ነሀሴ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የብአዴን አባል የሆኑ ታማኝ የኢሳት ምንጮች እንደገለጡት ሰሞኑን የብአዴን የኮር አባላት ለሁለተኛ ጊዜ በአቶ በረከት መሪነት በባህርዳር ከተማ ስብሰባ አድርገዋል።
የአማራ
ክልል የወጣቶች ፕሬዚዳንት የሆነው ወጣት ዘመነ ካሴ ከአገር መውጣቱና ለኢሳት ቃለምልልስ መስጠቱ፣ በክልሉ
የተነሳው የሙስሊሞች እንቅስቃሴ ከአቶ መለስ ዜናዊ የጤንነት ሁኔታ ጋር ተደማምሮ በብአዴን የኮር አባላት ላይ
ከፍተኛ ፍርሀት እና አለመረጋጋት መፍጠሩ የስብሰባው ዋነኛ የመነጋገሪያ አጀንዳዎች ነበሩ።
የብአዴን ዋና
ዋና አመራሮች በተገኙበት የኮር አባላቱ ያሳለፍነውን ጉዞ እንገምግም፣ ለወደፊቱም የማስተካከያ እርምጃ እንውሰድ
የሚል ሀሳብ ሰንዝረዋል። የወጣት ዘመነ ካሴ ከአገር መውጣት ብአዴን በወጣቱ ዙሪያ በቂ ስራ አለመስራቱን፣ የክልሉ
ወጣት ልብ ከድርጅቱ ጋር ሳይሆን ከጸረ ሰላም ሀይሎች ጋር መሆኑን ያመለካተ በመሆኑ ድርጅቱ፣ የወጣቱን ልብ መልሶ
ለመያዝ መንቀሳቀስ እንዳለበት አባላቱ መተማመን ላይ ደርሰዋል።