ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት
አዲስ አበባ
ጉዳዩ፡- ጥቅምት 15 ቀን 2ዐዐ5 ዓም በአዳማ ከተማ ቦርዱ
‹‹በ2ዐዐ5 ዓም በሚካሄደው የአካባቢ ምርጫ አፈፃፀም የጊዜ ሰሌዳ ረቂቅ›› ላይ ከፖለቲካ ድርጅቶች ከፍተኛ አመራሮች ጋር ባአደረገው
ምክክር ፕሮግራም ተገኝተው ፔቲሽን ከፈረሙ የፖለቲካ ፓርቲዎች የቀረበ ጥያቄ ስለማቅረብ፣
1. አጠቃላይ፡-
ከላይ በተጠቀሰው
ቀን፣ ቦታና ርዕሰ ጉዳይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አመራር (ቦርድ) እና ሥራ አስፈፃሚ (ጽ/ቤት ኃላፊና ሠራተኞች) በተገኛችሁበት
66 የፖለቲካ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተን ውይይት ማድረጋችን ይታወሳል፡፡ በዚህ የምክክር ፕሮግራም ላይ ከተሣተፉ የፖለቲካ
ድርጅቶች አብዛኛዎቹ ‹‹የአገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር እየጠበበ መምጣቱንና የምርጫ ውድድር ሜዳው የተስተካከለ ያለመሆኑን፣ ከዚህ በፊት
የተደረጉ ምርጫዎች በአፈፃፀም ችግሮች የተተበተቡ መሆናቸውን፣ እንዲሁም በየደረጃው ባሉት የምርጫ ቦርድ አመራርና አስፈፃሚ አካላት
ተአማኒነትና ተቀባይነት ላይ ያለውን ጥያቄ ተጨባጭ መገለጫዎችንና መሣያዎችን በማቅረብ ካስረዱ በኋላ
በእነዚህ መሠረታዊ ጉዳዮች ላይ መወያየት ከጊዜ ሠሌዳው ረቂቅ ላይ ከመወያየት ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል›› የሚል ሃሳብ ማቅረባችን
በእለቱ በተቀረፀው ኦዲዮ-ቪዲዮ ላይ ይገኛል፡፡
በወቅቱ ላነሳናቸው
ጉዳዮች በቂ መልስ ባለማግኘታችን በፕሮግራሙ ላይ የተሣተፍን 33 የፖለቲካ ድርጅቶች ከጊዜ ሠሌዳው በፊት የምርጫው ፍትሐዊነት፣
ዴሞክራሲያዊነትና ነፃ መሆን ላይ የሚደረግ ውይይት እንዲደረግ ፔቲሽን ለመፈራረም ተገደናል፡፡ የፔቲሽኑ ይዘት (1 ገጽ) እና የፈረሙ
የፖለቲካ ድርጅት አመራሮች ዝርዝር (2 ገጽ) ከዚህ ጋር ተያይዞ
ቀርቧል፡፡ በመቀጠልም ፔቲሽንኑን የፈረምነው ፓርቲዎች ተጠሪዎች በ25/ዐ2/2ዐዐ5 ዓም ተገናኝተን በጉዳዩ ላይ በጥልቀትና በስፋት
ተወይይተናል፡፡ ጥያቄአችን በዚህ መልክ እንዲቀርብ ተስማምተናል፡፡