- Sunday, 04 November 2012 00:00
- By Asrat Seyoum
በአስራት ሥዩም
እ.ኤ.አ. ከ2001 እስከ 2010 ባለው ጊዜ ውስጥ 15 ቢሊዮን ዶላር የሚገመት ገንዘብ ሕጋዊ በሆነና ባልሆነ መንገድ ከኢትዮጵያ እንዲወጣ ተደርጎ ወደ ውጭ ገበያዎች ማምራቱን በቅርቡ ይፋ የሆነ ሪፖርት አመለከተ፡፡
ይህ ችግር በመላ አፍሪካ ትኩረት እየሳበ እንደመጣ ታውቋል፡፡
የፋይናንስ ምንጭ በእጅጉ ከሚያስፈልጉዋቸው ታዳጊ አገሮች ወደ ሌሎች አገሮች ገንዘብን በማዘዋወርና በሕገወጥ የፋይናንስ ግብይት እየወጣ ያለውን ሀብት በተመለከተ እ.ኤ.አ. ከ2009 ጀምሮ ሲወጡ የነበሩ ሪፖርቶች የሚያረጋግጡት፣ ክስተቱ ትኩረት እየሳበ መምጣቱን ነው፡፡ ኢትዮጵያ ያላትን ውስን የውጭ ምንዛሪ መጠን ይኼው ከፍተኛ የካፒታል ማዛወር ወይም ማሸሽ ተግባር በእጅጉ እየታየባት በመምጣቱ፣ የመነጋገርያ አጀንዳ እንድትሆን አድርጓታል፡፡
ተሻሽለው የወጡ አኀዞች እንደሚያመለክቱት፣ እ.ኤ.አ. ከ1970 እስከ 2010 በነበሩት ሰላሳ ዓመታት 24 ቢሊዮን ዶላር ከኢትዮጵያ እንዲሸሽ ተደርጓል፡፡ ገንዘብ በከፍተኛ መጠን እየሸሸ መሆኑ ከተመዘገበባቸው ጊዜያት ትልቁን ድርሻ መያዝ የጀመረው እ.ኤ.አ ከ2000 በኋላ ያለው ሲሆን፣ በተለይ እ.ኤ.አ. በ2010 ብቻ 3.5 ቢሊዮን ዶላር በአገሪቱ ኢንቨስት ያደረጉ የውጭ ባለሀብቶች ያሸሹት ገንዘብ (ካለፈው ዓመት ኅዳር ወር አኳያ ከአገሪቱ የውጭ ምንዛሪ መጠባበቂያ ክምችት በላይ ሆኖ ተመዝግቧል) በከፍተኛነቱ ሲጠቀስ፣ ከዚህ መጠን ቀጥሎ የተመዘገበው ከፍተኛ የገንዘብ ማሸሽ እ.ኤ.አ. በ2002 የታየው የ3.1 ቢሊዮን ዶላር ነው፡፡ በሪፖርቱ የቀረቡት መረጃዎች ሲፈተሹ፣ ባለፉት ሰላሳ ዓመታት ውስጥ ከፍተኛ የካፒታል ማሸሽ የተመዘገበባቸው ጥቂት ዓመታት ሆነው ይገኛሉ፡፡