Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Saturday, 20 October 2012

ጉዞ ኃይለ ማርያም - ከአረካ እስከ አራት ኪሎ

Saturday, 20 October 2012 00:00, By Yonas Abiye
በዮናስ አብይ
የ43 ዓመቱ ጐልማሳ መንገሻ መንዳዶ የተወለደባትንና አድጐ የተማረባትን አነስተኛዋን የአረካ ከተማን ለቆ መኖርያውን በአርባ ምንጭ ከተማ ካደረገ ከሁለት አሥርት ዓመታት በላይ አስቆጥሯል፡፡
ዛሬ የሥራ ጠባዩ በፈጠረለት አጋጣሚ ሙሉ ጊዜውንና ኑሮውን በአርባ ምንጭ ላይ በመመሥረቱ አልፎ አልፎ በአዕምሮው ውልብ ከሚሉበት ትዝታዎች በስተቀር ስለተወለደባት የአረካ ከተማ ሲያወሳ አይሰማም፡፡ ነገር ግን ስለተወለደባት ከተማ ከማይረሳቸው የልጅነት ትውስታዎቹ ውስጥ አንድ አስገራሚ ታሪክን ከተማሪነት ዘመኑ መዝዞ በፈገግታና ኩራት በተሞላበት ሁኔታ ሲያወጋ፣ ያድማጭን ጆሮ በጉጉት ሊያቆም እንደሚችል በቅድሚያ ከገጽታው ደማቅነት መረዳት ይቻላል፡፡ የታሪኩ ክስተት ወደኋላ 28 ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ 300 ኪሎ ሜትር በምትርቀው በአረካ ከተማና በነዋሪዎቿ ታላቅ የመደነቅ ስሜትን ስለፈጠረ  የአንድ ጎበዝ ተማሪን አስደናቂ ጉዳይ ያወሳል፡፡

መንገሻ በወቅቱ ከሚማርበት የአረካ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ይልቅ ከከተማዋ ዕምብርት ሦስት ኪሎ ሜትር ርቀት ስለሚገኘው ዱቦ የካቶሊክ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ ስላለ አንድ ተማሪ ጉብዝና መስማትና ማውራት ይመስጠው ነበር፡፡

“በዚያ የሕፃንነት ዕድሜ ሁሉም ሰው ስለሱ ጉብዝና ብቻ ሲወራ ትዝ ይለኛል፡፡ እኔም በእኛ ትምህርት ቤት ውስጥ ካሉ ጐበዝ ተማሪዎች ይልቅ በዚያኛው ትምህርት ቤት ስላለው ጐበዝ ተማሪ ብሰማም ባወራም አልጠግም ነበር፤” በማለት የሚናገረው መንገሻ አገለለጹና ገጽታው ይህ ታሪክ እንኳን 28 ዓመታት ቀርቶ አሥር ዓመት የሞላው አይመስልም፡፡

ለካስ ኢህአዴግ ፈሪ ናት! .......... አቤ ቶክቻው

  • d
ሽመክት ውድነህ፤ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ቴኳንዶ ክለብ ምክትል አሰልጣኝ ነበር። በቴኳንዶ “ሶስተኛ ዳን” በሚባል ደረጃ ኢንተርናሽናል ቀበቶ አግኝቷል። በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2009 ዴንማርክ የቴኳንዶ ስፖርት ክለቡን ይዞ ሄዶ ተስፋ ሰጪ የሚባል ውጤት ይዞ ተመለሶ ነበር። (ይቺ ተስፋ ሰጪ… ከስፖርት ጋዜጠኞቻችን ኮርጄ ነው። ብቻ ከተስፋ አስቆራጭ ተቃራኒ የሆነ ውጤት ማለት ናት!)
በአዲስ አበባ ከተማ ወደ አስራ አምስት ሺህ የሚጠጉ ወጣት ልጆችን በቴኳንዶ ማሰልጠኑን አውግቶኛል። ሽመክት ከአምና በፊት የነበረው አምና (ካቻምና ማለት ነው)  ግንቦት ሃያ ሊቃረብ አካባቢ ግን አንድ ፈታኝ ነገር ገጠመው።
በግል ክለቡ ቴኳንዶ የሚያሰለጥናቸውን ተማሪዎች ጠርጣራው መንግስት “ግማሹን በኦነግነት ግማሹን በግንቦት ሰባትንነት እጠረጥራቸዋለሁ” አለው። በዚህም የተነሳ የደህንነት ሰዎች ነን የሚሉ ሰዎች “የምታሰለጥናቸው ለግንቦት 20 ላሰባችሁት አመፅ እና ብጥብጥ ነው” ብለው ስለጥናውን እንዲያቆም አስጠነቀቁት።
ከማስጠንቀቂያው ብዙም ሳይቆይ የቀበሌው ሊቀመንበር አምስት ኪሎ አካባቢ የነበረውን ማሰልጠኛው ሊዘጉበት መጡ። አሻፈረኝ ብሎ ሲሟገት ስምንት የሚሆኑ ፌደራል ፖሊሶች ስድስት ኪሎ አምበሳ ግቢ አጠገብ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ካምፕ ውስጥ አስገብተው ክፉኛ ደበደቡት። በዚህም የተነሳ ሁለት ወር ያህል አልጋ ይዞ ተኝቶ ነበር።
ያ ሰሞን ኢህአዴግ “ጭንቅ ጥብብ” የሚለውን ዘፈን ድምፁን ከፍ አድርጎ ይዘፍን የነበረበት ሰሞን እንደነበረ እኔም አስታውሳለሁ። “የድል ቀን” በሚል የፌስ ቡክ ግሩፕ አማካይነት “በቃ” የሚል  እንቅስቃሴ በሰፊው ታዋቂነት አግኝቶ ነበር።
ይህ እንቅስቃሴ፤ “ኢህአዴግ ግንቦት ሃያ በዓልን ሲያከብር አብዮት አደባባይ አብረን እንውጣ እና ለእስካሁኑ “ቴንኪው!” ከአሁን በኋላ ግን “ቻው” ብለን እናሰናብተው” በሚል፤ በአማርኛ፣ በኦሮምኛ፣ በወላይትኛ፣ በአፋርኛ፣ በትግርኛ ብቻ በሁሉም ቋንቋ  “በቃ” እያለ በርከቶችን ሲያስተባብር ነበር! ጊዜውም የአረቡ አገር አብዮት በየቦታው ይቀጣጠል የነበረበት ግዜ ነው።

ኢትዮጵያ በመልካም አስተዳደር ከአፍሪካ አገሮች 33ኛ ወጣች

ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የአፍሪካ ሀገራት የመልካም አስተዳደር ይዘትን የሚያጠናውና ደረጃ የሚያወጣው የ ሞ-ኢብራሂም ፋውንዴሽን ባወጣው የ2012 ሪፖርት፤ ኢትዮጵያ ከመቶ 47 ነጥብ በማግኘት 33ኛ ደረጃ መውጣቷን ይፋ አደረገ።
በትውልድ ሱዳናዊ፤ በዜግነት እንግሊዘዊ በሆኑት ቢሊዮኔር ዶ/ር ሞሀመድ ኢብራሂም የተቋቋመው ይህ ተቋም፤ የአፍሪካ ሀገራትን በተለያዩ ዘርፎች በመመርመርና በማወዳደር በሰጠው ደረጃ፤ ሞሪሸስ በ83 ነጥብ የአፍሪካ ቀዳሚ ሆና ተመዝግባለች።
ኬፕ ቬርድና ቦትስዋና በ78 እና 77 ነጥብ በ2ኛና ሶስተኛ ደረጃ ሲከተሉ፤ ጋና ደቡብ አፍሪካና፤ ታንዛኒያ ከፍተኛ ነጥብ በማግኘት ከቀዳሚዎቹ 10 ሀገራት ውስጥ ተመድበዋል። ኢትዮጵያ በ32 አገራት ተበልጣ፤ 19 ሀገራትን ቀድማ፤ በ47 ነትብ 33ኛ ሆና ተቀምጣለች።
ይሁን እንጂ፤ የአህጉሩ አማካይ 48 ከመቶ በመሆኑ፤ ኢትዮጵያ ያገኘችው ከአማካይ በታች ነው።
ሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን፤ በ4 ዋና ዋና ክፍሎች፤ 88 ንኡስ ርእሶች በመውሰድ በዝርዝር ባደረገው በዚህ ጥናት በህዝባዊ ተሳትፎ ለኢትዮጵያ የተሰጠው ነጥብ ከመቶ 25 ነው። የአህጉሩ አማካይ፤ 45 ሆኖ ተመዝግቧል።
ሰብአዊ መብትን በተመለከተም በተመሳሳይ ለኢትዮጵያ የተሰጠው ነጥብ 44 ሆኗል።
ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ከአማካይ በላይ ያገኘችዉ በጾታ እኩልነት ሲሆን፤ በዚህም የአፍሪካ አማካይ 54 ሲሆን፤ ኢትዮጵያ ያገኘችዉ 59 ከመቶ ነው።
በትምህርትና በጤና መስክ፤ ኢትዮጵያ ከ50 ነጥብ በላይ ያገኘች ቢሆንም፤ የአፍሪካ አማካይ በሆኑት 54 እና 66 ላይ መድረስ አልቻለችም።
ሀገሪቱ ለንግድ ያላት አመቺነትን በተመለከተ ያገኘችው ነጥብ 28 በመቶ ሲሆን፤ የአፍሪካ አማካይ 50 ሆኗል።
በመሰረተ ልማት ግንባታ ኢትዮጵያ ያገኘችው ነጥብ ከመቶ 33 ሲሆን፤ የአፍሪካ አማካይ 32 ሆኖ ተመዝግቧል።
በዶ/ር ሞሀመድ ኢብራሂም የተቋቋመው ሞ ኢብራሂም ፋውንዴሽን የአፍሩካ አገራትን የመልካም አስተዳደር ደረጃ እየገመገመ ባለፉት 6 አመታት ባወጣው ሪፖርት ኢትዮጵያ ከግርጌ አገራት ተርታ እንደተሰለፈች ቀጥላለች።

ESAT Daliy News-Amsterdam Oct. 19 2012 Ethiopia


ኦህዴድ ለሌላ አስቸኳይ ስብሰባ አዳማ ከተተ

ጥቅምት ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) አመራር አሁንም እንዳልተረጋጋ እየተነገረ ሲሆን፤ የድርጅቱ አመራር አባላት በመስከረም አጋማሽ ተጀምሮ ያልተቋጨውን ስበስባ ለመቀጠል አዳማ መክተታቸው ታውቋል።
ከኢትዮጵያ የደረሱን መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ከሆነ፤ ከወረዳ ጀምሮ የሚገኙት የድርጅቱ ከፍተኛ አመራር አባላትም በዚህ ስበሰባ እንደተካከቱ ለማወቅ ተችሏል።
ቀደም ሲል በአቶ አባዱላ ገመዳ፤ ኩማ ደመቅሳና ጁነዲን ሳዶ ይመሩ የነበሩት ሶስት አንጃዎች ወደአራት አድገው፤ አንድ አድፋጭ ቡድንም እንደተፈጠረ ታውቋል።
ኦህዴድ ከሁለት ሳምንታት በፊት ባደረገው ግምገማ አቶ ጁነዲን ሳዶን ከስራ አስፈጻሚነትና ከማእከላዊ ም/ቤት አባልነት አንስቶ ተራ አባል እንዳደረጋቸው የሚታወስ ሲሆን፤ የአቶ መለስን ሞት ተከትሎ በጠቅላይ ሚንስተር አሿሿም ላይ፤ ኦህዴድ በማእከላዊ መንግስት ባለው ስልጣንና በሙስና ምክንያት በአመራሩ መካከል የተነሳው ከፍተኛ ሽኩቻ እንደተካረረ ታውቋል።
ጠ/ሚንስትርነቱንና ምክትል ጠ/ሚነቱን ደኢህዴንና ብአዴን ከተቀራመቱት በኋላ፤ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርነቱ ለኦህዴድ እንዲሰጥ አባላት ግፊት ሲያደርጉ የሰነበቱ ሲሆን፤ ባለፈው ሳምንት ከጠ/ሚሩ ቢሮ በወጣ ደብዳቤ አቶ ብረሀነ ገ/ክርስሮስ ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ተደርገው መሾማቸው ይታወቃል።
የተፈጠረው ክፍፍል ሳይቋጭ ወደ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት መክፈቻ ስብሰባ ያመራው ከፍተኛ አመራርና ሌሎች የድርጅቱ አመራር አባላት በትናንትናው እለት ለአስቸኳይ ስብሰባ ወደ አዳማ ማምራታቸው ታውቋል።
ከጥቂት ቀናት በፊት በአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ የኦሮምኛው ክ/ጊዜ አንድ የኦህአዴድ ማእከላዊ ም/ቤት አመራር በመካከላቸው የተፈጠረውን ጭቅጭቅ “ተባላን” በሚል ቃል የእንደገለጹት የሚታወስ ሲሆን፤ እኚሁ ሰው በኦህዴድ አካሄድ ላይ የሕወሀትን ጣልቃገብነት ማንሳታቸውም ይታወሳል

Wednesday, 17 October 2012

እኛ “ነጋሲ” ስንልዎ እርስዎ “ሌጋሲ” እያሉ… እየተያየን ተለያየን!? አቤ ቶክቻው


ትላንት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማሪያም ደሳለኝ (በቅንፍም ቢያንስ ሌላ ጠቅላይ ሚኒስትር በመጥራቴ እኔም ደሳለኝ…!) በፓርላማ ጥያቄዎችን ለመመለስ ለመጀመሪያ ግዜ ቀርበው ነበር። በዚህ የመጀመሪያው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፓርላማ ላይ በርካታ ዋና ዋና የሟቹ ወዳጆች አልተገኙም ነበር አሉ። ወሮ አዜብም ካልተገኙት ውስጥ ናቸው። ወሮዋ ድሮ በሟቹ ጊዜ ስብሰባ ሲቀሩ ከፓርላማው ስብሰባ መልስ ለቀጣዩ መጂሊስ ስብሰባ ቤቱን ሞቅ ሞቅ አድርገው ሊጠብቋቸው ነው የቀሩት ብለን እናስብ ነበር። አሁን ደግሞ ምን ሆነው ቀሩ…? ብለን ስንጠይቅ “ላልተወሰነ ጊዜ ቤተመንግስቱን አምነው ርቀው አይሄዱም አሉ!” የሚል ሽሙጥ እናገኛለን።

የሆነው ሆኖ ግን አቶ ሃይለማሪያም በትላንቱ ፓርላማ መለስን ሆነው ሲተውኑ ነው የተመለከትናቸው። እንደውም አንድ ወዳጄ ሲናገር እንደሰማሁት አፈ ጉባኤው ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሲያስተዋውቁ “ቀጥሎ እንደ መለስ ዜናዊ ሆነው እንዲተውኑልን አቶ አርቲስት ሃይለማሪያም ደሳለኝን እጋብዛለሁ!” ማለት ነበረባቸው ብሎኛል።፡

የምር ግን ሰውዬው መለስን ለመምሰል በሚያድርጉት ጥረት ራሳቸውንም መለስንም ሳይሆኑ መቅረታቸው ነው ያሳዘነኝ።

እርግጥ ነው እነ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም ጊዜ ልንሰጣቸው ይገባል። ሲሉ መክረዋል። የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉም በዛሬው ፓርላማ ሰውዬው እንዲህ ማድረጋቸው በርካታ የኢህአዴግ አባላትን ያማልልላቸዋል። እናም አማራጭ አልነበራቸውም ብለዋል።

እኔ ግን ያልገባኝ ኢህአዴግ መስተፋቅሩን ያሰራባቸው ግለሰቦች (በቅንፍም መስተፋቅር ተብሎ የተገለፀው አበል እና ሌሎች ጥቅማጥቅሞች መሆናቸው ይታወቅ) እነዚህ ግለሰቦች “ጀግና አይሞትም” ብለው ያሉን እኮ ለለቅሶ ማድመቂያ መስሎኝ ነበር።

የምራቸውን መለስ አልሞቱም ብለው ነው የሚያስቡት እንዴ!? ግራ ነውኮ የሚያጋባው። ትላንት የኢቲቪው ተመስገን አቶ ሃይለማሪያም ቃል በቃል ያሉት ብሎ ስለ አቶ መለስ የተናገረው ነገር በእውነቱ ከሆነ ተስፋ አስቆራጭ ነው።

“የአቶ መለስን “ራዕይ” ማስፈፀም ላይ እና መለስን ዘላለም መዘከር ላይ ድርድር የለም።” “ወ…ይ ድርድር የለም!” ጋዜጠኛው የንግግሩ ዜማ ውስጥ እኮ አሁንም መለስ ይምሩን የሚል ነው የሚመስለው!

አስፈሪ የህወሃትና የወያኔ ደጋፊዎች የመነጣጠል ሴራ!!! (በኢዮብ ብርሃነ)

በአሁኑ ወቅት በባሕር ማዶ የሚኖሩትን ኢትዮጵያዊና ትውልደ ኢትዮጵያዊ ዜጎችን በአገራቸው ጉዳይ ላይ እንዳይሳተፉና አስተያየት እንዳይሰጡ የማግለልና ማንቋሸሽ፣
የመከፋፈሉ ዘመቻ በሰፊው ተጀምርዋል። ይህ አንዱ የከፋፍለህ ግዛው ዘዴ ውጤት ነው። እንደ አገርቤቱ ሕዝባችን ሊጠረንፉዋቸው ስላልቻሉ ያለንበት ወቅት ነቃ ማለትን ይጠይቃል ኢትዮጵያዊ ሱዳን ሆነ ደቡብ አፍሪካ፣አላስካ ሆነ ጂንካ፣ጅዳም ሆነ ካናዳ፣አውሮፓ ሆነ አውስትራሊያ የትም ይሁን ማርስ ላይም ጭምር ሁሉም ዜጋችን በአገሩ ጉዳይ ላይ እኩል ያገባዋል።ባሕር ማዶ ያሉት ዜጎቻችን ለጦርነትና ለድርቅ መ

ዋጮ ሲሆን ብቻ እጅ ከምን የሚባሉበት ዘመን ያብቃ!በፖለቲካም ሆነ በስራ፣በትዳርም ይሁን ውጪ በመወለድ ከአገራቸው ውጪ ያሉ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በአገራቸው
ጉዳይ ያገባቸዋል ደም ከውሃ ይቀጥናልና!

አዲስ ነገር ጋዜጣን፣አውራምባ ታይምስን የቅርቦቹን ለምሳሌነት ብንወስዳቸው
ይህን ስል ሌሎቹን እረስቼ አይደለም መርሳት የሃበሻ በሃሪ አይደል? ያ የለብኝም
የቀድሞዎቹን ጦብያን፣ኢትዮጵን፣ምኒልክ ወዘተ...ቅጅዎቻቸውን ከወዳጄ ቤት እያሰስኩኝ
ሳነባቸው ይህን ሰናይ ጅማሮ እንዲጠፋና እንዲደበዝዝ ያደረጉትን ገዥዎቻችንን ሳስባቸው
ነፍሴ ትጠየፋቸዋለች።መስፍን ነጋሽ አሸባሪ ነው ስትሉኝ እናደዳለሁ አይደለማ
አብይ ተ/ማርያም ፈንጂ ከሚያፈነዱ ጋር አንድ ላይ ሲጠራ ያመኛል!በአገረ እንግሊዝ ሕግን
የተማረ ብሩሕ ዐዕምሮ ያለው ለአገሩ የሚያስብ ምርጥ ዜጋ ነዋ ይህን ለማወቅ ስራዎቹን ማየት ይበቃል በአካል አይቸውም አላውቅም ስራዎቹ ግን ዘላለም ይኖራሉ።
አቤቶክቻውስ ምን አጥፍቶ ነው ወንድሙን እስከ መግደል ሰይጣናዊ ስራ የተሰራው?
እውነት በማሽሟጠጡ ብቻ እኮ ነው!
እስክንድር ለምን በወሕኒ ቤት አበሳውን ያያል? ሃቁን በመናገሩ ነው`ኮ!
እንስቷ ጋዜጠኛ ዕርዮት ዓለሙ ስለፅፈች`አሸባሪ ስትባል ምፀት ነው!
የሙስሊሙን ወንድሞቻችንን ድምፅ የሚያሰሙት ወኪሎች ለምን ታሰሩ?መልሱ ቀላል ነው
አብዮታዊ ቅብ ሙስሊም ስላልሆኑ ብቻ ነው!
የገዳማት አባቶች ለምን ይሰቃያሉ? ዕምነታችን ይዞታችን ይከበር ስላሉ ብቻ ነው !
ብዙ ማለት ይቻላል ግን ብዙ ቢባል ምን ፋይዳ አለው? ሆድ ሲያውቅ... ነውና ነገሩ!

Tuesday, 16 October 2012

አቦይ ስብሀት የፊታችን ኦክቶበር 20 ጀርመን ይመጣሉ

ጥቅምት ፮ (ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ (ህወሀት)መስራች አባል የሆኑትን በአቶ መለስ ጊዜ ከከፍተኛ የድርጅቱ ቦታዎች ተገፍተው የቆዩት አቶ ስብሀት ነጋ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር በመጪው መስከረም 20 በጀርመን-ቡንደስታግ ተገኝተው ንግግር እንደሚያደርጉ ተመለከተ።
በነባሮቹ የድርጅቱ አባላት ዘንድ <አቦይ>ተብለው የሚጠሩት አዛውንቱ አቶ ስብሀት ነጋ የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት ተከትሎ  በድርጅቱ ውስጥ ወደ ቀድሞ ተሰሚነታቸውና አድራጊ ፈጣሪነታቸው እየተመለሱ እንደሆነ የኢህአዴግ ከፍተኛ ካድሬዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
ከሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር እና ከባለቤታቸው ወይዘሮ አዜብ መስፍን ጋር ከፍተኛ ቅራኔ በመፍጠራቸው ከኢፈርት ዋና ሥራ አስኪያጅነታቸው ተወግደው  የኢትዮጵያ-የሰላምና የልማት ዓለማቀፍ ኢንስቲትዩት  ወደሚባል ተራ ቢሮ ተወርውረው አድፍጠው  የቆዩት አቶ ስብሀት፤ የአቶ መለስን ሞት ተከትሎ የተሰጣቸው ስልጣን ባይታወቅም  በአገሪቱ የወደፊት አቅጣጫ ዙሪያ ቀዳሚው ተናጋሪና ወሳኝ ሰው ሆነው ብቅ ብለዋል።
በመጪው ኦክቶበር 20 በጀርመን -ቡንደስታግ የሚመጡትም ሆነ የሚናገሩት በምን <ካፓሲቲ> እንደሆነ አልታወቀም።
አቶ ስብሀት ወደ ጀርመን ይመጣሉ መባልን የሰሙ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን በየፌስቡክና በየ ትዊተር ገፆቻቸው፦ <ልንቃወማቸው ይገባል>የሚል አስተያዬት እየሰጡ ቢሆንም፤በተደራጀ መልክ የተቃውሞ ሰልፍ  ስለመኖሩ እስካሁን ማረጋገጥ አልተቻለም።

የጌታቸው እና የደብረፅዮን ቢሮ (ከተስፋዬ ገብረአብ)

Deberetsion TPLF security
Deberetsion
ከተስፋዬ ገብረአብ
ስለ ጌታቸው አሰፋ ወይም ደብረፅዮን ምንም ልፅፍ አልችልም። ጌታቸውን በቅርብ አላውቀውም። የአማረ አረጋዊ የቅርብ ጓደኛ ስለነበር፣ አንድ ሁለት ጊዜ በአጋጣሚ ቡና ጠጥተናል። ጌታቸው አሰፋ ነባር የህወሃት አመራር አባል ሲሆን፣ በአቅም ደረጃ ሲመዘን ከላይኛው የህወሃት አመራር አባል አንዱ መሆኑ የሚታወቅ ነው።
ደብረፅዮንን በቅርብ አውቀው ነበር። ደርግ ከመውደቁ በፊት በሃገረሰላም የህወሃት ሬድዮ ጣቢያ በአንድ አካባቢ ነበርን። ሆኖም ደብረፅዮን ሰሞኑን እንደሚፃፍበት፣ ተራ የሬዲዮ ኦፕሬተር አልነበረም። የሬድዮ ስርጭቱ የቴክኒክ ሃላፊ ነበር። ደርግ ከወደቀ በሁዋላ ወዲያውኑ የተቋረጠ የዩንቬርሲቲ ትምህርቱን እንደቀጠለ አስታውሳለሁ። ከደብረፅዮን አንድ የሜዲያ ኮሚቴ ውስጥ አብረን ሰርተን ነበር። ብሩህ አእምሮ የነበረው፣ ባተሌ አይነት ሰው ነበር። ደብረፅዮንን የህወሃት ምክትል እና የፀጥታው መስሪያ ቤት ሁለተኛ ሰው አድርገው ማምጣታቸው በአጋጣሚ አይመስለኝም። ተጠንቅቀው አስበውበት ያደረጉት ነው። ደብረፅዮን በግማሽ ጎኑ ኤርትራዊ ስለመሆኑ ሰምቻለሁ፣ በጋብቻ ከስብሃት ነጋ ጋርም እንደሚዛመድ የተፃፈ አንብቤያለሁ። ርግጠኛ መረጃ ስለመሆኑ ግን አላውቅም።
ስለ ጌታቸው እና ስለ ደብረፅዮን ከዚህ በላይ ማለት የምችለው የለም። ይልቁን ከአጠቃላይ ነገር በመነሳት እነዚህ ሁለት ሰዎች ከሚመሩት ቢሮ ጋር በተያያዘ አንድ ብጫቂ ወግ ማንሳት ፈልጌያለሁ።

ዜና በጨዋታ፤ የኢቲቪው ጋዜጠኛ “ፕሮፖጋንዳ በቃኝ” ብሎ “ነካው!”

አቤ ቶኪቻው

ሰለሞን መንግስት ይባላል። በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ውስጥ የእንግሊዘኛው ክፍል ባልደረባ ነው። ዛሬ በፌስ ቡክ ግድድዳው ላይ “I have said “enough is enough“ and decided to never be back in that dirty propaganda factory called ERTA.”  የሚል ለጥፎ አስነብቦናል።ዜና በጨዋታ፤ የኢቲቪው ጋዜጠኛ “ፕሮፖጋንዳ በቃኝ” ብሎ “ነካው!”
መቼም ሰው ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን “በቃኝ ብያለሁ በቃኝ” ብሎ ቢማረር ምን ሆኖ ነው? ተብሎ አይጠየቅም። ምክንያቱም ቤቱ ኢቲቪ ነው!
ይልቅስ በኢቲቪ አሁን ድረስ እየሰሩ ያሉ ወዳጆቻችን ምን ሆነው ነው የማይለቁት? ኢቲቪው ላይ ምነው ወይዘሮ አዜብ ሆኑበት? የሚለው ጥያቄ መልሱ ግር ይላል።
በነገራችን ላይ አንድ ወደጄ ነው ይቺን አዲስ ፈሊጥ የነገረኝ። አንድ ሰው የሆነ ቦታ ገብቶ አልወጣ ካለ “ምነው አዜብ መስፍንን ሆንክ!?” እያሉ መጠየቅ በከተማው ተለምዷል አሉ። ይሄ ያነጋገር ፈሊጥ መፀዳጃ ቤት ገብቶ አልወጣ ላለ ሰው፣ ከመኝታው አልነሳ ላለ እንቅልፋም ሁሉ አገልግሎት ላይ ይውላል።
አሁንም በነገራችን ላይ ወሮ አዜብ በወሮ ሚሚ በኩል “ቤተመንግስት ይሄን ያክል ብርቅ ነው እንዴ! ቀስ ብዬ ወጣለኋ ሀዘኑ ይብረድልኝ እንጂ!” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል አሉ! “ወይ ጉድ ለእነዚህ ወሮዎች እና ለአንዳንድ ወሮበሎች የሚሆን መድሃኒት ጠፋ አይደል!?” አሉ አይደል በሆድዎ…? ተነቃቅተናል!

Ethiopia: Violent Land Grabs Leave Tribes Hungry


press release

Violent land grabs in Ethiopia's Lower Omo Valley are displacing tribes and preventing them from cultivating their land, leaving thousands of people hungry and 'waiting to die'.

As the world prepares to raise awareness of the issues behind poverty and hunger on October 16 (World Food Day), Ethiopia continues to jeopardize the food security and livelihoods of 200,000 of its self-sufficient tribal people.

Tribes such as the Suri, Mursi, Bodi and Kwegu are being violently evicted from their villages as Ethiopia's government pursues its lucrative plantations project in the Valley.

Depriving tribes of their most valuable agricultural and grazing land, security forces are being used brutally to clear the area to make way for vast cotton, palm oil and sugar cane fields.

Cattle are being confiscated, food stores destroyed, and communities ordered to abandon their homes and move into designated resettlement areas.

One Mursi man told Survival International how the process of villagization is destroying his family. 'The government is throwing our sorghum in the river. It has cleaned up the crops and put them in the river. I only have a few sacks left...We are waiting to die. We are crying. When the government collects people into one village there will be no place for crops and my children will be hungry and have no food.'

Monday, 15 October 2012

ጁነዲን፣ ኦህዴድ እና ኢህአዴግ – ልዩ ጥንቅር በደረጀ ሀብተወልድ (ኢሳት)

ልዩ ጥንቅር- በደረጀ ሀብተወልድ-ኢሳት
ESAT journalist Dereje Habtewoldየሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ አቶ ጁነዲን ሳዶና አራት ባለስልጣናት፤ ከኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ሥራ አስፈጻሚነት ሰሞኑን ተነስተዋል።
ሚኒስትር ጁነዲንና አራቱ አመራሮች  ከሥራ አስፈፃሚነታቸው እንዲነሱ የተወሰነው፤ የኦሕዴድ ሥራ አስፈጻሚ ካለፈው መስከረም 21 ቀን እስከ መስከረም 24 ቀን  ባካሄደው ዓመታዊ ጉባዔ ላይ ነው።
ከወራት በፊት አቶ ጁነዲን  ወደ አውስትራሊያ በመምጣት ከኢህአዴግ ደጋፊዎች ጋር ለማድረግ ያሰቡት ስብሰባ  ኢትዮጵያውያን ባደረጉት ከፍተኛ ተቃውሞ ተደናቅፎባቸው ተልዕኳቸውን ሳይፈጽሙ  ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ።
በውጪ አገር ከፍተኛ ተቃውሞ አስተናግደው  በተመለሱ   በጥቂት ቀናት ውስጥ  በዘንድሮው  የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ  የምርቃት ፕሮግራም ላይ የክብር እንግዳ  ሆነው የተገኙት የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ፤ በፕሮግራሙ ላይ ባደረጉት ንግግር ስለ ኮብል ስቶን  ማንጠፍ ሥራ ማንሳታቸው፤ በተመራቂዎቹ ዘንድ ከፍ ያለ ተቃውሞ አስነሳባቸው።
ብዙም ሳይቆይ ባለቤታቸው ወይዘሮ ሀቢባ ከሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ የሀይማኖት አታሼ ቢሮ 50 ሺህ ብርና 500 ቁርዓን ይዘው ሲወጡ በፖሊስ ተይዘዋል ተብለው ለእስር ተዳረጉ።
ቀደም ሲል የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት፣ከዚያም  የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስትር፣ቀጥሎም የሳይንስና ቴክኖሎጂ ከሚሽን-ኮሚሽነር እና አሁን ደግሞ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር በመሆን ለረዥም ዓመታት ኢህአዴግን በታማኝነት ሲያገለግሉ መቆየታቸው ለሚነገርላቸው ለአቶ ጁነዲን  ከኦህአዴድ ሥራ አስፈፃሚነት መወገድ ዋነኛው ምክንያት፦ ይኸው ባለቤታቸው ከሳዑዲ ኤምባሲ የሀይማኖት አታሼ ጋር በመሆን ፈጽመውታል የተባለው ድርጊት ነው።

ወ/ሮ ሚሚ ስብሀቱ ለወ/ሮ አዜብ መስፍን ያላቸውን ድጋፍ ገለጡ

ጥቅምት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ከአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ በሥነምግባር ችግር ከተባረሩ በኋላ በወ/ሮ አዜብ መስፍን ትዕዛዝ ያለጨረታ የደቡብ ክልል
መገኛኛ ብዙሃን የቴክኒክ ሥራን ተረክበው በአቋራጭ ከባለሃብት ጎራ የተቀላቀሉት ወ/ሮ ሚሚ
ስብሃቱ ፣ ዛሚ በተሰኘው ራዲዮ ጣቢያቸው ለወ/ሮ አዜብ መስፍን ከአጃቢ ጋዜጠኞች ጋር በመሆን ሲሟገቱ ውለዋል፡፡
ሰሞኑን የወጡ ጋዜጦች ወ/ሮ አዜብ ቤተመንግስቱን ለአቶ ኃይለማርያም አላስረከቡም በሚል ያወጡትን ተከታታይ
ዘገባዎች የጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ በሚለው ዝግጅታቸው ጋዜጠኞችን ሲተቹና እርምጃ እንዲወሰድባቸው ጠይቀዋል።
ወ/ሮ ሚሚ “እንዲህ ዓይነቱ ጥያቄ ከአዲሱ ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ዳሳለኝ መጥቶ ከሆነ የሚያሳዝን ነው በማለት ተናግረዋል።የወ/ሮ አዜብ የቅርብ ጓደኛ የሆኑት ወ/ሮ ሚሚ በጋዜጦቹ የቀረበው ዘገባ እውነትነትን ሳይክዱ አርባ እና ሰማንያ ሳይወጣ፣ የጠ/ሚኒስትሩ ውለታ ሳይረሳ እንዴት እንዲህ ይጻፋል ከማለት አንስተው ደርጊቱ በጠ/ሚኒስትሩ ሌጋሲና ውርስ ብቻ ሳይሆን በቀጣዩ ልማት ላይ የተቃጣ አደጋ ነው በማለት ገልጸዋል።
በጋዜጦቹ ዘገባ ክፉኛ የተበሳጩት ወ/ሮ ሚሚና ባልደረቦቻቸው ” አንድ ጊዜ ቤተመንግስት መኖር ያን ያህል
የሚያጓጓ አይደለም ሲሉ የተደመጡ ሲሆን፣ በሌላ በኩል ደግሞ ጋዜጦቹ ጉዳዩን መዘገባቸው ከፍተኛ ድፍረት ብቻም
ሳይሆን ለአቶ መለስ ሐዘኑን የገለጸው ሕዝብን መናቅ ነው በማለት የቅስቀሳ ሥራ ለመስራት ሞክረዋል፡፡
ወ/ሮ ሚሚ ለጓደኛቸው ለወ/ሮ አዜብ ውለታ ለመመለስ በሚመስል ድምጸት ወግነው ነገሩን ሲያቀጣጥሉ የአዲሱ ተተኪ
ጠ/ሚኒስትር ደህንነት ጉዳይ ጨርሶ እንደማያሳስብ እና ጠዋትና ማታ በመንገድ መዘጋት ለሚንገላታው ሕዝብ ደንታ
እንደሌላቸው አሳይተዋል በማለት አንድ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ ጋዜጠኛ ለኢሳት ተናግሯል።
አቶ ኃይለማርያም ለደህንነት አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እንዲሰሩና እንዲሸማቀቁም እንዲሁም የመለስ ራዕይ፣ ሌጋሲ የሚሉ ቃሎችን በማስተጋባት ለመናገር መሞከራቸው በአዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር እና በወ/ሮ አዜብ መካከል ለተፈጠረው አለመግባባት ጥሩ ማሳያ ሊሆን እንደሚችል ጋዜጠኛው አክሎ ተናግሯል።
ወ/ሮ ሚሚ ጣቢያቸው ያን ያህል በሕዝብ ተደማጭ ካለመሆኑ ጋር ተያይዞ የቀጠሩዋቸውን ጋዜጠኞች ወርሃዊ ደመወዝ እንኩዋን ለመክፈል የማይችሉበት ደረጃ መድረሳቸው ይታወቃል፡፡
ኢሳት ወ/ሮ አዜብ ቤተመንግስቱን እንዲለቁ መጠየቃቸውን መዘገቡ ይታወሳል። በአገር ቤት ደግሞ ሰንደቅ የተባለው ጋዜጣ ተመሳሳይ ዘገባ አቅርቦ እንደነበር ለማወቅ ተችሎአል።

አቶ ብርሀነ ገ/ክርስቶስ ተጠባባቂ ጠ/ሚር ሆነዋል

ጥቅምት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የውጭ  ጉዳይ ሚንስትር ዴኤታ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት ዕምባሳደር ብርሀነ ገብረክርስቶስ ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር ተደርገው እንደተሾሙ ታወቀ። የሹመት ደብዳቤው ተፈርሞ የወጣው ከጠቅላይ ሚ/ሩ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሙክታር ከድር ቢሮ እንደሆነ ታውቋል።
በአቶ ሀይለማሪያም ሹመትና በሌሎች ሁኔታዎች ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ በኢህአዴግ ነባር ፓርቲዎች በተለይም፤ በኦህዴድ ውስጥ ያለው ልዩነት እልባት አለማግኘቱ አዲስ ካቢኔ እንዳይቆቆም እንቅፋት መሆኑም ተመልክቶል::
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ስፍራ ለኦሆዴድ አባል እንደሚሰጥ በአንዳንድ ወገኖች ቢገመትም፤ ሌሎች ወገኖች ደግሞ ስፍራውን ሕወሀት እንደሚይዘው ሲገልጡ ቆይተዋል::
የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህውሀት) ማእከላዊ ኮሚቴ አባል አምባሳደረ ብርሀነ ገብረክርስቶስ ተጠባባቂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው መሰየማቸው በአዲሱ የካቢኔ ድልድል ስፍራውን በሙሉ ስልጣን እንደሚይዙት አመላካች ነው ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ቢናገሩም፤ አቶ ተቀዳ አለሙም ለውች ጉዳይ ሚንስትርነት እንደታጩ እንዳንድ ምንጮች ተናግረዋል::

ጅጅጋ፤ ሀረርና ድሬዳዋ ካለፉት ስድስተ ቀናት ወዲህ ጨለማ ውስጥ ናቸው

ጥቅምት ፭ (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ምስራቅ ከተማዎች ላለፉት 6 ቀናት የመብራት አገልግሎት እንደተቋረጠባቸው የታወቀ ሲሆን፤ የደብረዘይት ከተማ ነዋሪዎች ላለፉት 7 ቀናት የውሀ አገልግሎት እንደሌላቸው የኢትዮጵያ ምንጮቻችን ገልጸውልናል።
ከድሬዳዋ ጅጅጋና ሀረር ከተሞች የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው፤ የሀረር፤ ድሬዳዋና ጅጅጋ ከተሞች ላለፉት 6 ቀናት የመብራት አገልግሎት አልነበራቸውም።
የኢትዮጵያ መንግስት ባለፈው አመት ለጅቡቲ 20 ሜጋ ዋት ኤሌክትሪክ መሸጥ መጀመሩን መናገሩ የሚታወስ ሲሆን፤ በቀጣዮቹ አመታትም ለሱዳንና ለኬንያ ሀይል የመሸጥ እቅድ እንዳለውም ይታወቃል።
ኢትዮጵያ 45 ሺህ ሜጋ ዋት የሀይድሮ ኤሌክትሪክ የማመንጨት አቅም እንዳላት ቢገመትም እስካሁን ማምረት የምትችለው 2000 ሜጋ ዋት ብቻ ነው።
የኢህአዴግ አስተዳደር እስከ 2015 ድረስ የኢትዮጵያን የሀይል አቅርቦት በአራት እጥፍ ለመጨመርና 10 ሺህ ላመድረስ እቅድ የያዘ ሲሆን፤ ላለፉት 21 አመታት ተጨማሪ 1600 ሜጋ ዋት ብቻ መጨመር የቻለው ኢህአዴግ በቀጣዮቹ ሶስት አመታት የሀይል ቀእርቦቱን 10 ሺህ ለማድረስ ያስቸግረዋል ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
በሌላ ዜና፤ የደብረ ዘይት ከተማ ነዋሪዎች ላለፉት 7 ቀናት የውሀ አገልግሎት እንደሌላቸው ታወቋል። የውሀ አገልግሎቱ የተቋረጠው፤ በምን ምክንያት እንደሆነ አልታወቀም።
የአዳማ ከተማ ነዋሪዎች ባለፈው ወር ከ20 ቀናት በላይ የውሀ አገልግሎታቸው ተቋርጦ እንደነበር ይታወሳል።