Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Saturday, 2 June 2012

Egypt’s ex- ruler, Hosni Mubarak has been sentenced to life in prison after a court convicted him on charges of complicity in the killing of protesters during last year’s uprising that forced him from power.
Hosni Mubarak

As the judge announced the verdict on Mubarak, protesters and families of the martyrs outside the court began chanting with utter joy “God is great” and “Martyrs blood was not spilled in vain.” People were hugging each other with tears in their eyes, feeling elated and proud of the judiciary system. But after the initial sentencing was announced, matters began to go down hill for many standing outside. Violence soon erupted as Gamal and Alaa Mubarak and the six senior police heads were acquitted. Families of the martyrs soon began heatedly chanting, eventually clashing with the CSF. Soon protesters began chanting for the purging of Egypt’s judiciary while pro-Mubarak activists began to leave the scene.
According to analysts, Mubarak’s fate could be a lesson for Ethiopia’s Prime Minister Meles Zenawi who has clamped down on the opposition, stifled critical journalists and dissent, and rigged elections.

አንገት ሲደፋ ምን ፈሰሰ?....Fetehe


Pro. Mesfin Woldemariam
ፕሮፌሰር መስፍን ወ/ማርያም
ሰሞኑን አዲስ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፎቶግራፍ በብዛት በያለበት ይታይ ነበር፤ ያዘነ፣ የተከዘና አንገቱን የደፋ መለስ ዜናዊ! እኔን ቀልቤን የሳበው የጠቅላይ ሚኒስትሩን አንገት ሊያስደፋ የቻለው ነገር አይደለም፤ ወይም አበበ ገላው የተናገረው ነገር አይደለም፤ አበበ ገላው የተናገረውን ለመናገር ሙሉ መብት አለው፤ በተባለው ነገር የማይስማማ ሰው በማስረጃም ሆነ ያለማስረጃ የተባለውን ለማስተባበል መሞከር መብቱ ነው፤ የአሜሪካኑን ፕሬዚዳንት፣ ወይም የእንግሊዙን ጠቅላይ ሚኒስትር እንዲህ ያለ ሁኔታ ቢያጋጥማቸው፣ ወይም በጆርጅ ቡሽ ላይ አንዱ ኢራቃዊ እንዳደረገው ጫማውን እያወለቀ ቢወረውርም ምንም የሚያስደንቅ ነገር አይኖርም፤ በ1928 ነው 29 አጼ ኃይለ ሥላሴ በቀድሞ የዓለም መንግሥታት ማኅበር መድረክ ላይ ሲናገሩ የኢጣሊያ ፋሺስቶች ያሰማሩአቸው ሰዎች ንግግሩን ለማደናቀፍ ጩኸትና ፉጨት ያሰሙ ነበረ፤ አጼ ኃይለ ሥላሴን አንገታቸውን አላስደፋቸውም፤ አበበ ገላው የወረወራቸው ቃላት ናቸው፤ ቃላቱ እውነትን የሚገልጹ ከሆነ በተግባራዊ ማረሚያ ይለወጣሉ፤ ቃላቱ ሐሰትን የሚገልጹ ከሆኑ እውነትን በሚገልጹ ቃላት ይደመሰሳሉ።
እዚህ ላይ አንድ ሌላ ነገር እናስታውስ፤ በመስከረም ግድም ይመስለኛል አቶ ኢሳይያስ አፈወርቅ በኒውዮርክ ነበረ፤ በዚያን ጊዜ በአንድ ስቴድየም ውስጥ የኤርትራ ተወላጆች ሁሉ (የቀረም ያለ አይመስልም!) በስቴድየሙ ታምቀው የኢሳያስን ዲስኩር ከሰሙ በኋላ አስተያየታቸውን እየሰጡና ጥያቄያቸውንም እየጠየቁ ሲወያዩ ነበር፤ ያስቀኑ ነበር፤ የኤርትራም ማኅበረሰብ እንደኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ውስብስብና ጉራማይሌ ነው፤ መሪው ህዝቡን ሳይፈራ፤ ሕዝቡም መሪን ሳይፈራ ተቀራርበው ለመወያየት መቻላቸው እኛን የትና የት ጥለውን እንደሄዱ አያሳይም የሚል አለ? ይህንን እውነት ቢያንስ የዛሬ አሥራ አምስት ዓመት ግድም ሪፖርተር የመጀመሪያውን መጽሔት ባወጣ ጊዜ ሽፋኑ የኢሳይያስ አፈወርቅ ፎቶግራፍ ነበር፤ የመለስ አልነበረም፤ ለኢሳይያስም ከተደረደሩት የውዳሴ ርእሶች አንዱ ኢሳይያስ ለሕዝብ ቅርብ መሆኑ ነበር፤ በአንፃራዊ ዝምታ መለስን ይጎሽም ነበር፤ ዛሬ በጠብ ላይ በመሆናችን እውነትን የምናይበት ዓይናችን ተቸግሮ ይሆናል፤ ለማናቸውም የሪፖርተርን ዘገባ ያስታወስሁት በኒውዮርክ በተደረገው የኤርትራ ተወላጆች ስብሰባ የተነሣ ነው፤ ለመሆኑ በኒውዮርክ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስተር ስብሰባ ቢጠራ መጀመሪያ ስንት ሰዎች ይገኛሉ? ከተገኙትስ ጋር የሠለጠነ ውይይት ይደረጋል? ወይስ በፓርላማ እንደተለመደው ያለ ይሆናል? ሳይናናቁ መሪና ሕዝብ ተከባብረው በነፃነት ሀሳባቸውን መለዋወጥ መቻል ትልቅ እርምጃ ነው።
በኒውዮርክ የተሰበሰቡትን የኤርትራ ተወላጆች ቁጥር የሚያህል ኢትዮጵያውያን ተሰብስበው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር መወያየት የሚችሉ ቢሆን እንዴት ያኮራኝ ነበር፤ በበኩሌ ባንስማማም እንነጋገር እያልሁ ስጮህ ብዙ ጊዜ ሆነኝ፤ ክርር ምርር ብሎ ከዚህ ፍንክች አልልም፤ ለአጭሩም፣ ለረጅሙም፣ ለወፍራሙም፣ ለቀጭኑም፣ ለክርስቲያኑም ለእስላሙም፣ ለሁላችሁም የሚበጀውን እኔ አውቃለሁ ማለቱ አያቀራርበንም፤ መናናቅ አያቀራርበንም፤ መፈራራት አያቀራርበንም፤ አበበ ገላው የተናገረው እውነት መሆኑንና አለመሆኑን ወደጎን እንተወውና በኢትዮጵያ ውስጥ እነዚያኑ ቃላት፣ በዚያው የጋለ ስሜት ያለፍርሃት በልበ ሙሉነት መግለጽ የሚቻል ቢሆን የአሜሪካው ድራማ አያስፈልግም ነበር፤ ዋጋም የሚሰጠው አይሆንም ነበር፤ በአሜሪካ በድንገትና ዓለም ሁሉ በሚያይበት መድረክ ስለ መለስ ዜናዊ የተባለው ሁሉ በኢትዮጵያ ውስጥ ተዝናንቶና ኮርቶ ሊያዳምጥ የሚችልበትን መድረክ በሃያ ዓመታት ውስጥ ሳያዘጋጅ መቅረቱ አንገቱን ለማስደፋቱ አስተዋጽኦ አድርጓል።
በኢትዮጵያ ሳይሆን በአሜሪካ፣ በኢትዮጵያ ፓርላማ ሳይሆን በትልቅ ዓለም-አቀፍ ስብሰባ፣ ጥቂት የአፍሪካ መሪዎች ብቻ በተጋበዙበት ስብሰባ፣ በተለይም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ለአፍሪካ ተናጋሪ ሆኖ በተጋበዘበት የታላላቅ መሪዎች ስብሰባ ላይ መገኘቱ ኢትዮጵያውያንን ሁሉ ሊያኮራ የሚገባው ነገር ነበር፤ ቢመቸን የሚያኮራን ነበር፤ መኩራቱ ሳይሆንልን ቢቀርም የማናፍርበት በሆነ መልካም ነበር፤ ምስጋናና ከንቱ ውዳሴ እንደጠበል በሚረጭበት ትልቅ ዓለም-አቀፍ ስብሰባ ላይ ዘለፋና ነቀፌታ መስማት አንገትን ያስደፋል፤ ነገር ግን ከመለስ ዜናዊ ጋር ኢትዮጵያ በዚያ ስብሰባ ላይ አንገትዋን አልደፋችም?
በግድም ይሁን በውድ አንድ መሪ አንድ ሕዝብ አናት ላይ ከተቀመጠ፣ ብዙ ነገሮች ያያዝዋቸዋል፤ ከነዚህ ነገሮች አንዱ ክብር-- ወይም ውርደት ነው፤ ሕዝብ ተዋርዶ መሪው ክብር አያገኝም፤ መሪው ተዋርዶ ሕዝብ ክብር አያገኝም፤ የአንዱ ውርደት ለሌላው ክብር ሊሆን አይችልም፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በስብሰባው ላይ የተጋበዘው ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን የአፍሪካን አህጉርንም ወክሎ ነበር፤ በዚህ ሁኔታ ክብር ቢያገኝ ኢትዮጵያን ብቻ ሳይሆን አፍሪካን በሙሉም ያስከብር ነበር፤ ስለዚህም የዜና ማሰራጫዎች ሁሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሲያወድሱ ኢትዮጵያም አፍሪካም አብረው ይወደሱ ነበር፤ አሁን ግን አንገቱን ስለደፋው ሰው ሲናገሩ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር እያሉ ነው፤ ያኔ እኛም አንገታችንን ባንደፋም ወደግብዣው ቋጥረነው የገባነው ትንሽ ክብር ይደፋብንና ውርደቱ ይሰማናል፤ የሚገዙትን ሕዝብ ሳያከብሩ ማስክበር ያስቸግራል፤ የሚገዙትን ሕዝብ ሳያከብሩ መከበርም ያስቸግራል፤ መሪና ሕዝብ ክብርንና ውርደትን ይወራረሳሉ።
በሃያ ዓመት የመሪነት ቦታ ተቀምጦ አንገቱን ቀና አድርጎ በኩራት የሚወረወርበትን ጉድፍ ሁሉ ለመቀበል የሚችልበትን፣ የሚናገርበት ብቻ ሳይሆን አንገቱን ሳይደፋ ለማዳመጥ የሚችልበትን መድረክ ሳያዘጋጅ በመቅረቱ የደረሰበት ውጤት በዓለም አቀፍ ስብሰባ ላይ አንገት መድፋት ነው።
በስንቱ ነገር ነው አንገታችንን የምንደፋው? በደሀነትና በችጋር፣ በመረጃ ማነቆ፣ በቴሌቪዥን እኛ የምንፈልገውንና የምንመርጠውን ለማየት አንችልም፤ በቴሌቪዥን ፕሮግራም እንኳ አጥፍቶ መጥፋት ሊባል ወደሚችል እልህ ውስጥ ገብተን ከዓለም ጋር ብቻ ሳይሆን ከእውቀት ጥበብ (ከቴክኖሎጂ) ጋር የምንታገል ይመስላል፤ ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ እየተባለ መራራ ኮሶ የሚጋቱበት ዘመን አክትሞአል፤ ዓለም በሙሉ ጎረቤት ሆኖአል፤ በአንዱ አገር ውስጥ የሚሆነው ውቅያኖስንና አህጉሮችን አቋርጦ ይሰማል፤ ይታወቃል፤ ከጎረቤቶቻችን ከአፍሪካ አገሮች ጋር በመረጃ ልውውጥ በጣም ዝቅተኛ ነን፤ በቴሌቪዥን ብቻ ሳይሆን በኢንተርኔት አገልግሎት ችግር ፍዳችንን እየበላን ነው።
ለዚህ ነው አንገታችንን የምንደፋው፤ አንገታችንን ስንደፋ ክብራችን ይፈስብንና ገበናችን ይጋለጣል፤ መከባበሩ የሚበጀው ለዚህ ነው።

Friday, 1 June 2012

በከምሴ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ድዋ እንዳያደርጉ ተከለከሉ

ግንቦት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በከምሴ ልዩ  ዞን ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ሙስሊሞች ባለፈው አርብ ሶላት ሊያደርጉ በከተማዋ መሀል አደባባይ በሚገኘው መስጊድ ውስጥ  ለመሰባሰብ ጉዞ ሲጀምሩ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት አካባቢውን ተቆጣጥረዋል። ነዋሪዎቹ ከመስጊዱ ግቢ አልፈው  በአስፓልቱ ላይ በመቆማቸው የከተማው ትራፊኮች  ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ እና ከደሴ ወደ አዲስ አበባ የሚሄዱትን መኪኖች  ጉዞአቸው እንዲያቆሙ ለማድረግ ተገደዋል።
በፌደራል ከባድ መሳሪያዎች የተከበቡት ሙስሊሞች ሶላታቸውን  እንደጨረሱ፣ ፌደራል ፖሊሶች ወደ መስጊዱ ገብተው አባረዋቸዋል። አንድ ስማቸው እንዳይጠየቅ የፈለጉ በእድሜ የገፉ አዛውንት፣ እንደተናገሩት ሙስሊሞች ከሶላት ውጭ ድዋ ወይም ስብሰባ ማካሄድ እንደማይችሉ ተነግሯቸዋል። ሙስሊሞቹ ወደ ሌላ አካባቢ በመሄድ ሲሰባሰቡ ፣ የፌደራል ፖሊሶች ወደ ቦታው በመሄድ በድጋሜ እንዲበተኑ አድርገዋል።
ምንጮች እንደገለጡት በነገው ሶላት ምናልባትም ግጭት ሊነሳ ይችላል የሚልፍ ከፍተኛ ፍርሀት አለ።

በተለያዩ የአለም ክፍሎች የሚገኙ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፎችን አደረጉ

ግንቦት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በዋሽንግተን ዲሲ፣ በደቡብ አፍሪካ እና በስዊዘርላንድ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፎችን አካሂደዋል፣ በካናዳም ተመሳሳይ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ኣለም ኣቀፍ ጊዜያዊ ኣስተባባሪ ኮሚቴ (Ethiopia Muslims International Adhoc Committee)  ለ ሜይ 31  ቀን   2012 ዓ.ም በመላው ኣለም  «  ድምፃችን ይሰማ »  በሚል መሪ ቃል የጠራው አለም አቀፍ የተቃውሞ ሰልፍ አካል የሆነው እና በስዊዘርላንድ ውስጥ ካለፉት 4  ኣመታት ጀምሮ የሚንቀሳቀሰው  ቢላል ኢትዮ- ስዊዝ ማህበር ያስተባበረው የጄኔቫው የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ  የደመቀ ነበር
የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፉ የኢትዮጵያ መንግስት በሃይማኖት ተቋማት በተለይም በስልምና ሃይማኖት ተከታዮች መካከል መከፋፈል እንዲፈጠር ሆን ብሎ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት እንዲያቆም በኣንክሮት የጠየቀ ሲሆን  በሰልፉም ላይ በስዊዘርላንድ የሚገኙ የክርስትና እምነት ተከታዮችም ተካፍለውበታል ::
አቶ ኤልያስ ረሺድ  የቢላል ኢትዮ ስዊዝ ማህበር መስራችና ዋና ፀሃፊ  እንዲሁም የሰላማዊ ሰልፉ ዋና አስተባባሪ በተለይ ለኢሳት  መንግስት በእስልምና ሃይማኖት ጣልቃ መግባቱን የሚያሳዩ 11  ማስረጃዎችን በመዘርዘር አስረድተዋል ::
እንደ አቶ ኤልያስ ገለፃ   « መንግስት ዛሬ እያደረገ ያለውን የሃይማኖት ጣልቃ ገብነትን በመካድ እና ህጋዊና መሰረት ያለው የህገ-መንግስት ስልጠና እየሰጠሁ ነው የሚለውን የሃሰት ፕሮፓጋንዳና ዘመቻ ሃሰተኛ ሲሆን ሌላው ዛሬ የተጀመረው ሌላኛው አጀንዳ ደግሞ ክርስትያን ወገኖችንና እና ሙስሊሙን የጉሪጥ እንዲተያዩና በጉርብትናም ይሁን በአንድ ቤት ውስጥ የሚኖሩ የሃገር ልጆችን በመሃል መተማመንን ለማጥፋት ከፍተኛ ስራ እየተሰራ እንዳለ  ጠቁመው ይኸውም « ሙስሊሞች ሽርዕያዊ መንግስት ለመመስረት የሚጥሩትን አሸባሪዎች ነው እየታገልን ያለነው «  የሚል የሃሰት ፕሮፓጋንዳ እየነዛ ይገኛል ብለዋል ።

መንግሥት በእስልምና ሃይማኖት ጣልቃ ስለመግባቱ በርካታ ማስረጃዎችን ማቅረብ የሚቻል ቢሆንም በተለይም ካለፈው ዓመት ጀምሮ እጅግ አስገራሚና አሳዛኝ በሆነ መልኩ ጣልቃ ገብነቱ ግልጽ ሆኖ እየተስተዋለ እንደሆነና ይህ ማለቅያ የሌለው የሃሰት ሰንሰለት ከለት ወደ እለት መቀያየሩና አንዱ ሲያልቅ ሌላኛው መተካቱ አይቀሬ ስለሆነ ዋናውና መሰረታዊ የሙስሊሙ ህብረተሰብ ጥያቄ ምን እንደሆነ በግልጽ ቋንቋ ለማስቀመጥ ይረዳ ዘንድ በሚል  በጥቂቱ  አስራ አንዱን ብቻ ለማስታወስ

  1. መጅሊስ በደህንነቶች ተጽእኖ የሚመራ መሆኑ
  2. ከአመታት በፊት ከንቲባው አሊ አብዶ የመጅሊስ ባለስልጣን መሾማቸው
  3. የመንግስት ባለስልጣናት አህባሾችን ጋብዘው ማምጣታቸው
  4. የዶክተር ሽፈራው ንግግር
  5. የአዲስ አበባ ፍትሕ ቢሮ ሃላፊ አቶ ጸጋዬ ሀ/ማርያም ንግግር
  6. የአንዋር መስጊድ ኢማም ጣሃ መሀመድ ንግግር
  7. መንግስት ለመጅሊስ እያደረገ ያለው ህገወጥ ድጋፍ
  8. ስልጠናውን ያዘጋጀው ራሱ መንግስት መሆኑ
  9. የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር አቶ ወርቅነህ ገበየሁ በሻሸመኔ የተናገሩት ንግግር
  10. የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ አቶ ጁነዲን ሳዶ ንግግር
  11. ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ አንዱን መጤ ሌላውን ነባር ሲሉ መፈረጃቸው   ……

በመዘርዘር መንግስት በእስልምና ሀይማኖት ጣልቃ መግባቱን የሚያሳዩ በቂ ማስረጃዎች ናቸው በማለት  አስረድተዋል ::

ሰልፈኞቹ በዕለቱ ካሰሟቸው መፈክሮች መካከል
  • ሙስሊሙን እና ክርስቲያኑን በማጋጨት የስልጣን ዕድሜ ማራዘም አይቻልም
  • አክራሪነትና አሸባሪነት የኢትዮጵያ መንግስት የሃሰት ድራማ ነው
  • የኢትዮጵያ መንግስት በአርሲ ኣሰሳ በሰላሚ ሙስሊሞች ላይ የፈፀመውን ኢሰብዐዊ ጭፍጨፋ እናወግዛለን
  • ለመብት መታገል አሸበሪነት አይደለም
  • ኢትዮጵያ የሁሉም ሃይማኖት ሃገር ናት
  • ሙስሊም እና ክርስቲያን ወገኖች በአንድነት እንቁም……………………  የሚሉና ሌሎችም ይገኙበታል
የሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪዎች የሰልፈኞቹን ጥያቄ ለተባበሩት መንግስታት የሰብ ኣዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር በፅሁፍ አቅርበዋል ::

በአዲስ አበባ የሕዝብ ት/ቤቶች በመንግስት ተወረሱ

ግንቦት ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ ውስጥ ከሚገኙት 117 የህዝብ ትምህርት ቤቶች መካከል 115 ያህሉ ወደ መንግስት ትምህርት ቤትነት በያዝነው ዓመት ተዘዋወሩ፡፡

በህዝብ ይተዳደሩ የነበሩ ትምህርት ቤቶች ወደ መንግስት የተዛወሩት በህብረተሰቡ ጥያቄ መሰረት መሆኑን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ይግለጽ እንጂ ሕዝቡ የት እና መቼ  ጥያቄ እንዳቀረበ ያብራራው ነገር የለም፡፡

በህዝብ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ሲያስተምሩ የነበሩ መምህራንና ሰራተኞች ምድባ በአዲስ መልክ እየተዘጋጀ መሆኑንም ቢሮው በትላንትናው ዕለትበሰጠው መግለጫ አስታውቋል ;; በጉዳዩ ላይ ያነጋገርናቸው አንድ የአዲስ አበባ መምህራን ማህበር አመራር አባል በሰጡት አስተያየት የሕዝብ ት/ቤቶቹ ከፍለው ለመማር ለሚችሉ ጥሩ አማራጭ ነበሩ፡፡እውነት ለመናገር ከመንግስት ት/ቤቶች የተሻለ ብቃት ያላቸውም ናቸው፡፡ መንግስት በወሰደው እርምጃ የትምህርት ጥራቱ ወደ ኃላ እንዳይመለስ ሥጋት አለኝ ብለዋል፡፡

በፈለገዮርዳኖስ ት/ቤት ተማሪ የነበረ አንድ አስተያየት ሰጪም ውሳኔው አሳዛኝ ነው ብሎታል፡፡ “ እኛ ተማሪ በነበርን ግዜ በተመጣጣኝ ክፍያ ከፍተኛ ትምህርት እናገኝ ነበር፡፡በዚህ ላይ የመንግስት ት/ቤቶች ግማሸ ቀን ሲያሰተምሩ እኛ ግን ሙሉ ቀን እንማር ነበር፡፡በየሳምንቱ ትምህርታዊ ውድድሮች ሁሉ ስለነበሩ እርስ በርስ የነበረን ፉክክር ከፍተኛ ነበር፡፡ይህ ሁሉ በመንግስት ት/ቤቶች እንዴት ማግኘት ይቻላል” ሲል ጠይቋል፡፡

ሰለሞን ተካልኝ መፈክር ከመሸከም ውጪ ትንፍሽ እንዳይል በሰማዕታት ስም እጠይቃለሁ፡ የአቤ ቶኪቻው ደብዳቤ ለኢህአዴግ...\Abe tokichaw\

እናንት በአብዮታዊ ዴሞክራሲ የተባረካችሁ ክቡራን እና ክቡራት ሰላም እላችኋለሁ! ያው እንደምታውቁት ድርጅታችን መልካም ነገር ሲያጋጥመው የምንወዳደሰውን ያህል ችግር ባጋጠመን ግዜም ደግሞ እንዲህ በራችንን ዘግተን መገማገም እና ድርጅታችንን “ከመበስበስ” አደጋ መታደግ የዘወትር ተግባራችን እንደሆነ ይታወቃል።
ለዛሬ በአንድ ግለሰብ ላይ በዝግ ብሎግ እንድናወራ አነሆ ልጀምር ነው። (በነገራችን ላይ ዝግ ብሎግ ያልኩት እንደወትሮው ብሎጌ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ስለመታገዱ ላወራ አይይደለም። (በሌላ ቅንፍ ለድርጅታችን ከጠቀመ ልሳናችንም ቢዘጋ ቅር የማይለን ቁርጠኞች መሆናችንን በዚህ አጋጣሚ ለማረጋገጥ እወዳለሁ!) ይልቅስ በርዕሱ “ለኢህአዴግ አባላቶች ብቻ” ብዬ በማለቴ ሌሎች፤ ፅንፈኞች፣ አክራሪዎች፣ ነፍጠኞች፣ ነውጠኞች፣ ሽብርተኞች፣ ኒዬ ሊበራሎች፣ የሻቢያ ተላላኪዎች (ዉዉዉ ይሄንን ሁሉ ስም አውጥተንላቸዋል እንዴ ለካ…? ለነገሩ ከዚህም እጥፍ እጥፍ ስም አውጥተንላቸዋል። ለካስ ከኢኮኖሚ እድገቱ እኩል ተቃራኒዎቻችንን በመሞለጭም ታላቅ እምርታ አስመዝግበናልና! በእውኑ በድርጅቴ ኮራሁ! የሆነው ሆኖ፤ ባጠቃላይ እነዚህ ወዘተዎች ስለማያነቡት እና ጨዋታው የቤተሰብ ጨዋታ በመሆኑ ነው በዝግ ብሎግ ማለቴ!)))
http://www.youtube.com/watch?v=p7xtAH2aHA0&feature=youtu.be
Abe tokichaw
እንደሚከተለው እጀምራለሁ…!
እኔ የምለው ባለፈው ግዜ ሰለ ጓድ ሰለሞን ተካ አንዳንድ ነገሮችን አንስቼ ተናግሬ ነበር። በርግጥ ግለሰቡ የተናገርኩትን ቢሰማም ቅሉ ሂሱን አልዋጠም። ሰሞኑን እንዳሰማሁት ደግሞ እንኳን ሂሱን እና መድሃኒቱንም በአግባቡ መዋጥ እንዳቆመ ያመላከተኝ ነገር አስተውያለሁ።
ተጠቃሹ ግለሰብ በግል ስሜቱ በመነሳሳት ፅናት በተባለ ራዲዮ ጣቢያው ላይ ድርጅታችንን ለዝቅጠት የሚዳርግ አንዳች ንግግር ተናግሯል። ሰሞኑን ጋዜጠኛ አበበ ገላው ስመ ገናናውን ጠቅላይ ሚኒስትራችን አምባገነን ብሎ በተናገረበት ንግግሩ ላይ ጓድ ሰለሞን ተካ ምላሽ ለመስጠት ሞክሮ ነበር። በእውነቱ ሙከራውን ሳላንደንቅ አናልፈም።
ነገር ግን፤
1ኛ ጉድ ሰለሞን ተካ (ይቅርታ ጓድ በሚል ይስተካከል) በራዲዮ ጣቢያው ላይ በንባቡ አንድ ታዋቂ ጋዜጠኛን ለማስመሰል በግልፅ ጥረት ሲያደርግ ተስተውሏል። በተጨማሪም ተደጋጋሚ የንባብ ችግር ይታይበት ነበር። እንደውም ይህንን የሰማ አንድ ለድርጅታችን ቅርብ የሆነ ግለሰብ ይህ ሰው ራዲዮ ጣቢያ ሳይሆን ፖሊስ ጣቢያ ነበር የሚገባው” ብሎ አስተያየት ሰጥቷል። (ፖሊስ ጣቢያ ይገባዋል ያለው እንዲታሰር ፈልጎ መሆኑ የገባኝ በስተ መጨረሻ ነው።) በማስመሰል ጥረቱ እና በንባብ ድንቅፋቱ የራዲዬ ጣቢያውን ሚኒ ሚዲያ አስመስሎታል።
2ኛ አባሉ በአሁኑ ሰዓት በራዲዮ ጣቢያው እያስተላለፈ ያለው አበል የተቀበለበትን የድርጅት ስራ ሳይሆን የተጣሉትን ግለሰቦች ለማብሸቀያ እንደሆነ ፍንጭ አግኝቻለሁ። በዚህም የተነሳ ድርጅታችን ላይ ተደጋጋሚ ነጥብ ሲያስቆጥርባት ይስተዋላል።
3ኛ ጓድ ሰለሞን ራሱም ሳያውቀው “በህቡዕ” ለሌላ ድርጅት እየሰራ እንደሆነ ለማየት ችያለሁ። እንዲህ የምለው ከመሬት ተነስቼ አይደለም። ነገር ግን የሚናገራቸው እጅግ ርካሽ የሆኑ ደረጃቸውን ያልጠበቁ ስድባ ስድቦች ድርጅታችንን የሚያዋርዱ ከመሆናቸውም በላይ በተቃራኒው ደግሞ ለተቃዋሚዎች ትልቅ ግብአት እንደሚሆኑ በተግባር በመመልከቴ ነው።
4ኛ የዚህ አባል ጉዳይ ተዘርዝሮ የሚያልቅ አይደለም። የራዲዮ ፕሮግራሙ እንደማንኛውም ስልጠና እንደወሰደ ግለሰብ ተቃዋሚዎችን “የደርግ ርዝራዦች፣ ነፍጠኞች ሽብርተኞች…” ሲል መሳደቡ ጥሩ ሆኖ ሳለ በፕሮግራሙ መጨረሻ ላይ ግን “ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ቆራጥ አመራር ጋር ወደፊት!” በማለት የቀድሞ የደርግ አባላት ለኮሎኔር መንግስቱ የሚያሙትን ፉከራ ስም ብቻ ቀይሮ አሰምቷል። በእውኑ ይሄ በድርጅታችን ላይ ታላቅ የመበስበስ አደጋ አይደለምን…?
100ኛ ባጠቃላይ ግለሰቡ ከላይ አንድ ወዳጄ ብሎኛል እንዳልኩት ራዲዮ ጣቢያ ሳይሆን ፖሊስ ጣቢያ የሚገባው ቢሆንም ድርጅታችን የምትታገስ ናትና ለጊዜው በትዕግስ እንድታለፈው አስተያየቴን ስሰጥ ቀጥሎ የሚገኘው የውሳኔ ሃሳብ ተግባራዊ እንዲሆንበት አበክሬ እጠይቃለሁ።
የውሳኔ ሃሳብ
ይህ ግለሰብ ለኢህአዴግ እየሰራለት ነው ብዬ አላምንም። ከሆነም ደግሞ “ቆይ ባልሰራላችሁ!” በሚል ጥላቻ እና ቂም በቀል ኢህአዴግን ሊያጠፋ ቆርጦ የተነሳ ነው። (እርግጥ ነው ለተቃዋሚዎችም እየሰራ እንዳለሆነ ግልፅ ነው እናስ…? የተባለ እንደሆነ በግሉ ከወዲያ ማዶ ላለበት ብሽሽቅ ኢህአዴግን መጠቀሚያ ያደረገ ግለሰብ ነው። ይህም ግልፅ የሆነ ኪራይ ሰብሰቢነት እንደሆነ በተደጋጋሚ በተሰጡ ድርጅታዊ ስልጠናዎች ላይ ተረድተናል።) ስለሆነም በእውኑ ድርጅታችንን ከተጋረጡባት ሰርጎ ገቦች እና ጥቅመኞች የማዳን ጊዜው አሁን ነው። ከልባችሁ ለእናት ድርጅታችን ፍቅር ያላችሁ አባላት ዛሬውኑ ሰለሞን ተካ በኢህአዴግ ጉዳይ ላይ ትንፍሽ እንዳይል ድርጅታዊ ውሳኔ ይተላለፍ ዘንድ በተሰዉ ሰማህታት ስም እጠይቃለሁ። የግድ በአባልነት መቀጠል ካለበት ሰላማዊ ሰልፎች በሚኖሩ ግዜ መፈክሮችን ከተሸከመልን ይበቃል።
ከልማታዊ ሰላምታ ጋር!

Thursday, 31 May 2012

የቴሌኮም ማጭበርበር አዋጅፀደቀ

በኢንተርኔት ሰልክ መደወል እሰክ 8 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እሰራት ያስቀጣል
ከኢኮኖሚያዊ ኪሣራ ባሻገር የአገሪቱን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ስጋት ሆኗል በተባለው የቴሌኮም ማጭበርበር ላይ የወጣው ረቂቅ አዋጅ ፀደቀ፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከትናንት በስቲያ ያፀደቀው ረቂቅ አዋጅ እንደሚያመለክተው፤ ከኢንፎርሜሽንና ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ፈቃድ ውጪ ማንኛውንም አይነት የቴሌኮሚኒኬሽን መሣሪያ ማምረት፣ መገጣጠም፣ ከውጭ ሀገር ማስመጣት፣ መሸጥ እስከ 15 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራትና እስከ 150ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ያስቀጣል፡፡ በፀረሽብርተኝነት አዋጅ ከሚያስቀጣ ወንጀል ጋር የተያያዘ ሽብር የሚያስከትል መልዕክት ለማሰራጨት ወይም በወንጀል ህግ የሚያስቀጣ አስነዋሪ መልዕክቶችን ለማሰራጨት በማንኛውም የቴሌኮሙኒኬሽን መሣሪያና ኔትወርክ መጠቀም እስከ ስምንት ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራትና እስከ 80 ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ያስቀጣል፡፡
ምክር ቤቱ ያፀደቀው አዲሱ አዋጅ፤ ኢንተርኔትን በመጠቀም የስልክ ጥሪ ወይም የፋክስ አገልግሎት የሚሰጥ ማንኛውንም ሰው በወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ ከ3 ዓመት እስከ ስምንት አመት በሚደርስ ጽኑ እስራትና በስልክ ጥሪዎቹ ሊያገኝ ይችላል ተብሎ የሚገመተውን ገቢ አምስት እጥፍ በሚሆን መቀጫ ይቀጣል፡፡ በኢንተርኔት ስልክ በመደወል ተግባር ላይ የተሳተፈ ወይንም የስልክ ግንኙነቱን ያደረገው ሰው ደግሞ እስከ 2 ዓመት በሚደርስ እስራትና እስከ ብር 20ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ይወሰንበታል፡፡ ፍርድ ቤት በጥፋተኞቹ ላይ ቅጣት በሚወስንበት ወቅት ወንጀሉን ለመፈፀም በጥቅም ላይ የዋለ ማንኛውም የቴሌኮሙኒኬሽን መሣሪያ በመንግስት እንዲወረስ ትዕዛዝ ይሰጣል፡፡ በፀደቀው አዋጅ መሰረት፤ የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀሎች የመጀመሪያ ደረጃ የመዳኘት ሥልጣን የሚኖረው የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሲሆን የቴሌኮም ማጭበርበር ወንጀሉ ለመፈፀሙ ወይም ሊፈፀም ለመሆኑ ፖሊስ ካመነ በድብቅ የሚደረግ የብርበራ ማዘዣ ፈቃድ ከፍርድ ቤት አውጥቶ ለመበርበር እንዲችል ስልጣን ሰጥቷል፡፡ በህገወጥ መንገድ ሲምካርድ፣ ክሬዲት ካርድ፣ የደንበኞች መለያ ቁጥር ወይም ዳታ  የሚሰራ ወይም የሚያባዛ ወይም በህገወጥ መንገድ የተባዙትን ሲም ካርዶች፣ የደንበኞች መለያ ቁጥሮች ወይም ዳታዎች የሚሸጥ ወይም በማናቸውም መንገድ የሚያሰራጭ ማንኛውም ሰው በወንጀሉ ጥፋተኛ ሆኖ ከተገኘ፤ እስከ አስራ አምስት ዓመት የሚደርስ ጽኑ እስራትና 150ሺህ ብር የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ያስቀጣል፡፡ የቴሌኮም የማጭበርበር ወንጀል የብሔራዊ ደህንነትን አደጋ ላይ የሚጥልና ዜጐች በመንግስታቸው ላይ አመኔታ እንዲያጡ የሚያደርግ ከባድ ወንጀል መሆኑን የጠቀሰው አዋጁ ፤ወንጀሉ ለተለያዩ የሽብር ሃይሎች መጠቀሚያ መሆኑን፤ አሠራሩ ለሙስናና ብልሹ አሠራር የተጋለጠ እንዲሆን በማድረግ ተደራራቢ ወንጀሎች የሚፈፀሙበት እጅግ ሥር የሰደደ አደጋ እንደሆነ ገልጿል፡፡
አለም አቀፍ የስልክ ጥሪዎችን የአገር ውስጥ በማስመሰል (ኮልባክ) ወንጀል በየዓመቱ በበርካታ ሚሊዮን የሚገመት የውጭ ምንዛሪ አገሪቱ እንድታጣ እያደረጋት መሆኑን የጠቆመው አዋጁ፤   በወንጀሉ ተሳታፊ የሆኑትን እስከ 10 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲሁም በአገልግሎቱ ተጠቃሚ የሆኑ ሰዎች እስከ 2 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ይደነግጋል፡፡ ህገወጥ የቴሌኮም መሣሪያዎችን በሲስተሙ ላይ በመግጠም ድርጅቱ በአንድ የስልክ ጥሪ ማግኘት ከሚገባው ገቢ 83 በመቶ ያስቀራል በተባለውና ህገወጥ የቴሌኮም መሳሪያዎችን ከውጭ በማስገባት ከአገሪቱ የቴሌ ሲስተም ሳይገናኝ ራሱን የቻለ የቴሌኮሙኒኬሽን ሲስተም ለመፍጠር ያስችላሉ የተባሉት ወንጀሎች በአዋጁ በአደገኝነታቸው ከተለዩ ወንጀሎች መካከል ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከሦስት ዓመታት በኋላ ጡረታ እንደሚወጡ በድጋሚ አረጋገጡ

- የተዋጣለት ዴሞክራሲ አልገነባንም
- በሀገሪቱ መከላከያ ሠራዊት የብሔር ተዋፅኦ ቢሻሻልም አመራሩ ግን ቀድሞ ከሕወሓት ታጋዮች አልተላቀቀም
- እየተገነቡ ባሉ የውሃ ኃይል ማመንጫ ግድቦች ላይ የምዕራብ አካባቢ ተቆርቋሪዎችን ተፅዕኖ ፈርተውታል
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከእንግሊዛዊው ጋዜጠኛ ሪቻርድ ዳውደን ጋር ከሰሞኑ ቃለ-ምልልስ አድርገው ነበር። ሪቻርድ ዳውደን የሮያል አፍሪካ ሶሳይቲ ዳይሬክተር ሲሆን፤ በጋዜጠኝነት በታላላቅ የእንግሊዝ ጋዜጦችና በዘኢኮኖሚስት መፅሔት የአፍሪካ ኤዲተር ሆኖ ሰርቷል። በአፍሪካ ዙሪያ መፅሐፍቶች ፅፏል።
ሪቻርድ ዳውደን ለዓለም የኢኮኖሚክ ፎረም ስብሰባ እዚህ አዲስ አበባ ውስጥ በተካሄደበት ወቅት ከጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ጋር ቃለ-ምልልስ አድርጎ ነበር በቃለ-ምልልሳቸውም ከሦስት ዓመት በኋላ ጡረታ እንደሚወጡ አስታውቀዋል። ዳውደን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ቃለ-ምልልስ ዋና ዋና ነጥቦች በመለየት ከሰሞኑ በራሱ ብሎግ ላይ አስፍሮታል። በጎንዮሽም፤ “መለስ ኢትዮጵያን እንዴት እየመሯት ነው” የሚል ጠንከር ያለ ሐተታ አቅርቧል።
ሪቻርድ ዳውደን እ.ኤ.አ በ1901 ዓ.ም የተመሰረተውን ሮያል አፍሪካን ሶሳይቲ እ.ኤ.አ ከ2002 ጀምሮ በዳይሬክተርነት በመምራት ላይ ይገኛል። ሮያል አፍሪካን ሶሳይቲ የአፍሪካንና የታላቋን ብሪታንያን ግንኙነት ወደተሻለ ደረጃ ለማድረስ ተብሎ የተቋቋመ ተቋም መሆኑ ይታወቃል። በዚህ መነሻ ሪቻርድ ዳውደን በተቋሙ ድረገፅ ላይ በራሱ ብሎግ የአፍሪካን ሐተታዎችን በማቅረብ ይታወቃል። በአፍሪካ አንዳንድ ጉዳዮችም ላይ መጣጥፎችና ዘጋቢ ፊልሞች ሰርቷል።
ዳውደን አዲስ አበባ በመጣበት ወቅት አቶ መለስን ለማነጋገር ችሏል። በቃለ-ምልልሱም ላይ አቶ መለስ በኢትዮጵያ በሕዝቦች በፈቃደኝነት ላይ የተመሠረተ ሕገ-መንግስት ቢፀድቅም፣ በሀገሪቱ ያሉ ብሔረሰቦች በቋንቋቸው እንዲናገሩ በርካታ ስራዎች ቢሰራም የተዋጣለት ዴሞክራሲ አለመገንባቱን ግን አምነዋል።
ሌላው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት በዴሞክራሲና በኢኮኖሚ እድገት መካከል ቀጥተኛ ግንኙነት አለመኖሩን ነው። ምንም እንኳ ዴሞክራሲ በኢኮኖሚ እድገት ጥሩ እና አስፈላጊ ቢሆንም፤ የዴሞክራሲ ጉዳይ ግን በራሱ የሚቆም ነው ብለውታል።
የሀገሪቱን መከላከያ ሠራዊት የብሔር ተዋፅኦ እና የቀድሞው የትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር (ሕወሓት) በሠራዊቱ ላይ ስላለው ተፅዕኖ ተጠይቀው ተራ ሠራዊቱ ከብሔር ተዋፅኦ የተሻለ ደረጃ ላይ ቢገኝም አመራሩ ግን ከህወሓት የቀድሞ ታጋዮች ተፅዕኖ አለመላቀቁን ማመናቸውን ዳውደን በቃለ-ምልልሱ ላይ ይፋ አድርጎታል።
ኤርትራን በተመለከተም ከኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የድንበር አካላይ ኮሚሸን ውሳኔውን በመቀበል ለመነጋገር በወቅቱ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ ኮፊ አናን ደብዳቤ ፅፈው የነበረ ቢሆንም፤ ጥያቄአቸው ግን በኢሳያስ እምቢታ አለመሳካቱን፣ ነገር ግን ወደፊትም አምስቱ የሰላም ኀሳቦች እንዳሉም ሆነው ከኢሳያስ ጋር ለመነጋገር ፍላጎት እንዳላቸው መግለፃቸውን ጠቅሷል።
በተጨማሪ የጋዳፊ መውደቅ በተመለከተም ጋዳፊ በቀጠናው መጥፎ ተፅዕኖ ቢኖረውም ውድቀቱ ግን የተፈራውን ያህል አለመሆኑን፣ እንዲሁም የዓረብ አገራት ሕዝባዊ መነሳሳት በተመለከተም ተጠይቀው የቱኒዝያ ኢኮኖሚ ሁሉ አቀፍና ፍትሐዊ ባለመሆኑ የመጣ ስለመሆኑ እና ሙስናንም በተመለከተ የአፍሪካ መሪዎች በታላላቅ ኩባንያዎች አባላጊነት የሚፈፀም ስለመሆኑም ተናግረዋል። ሀገር በቀል የሙስና አስተሳሰብ በሕዝቡ እንዳይሰርፅ መደረግ እንዳለበትም መግለፃቸውን አትቷል።
በሀገሪቱ እየተገነቡ ያሉ የኃይል ማመንጫዎች እንደተፈራው ብዙ ሕዝብ የማያፈናቅሉ ቢሆንም፤ የምዕራብ የአካባቢ ተቆርቋሪ ነን የሚሉ ግን ከአካባቢ መቆርቆር ባለፈ የስለላ ስራ ሊያካሂዱ እንደሚችሉና ይሄም እንደሚያስፈራቸው ተናግረዋል።
የሀገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን በተመለከተም በሁለት ከፍለው እንደሚያዩዋቸው አንደኛዎቹ አሁን ያለውን ሕገ-መንግስታዊ ስርዓት መዘርጋቱን ሀገር ከመበተን አንፃር ወንጀል እንደተሰራ አድርገው የሚያዩ፣ ሌሎቹ ደግሞ በጣም መጥፎና ጨካኝ ሴራ በማራመድ የብሔር ብሔረሰቦችን ፍላጎት በማኮላሸት የራሳቸውን ሀገር ለመመስረት የሚሰሩ መሆናቸውን ነገር ግን ሁለቱም የማይጠቅሙ ቢሆኑም፤ ዋናው ነገር ወሳኙ ሕዝቡ መሆኑን መግለፃቸውን በቃለ-ምልልሱ ላይ አመልክተዋል።
ያም ሆኖ አቶ መለስ የገነቡት ስርዓት ካለፉት ስርዓቶች በተለየ ከአርብቶ አደሮች አካባቢዎች በስተቀር በሁሉም የሀገሪቱ መንደሮች ድርጅታቸው የተመረጠ መሆኑንና መንግስታቸው በሀገሪቱ ግልፅና ጠንካራ መሠረት መጣሉን፣ ተቃዋሚዎች ግን በገጠር ሙሉ በሙሉ የማይፈለጉ መሆኑን ተናግረዋል።
ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ሪቻርድ ዳውደን ካቀረበላቸው ጥያቄዎች መካከል ቀጣይ የስልጣን ዘመናቸውን በተመለከተ ሲሆን እሳቸውም እ.ኤ.አ በ2015 (ከሦስት ዓመት በኋላ) ጡረታ እንደሚወጡ፣ ጡረታ ከወጡም በኋላ ምናልባት በአመራር አካዳሚ ውስጥ እንደሚያስተምሩ፣ አልፎ አልፎ መፅሐፍ እንደሚፅፉ እና በአዳንዳንድ ዓለም አቀፍ ወይም የፓን-አፍሪካን ጉዳዮች ላይ በቋሚነት ባይሆንም በጊዜአዊነት መሳተፍ እንደሚፈልጉ ገልፀውለታል።
በኢህአዴግ የመተካካት ዕቅድ መሠረት አቶ መለስ ዜናዊ የአሁኑ የምርጫ ዘመን ሲጠናቀቅ ኃላፊነታቸውን ለተተኪያቸው በማስረከብ እንደሚለቁ በተደጋጋሚ መግለፃቸው የሚታወስ ነው።
ምንጭ: ሰንደቅ ጋዜጣ

Human Rights in Ethiopia(HRE):-Trials of Politicians, Journalists Test Ethiopia's Anti-Terrorism Law

May 30, 2012 by Peter Heinlein

ADDIS ABABA - In Ethiopia, a series of high-profile trials is being closely watched as a test of recently-enacted anti-terrorism legislation. A three-judge federal panel is hearing the trials of as many as 150 people arrested on terrorism-related charges last year, including prominent politicians and journalists.
Almost every week for the past few months, a small group of journalists and diplomats has  gathered at Addis Ababa's Lideta federal court complex to attend terrorism trials. 


The most high-profile is the case of journalist Eskinder Nega, recent winner of the PEN America “Freedom to Write” Award, and Andualem Arage, who had been one of the rising stars in Ethiopia's political opposition.  They are accused of collaborating with the outlawed Ginbot Seven (May 15th) political party to carry out terrorist attacks.
U.S. Ambassador to Ethiopia Donald Booth was in the courtroom last week when a verdict in the case was due, but the judges postponed the announcement till mid-June, saying they needed more time.
Among the other trials before the court was the case of two Swedish journalists captured in the restive Ogaden region in the company of members of the outlawed Ogaden National Liberation Front, or ONLF.  The journalists were convicted of supporting terrorism, and given 11-year prison terms.
In another case, the deputy editor of a now-defunct independent newspaper and a columnist for another paper were convicted of plotting terrorist acts.  Both received long sentences.
Then there is the case of a senior United Nations security official who played a key role last year in negotiating the release of two World Food Program employees abducted in the Ogaden.  Shortly after the release, the U.N. officer was arrested and charged with having ties to the ONLF.
Almost forgotten has been the case of more than 100 ethnic Oromo political activists.  Prosecutors have alleged they were involved with the outlawed Oromo Liberation Front, or OLF. 
Oromos are the largest of Ethiopia's ethnic groups, and the defendants include top leaders of the two main Oromo opposition parties, as well as former members of parliament.
The sheer number of these cases has drawn international attention to Ethiopia's anti-terrorism legislation.  The law was passed in 2009. and came into full effect last year when Ginbot Seven, the ONLF, the Oromo Liberation Front, and al-Qaida were declared terrorist groups.
In a report titled “Dismantling Dissent”, the rights group Amnesty International accuses Ethiopia of systematically using the law and the pretext of fighting terrorism to silence internal critics.
Amnesty researcher Claire Beston was expelled from Ethiopia last August shortly after meeting with senior Oromo opposition leaders Bekele Gerba and Olbana Lelisa.  Both men were arrested days later on terrorism charges. 
Beston says critics of Ethiopia's ruling party appear to be the law's main targets. "Since the law has been introduced, it's been used more to prosecute opposition members and journalists than persons who might be committing so-called terrorist activities," he said. 
The once-busy headquarters of the Oromo Federal Democratic Movement, Ethiopia's largest Oromo party, is deserted these days.  OFDM Deputy Secretary General Bekele Nega says the arrests of activists such as Bekele Gerba and Olbana Lelisa have frightened supporters away. "This is what the government wants.  This is the message they are sending to the people.  Don't work with these opposition groups.  They are terrorists.  I'll imprison you, just like Bekele, just like Olbana, so they don't come, fearing imprisonment, fearing torture," he said. 
Government spokesman Shimeles Kemal strongly denies there is any intent to crack down on ethnic Oromos. He accuses opposition groups of trying to steer the issue to their own advantage. "[The] government does not espouse a policy that would precisely target certain members of ethnic groups, isolating them, and prosecuting them.  So you journalists, you should not stick an ethnic tag to cases.  You should be careful because it would sound like the government is prosecuting a certain tribe or ethnic group.  This is misleading," he said. 
Shimeles and other officials, including Prime Minister Meles Zenawi have also rejected the charge that Ethiopia uses anti-terrorism laws to suppress dissent.  They allege that terrorists have used journalism and politics as a cover for their nefarious activities.
Opposition leaders point out, however, that none of the defendants is accused of carrying out an actual terrorist attack, and that Ethiopia has remained relatively free of terrorism despite its location in one of the world's most volatile regions.
The African Commission on Human and Peoples' Rights this month approved a resolution expressing alarm at Ethiopia's prosecution of journalists and political opposition members. The resolution calls on Ethiopia to remove the anti-terrorism law's restrictions on freedom of expression.

Wednesday, 30 May 2012

10ሩ የድህረ-ግንቦት 20 ኪሳራዎች

በፍቃዱ ዘ ኃይሉ | May 30th, 2012 at 3:20 am | |

አቶ መለስና ጓደኞቻቸው አምባገነን ስርአትን ለመቀየር ነፍጥ አንስተው፣ በጭቆና ላለመኖር ሲሉ በህይወታቸው ተወራርደዋል፤ አላማቸውን ለማሳካት ገድለዋል ሞተዋል፡፡ ድል ቀንቷቸው የዛሬ 21 አመት አምባገነኑን የደርግ ስርአት አስወግደው ምኒሊክ ቤተመንግስት ሲገቡ ኢትዮጵያን በለውጥ ጎዳና ሊመሩ፣ ዴሞክራሲን በማስፈን በሀገሪቱ አዲስ ታሪክ እንዲያኖሩ የሚያስችል ዕድል ነበራቸው ፡፡ አምባገነኑን የኮሎኔል መንግስቱ ኃ/ማርያምን ደርግ ካስወገዱ በኋላ ግን አምባገነኑን የአቶ መለስ ዜናዊን ስርአት ከማስቀመጥ ባለፈ በግንቦት 20 ድል ታሪክ ሊሰሩ አልቻሉም፡፡ 

ያ ሁሉ መስዋዕትነት የተከፈለበት፣ በተለያዩ ጎራዎች የተሰለፉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎችን ህይወት ዶጋ አመድ አድርጎ ግንቦት 20, 1983 ዓ.ም የተቋጨው ጦርነት አንድን ወታደራዊ አምባገነን መሪ በኃይል በማስወገድ የይምሰል ዴሞክራሲያዊ ስርአትን(pseudo democracy) የገነባ ሲቪል አምባገነን መተካት የተወሰነ ቡድንን ወይም ግለሰቦችን ፖለቲካዊ የበላይነት(hegemony) ለማረጋገጥ ያለመ እንዳልነበር በትጥቅ ትግሉ ተሳታፊ የነበሩ ግለሰቦች ያረጋግጣሉ፡፡ የህወሓት ነባር ታጋይና የቀድሞው የትግራይ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ገብሩ አስራት ሰኔ 19,2002 ለወጣችው አዲስ ፕሬስ ጋዜጣ አሞራው ስለተባለ የህወሓት ጀግና ታጋይ ሲያስረዱ ‹‹አሞራው ቀና ብሎ እየተደረገና እየሆነ ያለውን ነገር ቢያይ ይገርመው ነበር›› ካሉ በኋላ የአቶ መለስ መንግስት በአሞራውና በሌሎች ታጋይ ሰማእታት መስዋዕትነት ስልጣን እየነገደ መሆኑን አብራርተዋል፡፡  

ህወሓት/ኢህአዴግ ስልጣን የያዘበት ተመሳሳይ ወቅት አምባገነናዊ ኮሚኒስት ስርአቶችን በማስወገድ ዴሞክራሲያዊ ግንባታ የጀመሩት የምስራቅ አውሮፓ ሀገራት በአጭር ጊዜ ውስጥ አመርቂ ለውጥ ማምጣታቸውን Carleton UniversityInstitute of European and Russian Studies  አጥኚ የሆኑት ድራጎስ ፖፓ (DRAGOS POPA) ሮሜኒያንና ቡልጋሪያን ነቅሰው ያመላክታሉ፡፡ የባልካን ሀገራትም ሁለት አስርት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ዴሞክራሲያዊ እምርታ ማምጣታቸውን  The democratic transformation of the Balkans በሚል ርዕስ የቀረበው የሮዛ ባልፈር እና ኮሪና ስትራቱላት (Rosa Balfour and Corina Stratulat) ጥናት ያመላክታል፡፡  ጥናቱ የባልካን ሀገራት በአጭር ጊዜያት ውስጥ ሶስት መሰረታዊ ለውጦችን ማስመዝገባቸውን ያስረዳል‹‹ከጦርነት ወደ ሰላም፣ ከኮሚኒዝም የእዝ ኢኮኖሚ ወደ ነፃ ገበያ እንዲሁም ከአንድ ፓርቲ አገዛዝ ወደ መድብለ ዴሞክራሲ ተለውጠዋል›› ይላል፡፡ በዚህ ረገድ በኢትዮጵያ ባለፉት 21 አመታት የታየውና አሁንም ያለው ነባራዊ ሁኔታ ለግንቦት 20 ድል የወጣውን  የህይወት ግብር እና በድሉ ማግስት የተገኘውን የግንቦት 20 ፍሬ ስናወራርድ ውጤቱ ኪሳራን የሚያመላክት ነው፡፡
ይህ ጽሁፍ በህወሓት በስተመጨረሻም በህወሓት/ኢህአዴግ መሪነት ለ17 አመታት በተደረገው ፅኑ ትግል የተገኘው የግንቦት 20 ድል ሊያመጣ ያልቻላቸውን አስር አንኳር ነጥቦች ይፈትሻል፡፡   

ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን መገንባት ያለመቻሉ
ዴሞክራሲያዊ ተቋማት ግንባታ በሂደት ውጤት የሚያስገኝ ጥረት ነው፡፡ ጤናማ ሂደት እስከኖረ ድረስም የግንባታው እድገት አይቀሬ ውጤት ነው፡፡ ዛሬ በዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታቸው ምሳሌ የሚሆኑት ሀገራት በቅፅበታዊ ለውጥ/ክስተት ካሉበት ደረጃ ላይ አልደረሱም፡፡ ከ1983 ግንቦት 20 ወዲህ ኢትዮጵያ በዴሞክራሲያዊ ስርአት ግንባታ ሂደት ውስጥ መግባቷን የአቶ መለስ መንግስት ሲናገር ይደመጣል፡፡ ሆኖም ሂደቱ አንዴ ወደ ፊት ሌላ ጊዜ ደግሞ ወደኋላ ሲንሸራተት ቆይቶ በአሁኑ ጊዜ ተኮላሽቷል፡፡ ምርጫ ቦርድም ሆነ የሰብአዊ መብት ኮሚሽን ወይም የእንባ ጠባቂ ተቋም በኢህአዴግ ‹‹ሞተር›› የሚንቀሳቀሱ፣ በመንግስት ሳምባ የሚተነፍሱ በህዝብ አመኔታ የሌላቸው የስም ዴሞክራሲያዊ ተቋማት ናቸው፡፡ የአቶ መለስ መንግስት በ21 አመት የስልጣን ዘመኑ ዴሞክራሲያዊ ተቋማትን ለመገንባት አለመድፈሩ/አለመፈለጉ የድህረ ግንቦት 20 ኪሳራ ማሳያነው፡፡  

ከተፅዕኖ ነፃ የሆኑ የፍትህ አካላትን መገንባት አለመቻሉ
በኢትዮጵያ ለህግ የሚሰጠው ቦታ ከፍ ያለ ነው፡፡ ህግን የማክበር እና ለፍትህ አካላት አመቴታና ክብር የሚሰጥ ባህላዊ መሠረትም አለ፡፡ ይህ ባህላዊና ሞራላዊ መሠረት በተለይ ከደርግ መንግስት ስልጣን መያዝ በኋላ የመሸርሸር ምልክት ማሳየት ጀመረ፡፡ “የደርግ ሹማምንት በፍትህ አካላት ላይ የተለያዩ ጫናዎችን በማሳደር ፍርድን ለማጣመም ጥረት ያደርጉ ነበር” የሚሉት አቶ አለማየሁ አዱኛ በህግ አማካሪና ጠበቃነት ይሰራሉ፡፡ አቶ አለማየሁ እንደሚሉት ከመንግስት አካላት ጫና ቢኖርም የፍትህ አካላቱ ከነበራቸው ጠንካራ መሠረት አንፃር ነፃነታቸውን ያስደፈሩ አልነበሩም፡፡ ይህ ሁኔታ የደርግ ባለስልጣናት ለሚወስዷቸው እርምጃዎች ህጋዊ ከለላ ከመስጠት ይልቅ ግልጽ ፖለቲካዊ እርምጃ ይወስዱ ነበር፡፡ የደርግ አምባገነንነትና ጨፍጫፊነት አጠያያቂ ባይሆንም እነዚህ ህገወጥ እርምጃዎች የሚወስዱት በማናለብኝነት በተወጠሩ ባለስልጣናት “የጐበዝ አለቆች” እንጂ በፍትህ አካላት አልነበረም፡፡ ህወሓት /ኢህአዴግ ስልጣን ከያዘበት ጊዜ ጀምሮ ግን ሁሉንም ተቋማት በአንድ የፖለቲካ አስተሳሰብ የማጥመድ አባዜ የፍትህ አካላትንም አልተወም፡፡ ፖሊስ፣ አቃቤ ህግ እና ፍርድ ቤቶች ከመጋረጃ ጀርባ በኢህአዴግ ባለስልጣናት የሚሰጡ ፖለቲካዊ ውሳኔዎችን “በህግ” ስም ያስተላልፋሉ፡፡ ኢህአዴግ እራሱ ያፀደቀውን ህገ መንግስት በመጣሱ የፍትህ አካላትን ነፃነት ከመጋፋት ባለፈም፣ ፖለቲካዊ ተፅዕኖ የሚያደርሱ አፋኝና ኢፍትሀዊ ‹‹ህጐችንም›› በማፅደቅ ፍትህንና ህጋዊ ስርዓትን የሚያዋርዱ እርምጃዎችን ወስዷል፡፡ ግንቦት 20 ነፃ የፍትህ አካላት እንዲለመልሙ አለማድረጉ ሌላው የድህረ-ግንቦት 20 ኪሳራ ነው፡፡

ብሔራዊ ስሜትን መናዱ (ኢትዮጵያዊነትን ማኮሰሱ)
ብሔራዊ ስሜት መናድ ለአንድ ሀገርና በውስጧ ለሚኖሩ ዜጎች ደህንነት አደጋን ይደቅናል፡፡ የኢህአዴግ መንግስት ኢትዮጵያዊነት የሚንዱና ጎጣዊ ማንነት ላይ የሚያተኩሩ ፖለቲካዊ እሳቤዎችን በህዝቡ ውስጥ እንዲዘሩና እንዲስፋፉ ያላሰለሰ ጥረት አድርጓል፡፡ የኢትዮጵያን ጥንተ ታሪክ በመካድ ህዝቦች በግድ የተጠፈሩባት ‹‹የአጤ ምኒሊክ ፍጡር›› አድርገው ያስቀምጧታል፡፡ ይህ አስተሳሰብ ህወሓት ስልጣን ላይ ሳይወጣ ያራምደው እንደ ነበር ግልፅ ነው፤(የኤርትራ ህዝብ ትግል ከየት ወዴት 1979ን ልብ ይሏል) የአስተሳሰቡ መነሻ የኢትዮጵያን ጥንተ ታሪክ በመካድ ቢነሳም መጨረሻው የራስን እድል በራስ መወሰን እስከ መገንጠል የሚል ክፉ ድምዳሜ ላይ የሚያደርስ ነው፡፡ ይህ የፀረ ኢትዮጵያዊነት ውጤት በኢህአዴግ የስልጣን ዘመን መጀመሪያ ኤርትራን በማስገንጠል ተጀምሮ በ1987ቱ ህገ-መንግስት አንቀፅ 39ን በማካተት መሰረቱን አጠናከረ፡፡ ከኤርትራ መገንጠል በኋላ በተነሳው የኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ጦስ ከሁለቱም ሀገራት ‹‹ወደ ሀገራቸው› የተሸኙ ዜጎችን ሰቆቃ ለተመለከተ፣ የተሳሰረን ህዝብ ‹‹የራስን እድል በራስ በመወሰን›› ሰበብ መነጠል የሚያመጣውን ስነልቦናዊ፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጦስ ለማገናዘብ አይቸግረውም፡፡ ሆኖም ኢህአዴግ አደገኛ አስተሳሰቡን ለማረቅ የሚፈልግ አይመስልም፡፡
የአቶ መለስ መንግስት አራምዳለሁ ለሚለው ‹‹የልማታዊ መንግስት›› ፍልስፍና ብሔራዊ ስሜት የጎላ ሚና እንዳለው ምሁራን የተለያዩ ሀገራትን ልምድ በመጥቀስ ያስረዳሉ፡፡ በዚህ ተፋልሶ ውስጥ የሚዋትተው የአቶ መለስ ኢህአዴግ ከኢትዮጵያዊነት ጋር መላተሙ ሌላው የድህረ-ግንቦት 20 ክስረት አመላካች ነው፡፡

የብሔር ጥያቄ ምላሽ አለማግኘቱ
በ1960ዎቹ የተማሪዎች ንቅናቄ ይስተጋቡ ከነበሩ የፖለቲካ ጥያቄዎች ውስጥ የብሔር ጥያቄ አንደኛው ነው፡፡ ኢህአዴግ ይህን ጥያቄ እንደ ሰንደቅ አንስቶ የብሔረሰቦችን እኩልነት እንዳረጋገጠ ይናገራል፡፡ የብሔር እኩልነት የግንቦት 20 ፍሬ እንደሆነም ደግሞ ደጋግሞ ለማሳመን ጥሯል፡፡ ሆኖም ከግንቦት 20 በኋላም ተገፋን ተጨቆንን የሚሉ የብሔር ቡድኖች በየምክንያቱ ብቅ ብቅ ማለት ቀጥለዋል፡፡ ኢህአዴግ በቋንቋ ከመማርና ከመዳኘት ባለፈ ብሄረሰቦች ራሳቸውን የምር እንዲያስተዳድሩ የሚፈልግ አይመስልም፡፡ አቶ ገብሩ አስራትም በኢትዮጵያ የብሔረሰቦች መብት እንዳልተከበረ ያምናሉ፡፡ አቶ ገብሩ ‹‹ህወሓት ከጋርዮሽ አመራር ወደ አንድ ሰው ብቸኛ መሪነት›› በሚለው ፅሁፋቸው ብሔሮች በአካባቢያቸው ጉዳይ ፖለቲካዊ ስልጣን ኖሯቸው እንደማይወስኑና በአካባቢያቸው ኢኮኖሚያዊ ልማት ተጠቃሚ እንዳልሆኑ ያስረዳሉ፡፡  ለዚህም ይመስላል ከህወሓትና ከፌደራል መንግስት የሚወከሉ አካላት በክልል አስተዳደሮች ውስጥ ጣልቃ ገብ ተሳትፎ ያላቸው፡፡ በፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ በቁጥር 39 የተሰራጨው መረጃ እንዳመለከተው ‹‹ኦሮሚያ የምትተዳደረው በክልሉ ም/ቤት በተመረጡት አቶ አለማየሁ አቶምሳ ሳይሆን ከህወሓት በተመደቡት አቶ ገ/ተንሳይ ወ/ትንሳይ ነው፡፡›› ይኸው መረጃ አያይዞም ቀደም ሲልም ሰለሞን ጢሞ የተባሉ የህወሓት ሰው ኦሮሚያን ከመጋረጃ ጀርባ ሆነው ያስተዳድሯት እንደ ነበር አስታውሷል፡፡ የሌሎች ክልሎች ብሄረሰቦችም ራስን በራስ የማስተዳደር ዕድል እንደሌላቸው ይነገራል፡፡

በብሄር ብሄረሰቦች ቀን ብቻ በጭፈራ የሚታየውና በስርአቱ ተቺዎች ዘንድ ‹‹የብሔር ብሄረሰቦች መብት እስከ መጨፈር›› የሚል ስላቅ የሚገለፀው ‹‹እኩልነት›› በፖለቲካው መድረክ አይታይም፡፡ ይህ ሁኔታ ተጨማሪ የድህረ-ግንቦት 20 ኪሳራ ሆኗል፡፡  

ፍትሀዊ ያልሆነ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት መስፈን (corny capitalism)
የአቶ መለስ መንግስት በ21 አመት የስልጣን ቆይታው ሊያሳካ ካልቻላቸው መሰረታዊ የህዝብ ጥቅሞች መካከል ፍትሀዊ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት አለማረጋገጡ ዋንኛው ነው፡፡ መንግስት በኢኮኖሚ ውስጥ የሚያደርገው የበዛ ጣልቃ ገብነት፣ ኢትዮጵያውያን በኢኮኖሚው ውስጥ ፍትሀዊ ጥቅም እንዲያገኙ የሚያግዝ እንደሆነ ሹማምንቱ በተለያዩ መድረኮች ከመግለፅ አይታክቱም፡፡ መንግስትም የሚያንቀሳቅሳቸውን ግዙፍ ድርጅቶችም ከእጁ ለማውጣት አይፈልግም፡፡ የበታፈነ ደረጃ የተፈቀደው ‹‹የነፃ ገበያ ስርአት›› ሁሉንም የንግድ ህብረተሰብ ክፍል እኩል ተጠቃሚ አላደረገም፡፡
ኢህአዴግ ራሱ ያወጣውን ህግ ተላልፎ የፈለፈላቸው፣ በቢሊየን የሚቆጠር ካፒታል የሚያንቀሳቅሱትን የገዢው ፓርቲ ንብረት የሆኑ ኩባንያዎችን በማጠናከር እንዲሁም ከመንግስቱ ጋር ቅርበት ያላቸው ግለሰቦች የተለየ ጥቅም የሚያገኙበት ሁኔታ ፈጥሯል፡፡  የዘርፉ ባለሙያዎች ይህንን ስርአት ኮርኒ ካፒታሊዝም (crony capitalism) በሚል ይጠሩታል፡፡ ኮርኒ ካፒታሊዝም የሀገሪቱ ሀብት ከስርአቱ ጋር ስምም ወደ ሆኑ ጥቂት ባለፀጋ ግለሰቦች እንዲፈስ የሚያደርግ ስርአት ነው፡፡ ኢትዮጵያ እየገነባች ያለችው ኢኮኖሚም ሆነ ቁሳዊ ልማት ጥቂቶችን ብቻ ተጠቃሚ ማድረጉ የድህረ-ግንቦት 20 ኪሳራዎች መሀከል የሚጠቀስ ከመሆኑም በላይ አስተዳደሩ ለተዘፈቀበት ሙስና ምቹ ሁኔታን የፈጠረ ነው፡፡ 

የሙስና መስፋፋት
ፕሮፌሰር ሰይድ ሐሰን በኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ትንታኔዎችን በማቅረብ ይታወቃሉ፡፡ እኚህ ምሁር ሙስና ኢትዮጵያ ውስጥ ስር የሰደደ ስርአት እንደሆነ ያስረዳሉ፡፡ በቅርቡ ‹‹ሙስና ኡ!  ኡ! እሪ! እሪ!›› በሚል ርዕስ ባቀረቡት ጽሁፍ ዓለም ባንክ ባደረገው ጥናት ኢትዮጵያ ውስጥ ሙስና አደገኛ ስርአነት ወደ መሆን መሸጋገሩን ያብራራሉ፡፡ ፍርድ ቤት፣ ፖሊስ፣ ጉምሩክና የገቢዎች ባለስልጣን፣ የወረዳ አስተዳደርና ማዘጋጃ ቤቶች ሙስና በእጅጉ የተንሰራፋባቸው ናቸው፡፡
የህወሓት አንጋፋ መሪ የነበሩት አቶ ስብሀት ነጋም ሙስና በሀገሪቱ አደገኛ ደረጃ ላይ መገኘቱ እንዳሳሰባቸው በይፋ መግለፃቸውና አቶ መለስም የመንግስት አካላትም በአደገኛ ሙስና መዘፈቃቸውን ማመናቸው ሙስና ከድህረ-ግንቦት 20 ኪሳራዎች መሀከል የሚጠቀስ ሆኗል፡፡                             

                                                          
ስርአቱን የሚተቹ አካላትን ማፈን
የህወሓት/ኢህአዴግ ታጋዮች ደርግን ከተዋጉበት ምክንያት አንዱ የደርግ ተቃውሞን የማፈን እርማጃ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ታጋዮቹ ደርግን አስወግደው ሌላ ‹‹ደርግ›› መተካታቸውን የሚያስረዱ በርካታ ማሳያዎች አሉ፡፡ ስርአቱን የሚተቹ አካላትን የአቶ መለስ መንግስት ማሰር የጀመረው በቅርቡ ባይሆንም፣ በአረብ ሀገራት የተከሰተውን መነሳሳት ተከትሎ የተቃውሞ ፖለቲካ አመራሮችንና ጋዜጠኞችን ‹‹በሽብር›› ሰበብ ቃሊቲ አውርዷል፡፡ በይፋም ሆነ በኢመደበኛ ወጎች መንግስትን መተቸት የሚያስጠይቅበት ደረጃ በመድረስ ላይ ይገኛል፡፡ 

መንግስት ስርአቱን የሚተቹ አካላትን ለማሸማቀቅ የሚጠቀምባቸው መንገዶች ሰላማዊ ትግልን የሚያደናቅፉ ከመሆናቸውም በላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ብሶትና ተቃውሞ ወደ ግብታዊ አብዮት የመምራት ውጤትም ሊያስከትል ይችላል፡፡ በሰላማዊ ትግል ተስፋ ቆርጠው መሳሪያ ያነሱ ቡድኖችን ያበራከተው ይህ አካሄድ፣ ከኢህአዴግ ጋር ልዩነት ያላቸው የፖለቲካ ቡድኖች በሰላማዊ ትግል እንዲሳተፉ አለማበረታታቱ የአቶ መለስ ስርአት የድህረ-ግንቦት 20 ክስረት አንድ አካል ነው፡፡      

ነፃ የሲቪክ ማህበራት አለመጠናከራቸው
ነፃ ማህበራት በአንድ ሀገር ላይ ዴሞክራሲ እንዲያብብ ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታሉ፡፡ሚካኤል ባራቶን (Michael Bratton) ‹‹CIVIL SOCIETY AND POLITICAL TRANSITION IN AFRICA›› በሚል ፅሁፋቸው ከቀዝቃዛው ጦርነት መጠናቀቅ በኋላ ነፃ ማህበራት በዴሞክራሲ ግንባታ ያላቸው ሚና እየተጠናከረ እንደመጣ ያስረዳሉ፡፡ አያይዘውም ነፃ ማህበራት ይህን አበርክቷቸውን እንዲወጡ የመንግስትን ኃይል የሚዘውሩ አካላት ፈቃደኝነት አስፈላጊ መሆኑን አበክረው ይገልፃሉ፡፡ የነፃ ማህበራት አበርክቶ በኢትዮጵያ ከመዳከም አልፎ የተዳፈነ ይመስላል፡፡

ኢህአዴግ ከ1997 በፊት በአንፃራዊ መለኪያ ንቁ ተሳትፎ የነበራቸውን ማህበራት፣ ከድህረ 97 በኋላ ነፃነታቸውን የሚጋፋና ህልውናቸውን የሚፈታተን ህግ በማፅደቅ አልፈስፍሷቸዋል፡፡ የማህበራቱን ነፃነት በመጋፋት የፓርቲውን ፖለቲካ የሚያራምዱ ግለሰቦችን በአመራር ደረጃ በማስረግ ጭምር ተሳትፏቸውን አዳፍኗል፡፡ 

መንግስት ነፃ ማህበራት የህዝቡን ዴሞክራሲያዊ ባህልና ግንዛቤ በማዳበር የሚያበረከረቱትን አስተዋፅኦ ከማበረታታት ይልቅ፣ ከዚምባቡዌ፣ ሲንጋፖርና ሩሲያ የተወሰዱ አደገኛ ልምዶችን የቃረመ አደገኛ የበጎ አድራጎትና የሲቪክ ድርጅቶች አዋጅ አፅድቋል፡፡ በዚህ ህግ ምክንያት የመስራት አቅማቸው የተሸመደመደ እና ወደ ሌላ ዘርፍ ስራቸውን የቀየሩ ማህበራት ቁጥር በርካታ ነው፡፡

ይህ ማህበራትን የማዳከምና ነፃነታቸውን የማሳጣት ስትራቴጂ በቀጥታ የህዝቡን የነፃነት የመደራጀት መብት የሚጋፋ ከመሆኑም በላይ ዴሞክራሲ የማይዋጥላቸው አምባገነን መንግስታት ተግባር ነው፡፡ ከዚህ አንፃር 21 አመታትን በምኒሊክ ቤተመንግስት ያሳለፈው የአቶ መለስ መንግስት ነፃ ማህበራትን በስልት ማዳከሙ የድህረ-ግንቦት 20 ኪሳራዎች መካከል ይጠቀሳል፡፡ 
          
የነፃ ፕሬስስ ሀሳብን የመግለፅ መብት አለመከበሩ
 ኢህአዴግ ወደ ስልጣን እንደወጣ ከወሰዳቸው አበረታች እርምጃዎች ውስጥ የፕሬስና ሀሳብን የመግለፅ መብትን “መፍቀዱ” ነው፡፡ መንግስት ይህ መብት ህገመንግስታዊ እንዲሆን ቢያደርግም በተግባር ግን አፋኝ እርምጃዎችን ከጅምሩ መውሰዱ ነፃ ፕሬስ እንዳይዳብር እንቅፋት ሆኗል፡፡ 

የአንድ ዴሞክራሲያዊ ማህበረሰብ መገለጫ የሆነው የፕሬስና ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በኢትዮጵያ አደጋ ላይ ወድቋል፡፡ መንግስት ላይ ትችት የሚያቀርቡ ጋዜጠኞች እና ሀሳባቸውን በይፋ የሚገልፁ ፖለቲከኞች መታሰር፤ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የአደባባይ ምሁራንን አርቋል፡፡ 

ሀሳባቸው የሚገልፁ ጋዜጠኞችና ተቺዎች ከእስር ጋር ተፋጠው ለመስራት ተገደዋል፡፡ ኢህአዴግ ያወጣቸው የፕሬስና የፀረ ሽብር አዋጆች ኢትዮጵያውያን ሀሳባቸውን በፕሬስ ውጤቶች እንዳይገልፁ የሚጠፍር ከመሆኑም በላይ በአንዳንድ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ መረጃዎችን እንዳያገኙ አግዷል፡፡ በተለይም ኢህአዴግ በቅርቡ በብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት በኩል ቅድመ ምርመራን ለመጀመር እንቅስቃሴ መጀመሩ ከላይ ያየናቸው የድህረ ግንቦት 20 ኪሳራዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በሀገሪቱ የመድብለ ፓርቲ ስርዓቱ እንዲከስም አስተዋፅኦ አድርገዋል፡፡ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንዲያብብ በሚረዱት የፕሬስ ውጤቶች አለማደግ ብሎም መመናመን የድህረ ግንቦት 20 ኪሳራ ሌላው ማሳያ ነው፡፡

ሀገሪቱ በአንድ ጠቅላይ አምባገነን መሪ ስር መውደቋ
ጠቅላይ አምባገነንነት በአጭር ጊዜ የሚገነባ ሳይሆን ዴሞክራሲያዊ ስርአትን ከመገንባት የበለጠ ጊዜና ወጪ ይጠይቃል፡፡ ይህን አምባገነናዊ ስርአት ለመገንባት መንግስት በህዝቡ ሁሉን አቀፍ የህይወት ፈርጅ ውስጥ ቁጥጥር ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ በትምህርት ፣ በኢኮኖሚ ፣ ማህበራዊ፣ በባህልና ኪነጥበብ ውስጥ ፖለቲካዊ ቁጥጥር በማድረግ እንዲሁም ፖለቲካዊ እንነታቸውን በማጥመቅ አቶ መለስ ጠቅላይ አምባገነን መሆንን መርጠዋል፡፡ 

በ2002 ምርጫ 99.6 በመቶ በሆነ ውጤት ፓርላማውን የተቆጣጠረው የአቶ መለስ መንግስት አውራ ፓርቲ መሆኑን በመግለጽ የመድብለ ፓርቲ ስርዓት ተንኮታኩቶ ጠቅላይ አምባገነን ስርዓት መደላደሉን አብስሯል፡፡ ግንቦት 20 አቶ መለስን በኢትዮጵያ አንግሷል፡፡ በሀገሪቱ ላይ ብቸኛው አድራጊና ፈጣሪ አቶ መለስ ናቸው፡፡ ሙገሳቸውም ሆነ ወቀሳቸው ድጋፋቸውም ሆነ ተቃውሟቸው እንደ እግዜር ቃል ይታያል፡፡ ለግንቦት ሃያ የተከፈለው መስዋዕትነት አቶ መለስን የሀገሪቱን ቁንጮ ከማድረግ ያለፈ ውጤት ያመጣ አይመስልም፡፡ የድህረ ግንቦት 20 ኪሳራዎች የኢትዮጵያ ህዝብ ከህወሓት/ኢህአዴግ ነፃ የሚወጣውን የድል ቀን እንዲጠብቅ ሳያስገድዱት የሚቀር አይመስልም፡፡

ያለ ጨረታ ! ለነ ሌንጮ ለታ ? እንግዳ/ ከኦስሎ

May 29th, 2012 

’’የመለስና የሌንጮ የመግባባትና የስምምነታቸው መሰረት ከቶ ምን ሊሆን ይችላል? የድርድራቸው ማእከልና ያግባባቸው የጋራ ፍላጎት ምንድነው? አልገባኝም። መረጃም የለኝም። ማለት የሚቻል ነገር ግን ይኖራል። ሌንጮና ዲማ የዋህ ፖለቲከኞች አይደሉም። ’’የአበሻን ተንኮል አሳምረው የሚረዱ ናቸው ’’። ያግባባቸው አንድ የጋራ የሆነ ማእከላዊ ነጥብ ግን የግድ ይኖራል። ’’ተስፋዬ ገ/ አብ
መቸም ! ተስፋየ በጥሩ ብዕሩ እያዋዛ በሚለቃቸው መጣጥፎቹ ውስጥ በየመስመሮቹ መሃል ወሸቅ የሚያደርጋቸው አፋጀሽኝ ቃላቶቹ አሁንም አልለቀቁትም ፡፡ ’’ ያደቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም ’’ ሆነና አድባር ስትከፍትለ’ት በሚለቃቸው መጣጥፎቹ መስመሮች ውስጥ – በአብዛኛው በአማራና – ኦሮሞ ህዝብ ውስጥ ንትርክ እንዲቀጥል ሲፈልግ ፣ ዛሬ ደግሞ ሴሜቲኮችና ኩሺትኮች በሚላቸው ኢትዮጵያውያን መሃል ሽኩቻው እንዳያባራ – የአበሻን – ተንኮል አሳምረው ሌንጮና ዲማ ያውቁታል በሚል ጥርጣሬው እንዲጠጥር በር ይከፍታል፡፡ ይህች አንጓ አስታራቂ ናት ወይስ ቀጣይ ጥርጣሬን ጫሪ ? ደራሲ ተስፋዬ ?
ካልተሳሳትኩ ተስፋዬ በአንድ ጽሁፉ ላይ ከኦቦ ሌንጮ ለታ ጋር ጥብቅ የሆነ ወዳጅነት እንደነበረው ፣ ኔዘርላንድ በአንድ ወቅት አብረው እንደከረሙና ፣ በቀጣይነትም ኦቦ ሌንጮ ከሚገኙበት ስካንዲኔቪያዋ አገር ኦስሎ መጥቶ እንደሚጎበኛቸው በጽሁፉ አስነብቦን ነበር ፡፡ ይህ የሚያሳየው የወዳጅነታቸውን ጥብቅ ትሥሥር ሲሆን ፣ የቤተ መንግሥቷን ሹክሹክታ እንዳለ ሙሉ በሙሉ ባይነግሩትም በገደምዳሜ ግን ቅርፊት ቅርፊቷን እንዴት እንዳልነገሩት አልገባኝም፡፡ የድርድራቸው ማዕከልና ያግባባቸው የጋራ ፍላጎት ምንድነው ? አልገባኝም ፡፡ መረጃም የለኝም ላልከው ግርታ ለፈጠረብህ ድርድር ፣ ቅርበት አለኝ እስካልከን ድረስ ኦስሎና አምስተርዳም ፍላጎቱ እስካለኽ ድረስ ብዙም ስለማይራራቁ ዉነቱን አውጥተኽ ታሳየን ነበር ፡፡ ኦቦ ሌንጮ ለታ ደግሞ ለቡርቃ ዝምታህ ውለታ ሲሉ እጀ- ንፉግ የሚሆኑብህም አይመስለኝም፡፡
ደራሲና ጋዜጠኛ ተስፋዬ ! መቸም እንደቅርበትህም ሆነ እንደጋዜጠኝነትህ ፥ ኦቦ ሌንጮም ሆኑ ፣ ዶክተር ዲማ ነገዎ ኦነግ ውስጥ እንደሌሉ ሳትሰማ የቀረኽ አይመስለኝም ፡፡ ቢያንስ ፊርማና ወረቀቱን አይተናል ብለን ባንመሰክርም – ከኦነግ ተባረዋል ከተባለ ዘመን ባጅቷል፡፡ የቤተ መንግስቱ ሹክሹክታ ውነት ከሆነ ፣ አቶ መለስ ኦህዴድን የሚሸጡት ለቀድሞዎቹ የኦነግ አባሎች እንጂ አስመራ ለሚገኘው ኦነግ አይደለም ማለት ነው ፡፡ እሱም ላይ ቢሆን ገና ኦነግ በሁለት ሰዎች መሪነት የሚነቃነቅ እስከሆነ ድረስ ኦቦ ሌንጮ ለታ እስከአሁንም ድረስ ከነኝህ ሁለት የኦነግ ድርጅቶች ጋር የትሥስር አንጓ እንደሌላቸው ነው የሚነገረው፡፡
የፍትህ ጋዜጣ ባለቤት ተመስገን ደሳለኝ – ’’ህዝብና የተቃዋሚዎች ፓርቲዎች መንታ መንገድ ’’ በሚል ርዕስ በጻፋው መጣጥፍ ላይ እስከዛሬ አገሪቱ በተቃዋሚ ድርጅቶች ፥ ወይም የድርጅቶች መሪዎች ድክመት ላይ ፣ ነቅሶ ያወጣቸውን ነጥቦች ፣በፕሮፌሰር መስፍን ቀጣይነት አስተያየት ቢታከልባትም ፣ አዎ ልክ ነው ወይም የለም ሃሰት ነው የሚል ቀጣይ አስተያየት እስከአሁን በሌሎች ጸሃፊዎች ዙርያም ሆነ የድርጅት ደጋፊዎች ዙርያ አላነበብኩም፡፡ ተመስገን እንዲህ ይለናል ፡፡
’’በነገራችን ላይ ደጋግሜ እንደፃፍኩት ምክንያታቸው ምንም ይሁን ምን የተቃውሞውን ጎራ ለመምራት ወደ አደባባይ የወጡት ፖለቲከኞች በዛጎላቸው ከተሸሸጉት ‹‹ሌሎች ኢትዮጵያውያን›› የበለጠ ‹‹አክብሮት›› ይገባቸዋል። (ይሁንና ግን ሌሎች ኢትዮጵያውያኖች ማለት ምን ማለት ይሆን ? እዚህ ውስጥ የሚመደቡትስ እነማን ይሆኑ ? ከኢትዮጵያ ሌላ ትርፍ አገር ያላቸው ናቸው ወይስ የስርአቱ ምንደኞች ?) ብቻ ከዚህ ባለፈ ክንብንባቸውን ገልጠው ፊታቸውን ያስመቱ ፖለቲከኞቻችን ለእስከአሁኑ አበርክቶታቸው ዋጋ ሊያገኙ ይገባል። በዚህ በኩል ችግር የለም፡፡ ችግር የሚኖረው ያ የአክብሮት ዋጋ በየአመቱ እየተመነዘረ ‹‹መሪ›› በሚል ስም ዛሬም በስልጣናችን እንደተቀመጥን መቀጠል አለብን ሲሉ ነው። ይሄ ወደድናቸውም ጠላናቸውም ትልቅ ችግር ፈጣሪ ነው፡፡ ምክንያቱም አሁን ኢትዮጵያ ያለችበት አጣብቂኝ ከጥቆማና ከአጋላጭ ባለፈ ‹‹አንቂና አደራጅ›› መሪ የሚፈልግበት ወሳኝ ጊዜ ላይ ነውና።’’ ሰረዝ የኔ፡፡
በርግጥ እንደጋዜጠኝነትህ – ኦስሎ በነ – ኤፍሬም ይስሃቅ እንደተጎበኘች ያሰፈርከው ጽሁፍ ትክክል ነው ፡፡ ኤፍሬም ይስሃቅ ኦስሎን ከግር እስከራሷ እያሉ ከርመውባታል፡፡ በቅርቡም እንዳልከው ዶክተር ዲማም ጎብኝተዋታል፡፡ ከኦቦ ሌንጮም ጋር መክረዋል ፡፡ የቤተ መንግሥቱ ሹክሹክታ ለአቶ መለስ ሊሠራ የሚችለው ፣ ኦቦ ሌንጮ ከነሙሉ ክብራቸውና ዝናቸው የታገሉበትን ኦነግ የተባለውን የቀድሞ ድርጅታቸውን ከአስመራ አስነቅለው እንደ ሰባ ሰገል ሰዎች ፊንፊኔ ላይ ለአቶ መለስ ቢያስረክቡ እንጂ እሳቸው ዘወትር ኦስሎ ላይ በጀርባቸው አዝለዋት የሚሄዷትን ቦርሳቸውን ለመለስ ቢያስረክቡት ደስተኛ አይሆንም ፡፡
ችግሩ ምን ላይ መሰለኽ ! ደራሲና ጋዜጠኛ ተስፋዬ ! የፍትሁ ተመስገን እንዳለው ! ችግር የሚኖረው ያ! የአክብሮት ዋጋ በየአመቱ ተመንዝሮ ‹‹መሪ›› የሚለው ቃል ወርዶ ፥ ወርዶ በወጣቱ የኦነግ ደጋፊዎች ዘንድ አልቋልና ነው፡፡ ከዚህ በላይ ምንም የሚጨመር ነገር የለውም ፡፡ የችግሩ ምንጮችን ፣ የፈለግኽውን ሊፕስቲክ ቀባብተህ ፣ የጸጉር ስታይላቸውን ለውጠኽ ፣ አርተፊሻል ጸጉር ጭነኽ ምንይልክ ቤተ መንግሥት ብታቀርባቸው ፣ የችግሩ መፍትሄ አይሆኑም፡፡
በርግጥ ኦቦ ሌንጮ በርዮተ ዓለም ቅርበትና የአማራን ህዝብ በመጥላት ለአቶ መለስ ይቀርቧቸዋል ፡፡ የኢትዮጵያን አንድነት እያለ እስከአሁን የሚዘምረው ኃይል ዘወትር ለኦቦ ሌንጮ ራስ ምታታቸው ነው ፡፡ የሚሰማ’ቸው የሙዚቃ ቃና ’’ የአማራ በላይነት ነው ’’ ፡፡ በዚህ ችግር የተተበተበን ሰው አቶ መለስ ቤተ መንግሥት ወስዶ ቢያስጠጋቸውና ሁለቱንም የሚያስደስታቸውን የሰባራ ሸክላ ሙዚቃ አብሮ ከማድመጥ ሌላ የሚወጣ ምንም አዲስ ነገር የለም፡፡ ከንግዲህ ኦቦ ሌንጮ የኦሮሞን ህዝብ ከወያኔ ጋር ያስታርቃሉ ብሎ መገመት የዋህነት ነው ፡፡
እድሚያቸው ከጡረታ ስላለፈ ፣ የስካንዲኔቪያዋ ክረምትም ብርቱ ስለሆነች አጥንታቸው ድረስ ዘልቃ ስላንዘፈዘፈቻቸው ጸሃይቱን ፍለጋ ፊንፊኔ ቤተመንግሥት ቢያቀኑ አይፈረድባቸውም ፡፡ እንደ ሹክሹክታህ መሠረት ከሆነ ፡፡ ከዚህ በተረፈ ግን! የአቶ ሌንጮ መስራች መሪ የሚለው ቃል በየአመቱ እየተመነዘረ ፣ቁልቁል ስለወረደ ከኦሮሞ ወገኖቻቸው ክብሩ ዝቅ እንዳለባቸው ነው እየታየ ያለው፡፡ ኦነግን ይዞ ገብቶ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴርነትን ብለህ የተመኘኽላቸውን በጎ ምኞት እንዲህ በቀላሉ ይሳካላቸዋል ብዬ አላምንም፡፡ ህልም ከአለምን ምናልባት ለኦቦ ሌንጮ ጥሩ ብንመኝላቸው ፣ ለኦሮሞ ህዝብ ’’ መያድ ’’ Ngo ላቋቁምለት ብለው ቢያቀኑ ነው የሚበጀው ፡፡ እሱም ቢሆን ከወያኔ የስለላ መረብ ውስጥ ነጻ አይሆንም፡፡
ደራሲ ተስፋዬ ይልቅስ በቀልድ እያዋዛህ የምትነግረን ምጸታዊ ጆክህ እንዳለች ሆና ! የጥንት የጠዋቱን ሌንጮ ለታ አሁንም በኦነግ ላይ ኃይል አላቸው ብለህ ማመንህ ትንሽ ከመረጃ ውጭ ያስወጣህ ይመስለኛል፡፡ ኦህዴድ በጨረታ ለሌንጮ ለታ ሊሸጥ ነው ያልከን ቀልድ ግን እጅግ ከምር ነው ያሳቀችኝ ፡፡ ድሮ አጎዛ ሰፈር አካባቢ ’’ ነጻ ከብት ’’ የሚባል ሰፈር ነበር፡፡ የጠፉ ከብቶች የሚገኙበት ፡፡ ዛሬ አቶ መለስ አጋሰሶቻቸውን በጨረታ ነው ? ያለ ጨረታ የሚሸጡት ? የጋማዎቹን መንጋጋ አፍ እያስከፈቱ ጥርሳቸውን መሽረፋቸውንና አለመሽረፋቸውን ሳያዩ መቸም አቶ ሌንጮ አይገዟቸውም፡፡ ለመሆኑ ኦህዴድን አቶ መለስ ስንት ጊዜ ነው ገበያ የሚያወጧቸው ? እያልከን ነው በብዕርህ ? እባክህ ስለዳንሰኛው ባጫ ደበሌ አንድ አስቂኝ ቀልድህን ጻፍልን፡፡ በባጫ ብንላጥ ይሻላል ነው የሚሉት የሸገር ልጆች ፡፡
“Meles has to sell his Horse. Lencho wants to buy it.
¨Lencho: Is this horse faithful ?
Meles: Yes, I have sold it 3 times earlier also. It is so faithful, everytime it returned back to me.

Tuesday, 29 May 2012

መታወቂያችን አማራ ስለሚል ተመርጠን ታሰርን ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ



ከሚዛን ተፈሪ ወደ ዲማ ለሥራ ስንሄድ ኬላ ላይ መታወቂያ እየተመለከቱ ሲፈትሹ መታወቂያችን ብሔር በሚለው ቦታ ላይ አማራ ስለሚል መርጠው እስር ቤት ከተቱን፡፡ ሲሉ ለዝግጅት ክፍላችን ገለጹ፡፡ እነዚህ እስር ቤት ቆይተን ተፈታን የሚሉ ሰዎች እንደሚሉትዲማ በጉልበትህ ሠርተህ የምታገኘው ገንዘብ አለ የሚል መረጃ ስለደረሰን ሥራ ፍለጋ በመጓዝ ላይ ነበርን፡፡ ሚዛን ተፈሪ ስንደርስ ለፍተሻ ከመኪና ውረዱ አሉን፡፡ ወርደን ለፍተሻ ዝግጁ ሆንን፡፡ መታወቂያቸው ኦሮሞ፣ ትግሬ፣ ጋምቤላ፣ አፋር የሚል እንዲሳፈሩ ተፈቀደላቸው፡፡ አማራ የሚለውን 16 ሰዎች ሰብስበው እናንተ እንድታልፉ አይፈቀድም ብለው ሚዛን ተፈሪ ፖሊስ መምሪያ ወሰዱን፡፡ ከዚያም እስር ቤት አስገቡን፡፡ ከዚያም ሌላ 20 አማርኛ ተናጋሪዎች ተይዘው ታሰሩ፡፡ ምን አጠፋን? ወንጀል ሳንፈጽም ለምን ታስሩናላችሁ? ብለን ስንጠይቃቸው ወደዚያ ከሄዳችሁ አደጋ ይደርስባችኋል፡፡ ወደዚያ አማራ ሄዶ እንዲሰራ አይፈቀድም ብለውናል፡፡ሲሉ ቅሬታቸውን ይገልፃሉ፡፡ትኬት ቆርጣችሁ ወደ አማራ ክልል ተመለሱ ብለው ከሦስት ቀን በኋላ የተወሰንን ሰዎችን ለቀቁን፡፡ ብዙዎቹ አሁንም በእስር ላይ ናቸው፡፡ እኛ ወደ ትውልድ መንደራችን ለመሄድ ገንዘባችንን ጨርሰናል፡፡ ብንሄድም ቦታ ስለሌለን ማረፊያ የለንም፡፡ ለዚህ ነው የቀን ሥራ ሠርተንም ጉርጓድ ቆፍረንም ህይወታችንን እንቀይራለን ብለን ጉዞ ጀምረን የነበረው፡፡ ሆኖም ግን አማራ በመሆናችን ተዘዋውረን ሠርተን እንዳንበላ ተደርገናል፡፡ሲሉ አማረዋል፡፡ በመቀጠልም ሲናገሩእኛ ታስረን መፈታት ችለናል፡፡ ዛሬም ሥራ ፍለጋ ወደ ምንፈልግበት እንድንሄድና በነፃነት ከቦታ ቦታ እንድንቀሳቀስ አልተፈቀደልንም፡፡ ህጋዊን መንገድ ትተው በእግራቸው ጫካ ለጫካ ጉዞ የጀመሩ በርካታ ሰዎች ተገላዋል፡፡ በአውሬ ተበልተዋል፡፡ ሲገደሉም በአውሬ ሲበሉም የአካባቢው ኃላፊዎች ምንም የሚሰማቸው ፀፀት የለም፡፡ ህገ ወጦች ናቸው፡፡ እንኳን ሞቱ እንኳን ተበሉ እያሉ ሲሳለቁ ይሰማል፡፡ካሉ በኋላየሚመለከተው የመንግስት አካል ጉዳዩን በጥሞና ተመልክቶ ውሳኔ ይሰጠን፡፡ ተዘዋውረን የመኖርና ሠርቶ የመብላት መብታችን እንዲከበርልን አሳውቁልን፡፡በማለት ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡ የሚዛን ተፈሪ ፖሊስ መምሪያ በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጥበት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡