Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Wednesday 20 February 2013

ዴንማርካዊው ወያላ

በሳይስ  ፌልቦርግ ግሬገሰን (ቅንብር በምዕራፍ ብርሃኔ)
ዴንማርካዊው ሳይስ ፌልቦርግ ግሬገሰን የ19 ዓመት ወጣት ነው፡፡ ወጣቱ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን አጠናቆ ዩኒቨርስቲ ለመግባት በዝግጅት ላይ ነው፡፡
ሳይስ ዩኒቨርሲቲ ገብቶ የጋዜጠኝነት ትምህርትን መማር ስለመረጠ፣ ለትምህርቱ የሚረዳውን ልምድ ለማግኘት ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል፡፡ ሳይስ ኢትዮጵያ ከመጣ ሁለት ወር ከግማሽ ሲሆነው፣ በቆይታውም በዝግጅት ክፍላችን በተለማማጅ ጋዜጠኝነት የተለያዩ ማህበራዊ ጉዳዮችን (በእንግሊዝኛው ጋዜጣ ላይ) በጽሑፍ ሲዳስስ ቆይቷል፡፡ ወጣቱ ኢትዮጵያ ሲገባ ቀልቡን ስለሳቡት የታክሲ ረዳቶች ለመጻፍ በማሰብ ከአስራ ሦስት ቀናት በፊት (ዕለተ ዓርብ)  እነሱ የሠሩትን ሠርቶ ስለወያልነት ቀኑ የጻፈውን ተርጉመን እንደሚከተለው አቅርበናል፡፡     

 ዕለቱ ልክ እንደአብዛኛዎቹ ቀናት ሞቃታማ፤ ፀሐዩም ሃሩር ነበር፡፡ የታክሲ ተሳፋሪዎች ከምታቃጥለው ፀሐይ ለማምለጥ፣ መጠለያ ለማግኘትና ወዳሰቡበት ቦታ ለመድረስ ታክሲ ውስጥ ለመግባት ይጣደፋሉ፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ በፍጥነት የሚነጉዱ ሚኒባሶችን በፍጥነት ማውራት ከሚችሉ ወያላዎቻቸው ጋር መመልከት የዘወትር ክስተት ነው፡፡ ይህን ክስተት ለመጀመርያ ጊዜ ለተመለከተ ሁኔታውን ለመቀበል ይከብደዋል፡፡