Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Saturday 21 July 2012

Junedin Saddo Receiving Treatment after Car Crash


Junedin Sado, Ethiopian Civil Service Minister

July 21 (OPride) – Ethiopia’s Minister of Civil Service, former President of Oromia regional state and minister of Science and Technology, Junedin Saddo, is reportedly receiving treatment in South Africa after a car crash.
According to OPride sources, the incident occurred earlier this week near Kaliti, on the entrance to the capital, Addis Ababa. It is not immediately clear if foul play was involved. There was a brief report on social media about the crash but his whereabouts had since been unknown.
Mr. Saddo’s wife, Habiba Mohammed, is in detention suspected of aiding Muslim protesters opposed to the government’s interference in religious affairs. Mrs. Saddo was nabbed on July 17 at the Saudi embassy while trying to flee the country, sources told OPride.
Quoting Addis Ababa-based weekly Amharic newspaper, Sendek, De Birhan blog reported, Mohammed was arrested upon exiting the embassy after meeting with Fahadel Kahatani, Saudi Arabia’s religious attaché in Addis Ababa, “with a large sum of money and over 800 books written in Arabic language.”
A source close to the Junedi’s, who asked not to be named due fear of retaliation, told OPride that the government alleges Mrs. Saddo was trying to run away with the money. She is now being held at Maikilawi and no one has access to her.
Ethiopia’s ruling party, now in power for two decades, is cracking down harshly on peaceful protesters and their leaders. The Ethiopian Muslims have been demanding religious freedom and protesting against government interference for eight months now – an unprecedented development for a country known to the outside world mostly for its dominant Christian faith.
According to the protesters’ own official Facebook account, Dimtsachin Yisema (let our voices be heard), all but a few of the movement’s leaders are at large, with many detained overnight. The 17-member Islamic Arbitration Committee was selected by the protesters to arbitrate between Muslim protesters, the Islamic council, Mejlis, and the government.
Ahmedin Jebel, the group’s outspoken spokesperson was taken from his house last night, allegedly beaten by police and is now being held at Maikalawi prison. The houses of those not arrested had also been ransacked, the group said. According to De Birhan, Jebel, who has been arrested in the past for writing about religion and politics in Ethiopia, is “regarded by many as the man behind the horizontally structured protest movement.” Jebel was quoted in various news reports over the last few days.
Earlier today, shortly after Salatul Asr, police stormed the Anwar mosque compound before the protesters made their way out. “The police came out of no where and encircled the mosque,” Ismail told OPride from Addis Ababa. “At least 50,000 worshipers are trapped inside the mosque compound, literally stepping on each other’s toes.”
Other reports via Twitter and Facebook, seemingly the only two sources of information at the absence of media coverage, confirm that the riot police was everywhere and a tear gas was used against the protesters. No casualties were reported in today’s scuffle. According to Ismail, there is a general uneasiness in Addis at the moment. “But some people are screaming, crying and running toward tear gas in defiance,” he said. “Others are fleeing the scene…there is so much chaos,” he said in a phone interview from the mosque.
At least three military trucks have taken hundreds of protesters to an unknown location, according to Ismail. All roads leading to and from Merkato, Africa’s biggest open market, near Anwar mosque, have been blocked.
The government mouthpiece, ETV, confirmed the arrest of what it called “several extremists” and the group’s leaders. Although the government have been negotiating with the committee for months, Deputy Police Commissioner, Girma Kassa referred to the committee as “unlawful self-appointed group.” The protesters have been chanting “Islam is peace” and remained peaceful even when provoked. Eyewitnesses interviewed for this report said the activists did no throw rocks.
Mr. Saddo, who is seen as an able technocrat, was one of those accused by the protesters for pushing Meles Zenawi’s scheme to silence Muslim activists. The government, particularly the ministry of Federal Affairs, is blamed for using the resources of the state to crop up a pro-regime religious sect, Al-Ahbash, which did not have a footing in the country.
It is to be remembered that Hassan Ali, the former president of Oromia, who fled the country and settled in Atlanta, Georgia, faced a similar fate. Many say that the arrest of his wife is a harbinger of Mr. Saddo’s downfall

Ethiopia: Last remaining independent newspaper suspended



The authorities in Ethiopia have suspended publication of the Amharic-language weekly Fitih, an editor said today, after
Temesgen Desalegn Fteh newspaper publisher (PHOTO: FACEBOOK)
Temesgen Desalegn Fteh newspaper publisher
he refused to take out the front page news regarding the condition of Prime Minster Meles Zenawi, an issue that has preoccupied the nation.
The editor of the weekly, Temesgen Desalegn said today that the paper, Fitih, didn’t see the light of the day on Friday following a request by state-owned printing enterprise to take out the article. “The manager of the Berhanen Selam Printing Enterprise informed me that they had received orders from higher officials not to print the paper unless I take out the news item. We had a lengthy discussion about the matter, and I was later assured that the paper would come out on Saturday, “said Temesgen.
That didn’t happen. A letter written by the Ministry of Justice to the printing press today says the paper had been suspended. The letter did not elaborate on the matter but Temsegen said the reason was because he decided to “publish an article that was a threat to national security,” he was told. The entire, 30,000 copies edition is now locked in the printing press’s warehouse.
Recently there has been wide condemnation against the country’s main, state-owned printing enterprise that directed newspaper publishers to censor any content that may draw government prosecution under the country’s anti-terrorism law or face cancellation of their printing contracts.
Fitih was one of the last remaining weeklies that take critical stance against the government after papers with similar were closed down. The paper in the past was accused of “writing untruthful information” and “negative reporting and tarnishing the image of the ruling coalition,” – charges that the editor denied. The state prosecutor has brought more than 30 charges against the weekly. Temesgen was summoned by police a couple of times to hear the charges against him.
Ethiopia has arrested close to 200 people, among them journalists and opposition politicians and members, under last year’s anti-terrorism proclamation. According to the Committee to Protect Journalists, more journalists have fled Ethiopia than any other country in the world.

UPDATE: Arrest and savage beating of Ethiopian Muslims currently underway

July 21, 10 AM PM EST
The Woyanne junta security forces are savagely beating and rounding up young Muslims in the streets of Addis Ababa. Muslim leaders are also being rounded up. Shops are being closed… [ባሳለፍነዉ እሁድ ክዋስ ሜዳ በሚገኘዉ የኢትዮጵያና የምስራቅ አፍሪካ ታላቁ የዳዕዎ መርከዝ የዳዕዎ ሰዎች መደበኛ የሶስት ወር ሹራ ለማድረግ ከተለያዩ ቦታዎች ተሰብስበዉ የነበረ ሲሆን በስብሰባዉ ለተገኙ ሙስሊሞች የተዘጋጀዉን ምግብ የፌደራል ፖሊስ ለሰደቃ የተዘጋጀ ነዉ በማለት ምግቡን ማስደፉቱ ተገለፀ!!

በዛሬው እለት በታላቁ አንዋር መስጂድ ከ1.5 ሚሊየን በላይ ሕዝበ ሙስሊም እጅግ ሰላማዊ የሆነውን ተቃውሞ በአስጨናቂ ዝምታ ገለፀ መንግስት ኢስላም ላይ የከፈተውን ዘመቻ የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ ሕዝበ ሙስሊሙ ተቃውሞውን አሰምቶአል ከመፈክሮቹ ውስጥ ኮሚቴዎቻችንን መንካት ሕዝበ ሙስሊሙን መንካት ነው !! መብትን መጠየቅ ካሳሰረ ለመብታችን ለመሰዋት ዝግጁ ነን !! በሚዲያ ስም ማጥፋቱ ይቁም !! ሕገ መንግስቱ ይከበር !! መንግስት ከኀይማኖታችን ላይ እጁን ያንሳ !! የሚሉና ሌላ ብዙ መፈክሮች ታይተዋል:: በዛሬው የጁመዐ ሠላት ላይ የሕዝቡ ብዛት ከወትሮው የተለየ ነበር ሕዝቡ በሲኒማ ራስ እስከ ተክለ ኀይማኖት በጣና ገበያ እስከ መርካቶ ባስ ስቴሽን በበፒያሳ እስከ ሀብተ ጊዮሪጊስ በአውቶቢስ ተራ ጎጃም በረንዳን አልፎ ነበር:: ኢቲቪና መንግስት እንደሚሉት ይሔ ሁሉ ሕዝብ አሸባሪ ከሆነ ሀገሪቱ ውስጥ መንግስት የለም ማለት ነው::...]

July 20, 8:00 PM EST
The Woyanne junta has charged Ethiopian Muslim leaders with terrorism today in court
July 20, 6:00 PM EST
At the Anwar Mosque in Ethiopia’s capital Addis Ababa today over 1.5 million Ethiopian Muslims protested silently and peacefully against the Woyanne junta’s intervention in their religion. The regime has arrested several Mulsim leaders, but its action caused even more anger from Muslim Ethiopians

Ethiopia at Crossroads: What has to be done?

by Neamin Zeleke
Ethiopia at CrossroadsNews of Meles Zenawi’s deteriorating health offer an opportunity for reflection on his legacy and preparation for the day after his eventual demise. Whether Meles Zenawi passes away in the coming days or at some times in the future, we need to grapple with some serious vexing questions on where we are and where we are heading as a people and nation.
First, on the past two decades: What is Meles’ legacy? How will he be remembered? How was he able to squander unique opportunity to bring about an enduring democratic process and freedom in Ethiopia? What should we learn from the process that resulted in replacing one dictator with another? In particular his successors who are said to be locked in power struggle over succession should pause for a moment and reflect, if at all endowed with an iota of wisdom?  What factors enabled Meles to institute dictatorship and misrule for so long? What are the over-arching results of his policies? Did Meles’ policies brought Ethiopia closer to the goal of building a society bound by common purpose and united in building a strong and prosperous democratic nation or did it succeed in fracturing the society along ethnic and religious lines? We have to look back to go forward.
The future holds limitless possibilities and enormous potentials. Yet again, like all possibilities we can use it or lose it. Lack of vision and preparation will guarantee that we lose again.  To acquire the right vision, we need to answer some of these questions: What are the tasks awaiting the future leadership in rebuilding the nation and the national spirit? What are the challenges?
Assuming Meles’ is gone tomorrow, is the opposition ready to play any role? What should the role be inside and outside Ethiopia? Who should the opposition engage? On what terms? What preconditions? Should it engage without preconditions? What is the goal? The goal must be building the framework of enduring, true democracy, protection of human rights and individual freedom. Who are the players? What is their record on these principles? What about the army? Will it stay neutral? Will it take sides? With whom and why?
What should the role of western democracies and the US in working with groups committed to these principles. How can the opposition begin to strengthen and prepare itself to present a formidable power block? What are the lessons from previous coalitions and alliances? What type of coalition or collaboration should be formed? Should it be based on broad principles or specifics? Should it strive to be overly inclusive or selective? Is there a benefit to forming competing power blocks that loosely cooperate with one another where differences cannot be bridged among opposition groups? What are the metrix? These are but some of the questions that need speedy responses and actions.
Indeed Ethiopia is at a crossroads. We find ourselves, once again, at a moment of anxiety and uncertainly with the aforementioned and  plethoras of  other questions instead of clear answers leading towards the path of freedom, democracy and prosperity. A reflection and sober assessment of the balance sheet of Meles Zenawi regime’s as well as a reexamination of the very principles and vision we have espoused for the past decades are in order. Such very moments test our resolve, our backbone, and most importantly, our character to make reality many have struggled for and paid the ultimate sacrifice.
We need vision, principle and courage! We need individuals and groups to come together with common purpose and wedded to no other interest than to enshrine in our nation freedom, justice, and democracy for all citizens.
Make no mistake about it, whether we learn of Meles’s demise tomorrow or not, we have reached a watershed moment. The beginning of the end of the dictatorship demands from all forces of freedom and democracy the vision and courage to speak and act in unison. We should take stoke of lessons of past divisions. They did not get us anywhere. Past machinations, past power struggle, egos, and posturing have weakened us while strengthening Meles Zenawi’s position. The task is bigger than one person, one party, or one ethnic group. Individual ego and group loyalty, the Achilles Hill of the opposition forces, must give way to humility, common goal, and dedication to the common good. Let’s take positions not because they are our positions, but because they are the right positions. Let’s be open to change course if it becomes rational, logical and reasonable to do so. The time demands more pragmatism and less dogmatism. It is high time and the right time to do that right thing for the right reasons in the right way.
At this crucial juncture, it is imperative that all forces that aspire to bring freedom, democracy, and justice in Ethiopia, whether political or civic, armed or unarmed, ethic or multi-ethic, etc– create an alternative center and a unified voice. We don’t have to create a coalition or union. But we need to fight for a common goal. We need to support each other, find common ground and build positive relationships. This could be done based on a very bare minimum shared objective, a unity of purpose and political course of action. We can unite under an overarching principle to bring about a transition to a genuine and enduring democratic order in Ethiopia. We can agree that all stakeholders will participate in an all-inclusive transitional process.
The Western powers including the US can play a positive and constructive role as well. The western nations can help by becoming honest brokers towards a transition to a genuine democracy in Ethiopia instead of pursuing a continuation of the current cynical policy of providing support to yet another dictatorship, a post Meles status qou of his TPLF/EPRDF successors in the name of regional stability like they have been doing for the past two decades.
Ultimately  it is we , Ethiopians, who should come to an agreement  and work for the following for now  a) a speedy agreement by all stakeholders within the ranks of freedom and democracy forces  to speak with a unified voice , b) a call to the various sectors of the Ethiopian society that have been carrying the brunt of the regime’s repression. The call for vigilance and united action should also be made to the various ranks among the armed forces under the TPLF as these elements have been victims of ethnic and other forms of discrimination and favoritism.
And the role of opinion leaders and Ethiopian scholars is very important in shaping public opinion and putting pressure on all civic and political forces to close ranks. To speak as one, to act as one, to give that confidence and assurance to our people back home that we are there for them, fully on their side, in this times of anxiety and uncertainty. The average Ethiopian is in the dark, perturbed as regard to the uncertain future of Ethiopia. Ever ridden with anxiety instead of hopes, exasperation in place of inspiration, our unified voice will offer a glimpse of the bright future we can bring to our multiethnic and mulitreligious nation.
The Ethiopian people should not settle for anything less. Nothing short of liberty and justice, dignity and freedom for all people of Ethiopia can fulfill our mission. The dying and decaying TPLF must not get the chance to consolidate itself and continue the minority ethnic hegemony it has instituted for far too long. It must end, not only in its most important persona, Meles Zenawi, but the foundational body politic, i.e.  the ethnic apartheid regime must be replaced with an all inclusive transitional process that would take Ethiopia to a constitutionally liberal and pluralistic democratic and free political order.
The successors of Meles Zenawi have a choice to make too. They can choose to steer away from the destructive legacy he will be leaving for generations to come. They can choose to be part of an all inclusive transition to a genuine democracy. The other alternative is to continue the status qou ante to eventually, sooner or later, face their unceremonious demise like all dictatorships.
The only and sole alternative for Ethiopia and all stake holders is to agree on a new political configuration for the country.  An all inclusive transional process that will take Ethiopia towards the path of a truly democratic system in place of the sham repressive and minority ethnic hegemonic political order that has been in place for the past two decades. A democratic system where all Ethiopians can live in liberty and where, irrespective of their ethnic and other differences, all Ethiopians are treated justly and equally.
For this to materialize, all freedom and democratic forces and the public at large longing and demanding for a real change in Ethiopia need to cease the discordant chatter and cacophony and act in harmony and unis Labels on. Let us cooperate, listen, and be willing to lead as well as follow, win arguments as well as lose. Let us move along this path. Let us do our share, let us drop our egos and preoccupation of self, narrow organizational and other nefarious interests. Let us put Ethiopia and our suffering people beyond and above all sectarian interests. Let us be the generation that history will absolve, not condemn for failing. By commission and omission, for failing and thereby condemning our people to suffer under an inferno of misery and serfdom instead of freedom and dignity.
We need to speak and act as one. Let us all rise to the momentous occasion. This is the moment and this is the occasion. There are times that put the human soul on trial. This indeed is the very time will put each of us on trial. It is the time that each of us shall be tested whether we are for democracy and freedom or we are for capitulation and servitude under yet another round of tyranny by  a minority ethnic junta ad infinitum, in perpetuity.
This is a moment for a grand vision and a moment to act for national salvation, once and for all. Together we can. In unity we can move mountains of horror and injustice, and clear it for a bright new era of liberty and justice for all Ethiopians. Dignity and freedom for all. To be or not to be. Let us seize the Moment!

Azeb Mesfin arrives in Rome; Sebhat Nega back on the TPLF saddle


Ethiopian Review has received information that Ethiopian dictator Meles Zenawi’s wife, Azeb Mesfin, went to Rome, Italy, last night. Two days ago, we had reported that she received an Italian visa.

It is believed that Azeb left the country to escape from Sebhat Nega whom she forced out of the ruling party’s top leadership in 2009 [read here]. She also kicked him out of his chairmanship of the multibillion-dollar conglomerate named Endowment Fund for the Rehabilitation of Tigray (EFFORT) around the same time.
Ever since Meles Zenawi’s absence in the past two weeks, Sebhat Nega has been trying to come back as the TPLF kingmaker. It was Sebhat who engineered Meles Zenawi’s rise to power and he was the second most powerful figure in the ruling party until he was humiliated and kicked out by Azeb.
Sebhat is said to have the support of key TPLF leaders, including Tsegaye Berhe, Abay Woldu, Gen. Se’are Mekonnen, and Getachew Assefa, among others.
Sebhat Nega has no interest to replace Meles Zenawi, according to observers, but he wants to restore his honor and reclaim his status as the kingmaker.
Although Meles’s choice as the next TPLF chief is Berhane Gebrekiristos, Sebhat is vehemently against it, our sources said.
In the midst of all this power struggle inside the ruling party, the regime currently has no leader. The so-called “deputy prime minister,” Hailemariam Desallegn, is a puppet with no power. He is currently in China to attend some meeting. That could be an excuse for him NOT to get caught in the middle of a potentially bloody power struggle among his TPLF masters.
.

Why are Ethiopian eyes on Brussels?

By Ben Rawlence  -  19.07.2012 / 19:01 CET

The EU should be paying more attention to the abusive policies being pursued by Ethiopia's ailing president.
The cancellation of a scheduled press conference this week, to discuss the health of the Ethiopian Prime Minister Meles Zenawi – currently in Belgium for treatment – started rumours flying. Belgians might be interested to know why Ethiopians are watching events in Brussels so keenly.
Claiming to follow the Chinese model of development – economic growth first, rights later – is a tempting fig-leaf for despots around the world eager to justify their suppression of dissent at home. Ethiopia has praised the Chinese approach while insisting that it conforms to human-rights principles in its own constitution and respects the rule of law. Donors, keen to support Ethiopia's growth and attempts at reducing poverty, have been willing to tolerate its rights abuses in exchange for security partnerships and healthy statistics showing progress on the Millennium Development Goals.
Meanwhile, the Zenawi government has allowed serious human-rights abuses committed by security forces – including war crimes and crimes against humanity – to go unpunished. It has used a raft of repressive legislation to jail critical voices in the media and civil society, shut down or paralyse independent human-rights activity, and send a chilling message to Ethiopian citizens that any step out of line will meet with harsh consequences.
quote
Last week, the trial of journalists and opposition leaders ended in life sentences and one of 18 years for the renowned writer Eskinder Nega.
quote
Last week, the trial of 24 journalists, opposition leaders and others charged with terrorism-related offences – which had been marred by due process violations, lack of access to counsel and allegations of torture by defendants – ended in life sentences and one of 18 years for the renowned writer Eskinder Nega. On the same day, ongoing mass protests by Muslims at state attempts to control mosques were shut down by police with dozens arrested.
In December 2011 Ethiopia sentenced two Swedish journalists to 11 years in jail for the same offence. The pair were attempting to report on the closed Ogaden region where rights abuses against the indigenous Somali population are rampant.
You might think that such behaviour would make Zenawi and his government a pariah. But not at all: Ethiopia receives more EU and US aid than any other African country.
The European Union's current country strategy on Ethiopia states: “The promotion of sustainable security, the rule of law and inclusive, accountable governance ultimately depend on a conducive political climate.”  The climate in Ethiopia is now one where democracy is dead and dissent carries the highest penalty. Moreover, the price of Ethiopia's rush towards economic growth at any cost is increasingly being paid in the well-being and livelihoods of the very citizens the government claims to represent.
In Gambella, the ‘villagisation' programme is in its second year. The government has already removed thousands of indigenous people from their homes against their will and re-settled them in new areas which are often unfertile and lack schools and clinics.
And now, in southern Ethiopia, an ambitious new sugar project makes no pretence of consulting local indigenous communities before removing them from their land and destroying their way of life. A new Human Rights Watch report describes how 245,000 hectares of state-run sugar plantations are being developed without the environmental and social impact assessments that are required by Ethiopian law. Instead, the government is clearing the land, telling residents that it is time to leave, and constructing hundreds of kilometres of irrigation canals and sugar plantations, with plans for six sugar-processing factories.
The place where this is happening is the Lower Omo valley in southern Ethiopia, a UNESCO world heritage zone. The Mursi, Bodi, Suri, Hamer and other groups make the area among the most culturally distinctive and biologically diverse valleys in the world. The 200,000 people who live along the banks of the Omo River rely on the river to plant crops and graze their cattle, and their livelihoods, way of life and identity are under threat.
Under international law, the UN Declaration on the Rights of Indigenous Peoples, the African Charter, not to mention the Ethiopian constitution, indigenous communities cannot be displaced from their ancestral land without their free prior and informed consent, and even then, only as a last resort and with appropriate compensation.
The European Union is one of several donors that provide budget support to Ethiopia's district governments under the ‘protection of basic services' programme, including those where people are being displaced in South Omo and Gambella. It is likely that the EU and others are paying the salaries of the district officials overseeing the plans.
For now, all Ethiopian eyes are on Brussels. But many in Ethiopia wish that Brussels were paying more attention to what Zenawi is up to back home.
Ben Rawlence is senior researcher on Africa at Human Rights Watch.

ሰበር ዜና- ፍትህ ጋዜጣ እንዳይሰራጭ ታገደች!


በትላ ንትናው ዕለት ለስርጭት መብቃት የነበረባት ፍትህ የጠቅላይ ሚንስትሩን መታተም ተከትሎ በተፈጠረው የስልጣን ትግል እያሸነፈ በመጣው አክራሪ ሀይል ተስተጓጉላ የነበረ ቢሆንም በማግስቱ እንድትታተም ተፈቅዷል ተብሎ ታተመች፡፡ ትላንት ከምሽቱ 2 ሰዓት ላይም ሙሉ በሙሉ ታትማም አለቀች፡፡ ነገር ግን አንባቢያን እጅ ልትደርስ አልቻለችም፡፡ ምክንያቱ ደግሞ (በዛው ኃይል ትዕዛዛ ይመስለኛል) በአቃቢ ህግ ብርሃኑ ወንድምአገኝ ‹‹ለሀገር ደህንንት የሚያሰጋ ዘገባ በጋዜጣው ላይ መታተሙ መረጃ ስለደረሰን እንዲታገድ ወስነናል›› በሚል የተፈረመ የዕግድ ደብዳቤ ማተሚያ ቤቱ እንደደረሰው ገለፀልን፡፡ በዚህም ምክንያት በአሁኑ ሰዓት 30 ሺህ የፍትህ ጋዜጣ እትም በብርሃና ሰላም ማተሚያ ቤት ተቆልፎበት ይገኛል፡፡
…እንዴት ነው ነገሩ? ‹‹ትሻልን ፈትቼ ትብስን አገባሁ›› እየሆነ ነው? ይህ ሁኔታ ወደስልጣን እየመጣ ያለው ሀይል የባሰ እንደሆነ ምልክት እያሳየስ ይሆን? ለማንኛውም መጨረሻውን አይተን የራሳችንን እርምጃ እንወስዳለን፡፡
(ማተሚያ ቤቱ ለጋዜጣው ዝግጅት ክፍል የላከውን ደብዳቤ ከስር ይመልከቱ)

ታለቁ የፖታሽ ኩባንያ ኢትዮጵያን ለቆ ወጣ

ሐምሌ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ከፍተኛ የዜና ሽፋን አግኝቶ የነበረውና ኢትዮጵያን በአፍሪካ ቀዳሚ የፖታሽ ላኪ አገር ያደርጋታል ተብሎ የተነገረለት የአውስትራሊያው  ቢኤች ቢልተን ኩባንያ የአፋርን ክልል ለቆ ወጥቷል።
ኩባንያው አካባቢውን ለቆ እንደሚወጣ ለመንግስት ባለስልጣናት መናገሩን ብሉምበርግ ዘግቧል።
ኩባንያው ከኢትዮጵያ የወጣበትን ምክንያት አላስታወቀም።
በቅርቡ የአፋር ሰብአዊ መብቶች ድርጅት በአፋር አካባቢ ላሉ አለማቀፍ ኩባንአዎች የተቃውሞ ደብዳቤ መጻፉ ይታወሳል።

Friday 20 July 2012

አልጋወራሽ እንምረጥ ወይስ?....ከዳዊት ዋስይሁን


የተከበረና ጀግናው አበበ ገላው የአቶ መለስን አንገት ካስደፋቸው አንስቶ የሰውየው ስም በየትኛውም ጎራ ባለ የመገናኛ አውታርም ሆነ የማህበራዊ መረብ እስከ አሁን ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በሪኮርድ ማለት ይቻላል በየለቱ የመወያያና የመነጋገሪያ ርእስ ሆኖ እንደሚገኝ የየለት ትዝብት ነው፣ ጉዳዩን ልዩ የሚያደርገው በየወቅቱ የሚፈጠር አዳዲስ ክስተት ሲሆን በሚገርም ሁኔታም አንዱን ተነጋግረንና አንሸራሽረን ሳንጨርስ ሌላ አዲስ ነገር ይወለዳል ይኽው እስካሁን አለን ስንባትል፣ በአገር ቤትም በውጭም በሁሉ ቦታ የደራ የሞቀ መነጋገሪያ ሆኖአል እንደውም ከሰሞኑማ አገር ቤት ያሉ ስርእት አደር የእምነት ተቋማት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠት ለተፈጠረው ሁኔታ ሱባኤ ሊገቡ እያሰቡ እንዳለ የሚያሳይ ምልክቶች እየታዩ ነው እንግዲህ ይህ ነው እኔንም ብእሬን እንዳነሳ ያረገኝ።
መነጋገር መደማመጥና መቻቻል የአደገ ማህበረሰብ መገለጫዎች ሲሆኑ እኛም ይህንን በትእግስት አደረግነው ማለት ወደ አንድ ደረጃ ከፍ ማለታችንን ያሳያል እንደውም እንዲበዛልንና እንዲያድለን ተግተን ልንመኘው ልንለማመደው ያስፈልጋል፣ ነገር ግን በዚህ ሒደት ውስጥ በተለይ የአቶ መለስ ሁኔታ በፈጠረው ጉዳይ ላይ ጠንቀቅ ልንል ያስፈልጋል ምክንያቱም ትግልን ያማከለና ውጤትን ያነጣጠረ ስራ መሰራት ስላለበትና በ1997 የታጣው የህዝብ ጥያቄ ድጋሚ አሁንም በወያኔዎች ጮሌነት እንዳያመልጠን የሚነፍሰውን ንፋስ ለይተን ትግላችንን እንድንመራ ከማሰብ ነው።
ይህንን ስል እየታገልነው ያለው ስርአት ክፋትን፣ ሸርን፣ ተንኮልን፣ መርዘኝነትን፣ ዘረኝነትን፣ መከፋፈልን አንዲሁም በተለይ ትውልድን ባተሌ ማድረግ ለ21 አመት በአገራችን ፖሊሲ ነድፎ ያዋቀረና የተከለ ስለሆነ የምንሰማውን ወይም የሚፈጠረው አዲስ ነገር ሁሉ ልንደርስበት ካሰብነውና ካለምነው ለሰከንድ እንኳን ሊያጓትተን አይገባም፣ እንዲሁም መጠቀም ያለብንን እውቀት፣ ጉልበትና ሃብት አላስፈላጊ ቦታላይ እንዳናፈሰው መጠንቀቅ አለብን።
በተለይ ዋናውና ሃይለኛው የወያኔ ብልሃት ትውልድን ባተሌ ማድረግ ነው ይህ ስልት ከዚህ በፊት ያለፉ አሁንም ያሉ ወደፊትም የሚመጡ አስከፊ አምባገነኖች ሁሉ የሚጠቀሙበት ሃይለኛው መሳሪያቸው ነው። ህዝብን የወሬ ስራ መስጠት ማባተል፣ ህዝብ እንዲምታታ እዚህም እዚያም የተዘበራረቀ መረጃ መልቀቅ፣ የህዝብን የአስተሳሰብ ማእከላዊነት መበጥበጥ፣ በአንድ መረጃ ላይ ህዝብ ወጥ የሆነ አቋም እንዳይይዝና እንዳይፈታተናቸው የመዋከቡን ስራ ለሰፊው ህዝብ መተው በዚህ ሰአት እነሱ ለተንኮላቸውና ለእቅዳቸው መተንፈሻ ጊዜ ስለሚያገኙ የተነሱ ማናቸውንም አይነት አስተሳሰቦችና የለውጥ እንቅስቃሴዎች በእንጭጩ ማፈንን ይችላሉ። 
ስለዚህ እንግዲህ እዚህ ጋር ነው የኔ ፍርሃት ጠዋት ወዳጆቼን ሰላም ሰል አፋችንን የምንከፍተው የበረከት ስምኦን እና የደብረጽዮን ገ\ሚካኤል ቢሮ በፈጠረልን ስራ እንጠመዳለን ሰውየው ሞተ፣ አገርቤት ገባ፣ ከሳ፣ አበጠ፣ ጀርመን ነው ያለው አይደለም ቤልጅየም …. ትክክል ልንነጋገርባቸው ይገባል፣ ነገር ግን በአሁኑ ወቅት በጀግናው አበበ ገላው ተለኩሶ  እየተቀጣጠለ ያለው የለውጥ እንቅስቃሴ በዝባዝንኪ ብትቶ ወሬ ተጠምደን እድሉ ሊያመልጠን አይገባም እንደውም በምንም መስፈርት እነኝህ የጉዳያችን ዋና አጀንዳ አርእስት ሊሆኑ አይችሉም፣ ወያኔ በተወናበደና በተምታታበት ሰአት በተጠናከረና በተቀናጀ መንገድ ለለውጥ ወደፊት ማየት ይገባናል አሁን ሰአቱ የበለጠ የሚታሰብበትና ብረቱ እንደጋለ የሚቀጠቀጥበት ወቅት ነው።
ስለዚህ በፊት ለፊታችን ሁለት አማራጮች አሉ፣ አንድኛ በአሁኑ ሰአት ወያኔ ያላሰበው ትልቅ ክስረት ገጥሞታል ተምታቶበታል፣ ተርበትብቷል፣ ምንእደሚያረግ ግራ ገብቶታል፣ በትክክል እስከዛሬ ህዝብን እያባተለበት ያለው መንገድ በውስጡ ፈንድቷል ምክንያቱም አስፈሪው የስርአቱ ማእዘን ተመትቶ የማያስፈራ ደረጃ ላይ ደርሷል፣ ስለዚህ አሁን ሕውሓት በቀን ቅዠት ላይ ነው ያለው፣ ራሱ የፈለፈላቸው ብአዴን፣ ደኢሕዴን፣ ኦሕዴድ……. ነገ ምን ሊያረጉ እንደሚችሉ ስለማያውቅ ይፈራቸዋል ምክንያት ብዙ ናቸውና፣ በመቀጠል ሆድ አደር አባላቱን ይፈራል፣ ከመሬት ያፈናቀላቸው ገበሬውን ይፈራል፣ ህዝቡን ይፈራል፣ እራሱን ይፈራን ምክንት የሕውሓት ባህል መበላላትና መጠፋፋት ነውና፣ የውስጥና የውጭ ተቃዋሚዎችን ይፈራል ሲያስባቸው ይንቀጠቀጣል፣
እንግዲህ ውነታው ይህ ነው በተቃራኒው ህዝቡ አዲስ ነገር ይጠብቃል ተስፋም ያደርጋል ለዚህ ሰአት መፍትሄ የሚሆን የለውጥ እርሾ ይፈለጋል፣ አዲስ ራእይ ይዞ ወደዚህ ህዝብ ሄዶ ህዝቡን ወደትግል ለመምራት ከተቃዋሚዎች አንድ መሆንን እና ቁርጠኝነት ይጠበቃል፣ እስከዛሬ ደካማ የተከፋፈሉ እያለ ሲያሾፍና ሲቀልድ የነበረው ወያኔ አሁን ግን ይህ በሽታ ከመቅስፈት አጥቅቶታል ስለዚህ ይህ ታሪካዊ ወቅትና አጋአሚ ድጋሚ እንዳያመልጠን ሁላችንም ልዩነታችንን ወደኻላ ትተን ለአንዴና ለመጨረሻ በህዝባችን ጠላት ላይ እንነሳ፣
ወይም ሁለተኛው ምርጫችን እጃችንን ሰጥተን ወያኔ በሚሰጠን የቤት ስራ እየባተልን ከነሱ ጋር ሆነን የቀጣዩን አልጋወራሽ እንምረጥ፣ እየሰራንላቸውም እኮ ነው፣ ለለውጥ ማሰብ እና መነቃቃት ሲገባን እንቁ የሆነ ጊዜያችንን ሰለ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ወይም ኃይለማርያም ደሳለኝ አነጋገስ ላይ ስንለፋ እንገኛለ::  
  
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!
ፀሓፊውን ለማግኘት zoloaba112@yahoo.com

Wednesday 18 July 2012

የሸካ ሽማግሌዎች ኃይሌ ገብረሥላሴ ደን እንዳይጨፈጭፍ ገዘቱት

Wednesday, 18 July 2012 09:34

ዝነኛው አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በግብርና ሚኒስቴር አማካይነት በሊዝ የተፈቀደለትን 1,500 ሔክታር መሬት ለመረከብ በደቡብ ክልል ሸካ ዞን በተገኘበት ወቅት፣ የአካባቢው ሽማግሌዎች በመሬቱ ላይ ያለውን ደን እንዳይጨፈጭፍ ገዘቱት፡፡
ኃይሌ የተሰጠው መሬት በክልሉ ዋና ከተማ ከሐዋሳ ከተማ 951 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ሸካ ዞን ማሻ ወረዳ የጶ ቀበሌ ውስጥ ነው፡፡ መሬቱ ሙሉ ለሙሉ ጥቅጥቅ ያለ የተፈጥሮ ደን ያለበት ሲሆን፣ የአካባቢው ሽማግሌዎች አትሌቱ ደኑን እንዳይጨፈጭፍ ገዝተውታል፡፡

ኃይሌ ይህንን መሬት በሔክታር 63 ብር ሒሳብ ለ45 ዓመት የሊዝ ዘመን ተረክቧል፡፡ አካባቢው መንገድ የሌለው በመሆኑ ኃይሌ 14 ኪሎ ሜትር መንገድ መገንባት ይጠበቅበታል፡፡ ‹‹ከመንገዱ በተጨማሪ ሁለት ወንዞች ስላሉ ድልድይም እገነባለሁ›› ሲል ኃይሌ ለሪፖርተር ገልጿል፡፡ ኃይሌ ለሪፖርተር እንደገለጸው፣ የቡና፣ የቅመማ ቅመም ልማቱና የመንገድ ግንባታው ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ይፈልጋል፡፡

በአካባቢው ውብ ተፈጥሮ እጅግ መደሰቱን ለሪፖርተር የገለጸው ኃይሌ፣ ደኑን እንዳይቆርጥ የአካባቢው ሽማግሌዎች እንደገዘቱት አስረድቷል፡፡ ቡና በተፈጥሮው የዛፍ ጥላ ስለሚወድ ደኑን እንደማይጨፈጭፍ ኃይሌ አስታውቆ፣ የአካባቢው ሕዝብ ፍላጎት ከሆነ ቦታውን በይዞታው ሥር በማድረግ እንዲሁ ሊዝ እየከፈለ እንደሚያቆየው አስረድቷል፡፡

በሕንፃ ግንባታ፣ በሆቴል፣ በአውቶሞቢል አስመጪነትና በተለያዩ የንግድ ሥራዎች የተሰማራው  አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ፣ በእርሻ ሥራ የመሰማራት ህልም እንዳለው ሲገልጽ ቆይቷል፡፡ ይህንን ዕቅዱን ለማሳካት ለደቡብ ክልል መንግሥት ከዓመታት በፊት የቦታ ጥያቄ ቢያቀርብም እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ተፈጻሚ ሳይሆን ቆይቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት ግን የግብርና ሚኒስቴር 1,500 ሔክታር መሬት እንዲሰጠው በመወሰኑ ቦታውን የደቡብ ክልል መንግሥት አስረክቦታል፡፡

ወደ ውጭ የሚላኩ የግብርና ምርቶችን ማልማት ህልሙ እንደሆነ የተናገረው ኃይሌ፣ በቀጣይነት ሙሉ ትኩረቱን በእርሻ ልማት ላይ እንደሚያደርግ ገልጿል፡፡ በሸካ ዞን ጥቅጥቅ ደን ውስጥ መሬት መመራቱን በጥርጣሬ የሚመለከቱ አልጠፉም፡፡

ለሪፖርተር ሥጋታቸውን የሚገልጹት የአካባቢ ተቆርቋዎች እንደሚሉት፣ የሸካ ደን ጥቅጥቅና በውስጡ ብዙ ዓይነት ዕፅዋቶች ያሉት ነው፡፡ በዚህ አካባቢ የሚገኘው የደን ሀብት መነካት እንደሌለበት በአፅንኦት በመናገር ለአትሌቱ መሬቱ ሊሰጠው እንደማይገባ ይናገራሉ፡፡

የሸካ ነዋሪዎች ለዘመናት ደን ሲንከባከቡ የኖሩ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ማኅበረሰቡ ከደን ሀብቱ ማርና ቅመማ ቅመም በማምረት የሚተዳደር ሲሆን፣ ነዋሪዎች ለሕመማቸው ፈውስ የሚያገኙት በደን ውስጥ ካሉ ልዩ ልዩ ዕፅዋት ነው፡፡ የአካባቢው ነዋሪዎች ኃይሌ ደኑን ሳይነካ ልማቱን ቢያካሂድ እንደማይቃወሙ ታውቋል፡፡

Monday 16 July 2012

ሃይማኖትና አክራሪነት (ፕ/ር መስፍን ወልደማርያም)

አንድ የአሜሪካ ፈላስፋ የሚተርከው ገጠመኝ አለው፤ አንድ ቀን በእግሩ ሲንሸራሸር ሰዎች አንድ ዛፍ ከብበው ሲጨቃጨቁ ያያል፤ ይጠጋና ሲያዳምጥ ክርክሩ በአንዲት ዛፉ ላይ ባለች የዛፍ አይጥ (የዛፍ አይጥ እኔ ያወጣሁላት ስም ነው፤ በእንግሊዝኛ ስኮረል ትባላለች ረጅም ጭራ ያላት ጸጉራማ ፍራፍሬ ለቃሚ ነች፤) የተነሣ ነው፤ አንዱ ሰው ይቺን የዛፍ አይጥ እዞራታለሁ ይላል፤ ሌላው ደግሞ የለም ዛፉን ትዞራለህ እንጂ አይጥዋን ልትዞራት አትችልም ይላል፤ እዞራታለሁ የሚለው ሰው ለማስረዳት ዛፉን ይዞራል፤ አይጥዋም በዛፉ ላይ ትሽከረከራለች፤ የተሰበሰቡት ሰዎች በዚህ ጉዳይ ለሁለት ተከፍለው ይጨቃጨቃሉ፤ ፈላስፋው ሲደርስ የሱን አስተያየት ይጠይቁታል፤ ክርክሩ በመዞር ትርጉም ላይ ልዩነት መሆኑን እንደሚከተለው ያስረዳቸዋል፤ አይጥዋን መዞር ማለት አይጥዋን በተለያዩ አቅጣጫዎች፣ ማለትም አንድ ጊዜ ከፊትዋ፣ ሌላ ጊዜ ከግራዋ፣ እንዲሁም ከቀኝዋና ከኋላዋ ማየት ነው ወይ? ወይስ አይጥዋ ዛፉ ላይ ስላለች ሰውዬው ዛፉን በመዞሩ አይጥዋንም ይዞራል?
እሁድ ማታ ሰዎች ደወሉልኝና በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ስለአክራሪነት የሚተላለፈውን ፕሮግራም እንድመለከት አስታወቁኝ፤ ተመለከትሁት፤ በጥንቃቄ በተመለመሉት ሰዎች መሀከል ነጻነት፣ መቻቻል፣ አክራሪነት የሚሉት ቃላት እንደልብ ይወረወሩ ነበር፤ በእነዚህ በጣም ቁልፍ በሆኑ ቃላት ላይ ክርክር አልተከፈተም ሊከፈትም አይቻልም፤ ክርክር ሊነሣ የሚችለው በአእምሮአቸውና በኅሊናቸው እየተመሩ፣ ምንም ዓይነት የውጭ ኃይል አስተሳሰባቸውን ሳያዛባባቸው ለመነጋገር በተሰለፉ ሰዎች መሀከል ነው፤ የተለያየ ካባ የለበሱና የተለያየ ሃይማኖት አለን የሚሉ ካድሬዎች በአንድ ቀጭን ክር ይታሰሩና ቋንቋቸው አንድ ይሆናል፤ አስተሳሰባቸው አንድ ይሆናል፤ ሀሳባቸው አንድ ይሆናል፤ ኦርቶዶክስ፣ እስላም፣ ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት፣ መናፍቅ መሆን ወግ ብቻ ይሆናል።
ፕሮግራሙ ለእኔ ያስተላለፈልኝ መልእክት በእውነትና በድፍረት ከፍርሃትና ከጥቅም በላይ ሆነው ክርስቲያንነትንም ሆነ እስላምነትን፣ ወይም መናፍቅነትን በማስረዳት ብዙዎቹ ከጠቀሱት ሕገ መንግሥት ጋር እነሱን ሁሉ የሚያስተሳስራቸው ምን እንደሆነና እንዴትስ እንደሚተሳሰሩ በግልጽ አላወጡትም፤ እነዚህን ሁሉ የሚያስተሳስራቸውና ለሕገ መንግሥቱ ተገዢ የሚያደርጋቸው ዜግነት ነው፤ ዜግነት የሚል ነገር በቀበሌ መታወቂያ ላይ እንኳን አይገባም፤ የሚደንቀው ሃይማኖትም ከጉዳይ ተቆጥሮ በቀበሌ መታወቂያ ላይ አለመግባቱ ነው፤ ጎሣ የለኝም ብሎ በኢትዮጵያዊነት ለመመዝገብ አይቻልም ነበር፤ ከዛሬው የተሻለ ፍርድ ቤት በነበረበት ጊዜ ልጅ ይስሐቅ ክፍሌ በፍርድ ቤት ከስሶ ነው በኢትዮጵያዊነቱ የመታወቅን መብት ያረጋገጠው፤ አሁንም ቢሆን በቀበሌም ሆነ በየመሥሪያ ቤቱ ቅጽ ሲሞላ ጎሣ የለኝም የሚል ሰው ክርክር ይገጥመዋል፤ ሁሉንም ሰው በግድ በጎሣ ከረጢት ውስጥ ለማስገባት ጥረት ይደረጋል።
የሃይማኖት ሰዎች ነን የሚሉት ሕገ መንግሥቱን ሲጠቃቅሱ የሚያምኑበትን የእግዚአብሔርን ሕግ ለመጠቃቀስ የደፈሩ አይመስሉም፤ አንድ ጊዜ በጀኔቭ የተባበሩት መንግሥታት የሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ ላይ ሱዳን የሰብዓዊ መብቶች የሚረገጡበት አገር ተብሎ ሲወቀስ፣ የሱዳኑ መልእክተኛ እኛ የምንከተለው የአላህን ሕግ ነው እንጂ የሰውን ሕግ አይደለም፤ ብሎ መለሰ፤ የእግዚአብሔር ሕግ የተባለው ውስጥ ሰብዓዊ መብቶች የሉበትም የማለት ዝንባሌም እንኳን ማሳየት ሃይማኖቱንም እግዚአብሔርንም የሚያስቀይም አይሆንም?
ለእኔ አክራሪ ማለት ለእግዚአብሔር ጠበቃ እቆማለሁ የሚል ኦርቶዶክስ፣ ለእግዚአብሔር ጠበቃ እቆማለሁ የሚል ካቶሊክ ወይም ፕሮቴስታንት፣ ለአላህ ጠበቃ እቆማለሁ የሚል እስላም፤ ሃይማኖት ሁሉ ድንቁርና ነው የሚል ደንቆሮ… እነዚህ ሁሉ ክፉ አክራሪዎች ናቸው፤ በእግዚአብሔር የሚያምኑት የእግዚአብሔርን ኃያልነት ጠዋትና ማታ እየሰበኩ፣ እግዚአብሔር ራሱን ያልቻለ፣ ጠበቃና ፌዴራል ፖሊስ ጠባቂ የሚያስፈልገው አድርገው የሚገምቱት ሃይማኖተኞች ይባላሉ ወይስ መናፍቅ? እግዚአብሔር በየትኛውም ስም ቢጠራ የኃያሎች ኃያል ነውና ከፈለገ እንኳን እሱን ራሱን ጎረቤታቸውንና ደሀዎችን የሚበድሉትን በማናቸውም ጊዜና በየትኛውም ቦታ ፍርዳቸውን ለመስጠት የሚችል መሆኑን የማይቀበል ሃይማኖተኛ ያለ አይመስለኝም፤ ታዲያ እግዚአብሔርን አዋረደ፣ ወይም ናቀ ብሎ በዚያ ሰው ላይ የኃይል እርምጃ መውሰድ የእግዚአብሔር መንበር ላይ መቀመጥ አይሆንም? በእግዚአብሔር መንበር ላይ ለመቀመጥ ከመንጠራራት የበለጠ የአክራሪነት ዕብሪት ምን አለ?
በአክራሪው ግምት እግዚአብሔርን የሚያስቀይም ንግግር ሲሰማ፣ ወይም እግዚአብሔር የማይወድደው ነገር ሲደረግ ሲያይ፣ እግዚአብሔር አይሰማም፣ አያይም፣ በማለት ነው አክራሪዎቹ ለእግዚአብሔር ጠበቃ ቆመናል ብለው ሰውን የሚያጠቁት? ይህ እግዚአብሔርን መስደብ አይሆንም ወይ? እስቲ እግዚአብሔር የሰጠንን አእምሮ ተጠቅመንበት እናስበው፤ የሁለት የተለያዩ ሃይማኖቶች አክራሪዎች በእግዚአብሔር ስም ቢጨፋጨፉ ሁሉም እግዚአብሔርን ያስቀይማሉ? ሁሉም እግዚአብሔርን ያስደስታሉ? ወይስ አሸናፊው እግዚአብሔርን ያስደስታል? ወይስ መናፍቃንን ያስደስታል?
መቻቻልንና ነጻነትን እያብላላናቸው እንቆይ።

አቶ መለስ ዜናዊ ያልተጠየቁትን ሲመልሱ......ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ



የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግምባር ሠራዒ መጋቢ መሀንዲስ አቶ መለስ ዜናዊ በሠሩትና በሚመግቡት ምክር ቤት ሲሰብኩና ተመጋቢዎቹ ጥያቄ እየጠየቁ ሲብራራላቸው ብዙ ጊዜ በመገናኛ ብዙኃን አማካይነት ሰምቻለሁ፤ አይቻለሁ። ትርኢቱ የመምህርና የተጋባዥ ተማሪዎች ግንኙነትን የያዘ ሆኖ ስለሚቀርብ፥ ዜናው ሲደርሰኝ አዳማጮቹ ምን ዓይነት ጥያቄ እንደሚያነሡ ከማወቅ ያለፈ ትኩረት አልሰጠውም ነበር። ግን አሜሪካን አገር አቶ አበበ ገላው ራሳቸውን ያስደፋቸው ዕለት ሳይጠየቁ የሰጡት መልስ ልቤን ማርኮታል።
ጠያቂው አንድ አፍሪካዊ ነው። ጥያቄው “እድገትና ዲሞክራሲ አብረው ይሄዳሉ? ወይስ፤ እድገት ለማምጣት መጀመሪያ ዲሞክራሲን መስፈን አለበት?” የሚል ነበር። መሀንዲሱ ላልተጠየቁት ጥያቄ የሰጡት መልስ በተለየ መልኩ የተሰማኝ በአጋጣሚው ምክንያት ነው። “አጋጣሚ” ያልኩት እርሳቸው ሲመልሱ አቶ ሲሳይ አጌና “የቃሊቲው መንግስት” በሚል ርእስ የጻፈውን መጽሐፍ እያነበብኩ ወደ ማገባደዱ ደርሼ በነበረበት ጊዜ መሆኑን ነው። መሀንዲሱ ሲመልሱ መጀመሪያ እድገትና ዲሞክራሲ ምንም ግንኙነት እንደሌለው አብራሩ። ይኸን መልስ ስሰማ፥ የኢትዮጵያን ሕዝብ ለምን ዲሞክራሲን እንደነፈጉት ማብራራታቸው መስሎኝ ነበር፤ አይደለም። መሀንዲሱ ዴሞክራሲን ለሕዝቡ ለመስጠት ሳይፈልጉ ከኢትዮጵያ ምድር እንደሚለዩ መርሣት አልነበረብኝም።
ከዚህ ቀጥለው ላልተጠየቁት ጥያቄ መልሳቸውን አስከተሉ፤ “ይህ ማለት” አሉ፤ “ይህ ማለት፥ ያለ ዲሞክራሲ በሰላም መኖር ይቻላል ማለት አይደለም። በተለየ እንደ ኢትዮጵያ ያለች ብዙ የተለያዩ ሕዝቦች በሚኖሩባት ሀገር ሰላም ሰፍኖባት እድገትን ለማካሄድ እንዲቻል ዲሞክራሲ የግድ መስፈን አለበት” አሉ፥ ምንም ሳያወላውሉ፤ በሽብርተኝነት ክስ ጥፋተኛ የተባሉት እነ እስክንድር ነጋ ከምድር ገሃነም ሆነው የሚጮሁት ዋይታ ምንም ሳይወቅሳቸው። (ጥያቀውና መልሱ የተካሄደው በእንግሊዝኛ ስለነበረ የአማርኛ ትርጒሜ ስሕተት ካለበት መሀንዲሱ ሊያስተካክሉት ይችላሉ።) ከአዳማጩ ማህል መልሳቸውና አገዛዛቸው ያልተገናኙ መሆኑ ያልገባው እሳቸውንም ግር እስኪላቸው ድረስ አጨበጨበ። “መሀንዲሱ ምዕራባውያን መስማት የሚፈልጉትን መናገር ይችላሉ” የሚባለው ከመቸውም ግልጽ የሆነልኝ ይኸንን ያልተጠየቁትን ጥያቄ ሲመልሱ ስሰማ ነው። እውነትም ፤ ተክነውበታል። ወደ አልተጠየቁት መልስ የተጣደፉት ምናልባት አቶ አበበ ገላው ያስደፋቸውን አንገት ቀና ለማድረግ ይጠብቁት የነበረው ዕድል ስላጋጠማቸው ይሆናል።
ዲሞክራሲና መሀንዲሱ እንደማይተዋወቁ፥ ወደመጀመሪያው ላይ ተታልለን ይሆናል እንጂ፥ ከምርጫ 97 ወዲህ እቅጩን ዐውቀነዋል። መግዛትን የጉልበተኛ ተራ ጉዳይ እንዳደረጉት መላ ዓለም አይቷል። ድምጽ መስጫ ወረቀቶች በአንዳንድ ዲሞክራሲያዊ አገሮችም ይሰረቃሉ፤ ግን እንደዚህ ያለ ዝርፊያ የሚካሄደው ዲሞክራሲ በሌለበት አገር ብቻ ነው።
የምርጫ 97 ጉዳይ ከተነሣ፥ በዚያ ጊዜ ስለሆነው የምናውቀው ሕዝቡ በምርጫ ያገኘውን ድል መነጠቁንና አዝማቾቹ ድሉን ስለመሩ ተወንጅ እስር ቤት መግባታቸውን እንጂ፥ አቶ ሲሳይ አጌና በዝርዝ እንደገለጠው እስረኞቹ በመሀንዲሱ ትእዛዝ እንዲህ በምድር ገሃነም ውስጥ መሰቃየታቸውን መቸ ዐወቅን? ውይ፥ ውይ! እውነትም ሕገ-አራዊት! ከጭካኔዎቹ ውስጥ አንዱን ለማንሣት ያህል፥ ሲመሽ ዘበኞቹ ከሦስት መቶ በላይ የሚሆኑ እስረኞችን አንድ ክፍል ውስጥ ዘግተውባቸው በርቀት ሊቆሙ ይችላሉ። ማንም በምንም ምክንያት በሩን ቢያንኳኳ፥ የቱንም ያህል ከፍ ባለ ድምፅ ቢጮህ፥ ከመንጋቱ በፊት የሚከፍትለት የለም። ሆዱን የጎረበጠው ሰው እዚያው በሁሉም ፊት ከመዋረድ ሌላ፥ ሁሉም ምነው አፍንጫ ባልኖረኝ ሲያሰኝ ያነጋል። እሳት ቢነሣ ሁሉም ያልቁ ነበር።
የፍርድ ቤቱ ሂደት ድራማ ነበር፤ የዳኝነት ወምበሮች የተያዙት በገለልተኛ ሳይሆን የበላይ ትእዛዝ በሚያወዛውዛቸው ገለልትኞችን በተኩ ዳኞች ነው። በሐሰት እንዲመሰክሩ ከታዘዙት መስካሪዎች ውስጥ አንዱ ሲጠየቅ፥ የመንግሥት ታዛዥ መሆኑን በኩራት ለማሳየትና በይፋ ለመመስገን፥ “ያየሁትም የሰማሁትም ነገር የለም፤ የመጣሁት መንግሥት መስክር ብሎ ስላዘዘኝ የመንግሥት ትእዛዝ ለመፈጸም ነው” ብሎ መሰከረ።
በምርጫው ሳቢያ የመሀንዲሱ ፖሊሶች ሁለት መቶ የሚሆኑ ሰላማዊ ሰልፈኞች ገድለው ነበር። ሰዎቹ ለምን እንደተገደሉ የሚመረምር አንድ ቡድን መንግሥት አቋቁሞ ነበር። ያም ሆኖ፥ መርማሪው ቡድን ጥፋቱ የመንግሥት መሆኑን አረጋገጠ። መሀንዲሱ የፈለጉት ግን ሕዝቡን ጥፋተኛ ለማድረግ ነበር። ስለዚህ የቡድኑን አባላት እቢሮዋቸው ድረስ ጠርተው ሪፖርቱን እንዲቀይሩ አስፈራሯቸው። አለዚያ እኮ በመሀንዲሱ ዘመን በኢትዮጵያ ዲሞክራሲ የለም ሊባል ነው። ከቢሮዋቸው ሲወጡ፥ ከአባላቱ አንዳንዱ ሪፖርቱን እንቀይር አለ፤ ሌላው (ከመቃጠል) እናቃጥለው አለ፤ አንዳንዶቹ ከአባልነቱ በፈቃዳቸው (ያለፈቃዳቸው) ለመሰናበት ተገደዱ፤ ሌሎቹ የመጣው ይምጣ ብለው በቃላቸው ረጉ። መፍትሔው ለመሀንዲሱ ቀላል ነበረ፤ ከዚህ ሁሉ ጭቅጭቅ እራሳቸው እንደፈለጉት ጽፈውም ይሁን አስጽፈው፥ የቡድኑ ሪፖርት ሆነ፤ አለቀ ደቀቀ።
የሽማግሌዎቹ ሚና ከማስገረም ይልቅ የሚያስቅ ነው። ሊቀ መንበሩ ስለሽምግልና ባህላችን በሰፊው ያብራራል። ያደረገው ግን መሀንዲሱ ያሉትን ተቀበሉ (ጥፋተኞች ነን በሉ) ብሎ ከጫማቸው ላይ መውደቅ ነበር። አስፈታኋቸው ብሎ ስም ለማትረፍ መሆን አለበት። አወይ ባህላችን!! በመጨረሻ፥ ከእስረኞቹ አንዱ፥ “የጎበዝ በር እንልቀቅለት” ብሎ ባቀረበው ሐሳብ (ይኸንን ከሲሳይ መጽሐፍ ሳይሆን ከሌላ ነው የሰማሁት) ተስማምተው የመሀንዲሱን ወንጀል ግማሹን ወስደውለት ተፈቱ። ሲፈቱ ከመሀንዲሱ ተከታዮች አንዱ “ሕገ-አራዊት ሲሉ ያጣጣሉትን ሕገ-መንግስትንም እንደሚቀበሉ በማረጋገጥ ተንበርክከው ይቅርታ ጠይቀዋል” ብሎ ፎከረ፤ ጊዜ ስለሰጠው ብቻ የኢትዮጵያ ዓይኖችን በማሰቃየቱና ክብራቸውን በመንካቱ መግቢያ ቀዳዳ እስኪጠፋው በማፈር ፈንታ በአነጋገሩ እውነትም ሕገ-አራዊት መኖሩን መልሶ አረጋገጠ።
ተረቱ የታወቀ ቢሆንም አጋጣሚው እንድደግመው ይጋብዘኛል፤ አሽከር ጠዋት የጌታውን ጫማ ሊጠርግ ሲያነሣው አይጥ በልታለት አገኘው። “አወይ፥ አወይ! ወይ ጉድ፥ ወይ ጉድ!” እያለ ሲጮህ፥ ጌታው ሰምቶት፥ “ምን ጉድ ተፈጠረ?” ብሎ ጠየቀው። የሆነውን ሲነግረው፥ “ምን ሞኝ ነህ እባክህ? ጉዱ ጫማው አይጧን ቢበላት ነበር እንጂ፥ አይጥ ቆዳ መብላቷማ የተፈጥሮ ጠባይዋ ነው” አለው ይባላል። መሀንዲሱ ባላቸው የማይለወጥ ጠባይ የተነሳ በደል በፈጸሙ ቊጥር እንደ አዲስ ነገር ማየታችንን አቁመን ነፃነታችንን በምናገኝበት ዘዴ ላይ ብቻ ማተኮር አለብን። “ወይ ጉድ!” ማለታችንን ከምናቆምበት ዘዴ አንዱ የመወያያ አርእስት እነሱ ሲሰጡን አለመቀበል ነው። አለዚያ አንድ የማንወደውን ነገር ጣል ያደርጉልንና እሱን ማስተባበል የሚገባ ቢሆንም፥ ማስተባበሉን በመጠኑ ካላደረግን በመፍትሔው ላይ የመሰለፍ አቅማችንን እናጠፋበታለን። የመሀንዲሱ “ክልል”፥ “አንቀጽ 39”፥ “የብሔሮች ጥያቄ”፥ “ወዘተ” ስንት ጊዜ አከራከሩን!!
አንቀጽ 39ን እንተወው፤ እንደማየው፥ የመሀንዲሱ ቡድን በሥልጣን ላይ እስካለ ድረስ ይህ አንቀጽ ኢትዮጵያን አያሰጋትም። ሕገ መንግሥቱ ውስጥ የገባው በአንድ በኩል ሀገር ወዳዱን ለማስፈራራትና የመወያያ ርእስ ለመስጠት ሲሆን፥ በሌላ በኩል ለመገንጠል የሚጓጓውን ለመደለል ነው። እንደእውነቱ ከሆነ ግን በመሀንዲሱ ሕገ መንግሥት መሠረት፥ አንድ ክልል የሚገነጠለው ራሱ መሀንዲሱ የሚያስገነጥሉ ብለው የዘረዘራቸውን ምክንያቶች መንግሥት ሲያጓድል ነው። የሚያስገነጥሉትን ምክንያቶችን እሳቸው መርጠው ከሰጡ፥ እነዚያንም ቢሆን ተገንጣይ ወገን “መንግሥት አላሟላልኝም” ቢል ማነው የሚሰማው? የመሀንዲሱ መንግሥት ነው? እስቲ ተሰምተው እንደሆነ የመገንጠል ጥያቄ ያነሱትን እንጠይቃቸው! ኢትዮጵያ የወያኔ ጒልት ሆናለች፤ ማን ይድላው ብሎ ነው ወያኔ ሳይገደድ ጒልቱን የሚያስቈርሰው?
መሀንዲሱ ስለጒልቱ መልማትም በሰፊው ያስወራሉ። ወያኔና ሻዕቢያ በጣምራ ባይወጥሯቸው የንጉሡ መንግሥትና የደርግ መንግሥት የእድገቱ እርምጃ የትና የት ይሄድ ነበር! አርበኞች ባያስቸግሩት ኖሮ የዱካ ዳዎስታ አገዛዝ ኢትዮጵያን በእድገት ከኢጣልያ ጋር ያወዳድራት ነበር። ፕላኑን ያየ ይደነቃል። ግን ጥያቄው መጀመሪያ ነፃነትን ማግኘት ስለሆነ ማንም አልተባበራቸውም። በኃይል ገዝተው ሲያቅታቸው አልፈዋል። ነፃነት የሁሉ መጀመሪያ እንጂ ለምንም ነገር ሁለተኛ አይሆንም። ነፃነት አምሳያ የሌለው ሰውን በሰው ደረጃ የሚያስቀምጥ የአምላክ ስጦታ ነው። አንድን ሰው ነፃነቱን ነፍጎ ቢያበሉት እንኳን፥ ሰውየው እንደ ከብት ቅልብ ነው የሚሆነው፤ ጌታ ሰው በእንጀራ ብቻ አይኖርም ያለው ስለዚህ ነው። እንጀራን የምንፈልገው ላለመሞት ሲሆን ነፃነትን የምንጠይቀው ለመኖር ነው። ያሁኖችም ኃይላችሁ እስከፈቀደላችሁ በኃይል ገዝታችሁ ታልፋላችሁ፤ ነፃነቱን ከገፈፋችሁት ሕዝብ ጋራ ሳትጣጣሙ።
መሀንዲሱ ስለሕግ የበላይነት በሰፊው ያስወራሉ። እንደ እውነቱ ከሆነ፥ የሕግ የበላይነት ወደታችነት የወረደው በደርግና በወያኔ የጭቆና አገዛዝ ዘመን ብቻ ነው። ፍርድ ቤቶች እስከዛሬ የሚሠሩት በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመን በታወጁ ሕጎች ነው። የዚያን ጊዜው ዳኝነትና ሽምግልናው ከዛሬው ጋር ሲተያይ ምድርንና ሰማይን፥ ጭለማንና ብርሃንን ማስተያየት ይሆናል። የታሪክ ምንጮች እንደሚመሰክሩት፥ የጥንት ነገሥታትም ቢሆኑ የሚገዙት በሕግ ነበር። ነገሥታቱን ከሚያጅቡት ባለሥልጣናት ማህል ትልቁን የክብር ቦታ የሚይዙት ሕግ ዐዋቂዎችና ዳኞች ነበሩ። ለምሳሌ፥ ነገሥታቱ ርስት ለገዳማት ሲጐልቱ፥ በሃይማኖት ጭቅጭቅ ጊዜ ዳኝነት ሲቀመጡ፥ በዓላት ሲያከብሩ፥ ከመኳንንቱ ጋር ለምስክርነትና ሕግ ለመጥቀስ ሕግ ዓዋቂ ታላላቅ ሰዎች በቦታው ይገኛሉ። ይህም ነገሥታቱ ለሕግ የቱን ያህል አክብሮት እንደነበራቸው ያሳያል። የፍርድ ጒዳይ ከንጉሡ ችሎት ሲደርስ ንጉሡ ብቻውን አይፈርድም። ከችሎት ላይ የሚቀመጡ መኳንንትና ሊቃውንት የክብር ተራቸውን ጠብቀው ከታች ወደላይ ይፈርዳሉ። ንጉሡ ሁሉን አዳምጦ የማይሻረውን የመጨረሻውን ፍርድ ይሰጣል።
ገዢዎቹ ሃይማኖተኞች ስለነበሩ ጭካኔያቸውን ለመቆጣጠር ሃይማኖታቸው ከዲሞክራሲ የበለጠ ኀይል ነበረው። ሕግን ከሚፈራ እግዚአብሔርን የሚፈራ ይሻላል። በአንድ ዘመን ንጉሡ ይሙት በቃ የፈረደበትን ሰው እንዲምረው ሽማግሌዎች ቢለምኑት እምቢ ብሎ ነበር። ድንገት በዚያው ጊዜ ፀሐይ ብርሃኗን ነፈገች። ይህ የሆነው በእሱ እምቢተኝነት መሆኑን ያመኑ ንጉሡን ስላሳመኑት፥ ይሙት በቃ የፈረደበትን እስረኛ ነፃ ለቀቀው። ትልቁ ችግር ነገሥታቱ ፍጹም ጻድቃን ሲሆኑ፥ ወይ መንፈሳዊነቱ ላይ ብቻ ያተኲራሉ፤ ወይም ገዳም ገብተው ይመነኲሳሉ።
ከዓሥራ ሰባተኛው ምእት ዓመት ጀምሮ እስከ ሃያኛው ምእት ዓመት ድረስ የሃገሪቱ መተዳደሪያ ሕግ ፍትሐ ነገሥት ነበር። ፍትሐ ነገሥት ስለ ንጉሥ ሲናገር፥ “ከዙፋኑ ላይ ሲቀመጥ፥ በእድሜ ልኩ አብሮት የሚኖር አምላካዊ (የተግሣጽ) ጽሑፍ ካህናት ይጻፉለት፥ ያንን እያነበበ ፈጣሪውን እግዚአብሔርን መፍራት እንዲማርና ትእዛዞቹን እንዲያከብር” ይልና፥ “በመንጋው ላይ በትክክል ይፍረድ፤ ለራሱም ሆነ ለሌሎች፥ ለልጆቹም ሆነ ለዘመዶቹ፥ ወይም ለባዳ አያዳላ” ይላል። ጦርነት ሲታወጅ ጠላት እንዲያሸንፍ የሚያጋልጥ፥ የተመከረውን ምክራችሁን የሚያወጣ፥ ወይም ወደነሱ ሄዶ መሣሪያ የሚሸጥላቸው ይሰቀል፤ ይቃጠልም” ይላል። ኢትዮጵያን ለመገነጣጠል እንደ ታጠቀው እንደ ሻዕቢያ ካለ የሀገር አንድነት ጠላት ጋር የዶለተ ማለት ነው።
የጎንደር ቤተ መንግሥት ዘርፈ ብዙ ወግና ሥርዓት በጥንቃቄ ስለተመዘገበ፥ የረቀቀ ሥልጣኔያችንንና በቤተ መንግሥት የዜጎች መብት እንደ ታቦት ይከበር እንደነበረ ለማሳየት በግዕዝ የደረሰንን አጭር ሰነድ ወደአማርኛ እየተረጐምኩ ላቅርብ፤
ግራና ቀኝ ወምበሮች ለፍርድ በችሎት ሊቀመጡ ሲሉ፥ መጀመሪያ በቅዱስ ያሬድ ቃል በዜማ እንዲህ ብለው ይጸልያሉ፤ “ሃሌ ሉያ፤ ዕዳ በሚከፈልባት በዚያች ዕለት፥ ፍርድ በሚሰጥባት በዚያች ዕለት፥ በዚያች በእግዚአብሔር ዕለት ነፍሳችንን ምን እንላታለን? . . .” ይኸንን ጸሎት ሦስት ጊዜ እስከመጨረሻው ይሉና ትርጓሜውን ከጽራግ ማሠሬ (ከንጉሥ አልባሽ) እና ከሊቀ ማእምራን (ከትልቁ ሊቅ) ይሰማሉ። ከዚያ በኋላ (ዳኞቹ) በንጉሥ ሰቀላ ቤት ለፍርድ በቀኝና በግራ ይቀመጣሉ። ከበሽተኞች፥ ከሴቶች፥ ከመምህራን በቀር ትንሹም ትልቁም ሹምም ብሕትወደድም ደጃዝማችም ተቀምጦ አይፋረድም። ቁጭ ብሎ የሚፋረድ ባለሥልጣን የአክሱም ነብርድ ብቻ ናቸው።
“ትርጓሜ” የሚለው በግዕዝ የተነበበውን እንደዚህ እኔ ወደ አማርኛ እንደተረጐምኩት ጥሬ ትርጒም ማለት አይደለም። የምጽአት ዕለት ነፍስ በታላቁ ዳኛ ፊት ቆማ፥ እያንዳንዱ ሰው የሠራው ሥራ በጎውና ክፉው ይመዘናል። የሰውየው የዘላለም ሕይወት የሚወሰነው በሚመዘነው ሥራ ነው። ሚዛኑን የሚይዙት መላእክት ስለሆኑ፥ ተዳላብኝ የሚል አይኖርም። ማንም ሰው ወደፈለገበት ሕይወት ለመሄድ ዕድሉ አሁን እንደሆነ ሊቃውንቱ ያስረዷቸዋል። ለዳኞቹ በተለየ የሚጠቅሱላቸው፥ “እንዳይፈረድባችሁ በአድላዊነት አትፍረዱ” የሚለውን የክርስቶስ ቃል ነው። አባ አበክረዙን የሚባሉ መነኲሴ የገዳማቸው አለቃ (አበ-ምኔት) እንዲሆኑ ሲጠየቁ፥ እምቢ ለማለት፥ “እርጉሞች ሆይ፥ ወዲያ ለሰይጣንና ለሠራዊቱ ወደተዘጋጀው እሳት ሂዱ” የሚለውን የጌታ ቃል ጠቅሰው፥ “ከዚህ ቃል በቀር ሰውን እንደማዘዝ የሚያስፈራኝ ሌላ ነገር የለም” ማለታቸው የዕለተ እግዚአብሔርን አስፈሪነት በማስታወስ ነው። ከድርሰቶቻቸው እንደምገምተው፥ አባቶቻችንና እናቶቻችን እግዚአብሔን ያከብራሉ፤ ፍርዱንም እንደማይስት ተወርዋሪ ጦር ይፈሩ ነበር።
የሰው ልጅ፥ በተለየም ገዢ፥ ሌላውን እንዳይበድል የሚቆጣጠረው፥ አንደኛ፥ ፈሪሃ እግዚአብሔር ሲያድርበት፥ ሁለተኛ፥ በትምህርት የዳበረ የተፈጥሮ ርኅራኄ ሲኖረው፥ ሦስተኛ፥ የመንግሥት የጸጥታ ኀይል በጎኑ ሲቆም፥ አራተኛ፥ ገዢውን የሚያሰጋ የተደራጀ የሕዝብ ኀይል ሲኖር ነው። በአሁኑ ሰዓት የኢትዮጵያ ሕዝብ እምነቱ ከነዚህ ውስጥ በየትኛው ነው?

Sunday 15 July 2012

የኤክስፖርት ገቢ መቀነስ ለትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ፈተና ነው ተባለ

የዘንድሮ የወጪ ንግድ አፈጻጸም ከታቀደው በታች የቀነሰ በመሆኑ፣ ለአምስት ዓመቱ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽ ዕቅድ ለታሰበው ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ትልቅ ፈተና ሊሆን እንደሚችል ተጠቆመ፡፡ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትና የኢትዮጵያ ልማት ምርምር ተቋም በጋራ ባዘጋጁት ዓውደ ጥናት ላይ የተገኙት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አብርሃም ተከስተ ከሁለት ዓመት በላይ የሆነው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ የወጪ ንግድ ገቢ ምን ያህል ሊሆን እንደሚገባው ተዘርዝሮ የተቀመጠ ቢሆንም፣ በተያዘው በጀት ዓመት በዕቅድ የተቀመጠውን ያህል ያለመሆኑ ሊያሳስብ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

ባለፈው ማክሰኞ በተካሄደው በዚህ ዓመታዊ ጥናት ላይ በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ የግሉ ዘርፍ ሚናና ተሳትፎን በሚመለከት በሚኒስትር ዴኤታው በቀረበው ጽሑፍ፣ የአገሪቱን ኢኮኖሚያው ዕድገት ለማስቀጠል የወጪ ንግዱ ትልቅ ቦታ ተሰጥቶታል፡፡

በ2003 ዓ.ም. የተገኘው የውጭ ምንዛሪ በ2002 ዓ.ም. ከተገኘው በ37 በመቶ ብልጫ ነበረው፡፡ የ2004 በጀት ዓመት አጠቃላይ መረጃው ባይደርስም በአሥር ወራት የተገኘው ገቢ ሲታይ ከአምናው ብልጫ ያለው ቢሆንም ከታቀደው ጋር ሲነፃፀር አነስተኛ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

የወጪ ንግድ ገቢው በዚህ ሁኔታ ከታቀደው በታች መገኘቱ በተከታታይ እየታየ ያለውን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ከ2005 ዓ.ም. በኋላም ለማስቀጠል ትልቅ ፈተና ስለሚሆን፣ በዘርፉ ብዙ መሠራት እንዳለበት በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

በተለይ በአገሪቱ የወጪ ንግድ ዋነኛ ተሳታፊ የሆነው የግሉ ዘርፍ ትልቅ ኃላፊነት እንዳለበት የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው፣ በታቀደው ልክ ለምን መላክ እንዳልተቻለና በተለምዶ ለረጅም ዓመታት ወደ ውጭ የሚላኩ ምርቶች ሳይቀሩ በተፈለገው መጠን ያለመጨመራቸው ምክንያት በአግባቡ መዳሰስ አለበት ብለዋል፡፡ የወጪ ንግድ ገቢ ቀነሰ ከተባለ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የግሉ ዘርፍ ተጠያቂ ሊሆን እንደሚችል ጭምር ገልጸዋል፡፡

ከወጪ ንግድ እንቅስቃሴ ጋር በተያያዘ የጨርቃ ጨርቅና ጋርመንት ምርቶች በዕቅድ ዘመኑ መጨረሻ ላይ አንድ ቢሊዮን ዶላር እንደሚገኝባቸው የታቀደ ቢሆንም፣ አሁን እየተገኘባቸው ያለው ገቢ ግን እጅግ አነስተኛ ሆኖ መገኘቱን በምሳሌነት ጠቅሰዋል፡፡ መንግሥት በቀጥታ ምርት ወደ ውጭ እንደማይልክ ያስታወሱት ሚኒስትር ዴኤታው፣ በዚህ ረገድ ትልቅ ኃላፊነት ያለበት የግሉ ዘርፍ ነው ብለዋል፡፡ ሆኖም መንግሥትና የግሉ ዘርፍ በጋራ እስካልሠሩ ድረስ የታሰበውን ዕቅድ ለማሳካት አስቸጋሪ ሊሆን እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል፡፡

እንዲህ ዓይነቱ ችግር ሊታሰብብት የሚገባና መንግሥትና የግሉ ዘርፍ በጋራ መሥራት እንዳለባቸው ያመለከተ ከመሆኑም በላይ፣ በጋራ ለውጤት የሚያበቃ ምክክር ማድረግ አስፈላጊ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

ዶ/ር አብርሃም የዕድገትና ትራንስፎርሜሽነ ዕቅዱ ከግሉ ዘርፍ ጋር ስለሚኖረው ሚና አስመልክተው ሰፊ ማብራሪያ በሰጡበት በዚህ መድረክ፣ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ሰፊ ውይይት ተደርጐበት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀ በመሆኑ፣ የሕግን ያህል አስፈላጊና ከዚህም አንፃር ተጠያቂነት የሚያስከትል ዕቅድ ተደርጎ መታየት እንዳለበት አስረድተዋል፡፡

ተጠያቂነት ሲባል ደግሞ ሁሉንም ዜጐች ተጠያቂ የሚያደርግ ዕቅድ ነው፡፡ ዕቅዱ የመንግሥት ብቻ ተደርጐ መወሰድ የሌለበትና የአገር ብሎም የሁሉም ዜጋ ዕቅድ መሆኑን በማመን፣ በተለይ የግሉ ዘርፍ አፈጻጸም ትልቅ ቦታ ይሰጠዋል ብለውል፡፡

መንግሥት በተመረጡ ዘርፎች ላይ ብቻ የሚሳተፍ መሆኑን ያስታወሱት ሚኒስትር ዴኤታው፣ መንግሥት በብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ፣ በማዳበርያና በስኳር ልማት ብቻ ተሳታፊ ሲሆን፣ ሌላው ለግሉ ዘርፍ የተተወ በመሆኑ ለዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ተፈጻሚነት ዋነኛ ተዋንያኑ የግሉ ዘርፍ መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል ብለዋል፡፡

የግል ዘርፉን ለማበረታታት በዕቅዱ ውስጥ በርካታ ጉዳዮች እንዳሉና በተለይ በግሉ ዘርፍና በመንግሥት መካከል የሚደረገው የምክክር መድረክ ወሳኝ ቦታ ይሰጠዋል በማለት ገልጸዋል፡፡ የግሉ ዘርፍ በመንግሥት ላይ በጎ ተፅዕኖ የማሳደር፣ መንግሥትም ከግሉ ዘርፍ የሚነሳውን ሐሳብ በቅንነት በመቀበል ተግባራዊ እንዲሆን የማድረግ አሠራር እንዲኖረው በማድረግ፣ ከዚህ ቀደም ከተደረጉት የምክክር መድረኮች በተሻለ መንገድ እንዲካሄድ ይደረጋል ብለዋል፡፡ እንደ ምሳሌ ያቀረቡትም በኤክስፖርት ዘርፍ ምክክር ሲደረግ የተለመደው ዓይነት ሳይሆን እንሠራዋለን ተብሎ በዕቅድ የተያዘውን ማስፈጸም የሚያስችል ምክክር ዓይነት መሆን እንዳለበትና የጋራ ተጠያቂነት እንዳለበትም አስታውቀዋል፡፡

መንግሥት መሥራት ያለበትን ሥራ ካልሠራ፣ ባለሀብቱም ውጤት ካላስገኘ ለምን የሚባልበት የምክክር መድረክ መፈጠር ይኖርበታል ያሉት ሚኒስቴር ደኤታው፣ ለዕቅዱ አፈጸጸም መጓደል ሁሉም ወገኖች እንደ ድርሻቸው ተጠያቂ እንደሚሆኑ አሳስበዋል፡፡

መንግሥት በኮብልስቶን ሥራ የተሰማሩ ምሩቃን መበረታታት አለባቸው አለ.......ጉድ ነው !!!

Sunday, 15 July 2012 00:00 
“የእኛ ዜጎች ፒኤችዲ ይዘው በአሜሪካ የጥበቃ ሠራተኞች ናቸው” የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር
ዜጎች አንደኛም ይሁን ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ይዘው በኮብልስቶን ሥራና በሌሎችም ሥራዎች ላይ ተሰማርተው ከተገኙ፣ መንግሥትም ሆነ ኅብረተሰቡ ማበርታት እንዳለበት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስቴር ሐምሌ 4 ቀን 2004 ዓ.ም በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቀ፡፡
የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትሩ አቶ መኩሪያ ኃይሌ እንደገለጹት፣ የተማሩ ወገኖች ራዕይ ሰንቀው በሆነ ሥራ ላይ በመሰማራት የአስተሳሰብና የመንፈስ ነፃነት ኖሯቸውና ወደፊት እንደሚቀየሩ አምነው ከሠሩ፣ እነሱን የሚፈታተን ነገር መደረግ እንደሌለበት አሳስበዋል፡፡

ያልተማረን የኅብረተሰብ ክፍል ለተወሰነ ቀናት በማሠልጠን ሊሠራው በሚችለው የኮብልስቶን ጠረባ ሥራ ለ15 እና ለ16 ዓመታት የተማሩ ዜጎችን ማሰማራት “ብክነት አይሆንም?” በማለት የተጠየቁት አቶ መኩሪያ፣ “አንዳንድ ጊዜ በደንብ ማሰብ ይገባናል፤ የእኛ ዜጐች ፒኤችዲ ይዘው በአሜሪካ አገር የጥበቃ ሥራ ይሠራሉ፡፡ በዚህ ጊዜ ግን ማንም አጀንዳ አድርጎ ያነሳው የለም፤” በማለት በአገራቸውና ለአገራቸው እየሠሩ ነገ የሚቀየሩ መሆናቸውን አስበው፣ አውቀውና ፈልገው ቢሠሩ መደሰት ያለባቸው እንደሚመስላቸው ተናግረዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ ብዙ ዓይነት የሥራ ዕድሎች የተፈጠሩ መሆናቸውን፣ የተወሰነ ሀብት ያለው ቤተሰብ ያላቸው ምሩቃን የተወሰነ ገንዘብ ስለሚያገኙ በተማሩበትና በሠለጠኑበት ሙያ መሰማራት የሚችሉበት ዕድል እንዳላቸው የገለጹት አቶ መኩሪያ፣ የተወሰኑ ምሩቃን ግን ተመርቀው በሚወጡበት ጊዜ ምንም ጥሪት ስለሌላቸው፣ ለተወሰነ ጊዜ በመረጡት ሥራ ላይ ተሰማርተው [ኮብልስቶን መጥረብን ጨምሮ] ጥሪት ከያዙ በኋላ እንደሚለወጡና አገራቸውንም እንደሚጠቅሙ አስታውቀዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በተለይ በያዝነው የበጀት ዓመት ግዙፍ ግንባታዎችና የተለያዩ ሰፋፊ ፕሮጀክቶች በስፋት እየተሠሩ በመሆናቸው፣ አገርን ከመገንባት አኳያ የተማረውም ያልተማረውም በማንኛውም የሥራ መስክ ተሰማርቶ መሥራት እንዳለበትም አቶ መኩሪያ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ቀደም ባሉት ዘመናት ስሟ በምን ይጠራ እንደነበርና በአሁኑ ጊዜ ስለሷ ዓለም ምን እያወራ እንደሚገኝ ማንም ዜጋ የሚያውቀው መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፣ “ማንም ኢትዮጵያዊ የሆነ ዜጋ ሁሉ በማንኛውም ሥራ ላይ ቢሰማራ [በኮብልስቶን ጠረባ ላይም ቢሆን] አገሩን እየገነባ መሆኑን አውቀንና የኩራታችን መገለጫ አድርገን መውሰድ ይገባናል፤” በማለት አሳስበዋል፡፡

“የተማረ ሰው የሚሠራበት የሥራ ወሰን የለውም፤ በምርምር፣ በአገልግሎት፣ በቴክኖሎጂ፣ ወዘተ” ሊሰማራ እንደሚችል የገለጹት አቶ መኩሪያ፣ የተማረ ዜጋ የሥራ መስክ እንደጠበበት ተደርጐ መወሳት እንደሌለበትና የተወሰነው በኮብልስቶን፣ የተወሰነው ደግሞ በከተማ ፅዳት፣ የተወሰነው ደግሞ በአረንጓዴ ልማት ሊሰማራ የሚችልበት ሰፊ የሥራ ዕድል መኖሩን ጠቁመዋል፡፡ ይህም በመንግሥት በኩል እንደሚበረታታና ድጋፍ ስለሚደረግለት እንደሚያድግና እንደሚለወጥ ያላቸውን እምነት አክለዋል፡፡

ሚኒስትሩ በመግለጫቸው እንዳስታወቁት፣ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ የሥራ አፈጻጸም ለ1‚148 ሺሕ ዜጐች የሥራ ዕድል መፈጠሩንና ከዕቅዱ በላይ የተሳካ ሥራ መሠራቱን ነው፡፡

በዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ 3.05 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጐች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዶ እንደነበር የተናገሩት ሚኒስትሩ፣ በ2004 በጀት ዓመት ያለው አፈጻጸም ግን 1.15 ሚሊዮን ወይም 189 በመቶ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይህም በግል ባለሀብቶች የተሰማራውንና በመንግሥት ሲቪል ሰርቪስ መዋቅር የተቀጠረውን እንደማያካትት አረጋግጠዋል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ የተፈጠረው የሥራ ዕድል በኮንስትራክሽን 237 ሺሕ፣ በአገልግሎት 128 ሺሕ፣ በንግድ 116 ሺሕ፣ በማኑፋክቸሪንግ 107 ሺሕና በከተማ ግብርና 73 ሺሕ መሆኑንም ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡ ከዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ፕሮጀክቶች ማለትም ከቤቶች፣ ከመንገድ፣ ከጥርብ ድንጋይ፣ ከኃይል አቅርቦት፣ ከውኃና መስኖ፣ ከባቡርና ከስኳር ፕሮጀክቶች በድምሩ ለ1‚148 ሺሕ ዜጎች የሥራ ዕድል መፈጠሩን አውስተዋል፡፡ በክልሎችም የተሟላ መረጃ ባይገኝም በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በደቡብ፣ በአዲስ አበባና በትግራይ በድምሩ 66 ሺሕ ለሚሆኑ ዜጐች የሥራ ዕድል መፈጠሩን ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡