ከዳዊት ዋስይሁን
እንደተለመደው ሁሌም ጠዋት ከምሰራቸው ስራዎች አንዱ
የማህበራዊ ገጽ ጓደኞቼን እንኳን አደራችሁ ማለት እና ባንዳንድ ጉዳዮች ላይ ኦንላይን መጻጻፍ ነው። በተለይ ከተወሰነ ጊዜ ወዲህ
መልእክቶች በሰፊው ከማውቃቸውም ከማላውቃቸውም ሰዎች ይደርሱኛል ባብዛኛው ገንቢና ትግላችንን አጠናክረን ለውጡን ማፍጠን እንዳለበት
የሚያሳስቡኝ ሲሆኑ አንዳንዶቹ ግን መረን የለቀቀ ከባህላችን ውጭ በሆነ መንገድ በሚያንቋሸሹና በጥላቻ የተሞሉ መልእክቶችን የያዙ
ናቸው ይህም ከመገረም አልፌ ተደምሜባቸዋለሁ፣ በተለይ ከሰሞኑ የጻፍኳት መለስን የማልወድበት ምክንያት የምትል ጽሁፌን ያነበቡ ጥቂት
/ይህንን ቃል ተውሼ ነው/ የመለስ ደጋፊዎች በመቅበጥበጣቸው አቋሜ በግልጽ እንዲያውቁ ይህንን ደግሜ ጽፌያሁ።
ጥያቄው ለምን በአሁን ሰአት ስድቡና ማንቋሸሹ እንዴት
እንዲህ ሊበዛ ቻለ የሚለው ነው። አንድ መምህሬ ባንድ ወቅት ሲያስተምሩኝ ሰዎች በራሳቸው መተማመን ሲያቅታቸው እና ነገሮች ከቁጥጥር
ውጪ ሲሆኑባቸው የውስጣቸውን መሸነፍ፣ መረበሽ እና መታመስ ያሸነፉ ስለሚመስላቸው ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ከመሳደብና እራሳቸውን ከማዋረድ
ወደኋላ አይሉም ምክንያቱም በምክንያታዊነት ከማሳመንና ከማሸነፍ ይልቅ ሌሎች ላይ በሚሰነዝሩት አስጸያፊ ቃል ሰዎች ተንቀጥቅጠው
የሚገዙላቸው ስለሚመስላቸው ነው ያሉት ትዝ ያለኝም ወቅት ነው።