ተቀበለ፡፡ ወደፊት አካባቢ ስለነበር አካላዊ ገፅታው አይታየኝም፡፡ ድምፁ ግን ወፍራም ነው፡፡ “በእውነቱ ዛሬ የተወያየንበት ነገር በጣም አስፈላጊ ነው ብዬ አላምንም፡፡ እህ! (ድምፁ ይበልጥ እየወፈረ መጣ) ሥራ አጥነት አገብጋቢ ሆኖብን ፣ ተምረን መውደቂያ እያጣን እናንተ አክራሪነት ትላላችሁ!” ከባድ ጭብጨባ፡፡ ክቡር ሚንስትሩ ገላመጡን፡፡ “ስሙ! ይሄ ጭብጨባ እኮ የደርግ መገለጫ እንጂ የግንባር ቀደሞች አይደለም፡፡ ደርግ ነው በባዶ አዳራሽ የሚያስጨበጭብ፡፡” ሌላም ተግሳፅ አወረዱብንና ለሌላኛው እድል ሰጡ፡፡ ሁለተኛው ተናጋሪ ስሙንና ድርጅቱን ተናግሮ ቀጠለ “እኔም የምለው ነገር ስለ ሥራ ነው፡፡ ሥራ ስጡነ ስንል ‘ኮብልስቶን’ ስሩ ትሉናላችሁ፡፡ የተማረውም ያልተማረውም ‘ኮብልስቶን’ ከሰራ ልዩነቱ ምንድነው?” ደማቅ ጭብጨባ ፤ በጭብጨባው ታግዞ ንግግሩን አረዘመ፡፡ “እናንተ መብታችሁ ተከብሮ ትላላችሁ የትኛው መብታችን ነው የተከበረው? በቀደም ለታ እሁድ ቀን ኳስ ልናይ ከተሰለፍንበት ፌደራል ቀጠቀጠን፡፡ ስንቱን ሽባ አደረገው፡፡ ደሞ… ምን መብት አለነ፡፡” ሌላ ጭብጨባ… “ደሞ ሚዲያዎቻችን ውሸት ብቻ ነው ሥራቸው፡፡ ትናንት በቴሌቭዥን 40 ኩንታል ጤፍ በጭልጋ ተመረተ ሲል ነበር፡፡ እኔ ራሴ የጭልጋ ልጅ ነኝ፡፡ እንኳን 40 ኩንታል አንድ ገበሬ ሊያመርት 4 ኩንታልም የለ፡፡ ይህ ለምን ነው እሚዋሽ? እንዴ! ነውር አይደለም?” አዳራሹ በሁካታ ተሞላ፡፡ የ‘ህዋስ’ አመራሮች ዐይናቸውን ማፍጠጥ ጀመሩ፡፡ የአንዳንዶቹ ጉንጭ የበሰለ ቲማቲም ይመስል ጀምሯል፡፡ ክቡር ሚንስትሩ ድምፅ ማጉያውን አበሩ፡፡ “ጎበዝ! ይሄ እኮ የግንባር ቀደሞች ስብሰባ መስሎኝ ነበር (ትንሽ ፋታ ወስደው)… እና እንግባባ፡፡ አታጨብጭቡ ማለት አታጨብጭቡ ነው፡፡ በቃ!... እንስማማ እንጂ…”

ከሚሴ በልዩ ሁኔታ በፌደራል ፖሊሶች ተወራለች


ጥቅምት ፲፫ (አስራ ሶስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በደቡብ ወሎ ከሚሴ አካባቢ በፌደራል ፖሊሶች ከወትሮው በተለየ ሁኔታ መከበቦን ነዋሪዎች ገለጡ::
ከከሚሴ ኢሳት ሬዲዮ ያናገረው አንድ ሙስሊም እንደገለጠው የአካባቢው ሰዎች በግዴታ ስብሰባ እንዲያደርጉ ተጠርተው ሽብር ፈጥራችኋል፤ ከዚህ ተግባራችሁ ታቀቡ ያለበለዚያ ግድያው ይቀጥላል ብለው እንዳስፈራሯቸው ገልጠዋል::
ከትላንት በስቲያ በገርባ ፖሊሶች በሰላማዊ መንገድ ሰላማዊ ጥያቄ ባነሳው የሙስሊሙ ህዝብ ላይ ተኩስ ከፍተው ሁለት ሰው ከገደሉና ሌሎችን ካቆሰሉ በሆላ የተፈጠረው ውጥረት እንደቀጠለ መሆኑን የገለጡልን የአካባቢው ነዋሪዎች፤ ጥያቂያቸው መልስ እስካላገኘ ድረስ ተቃውሞቸውና ጥያቄያቸው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል::
ከተለያዩ ቦታዎች በዳፍ መኪኖች የተጫኑ የመከላከያ ሰራዊትና የፌደራል ፖሊሶች በከሚሴና በደሴ አካባቢ እየገቡ መሆናቸውን የገለጹልን ምንጮቻችን፤ በወታደርና በመሳሪያ ጋጋታ ጥያቂያችንን ለማፈን የሚደረገው ጥረት አይሳካም ብለዋል::
በመንግስት ተይዘው የታሰሩ የሙስሊሙ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አመራር አባላት እንዲፈቱን ጨምሮ የተለያዩ ጥያቄዎች ይዘው የተነሱት ሙስሊሞች ጥያቄቸውን በሰላማዊ መንገድ ተቃውሞ ማሰማት ከጀመሩ ወራቶች ያለፉ ሲሆን፤ በተለይ ከትላንት በስቲያ በሰላማዊ ሙስሊሞች ላይ የመንግስት ወታደሮች የወሰዱት የግድያ እርምጃ አለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሀን የዜና ሽፋን እየሰጡት ይገኛል::
በዚህ መሰረት የእሁዱን ግድያ ከዘገቡት መሀከል ቺካጎ ትሪቡን ኒውስ ቱዌኒ ፎር እና ኦል አፍሪካ ይገኙበታል::

Tuesday 23 October 2012

DW:- "የኢትዮጵያ ህዝብ ለዲሞክራሲ ብቁ አይደለም"......አቦይ ስብሃት ነጋ


ኢሳት ዜና:-አቶ ስብሀት ይህን ያሉት <የኢትዮጵያ የውጪ ጉዳይ ፖሊሲ ከ አቶ መለስ ሞት በሁዋላ ምን ለውጥ ይኖረዋል?>በሚል ርዕስ ከጀርመን ምክር ቤት አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት ነው። በበርሊን በተደረገውና ኢትዮጵያ፤ኬንያ እና ማላዊ ላይ ባነጣጠረው በዚሁ ስብሰባ ኢትዮጵያን ወክለው የተገኙት አቶ ስብሀት ነጋ አቶ መለስ ቢሞቱም ፖሊሲን በተመለከተ ምንም ዓይነት ለውጥ እንደማይኖር ተናግረዋል። <<መለስ አንድ ሰው ነው፤በ አንድ ሰው ሞት የድርጅቱ ዓላማ አይቀየርም፤ስለዚህ በ ኢትዮጵያ መንግስት በኩል የፖሊሲ ለውጥ አይኖርም” ነው ያሉት አቶ ስብሀት። መንግስታቸው የደርግ ተከታዮችንና የፊውዳል ርዝራዦችን ለመቆጣጠር ብዙ ዓመታት እንደሠራ የጠቀሱት አቶ ስብሀት፤<<በደርግ የተበላሸውን የ ኢትዮጵያ ህዝብ ለማስተማር ብዙ ጊዜ አጥፍተናል>ብለዋል። ንግራቸውንም የዘጉት፦<የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዲሞክራሲ ብቁ አይደለም>> በማለት ነው። መድረኩ ለውይይት ክፍት መሆኑን ተከትሎ በስፍራው የተገኙት ኢትዮጵያውያን በ አቶ ስብሀት ላይ ጠንካራ የተቃውሞ ጥያቄዎችንና አስተያየቶችን ሰንዝረዋል። በተለይ አንድ ተናጋሪ፦<<የኢትዮጵያ ህዝብ ሥርዓት ያለው ሕዝብ ነው። ከላይ ሆናችሁ በቴሌቪዥንና በሚዲያዎቻችሁ ጭምር እየተሳደባችሁ ሰውን ሥነ-ስርዓት እንዳይከተል ያደረጋችገሁት እናንተ ናችሁ”ብለዋል። <<ባለፉት ዓመታት የብዙሀንን ንጹሀን ደም በከንቱ አፍስሳችሁዋል>> በማለት በአቶ ስብሀት ተቃውሟቸውን ያሰሙ ሌላው ኢት ዮጵያዊ፦<< በኬንያ የሰው ደም ያፈሰሱት ለፍርድ እንደቀረቡ ሁሉ እናንተም ለፍርድ ልትቀርቡ ይገባል”ብለዋቸዋል። ከዚህም ባሻገር በ 1997 ምርጫ ወቅት የተገደሉትን ኢትዮጵያውያን ፎቶግራፎች በመያዝ ወደ ስብሰባው የመጡ ኢትዮጵያውያን፤ ሟቾቹን ፎቶዎች ለጀርመኑ የምክር ቤት አባላትና ለስብሰባው ታዳሚዎች በማሳየት አቶ ስብሀትና መንግስታቸው በደም የተጨማለቁ ወንጀለኞች መሆናቸውን አሳይተዋል። ሌሎች በርካታ ኢትዮጵያውያንም በስብሰባው በመገኘት በአቶ ስብሀት ላይ ተቃውሟቸውን ሰንዝረዋል። በስተመጨረሻም ስብሰባውን ሲመሩ ከነበሩት ጀርመናውያን አንዷ፡- ከ ኢትዮጵያ ተወካይ ጋር መወያዬት ያስፈለገው ከ አቶ መለስ በሁዋላ ምን ዓይነት ለውጥ ይኖራል?በሚለው አጀንዳ ላይ እንደነበር፤ሆኖም ምንም ለውጥ እንደማይኖር መነገሩን በመጥቀስ የኢትዮጵያን አጀንዳ እንደዘጉት የደቸ-ቨለ ሪፖርት ያስረዳል። አቶ መለስ መሞታቸውን ተከትሎ ወደ መድረክ መውጣት ጀመሩት አቶ ስብሀት በቅርቡ ከ አዲስ ጉዳይ መጽሔት ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ አንዳንድ ተቃዋሚዎች ስለ ጥምር መንግስት ባላቸው ሀሳብ ጉዳይ ለቀረበላቸው ጥያቄ፦<እነዚህ ጥምር መንግስት የሚሉ ተቃዋሚዎች በህጋዊነት መቀጠል አለባቸው?ወይስ የለባቸውም?”በሚለው ነጥብ ዙሪያ ከምርጫ ቦርድ ጋር እነጋገርበታለሁ”ማለታቸው ይታወሳል።

“የመለስ ራዕይ” እየተተገበረ ነው! ከአቤ ቶክቻው

በምርጫ ዘጠና ሰባት ሰሞን በጠቅላይ ሚኒስትሩ እዝ ስር የሆነው መሳሪያ የታጠቀው ሃይል አንዱ ከአንዱ በመተባበር ከምርጫ ጋር ተያይዞ በመጣ ቀውስ ምስኪኑን ህዝብ በተለይ በሰኔ 97 እና በጥቅምት 98 ዓ.ም እያለሙ አጥንቱንም ቅስሙንም ህይወቱንም ይሰብሩት ነበር።
ታድያ በተለይ የጥቅምቱን ግድያ የተመለከቱ አንድ አዛውንት “እነዚህ ሰዎች በጥቅምት አንድ አጥንት ሲባል የሰው አጥንት መስበር መሰላቸው እንዴ!?” ብለው በህመማችን እንድንስቅ አድርገውን እንደነበር ከዚህ በፊትም አውግተናል።
ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩት መለስ ዜናዊ ትላንት በእርሳቸው እዝ ሲገደሉ የነበሩ ሰዎች ዘንድ ሄደዋል። እነዛ ምስኪን ሟቾች መለስን ሲያገኟቸው እንዴት ያደርጓቸው ይሆን? ብዬ ልጠይቅ ነበር ለካስ የገደለ እና የተገደለ ቦታው ለይቅል ነው!
በነገራችን ላይ ባለፈው ግዜ ኢሳት ቴሌቪዥን “ሰብዓዊ መብት” በተባለው ፕሮግራሙ አንድ ዶክመንተሪ አሳይቶን ነበር። “ባለ ራዕዩ” መሪ ያስገደሏቸውን ሰዎች የሚዘክር ዶክመንተሪ። ይህንን ፕሮግራም የተከታተለ አንድ በአዲሳባ የሚገኝ ወዳጄ፤ “ባለፈው “ህዝቡ ሲያለቅስላቸው” አሳዝነውኝ እኔም አልቅሼ ነበር። ለካስ ይሄንን ሁሉ አድርገውናል!? በእውነቱ ለቅሶዬ ተጭበርብሯል ቤተመንግስት ሄጄ እንባ መልስ ጠይቃለሁ!” ብሎኛል። የምርም አቶ መለስ እኔ ራሴ ካሰብኩት በላይ ነፍስ በእጃቸው ጠፍቷል። የሆኑ ሰው የማይበረክትላቸው ሰው ነበሩና!
ከመለስ በኋላ አዲስ ባለ ራዕይ ንጉስ ይመጣልናል ብለን ብንጠብቅ “ከኔ በፊት የነበረውን ጫማውን እንኳ ልሰም አቅም የለኝም! እኔ የርሱን ራዕይ አስፈፅማለሁ እንጂ ከኔ ራዕይ አትጠብቁ!” ብለው የተናገሩት ሰውዬ መጡ!
አሁን የመለስ ራዕይ በአግባቡ እየተፈፀመ እንደሆነ ተጨባጭ ነገሮች እየታዩ ነው