Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Sunday, 7 October 2012

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ የነበሩት አቶ ከፍያለው አዘዘ ኮበለሉ

በውድነህ ዘነበ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ የነበሩት አቶ ከፍያለው አዘዘ አሜሪካ ሄደው ሳይመለሱ መቅረታቸውን ምንጮች ገለጹ፡፡
አቶ ከፍያለው ከወራት በፊት ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ ኔትወርክ በመዘርጋት ሥራዎች በአግባቡ እንዲካሄድ አድርገዋል በሚል ከምክትል ከንቲባነት ተነስተው የከንቲባ ኩማ ደመቅሳ የውጭ ግንኙነት አማካሪ ሆነው ተሾመው ነበር፡፡ ምንጮች እንደሚገልጹት፣ አቶ ከፍያለው ከነበራቸው ኃላፊነት ዝቅ በመደረጋቸው ይበሳጩ ነበር፡፡

አቶ ከፍያለው ምክትል ከንቲባ እያሉ የአዲስ አበባ መገናኛ ብዙኅን ኤጀንሲ ሊገነባ ላቀደው አዲስ የቴሌቪዥን ጣቢያ ዕቃዎችን ለመምረጥ ከባልደረቦቻቸው ጋር አሜሪካ ተጉዘው ነበር፡፡ በወቅቱ አቶ ከፍያለውና የሚመሩት ልዑክ ከ15 ቀናት የአሜሪካ ቆይታ በኋላ ወደ አገሩ ሲመለስ፣ የመገናኛ ብዙኅን ኤጀንሲ አንድ ቴክኒሻን ሳትመለስ ቀርታለች፡፡ አቶ ከፍያለው ከአሜሪካ ከተመለሱ ከጥቂት ወራት ቆይታ በኋላ ከምክትል ከንቲባነታቸው ተነስተዋል፡፡

ከዚህ ጊዜ በኋላ አቶ ከፍያለው ከደረጃቸው ዝቅ መደረጋቸው ሲያብሰለስላቸው በነበረበት ወቅት ድንገት የመገናኛ ብዙኅን ኤጀንሲ ለሚገነባው የቴሌቪዥን ጣቢያ ተጨማሪ ዕቃ ለመግዛት ለዱባይ ጉዞ አዘጋጀ፡፡ አቶ ከፍያለው ወደ ዱባይ የሚጓዘው ቡድን አካል ሆነው ዱባይ የተጓዙ ሲሆን፣ ቡድኑ ሥራውን አጠናቆ አዲስ አበባ ሲመለስ አቶ ከፍያለው በዱባይ አድርገው አሜሪካ ገብተዋል፡፡

አቶ ከፍያለው አሜሪካ መቅረታቸውን የተረዳው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አቶ ከፍያለው ሲገለገሉበት የቆዩትን ተሽከርካሪ ተረክቧል፡፡ ምንጮች እንደገለጹት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አባተ ስጦታው የአቶ ከፍያለው ሾፌር የሆኑትን አቶ ደምስ አሰፋን በጉዳዩ ዙርያ ማነጋገራቸው ተሰምቷል፡፡ ‹‹ከፍያለው ሲሄድ ለምን አልተናገርክም?›› ሲሉ አቶ አባተ ለአቶ ደምስ ጥያቄ ማቅረባቸውን ምንጮች ተናግረዋል፡፡

የኤርፖርቶች ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚና ሰባት ኃላፊዎች ከአገር እንዳይወጡ ታገዱ

-    ቃላቸውን ሰጥተው በ10 ሺሕ ብር ዋስ ተለቀዋል
-    በተርሚናል ውስጥ ያሉ ሱቆች ጨረታ ጊዜ ማለፉ እያነጋገረ ነው

በታምሩ ጽጌ
ከዓመታት በፊት ወጥቶ ከነበረ ጨረታ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ዓለሙና ሌሎች ሰባት የድርጅቱ ከፍተኛ ኃላፊዎች ከአገር እንዳይወጡ መታገዳቸውን ምንጮች ገለጹ፡፡ ኃላፊዎቹ ከአገር እንዳይወጡ የታገዱት የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ለደኅንነት፣ ኢሚግሬሽንና ስደተኞች ባለሥልጣን የኢሚግሬሽንና ዜግነት ጉዳይ ዋና መምርያ መስከረም 4 ቀን 2005 ዓ.ም. ደብዳቤ በመጻፉ ነው፡፡ መምርያው ደግሞ ለቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ቅርንጫፍ መሥሪያ ቤቱ መስከረም 8 ቀን 2005 ዓ.ም. ባስተላለፈው ትዕዛዝ መሠረት መታገዳቸውን ምንጮች አረጋግጠዋል

እግድ እንደተጣለባቸው ምንም መረጃ ያልነበራቸው የኢትዮጵያ ኤርፖርቶች ድርጅት ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሽፈራው ዓለሙና የቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ሥራ አስኪያጅ አቶ ኃይላይ ገብረፃዲቅ፣ ከመስከረም 22 ቀን ጀምሮ ለአራት ቀናት በዱባይ ይካሄድ በነበረው ዓለም አቀፍ ስብሰባ ላይ ለመገኘት መስከረም 21 ቀን 2004 ዓ.ም. ለመሄድ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ፣ ከአገር መውጣት እንደማይችሉ ተነግሯቸው መመለሳቸውንና አብረዋቸው የነበሩት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክተርና አንድ ኤክስፐርት ግን መሄዳቸውን ምንጮች አረጋግጠዋል፡፡

ሥራ አስፈጻሚውን ጨምሮ ስምንቱ የማኔጅመንት ከፍተኛ አመራሮች ከአገር እንዳይወጡ እግዱ የተጣለባቸው፣ ድርጅቱ ከዓመታት በፊት ለመንገደኞች ሸኚዎችና ተቀባዮች ትኬት ሽያጭ ከወጣ ጨረታ ጋር በተያያዘ ሲሆን፣ በወቅቱ ጨረታውን አሸንፎ የነበረው ሴፍቲ ራይት ፓርኪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ካቀረበባቸው ክስ ጋር በተገናኘ ሳይሆን እንደማይቀር ምንጮቹ ጠቁመዋል፡፡

አቶ ጁነዲን ሳዶ ከኦሕዴድ ሥራ አስፈጻሚነት ተወገዱ

በታምሩ ጽጌ
የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትሩ አቶ ጁነዲን ሳዶ ከኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦሕዴድ) ሥራ አስፈጻሚነት ተነስተው በተራ አባልነት እንዲቀጥሉ ድርጅቱ መወሰኑን ምንጮች ለሪፖርተር አስታወቁ፡፡
የኦሕዴድ ሥራ አስፈጻሚ ከመስከረም 21 ቀን እስከ መስከረም 24 ቀን 2005 ዓ.ም. ባካሄደው ዓመታዊ ጉባዔው ላይ፣ በሟች እናታቸው መኖሪያ ላይ እያሠሩት ካለው መስጅድ ጋር በተያያዘ የተገመገሙት ሚኒስትር ጁነዲን፣ ከፍተኛ የዲሲፕሊን ጉድለት መፈጸማቸውንና ካሉበት ኃላፊነትና ሥልጣን አኳያ ተገቢ ያልሆነ ሥራ መሥራታቸው በዋናነት እንደተገመገሙበት ምንጮቹ አረጋግጠዋል፡፡

አቶ ጁነዲን በእናታቸው የኑዛዜ ቃል መሠረት በመኖሪያ ቤታቸው ላይ መስጅድ ለማስገንባት፣ በሚኒስትርነታቸው ሳይሆን በግለሰብ ደረጃ ለመስጅዱ ማስጨረሻ ከሳዑዲ ዓረቢያ ኤምባሲ ዕርዳታ በመጠየቃቸው፣ የመስጅዱ የመጀመሪያ ደረጃ ምርቃት ሲደረግ በኢትዮጵያ የሳዑዲ ዓረቢያ አምባሳደር ተገኝተው 500 ቅዱስ ቁርአንና 50 ሺሕ ብር ዕርዳታ መስጠታቸውን ራሳቸው አቶ ጁነዲን በጻፉት ደብዳቤ አረጋግጠዋል፡፡

ባለቤታቸው አምባሳደሩ የሰጡትን 50 ሺሕ ብር ለመቀበል ኤምባሲ ሄደው ተቀብለው ሲወጡ፣ ለሽብር ተግባር የሚውል ገንዘብ ተቀብለዋል በሚል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው መዘገቡ ይታወሳል፡፡ አቶ ጁነዲን በጻፉት ደብዳቤ ግን ባለቤታቸው የተከበሩ የቤት እመቤት መሆናቸውን ገልጸው ነበር፡፡

በዚህም ምክንያት በኦሕዴድ ሥራ አስፈጻሚ ስበሰባ ላይ በተደረገው ግምገማ፣ ከሥራ አስፈጻሚነት ተነስተው በተራ አባልነት እንዲቀጥሉ መወሰኑን ምንጮቹ አረጋግጠዋል፡፡

ድርጅቱ የ2004 ዓ.ም. በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸምን አንድ በአንድ የገመገመ መሆኑን የገለጹት ምንጮች፣ በፀጥታው ዘርፍ በተለይ ቦረና አካባቢ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት ላይ ድክመት መታየቱንና ወደፊት ሊታሰብበት እንደሚገባ ሰፊ ውይይት እንደተደረገበት ተናግረዋል፡፡

በሪፖርቱ ላይ የታዩትንና ድክመት ያለባቸውን አንዳንድ የሥራ ዘርፎች በቀጣይ እንዲስተካከሉ ሐሳብ ተሰጥቶ ጉባዔው መጠናቀቁ ታወቋል፡፡ በድርጅቱ ውስጥ ያሉ አመራሮች እንዳሉ እንዲቀጥሉ ከማድረግ ውጭ ከኃላፊነቱ የተነሳም ሆነ የተሾመ አመራር እንደሌለ ታውቋል፡፡

የ21ኛው ክፍለ ዘመን ይሁዲ........ ከማተቤ መለሰ ተሰማ

በ20ኛው ክፍለ ዘመን የአርያንን ዘር በዓለም ላይ ማንገስን ሰነቆ የተነሳው የጀርመኑ ናዚ፡ በይሁዲያዊያን ላይ የፈጸመው የዘር ማጥፋት ሰቆቃ ዛሪ ድረስ የዓለምን ህዝብ ሲያሳዝን ይገኛል። አሁን በ21ኛው ክፍለዘመን ደግሞ ወያኔ የአማረኛ ቋንቋ ተናጋሪና የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታይ የሆነውን ኢትዮጵያውያን ከምድረገጽ ለማስወገድ እንደ ያኔው ናዚ ዘግናኝ ድርጊት በመፈጸም ላይ ነው።
ይህ የጥፋት ዘመቻ በአጋጣሚ የተከሰተ ሳይሆን በእቅድ ተነድፎ እየተከናወነ ያለ መሆኑን የህዋሀቱ አንጋፋ ታጋይ አቶ ስብሃት ነጋ የአቶ ሐይለማርያም ደሳለኝን የኢስሙላ ጠቅላይ ሚኒስተርነት ሹመት አስመልክቶ ገዛ ተጋሩ ከተባለ ፓለቶክ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ፡ ስልጣንን ከኦርቶዶክስ እምነት ተከታይና ከአማራ ነጥቀነዋል አላማችንም የኸው ነበር ሲሉ ሰነምግባር ባልገራው አንደበታቸው በድፍረት መናገራቸው የወያኔ ጉዞ ከየት ወዴትነት ማሳየት ከሚችሉ ኩነቶች እንደ አንዱ ሊወሰድ የሚገባው ነው።
ሟቹ ጠቅላይ አጥፊያችን አቶ መለስ ዜናዊም፡ በአንድ ወቅት ይህነን የበሰበሰ ሐይማኖት ኦርቶዶክስንና አማራን ካላጠፋን መሪት ትክበዳቸውና መቸም ስሟን መጥራት ያስጠላቸው ነበር፡ ሀአገሪቷን በምንፈልገው መንገድ መምራት አንችልም። ያሉ ሲሆን የህንኑ ቃል ሳይቀነስ እንዳለ ፡ አማራው የራሱ የሆኑ ልጆች አጥቶ በረከት ሰሞንን ከኤርትራ እንደተበደረ ሁሉ፡ ከደቡብ ኢተዮጵያ የተዋሳቸው አቶ ተፈራ ዋልዋ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲቫ በነበሩበት ወቅት ደግመውታል።
ለነገሩማ ህዋሃት በኢትዮጵያ አቆጣጥር 1968 ዓ.ም ደደቢት ውስጥ እያለ በነደፈው የትግል ማንፊስቶው ላይ፡ ከአላማው የመጀመሪያው አድርጎ ያሰፈረው አማራን ማጥፋት የሚል ነው። በዚህ መርሃ ግብሩ መሰረት ለ17 አመት ባካሄደው ጦርነት ሁሉ የሚማርካቸውን ወታደሮች ዘራቸውን በመጠየቅ አማራነኝ ያለውን ብቻ መርጦ እየገደለ ሌላውን ማለትም እንደ አባዱላ ገመዳና ኩማ ደመቅሳ አይነት ፈቃደኛ ምርኮኞችን ወደእራሱ ሰራዊት እንዲቀላቀሉ ሲያደረግ አልፈልግም ያለውንና አማራ አለመሆኑ የተረጋገጠለትን ወደዬ ትውልድ መንደሩ ይመልስ ነበር።
ወያኔ በምዕራባውያን ሃአገሮች ሙሉድጋፍ የኢትዮጵያን መንግስትነት በትረ ስልጣን ከጨበጠ በሗላም የመጀመሪያ ስራው ያደረገው ሌላው ኢትዮጵያውያን በአማረኛ ቋንቋ ተናጋሪው ሕዝብ ላይ እንዲነሳ መቀስቀስ ነበርና፡ አቶ ታምራት ላይኔ በሃረርጌ፣ በባሌ፣ በአርሴ፣ በቦረና። አቶ ዳዊይት ዮሀንስ ደግሞ በጀማ፣ በወለጋ በኢሉባቦር ወ.ዘ.ተ.ኦሮሞኛ ቋንቋ ተናጋሪው ማህበረሰብ ባለበት ሁሉ እየተዘዋወሩ ይህ አማራ የተባለ ነፍጠኛ ለመቶ አመታት ሲዘርፍህ፣ ሲገፍህ ሲያሰቃይህ ኖሯል። አሁን ሜዳውም ፈረሱም እነሆ፡ ልትበቀለው ትችላለህ በማለት ቀስቀስው እንደተመለሱ በአርባጉጉ፡ በበደኖ፣ በባሌ፣ አርሴ፣ በቦረና፣ በጅማ፣

የወደፊቱ፡ የዓለም ስጋትና የሀገራችን ሁኔታ፡

ማተቤ መለስ
የሰውን ልጅ ታሪክ ወደኋላ መለሥ ብለን ሥንመረምር፡ ከፍጡራን ሁሉ በተሻለ ሁኔ ዓለምንና ተፈጥሮን አጣጥሞ በመግራት እየተጠቀመባት እንዳለ ለመረዳት አያዳግተንም፡፡ በዚያው ልክ ደግሞ አንዱ ሌላውን የበታች አድርጎ ለመግዛትና ለመበዝበዝ ሌላው ላለ መገዛትና ላለመበዝበዝ በሚደረጉ ፍልሚያዎች መነሻ ነት ለጥፋትም እያዘጋጃት መሆኑን እናያለን፡፡ በእነዚህ ትንቅንቆች ሂደት መጠነ ሰፊ የህይወትና የንብረት ውድመቶች የደረሱና እየደረሱም ያሉ ወደፊትም በዳይና ተበዳይ በዝባዢና ተበዝባዥ በአንድ ቃል አምባ ገነኖች፡ ከምድራችን እስካለተወገዱ ደረስ እንደማያቆሙ የታወቀ ነው። ለሰው ልጅ ደመኛ ጠላት የሆኑት አምባገነንነት፣ የግልጥቅም አሳደጅነት፣ ተስፋፊነት ወ.ዘ.ተ. ጨርሰው ተወግደው የሁሉም ሰባዊ ፍጡር ሰላም ዲሞክራሴና ነጻነት በውል እሰካልተከበሩ ድረስ የጥፋቱ መጠንና አይነት ይለያይ እንጅ ጦርነት የማይቆም ቀጣይ ሂደት ነው የሚሆነው። ከዚህ አንጻር ፈጣሪያችን በስልጣኑ ካወረዳቸው ማታት ባሻገር የእውቀት አድማሳችን የፈቀደለንን ያህል ርቀን የዓለምን እውነታ በአይነሕሌናችን ብንዳስስከ20ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ እስካሁን ድረስ እንዳለው ጊዜ ሰብዓዊ ፍጡር ለጦርነት አደጋ የተጋለጠበት ወቅት ከዚያ በፊት የለም፡፡ ለተከሰተው ሁሉ ጥፋት ደግሞ መነሻዎቹም ሆነ መድረሻዎቹ እኛው እራሳችን ሰዎች ነን፡ ከፍጥረታት ሁሉ መጥፊያውን የሚሰራ ቢኖር ሰው ብቻ ነው ይባል የለ።