- ሌሎች 50 ኩባንያዎች በተለያዩ ዘርፎች ኢንቨስት ለማድረግ ጠይቀዋል
- እስራኤል በአፍሪካ ኅብረት መድረክ አለማግኘቷ ቅሬታ ፈጥሮባታል

በታደሰ ገብረማርያም
የእስራኤል ኤሌክትሪክ ኩባንያ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽንን ማኔጅመንት ተረክቦ ለሦስት ዓመታት ያህል ለመምራት የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት አጠናቅቋል፡፡
ሌሎች ወደ 50 የሚጠጉ የእስራኤል ልዩ ልዩ ኩባንያዎች ኢትዮጵያ ውስጥ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ወይም ኢንቨስት ለማድረግ መጠየቃቸውን በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር በላይነሽ ዘቫዲያ ገለጹ፡፡
የእስራኤል ኤሌክትሪክ ኩባንያ 20 መሐንዲሶች በቅርቡ ወደ አዲስ አበባ መጥተው ሥራውን ይጀምራሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ አምባሳደሯ አስረድተዋል፡፡ የእስራኤል የኤሌክትሪክ ኩባንያ የኮርፖሬሽኑን ማኔጅመንት ለሦስት ዓመታት ለመምራት የሚያስችለውን ሥራ ያገኘው ለዚህ ተብሎ የወጣውን ዓለም አቀፍ ጨረታ በማሸነፉ መሆኑ ታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ኮርፖሬሽን በሁለት እንዲከፈል የተወሰነ ሲሆን፣ የኃይል ሽያጭ፣ የደንበኞች አገልግሎትና አስትዳደራዊ ጉዳዮች ለእስራኤሉ ኩባንያ ይሰጣሉ፡፡ ሁለተኛው ኃይል የማመንጨትና የማስፋፋት ሥራዎች በኮርፖሬሽኑ አማካይነት ይከናወናል፡፡ ከዚህ ቀደም መንግሥት የቀድሞውን ቴሌኮሙኒኬሽን ኮርፖሬሽን ማኔጅመንት ለፈረንሳዩ ፍራንስ ቴሌኮም መስጠቱ ይታወሳል፡፡
ሌሎቹ 50 ኩባንያዎች ለመሰማራት የሚፈልጉት በሶላር ኢነርጂ፣ በውኃ ቴክኖሎጂ፣ በመስኖ ልማት፣ በጤናና በሌሎችም በርካታ የልማት ዘርፎች መሆኑን አምባሳደሯ አስረድተው ከኩባንያዎቹ መካከል የተሟላ አቅም፣ ብቃትና የአሠራር ጥራት ያላቸውን ለይቶ ለማወቅ የሚያስችል የማጣራት ሥራ ኤምባሲው በማከናወን ላይ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡