Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Thursday 4 October 2012

ኦህዴድ ውስጡን እየታመሰ ነው!

ህወሃት እንደበሬ ጠምዶ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ለቆበት የነበረው ኦህዴድ፤ “ካሁን በኋላ ህዝቤን ኣላስንቅም፣ ኣላስመዘብርም፣” በማለቱ የምንጠራ ዘመቻ ጀምሮበታል። የኦህዴድ ኣባላት በህወሃት ተደልለው ወይም ፈርተው ወንድሞቻቸውን ይበሉ ይሆን? መቼም ወያኔ ደፍሮ ጦሩን ኣያዘምትም። የሚልከው ያው የኦሮሞ ልጅ የኦሮሞ ልጅን እንዲበላ ነው። ቁርጥ ቀን እየመጣች ነው።
(ሰንደቅ ጋዜጣ)፦ የኢህአዴግ መተካካትን ተከትሎ በኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ውስጥ አነጋጋሪ ስሜት ፈጥሯል። ድርጅቱ በኢህአዴግ አመራር መተካካት መሠረት ከፊት አለመምጣቱ ድርጅቱ አመራር ባለማብቃቱ ነው የሚሉ ትችቶች እየተሰነዘሩ ነው።
አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈጉ የድርጅቱ ምንጭ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት በኦነግ አስተሳሰብ የተወጠሩ መተካካቱን ባልሆነ መስመር እያራገቡት ነው ብለዋል። አራቱ ድርጅቶች አንድ ግንባር ፈጥረዋል። በብሔራዊ መግባባት የተጀመረውን ልማት በማስቀጠል የሕዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የድርጅቱ ዋነኛ ዓላማ መሆኑን ተናግረዋል።
ይሄንን መተካካት የሚያራግቡ የኦሮሞ ሕዝብ እንዲገነጠል የሚፈልጉ “ጠባቦች” መሆናቸው የጠቀሱት ምንጫችን የኦሮሞ ሕዝብ ከኢትዮጵያውያን ወንድሞቹ የሚገነጠልበት አመለካከት የመሸበት ጊዜ ላይ መድረሱን ገልፀዋል። 8 ነጥብ 9 ሚሊዮን የኦሮሞ ሕዝብ ከትግራይ በስተቀር በሚያዋስኑት ክልሎች ድንበር ላይ እንደሚኖር በማስታወስ የኦሮሞ ሕዝብ ተገንጥሎ እየደማ እንዲኖር የሚፈልጉ ኃይሎች መተካካቱን እያጥላሉ ነው ብለዋል።
መስከረም 5 ቀን 2005 ዓ.ም የኢህአዴግ ም/ቤት የመተካካት ጉባኤ ባካሄደበት ወቅት የህወሓት ሥራ አስፈፃሚ አባል በሆኑት በወ/ሮ አዜብ መስፍን አማካይነት የኦህዴድ ሥራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ ሶፊያን አህመድ ለግንባሩ አመራር መጠቆማቸው ድርጅቱ በኢህአዴግ ውስጥ የእራሱን ዕጩ ማቅረብ አልቻለም የሚሉ ትችቶችን አስከትሏል። የኦህዴድ ሊቀመንበር አቶ አለማየሁ አቶምሳ እና ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ሙክታር ከድር ተዘለው አቶ ሶፊያን መጠቆማቸው ድርጅቱ ብቁ አመራሮችን አላሰለፈም የሚል ጉምጉምታን አስነስቷል።

TPLF CC member & EFFORT director defects to the US with his family

The rumor that has been swirling around has been confirmed by TPLF mouthpiece. How much money did Getachew Belay bring along or has he already stashed away? Is he in the US to help other TPLF heads in case of a meltdown? Can he be investigated by the US for money laundering (stealing aid money, diverting finances gained illegally abroad...) and looting of Ethiopia?


(Reporter) -- የግል ተቋማት ሠራተኞች የማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው በላይ ከአገር እንደወጡ አለመመለሳቸውን ምንጮች ገለጹ፣ ኤጀንሲው በሥራ ገበታቸው ላይ በአጭር ቀን ውስጥ ካልተመለሱ ዕርምጃ እወስዳለሁ ብሏል፡፡

የቀድሞ የገቢዎች ሚኒስትር በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ጌታቸው በላይ፣ በመቀጠልም የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕውሓት) ኢንዶውመንት የሆነው ኤፈርት ምክትል ሥራ አስፈጻሚ በመሆን እስከ ቅርብ ጊዜ አገልግለዋል፡፡ ከዓመት በፊት ደግሞ የግል ተቋማት ሠራተኞች የማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመሆን ተሾመው ነበር፡፡

Wednesday 3 October 2012

ጉዞ ወደ ለንደን ሚጢጢ ማስታወሻ! ከአቤ ቶኪቻው

በአሁኑ ሰዓት ራሷን “ታላቋ” እያለች መጥራት የሚቀናት “ግሬት ብሪታኒያ” ውስጥ እገኛለሁ። ከሀገሬ ከተሰደድኩ በኋላ እንግሊዝ ሁለተኛዋ መቀመጫዬ ሆነች ማለት ነው። ከዚህ በፊት ለነበሩት አስር ወራት ኬኒያ ናይሮቢ ከጆጎ ቤት ፊት ለፊት ባለው ግቢ ውስጥ እኖር ነበር።
ኬኒያ በርካታ ኮሚክ ነገሮች አሉ። ከፖሊስ እና ሀበሻው አባሮሽ ጀምሮ አስከ ሙስናቸው ድረስ አስማታዊ ክስተቶች ሁሉ እንደመደበኛ ነገር የሚቆጠሩበት ሀገር ኬኒያ ነው። ኬኒያውያን፤ መንግስታቸውን እግዚአብሄር፣ አሜሪካ እና እንግሊዝ ደግፈው ባይዙላቸው ኖሮ በሙስና ጎርፍ ተጥለቅልቀው አጠገባቸው ያለው ህንድ ውቂያኖስ ውስጥ ይሰጥሙ ነበር። ቆይ እዝች ጋ ፍሬን ያዝ እናድርግ ስለ ኬኒያ ሌላ ጊዜ እንመለስበታለን።
አሁን ስለ ታላቋ እንግሊዝ እናውራ፤ እግረ መንገዳችንንም ከታለቋ ኢትዮጵያ ጋር አንዳንድ ጉዳዮች ላይ እናነፃፅራት ምናባቱ፤ የፈጀውን ይፍጅ…! ፤አንቺም ጠጪ ለኔም ቅጂ ነው ነገሩ…!
እንግሊዝ እንደገባሁ አንድ ኮንዶሚኒየም ህንፃ ላይ አንድ መኝታ ቤት አንድ ሳሎን አንድ ኩሽና… አሃ… ማድቤት ጢስ አልባ ሲሆን ለካ “ኪችን” ነው የሚባለው ስለዚህ እናስተካክል… አንድ ኪችን… አንድ ባኞ ቤት እና አንዲት የእቃ ቤት ያለው ክፍል ተሰጠኝ።
ከኬንያ ስመጣ የራሴን አንድ የሰው ረከቦት እና ከሰል ምድጃ ይዤ ነው የመጣሁት። መቼም ሀበሻ ተሰዶ አይሰደድም። ወደ እንግሊዝ እንደምሄድ የሰሙ አንድ እናት ለንደን ለምትገኝ ልጃቸው ረከቦት እና ከሰል ማንደጃ ሲልኩኝ። ከዚህ በፊት አንድ ሰው፤ “ሀበሻ ሀገሩን ይዞ ነው የሚሰደደው” ብለው የተናገሩት ነው ትዝ ያለኝ። እውነትም በስደት ሀገር የጎበኘኋቸው አበሾች፤ አብዛኛዎቹ ቤታቸው ውስጥ ስገባ ኢትዮጵያ ያለሁ እስኪመስለኝ ድረስ፤ ከጤፍ እንጀራ ጀምሮ ሽሮ ወጥ በቃሪያ ሁሉ አግኝቻለሁ። አረ ያዩትን ሁሉ ማውራት ምንድነው ብዬ እንጂ ለንደን በእንግድነት የተቀበሉኝ ወዳጆቼ ቁርጤን አውቄ የተውኩትን ቁርጥ እና ከየት ይምጣል ብዬ የተውኩትን የዶሮ አይን የመሰለ ጠላም አጠጥተውኛል። ሀገርን ይዞ መሰደድ ታድያ ይሄ አይደል!?

ንግድ ባንክ ለሼክ አል አሙዲ ፈቅዶት የነበረው የ850 ሚሊዮን ብር ብድር ታገደ

(ሪፖርተር ጋዜጣ)
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ በቅርቡ ለሼክ መሐመድ አል አሙዲ የፈቀደው የ850 ሚሊዮን ብር ብድር እንዲታገድ መወሰኑን የንግድ ባንክ ምንጮች ገለጹ፡፡ ንግድ ባንክ ይህን ብድር ለመስጠት ሲስማማ የማበደር አቅሙን አልፈተሸም፣ ዘንድሮ ከባንኩ ብድር የሚፈልጉ እንደ ስኳር ፕሮጀክቶች የመሳሰሉ የመንግሥት የልማት ዕቅዶች የብድር ፍላጎት በአግባቡ አልተጤነም፣ እንዲሁም በአንድ ጊዜ ለአንድ ተበዳሪ ከፍተኛ ገንዘብ ለመልቀቅ መወሰኑ አግባብ አለመሆኑ ስለታመነበት፣ ብድሩ ለጊዜው እንዲቆም መንግሥት መወሰኑን እነዚህ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ ተበዳሪው ሼክ አል አሙዲ ብድሩን ለመውሰድ ጥያቄ ያቀረቡት ለአፍሪካ ኅብረት ለሚያሠሩት ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ሕንፃ ሊፍት መግዣና መግጠሚያ ነው፡፡ ብድሩም በቀጥታ ሊሰጥ የታቀደው ሊፍቱን ለሚያስመጣው ኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ለተባለው ሌላኛው የሼክ አል አሙዲ ኩባንያ ሲሆን፣ ንግድ ባንክ ለሊፍቱ ማስመጫ ራሱ ኤልሲ ከፍቶ ኮሚሽን ከማግኘት ይልቅ፣ በኤልሲ ኮሚሽን የሚያገኘውን ገቢ ትቶ በቀጥታ ለኢኳቶሪያል ቢዝነስ ግሩፕ ብድሩን ለማስተላለፍ መምረጡ፣ የብድር ክፍል ሠራተኞችን ያስገረመ ጉዳይ እንደሆነ የባንኩ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዳይሬክተሮች ቦርድ ለሼክ አል አሙዲ ኩባንያዎች 942 ሚሊዮን ብር ብድር መፍቀዱን መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን፣ ብድሩ የፀደቀው ሚድሮክ ኢትዮጵያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት ለሚገነባው የአፍሪካ ኅብረት ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ሕንፃና ለማያ ፒፒ ከረጢት ፋብሪካ ግንባታ ነው፡፡ ለአፍሪካ ኅብረት ሆቴል ሕንፃ ማጠናቀቂያ 850 ሚሊዮን ብር ተፈቅዶ የነበረ ሲሆን፣ ለከረጢት ፋብሪካው ግንባታ ደግሞ 92 ሚሊዮን ብር ነበር ቦርዱ ያፀደቀው፡፡ ለብድር ማስመለሻ የተያዙት ዋስትናዎች (ኮላተራልስ) እየተገነቡ ያሉት የሆቴል ሕንፃና የከረጢት ፋብሪካዎች ነበሩ፡፡ ሚድሮክ የአፍሪካ ኅብረትን ባለአምስት ኮከብ ሆቴልን ለመገንባት በ1998 ዓ.ም. 90 ሺሕ ሔክታር መሬት መረከቡ ይታወሳል፡፡ ሚድሮክ የወሰደው የአዲስ አበባ

Sunday 30 September 2012

የታላቁ ሩጫ ሀብትና ንብረት ሊወረስ ነው

‹‹ከሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ጋር እየተደራደርን ነው››  አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ
በዮሐንስ አንበርብር
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ (Great Ethiopia Run) ላለፉት 12 ዓመታት በአዲስ አበባና በተለያዩ ክልልሎች የጎዳና ላይ ሩጫ ለተለያዩ ዓላማዎች በማካሄድ ያገኘው ሀብት ሕገወጥና ከተመሠረተበት ዓላማ ውጪ ነው ተብሎ ሊወረስ ነው፡፡
ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በአትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴና ጓደኞቹ የተመሠረተ ሲሆን፣ ለትርፍ ያልተቋቋመ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በመሆንም ከ12 ዓመታት በፊተ በፍትሕ ሚኒስቴር ሥር ተመዝግቦ ዕውቅና አግኝቷል፡፡

ከተመሠረተ ጀምሮ በየዓመቱ በአዲስ አበባ ላይ የ10 ሺሕ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ  በማከናውን የበለጠ ትኩረትን ያገኘው ታላቁ ሩጫ፣ በአዲሱ የበጎ አድራጎት አዋጅ መሠረትም ተመዝግቦ ዕውቅና አግኝቷል፡፡

ይሁን እንጂ የበጎ አድራጎትና ማኅበራት ኤጀንሲ ባካሄደው የኦዲት  ሥራ ታላቁ ሩጫ የበጎ አድራጎት ሥራ ለመሰማራት ፈቃድ ቢሰጠውም ተግባሩ ግን ከተመዘገበበት ዓላማ ውጪ መሆኑን፣ በአትራፊ ድርጅትነት ሲንቀሳቀስ መገኘቱንና ከዚህም መንግሥት ተገቢውን ጥቅም አለማግኘቱን ለመረዳት እንደተቻለ፣ የኤጀንሲው የሕዝብ ግንኙነት የሥራ ሒደት ባለቤት  አቶ አሰፋ ተስፋዬ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

በአብዛኛው አትራፊ ሥራዎችን ሲያከናውን የቆየው ታላቁ ሩጫ፣ አልፎ አልፎም የበጐ አድራጐት ተግባራትን ያከናውን እንደነበረ አቶ አሰፋ ይናገራሉ፡፡  ከዚህም ውስጥ ሜሪ ጆይና አበበች ጐበና የተባሉ የበጐ አድራጐት ድርጅቶች ከታላቁ ሩጫ የገንዘብ ልገሳ አግኝተው እንደሚያውቁ አስረድተዋል፡፡

ኤጀንሲው የታላቁ ሩጫን ሕገወጥ እንቅስቃሴ በተረዳበት ወቅት የድርጅቱን ኃላፊዎች በመጥራት ማነጋገሩን ታላቁ ሩጫ በበጐ አድራጎት ድርጅትና የተመዘገበው በፍፁም የዋህነት እንደሆነና ምንም ዓይነት የማጭበርበር ተግባር ለመፈጸም እንዳልነበረ ለመረዳት እንደተቻለ፣ የሕዝብ ግንኙነት ሥራ ሒደት ባለቤቱ ተናግረዋል፡፡

አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴም ይህንኑ ሁኔታ ለሪፖርተር አስረድቷል፡፡ “ታላቁ ሩጫን ለመመሥረት በመጀመሪያ የሄድነው ይመለከታቸዋል ብለን ካሰብናቸው ፈቃድ ሰጪ የመንግሥት ድርጅቶች ዘንድ ነበር፡፡ እንደ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የመሳሰሉት ማለት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ከእነዚህ ድርጅቶች ተገቢውን ትብብር ማግኘት አልቻልንም፤” በማለት ኃይሌ በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ያስታውሳል፡፡

“በመጨረሻ የነበረን አማራጭም በአትራፊ ድርጅትነት ለመሥራት ካልተፈቀደልን ለትርፍ ያልተቋቋመ የበጐ አድራጐት ድርጅት ሆነን መሥራት የመጨረሻ አማራጫችን በመሆኑ ነው ወደ ፍትሕ ሚኒስቴር አምርተን ፈቃዱን ያገኘነው፤” ሲል አትሌት ኃይሌ ገልጿል፡፡

ፍትሕ ሚኒስቴር  በበጎ አድራጎት ድርጅትነት ከመዘገበውና ፈቃድ ከሰጠው በኋላ ዓመታዊ የጐዳና ላይ ሩጫ ማዘጋጀት የጀመረው ታላቁ ሩጫ፣ ከተለያዩ ግዙፍ ዓለም አቀፍና አገር አቀፍ ተቋማት ከፍተኛ የስፖንሰር ድጋፍ ያገኝ የነበረ መሆኑ በግልጽ የሚታወቅ ሲሆን፣ ፍትሕ ሚኒስቴር ግን አንድም ቀን የታላቁ ሩጫን ተግባር ከሕግ አግባብ በመፈተሽ ችግሮችን ለመለየት አልሞከረም፡፡

በአዲሱ አዋጅ መሠረትም በበጐ አድራጐትና ማኅበራት ኤጀንሲ በድጋሚ ሲመዘገብም ምንም ዓይነት እክል አልገጠመውም፡፡ ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ የሥራ ሒደት ባለቤቱን ‹‹ለምን?›› ያልናቸው ሲሆን፣ የሰጡት ምላሽም አጭርና “በወቅቱ ሁላችንም ለሥራው አዲስ ነበርን፤” የሚል ነው፡፡

በአዲሱ የበጐ አድራጐትና ማኅበራት አዋጅ መሠረት አዋጁን በመጣስ እንቅስቃሴ ውስጥ የተገኙ ድርጅቶች እንዲዘጉ ሲወሰንባቸው፣ ሀብትና ንብረታቸውም ተወርሶ በበጐ አድራጐት ሥራ ላይ ለተሰማሩ ተመሳሳይ ተቋማት እንዲከፋፈል ይደረጋል፡፡ አሊያም መንግሥት ኅብረተሰቡን ለሚጠቅም የልማት ሥራ ያውለዋል፡፡

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታም በዚህ ሕግ የሚወሰን ቢሆንም፣ በአገር ገጽታ ግንባታ ላይ ባደረገው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ግን የተለየ አስተያየት ተደርጐለታል፡፡

ከዚህም መካከል ድርጅቱን በአፋጣኝ ከመዝጋት በመቆጠብ ወደ አትራፊ ድርጅትነት ወይም በተለየ አወቃቀር እንዲደራጅና ከሌላ የመንግሥት አካል ፈቃድ እንዲወስድ ቀነ ገደብ ተሰጥቶታል፡፡

በመሆኑም እ.ኤ.አ. እስከ ዲሴምበር 2012 መጨረሻ ድረስ አሁን ያለው ሕጋዊ ሰውነት የሚጠበቅለት ሲሆን፣ ከዚህ በኋላ ግን ከኤጀንሲው መዝገብ እንደሚሰረዝና ሀብትና ንብረቱም ተወርሶ በሕጉ መሠረት እንደሚስተናገድ አቶ አሰፋ ለሪፖርተር አስታውቀዋል፡፡

በባንክ ያለው ገንዘብ ተጣርቶ አሥር ሚሊዮን ብር እንዳለው የተረጋገጠ ሲሆን፣ ሌሎች ተንቀሳቃሽና ቋሚ ንብረቶችም ተመዝግበዋል ያሉት ኃላፊው፣ እስከተሰጠው ቀነ ገደብ ድረስ የሚያገኘውን ሌሎች ገቢዎች ጨምሮ ለኤጀንሲው እንዲያስረክብ  መስማማታቸውን ተናግረዋል፡፡

ይህ ካልሆነ ግን ኤጀንሲው ሕጋዊ ዕርምጃ እንደሚወስድ አቶ አሰፋ ገልጸዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት ከስፖርት ኮሚሽንና ከአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመነጋገር ውድድሩን ማስቀጠል የሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከመግባባት ተደርሷል ያለው ኃይሌ ገብረ ሥላሴ፣ የታላቁ ሩጫን ሀብትና ንብረትን በተመለከተ ግን ከሚመለከታቸው የመንግሥት ኃላፊዎች ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን ለሪፖርተር ተናግሯል፡፡

“አንድ ቀን ስፖንሰሮችን ብናጣ ሩጫው መቋረጥ የለበትም በሚል እሳቤ ያስቀመጥነው ሀብትና ንብረት አለ፤ ይህ ሀብት ተወርሶ ታላቁ ሩጫን ማስቀጠል አስቸጋሪ ይመስለኛል፡፡ የለፋንበትን ታላቁ ሩጫን በገንዘብ እንደመግዛት ይሆንብኛል፤” ሲል ይህ እንዳይከሰትና ታላቁ ሩጫ ሳይቋረጥ እንዲቀጥል ኃይሌ ምኞቱን ገልጿል፡፡