
ወደ አካባ በማግስቱ ማርች 17፣ ከ2 ሺ በላይ የሚሆኑ ልዩ የሚሊሺያ አባላት ወደ ወረዳው ተመልሰው በመሄድ ከቤት እያወጡ ሰዎችን ገደሉ። ቢው በመሄድ ነዋሪዎችን ሲገድሉ፣ ሴቶችን ሲደፍሩና ንብረት ሲዘርፉ መቆየታቸውን የአካባቢው ሰዎች ለኢሳት ገልጸዋል። “ህዝቡ በቃን” ብሎ እንዲነሳ ያደረገውም የግፉ ጽዋ ሞልቶ በመፍሰሱ መሆኑን ነዋሪዎች ይናገራሉ።
![]()
ከአቶ ግደይ ዘርዓፅዮን የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ ዋና ፀሐፊ ጋር የተደረገ ቃለምልልስ
“የመለስ ሞት በስርአቱ ላይ የአመለካከት ወይም የአሰራር ለውጥን አላመጣም። አሁን ያሉት መሪዎች ግን ሥርዓቱን የመለስን ያህል ሊቆጣጠሩት አይችሉም። በውስጣቸውም የመከፋፈልና የስልጣን ፉኩቻ ፈጥሯል። ይህ ሁኔታ ለትግላችን አንዳንድ ቀዳዳዎችንና አመቺ ሁኔታዎችን ሊፈጥር ይችላል።”
አቶ ግደይ ዘርዓጽዮን
በጀርመን ሀገር በአማርኛና በእንግሊዝኛ ቋንቋ የሚታተመው “ጥላ” መጽሔት በአንደኛ ዓመት ቁጥር አምስት ዕትሙ ከአቶ ግደይ ዘርዓፅዮን ጋር ቃለምልልስ ያደረገ ሲሆን፤ ሙሉ ቃለምልልሱን ከዚህ በታች ያገኙታል። (ቀሪዎቹን የጥላ መጽሔት ጽሑፎች በፒ.ዲ.ኤፍ. ለማንበብ እዚህ ይጫኑ!)
የዛሬው የጥላ አንደኛ ዓመት ልዩ የክብር እንግዳ አቶ ግደይ ዘርዓፅዮን ይባላሉ። አቶ ግደይ ህወሓትን ከፈጠሩት ጥቂት ግለሰቦች ውስጥ የአንበሳውን ድርሻ ይይዛሉ። እሳቸው ታዲያ እስካሁን የእድሜያቸውን ሁለት ሶስተኛ በኢትዮጵያ ትግል ውስጥ በማሳለፍ ላይ ናቸው። አገራችን ውስጥ ባላቸው የፖለቲካ ህይወት ልምድ ከጠገቡትና አንቱ ከሚባሉት በጣም ጥቂት ሰዎች መካከልም እጅጉን ቦታ የሚሰጠው ስፍራ አላቸው።
የቀድሞውን የፊውዳል ሥርዓት ከመቃወም ጀምሮ ደርጉንም በማፍረክረክ ከተሰሩት ታሪኮች አብዛሃኛው ላይ የእሳቸው አሻራ አለበት። የተወለዱት በፈረንጅ አቆጣጠር በ1950 ዓ.ም. ነው። በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍለ ሀገሮችም አድገዋል። ተምረዋል። በቀድሞው አፄ ኃይለሥላሴ/የአሁኑ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እአአ ከ1968 – 1974 ዓ.ም. ቆይተዋል። በተለያዩ ክልሎች ማደጋቸውና መማራቸውም የኢትዮጵያን ፖለቲካ በቀላሉ ለመረዳትና ብሔራዊ አስተሳሰብ ያላቸው ሰው እንዲሆኑ እንዳደረጋቸው ብዙዎች ይስማማሉ። የተለያዩ የአገሪቱን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በተመለከተ ብዙዎች መፅሃፍ ሲያገላብጡ ጊዚያቸውን ከማጥፋት ይልቅ አቶ ግደይ ጋር በመደወል ወይም በአካል በመገናኘት የካበተ ልምዳቸውን በማስረጃ አስደግፈው ማግኘት እየቀለላቸው ከመጣ ውሎ አድሯል።
|