Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Wednesday, 2 May 2012

ብአዴን ማነው?

አልታደልንም እንጂ ሕዝብ የመሪዎቹን ማንነትና ምንነት የማወቅ መብት ነበረው፡፡ የኛ መሪዎች ግን እንኳንስ ማንነታቸውን ለሕዝብ ሊያስተዋውቁ 
ይቅርና ስማቸውን ሳይቀር ቀይረው ያሸመቁ ናቸው፡፡ ይህ ብቻ አይደለም የመጡበትን የዘር ግንድ ሳይቀር የደበቁና የቀየሩ ናቸው፡፡ ለማንኛውም 
የብአዴን ቁንጮ መሪዎች የሚከተሉት ናቸው፡-

1. አዲሱ ለገሠ (ኦቦ) የአሰበ ተፈሪ ልጅ  ወይንም ተወላጅ 

2. በረከት ስምዖን (መብራቱ) ጎንደር ተወልዶ ያደገ በእናቱም በአባቱም ኤርትራዊ 

3. ተፈራ ዋልዋ የሀገር ማርያም ልጅ ወይንም ተወላጅ በአባቱ አማራ በናቱ ሲዳማ 

4. ታደሰ ካሣ (ጥንቅሹ) ኮረም ተወልዶ ያደገ በግማሽ ትግሬ በግማሽ አገው

5. ካሳ ተክለ ብርሃን (ሸሪፎ) ሠቆጣ ተወልዶ ያደገ ትግሬና አገው

6. ሕላዊ ዮሴፍ (ቦግን) የአ.አ ልጅ ትግሬ  ምናልባትም የኤርትራ ዘር ያለበት 

7. ዮሴፍ ረታ (ገይድ ወይንም ዶሪ) የናዝሬት ልጅ ቤተሰቦቹ አርሲ

8. ተሠማ ገ/ሕይወት (የጎንደር ልጅ) ሙሉ በሙሉ ትግሬ (አድዋ)

9. ከበደ ጫኔ (ጣሣ) የራያ (ዋጃ) ልጅ ትግሬና አማራ 

10. መለሠ ጥላሁን አርሲ ተወልዶ ያደገ ኦሮሞ 

11. ኃይሌ ጥላሁን (ዘሪሁን) ሰሜን ሸዋ
 
እነዚህ ናቸው የብሔር አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) መሪዎች የነበሩት፡፡ ከላይ የተጠቀሱት ዜጎች ኢትዮጵያውያን ናቸው፡፡ 
እንደ ኢትዮጵያዉያንነታቸው የአማራን ሕዝብ የመምራትም ሆነ የማስተዳደር መብት አላቸው፡፡ ጥያቄው የሚነሳው ‹‹ሁልህም ወደ ወገንህ ሲባል 
አክንባሎም ወደ በረት፤ርኮት ወደ ቁርበት ተጠጉ›› እንደሚባለው ሁልህም በየክልልህ በገዛ ብሔረሰብህ ተዳደር ከተባለ መብቱን ለብሔሩ ተወላጅ መተው ነበረበት ነው ነቀፋው፡፡
‹‹በቅሎ አባትሽ ማነው ቢሏት ፈረስ አጎቴ ነው አለች''
    ምንጭ ፍኖተ ዲሞክራሲ

ለኢህአዴግ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የለገሰው ግለሰብ፧ በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ አጭበርብሯል የሚል ክስ ቀረበበት

ሚያዚያ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ዮሐንስ ሲሳይ የተባለው የ40 አመት ጎልማሳ ኢህአዴግ አገሪቱን ከተቆጣጠረ በሁዋላ በአጭር ጊዜ ቢሊየነር ለመሆን የበቃ የዘመኑ ባለሀብት ነው።
የሱ እና ሸበል የሚባሉ ኩባንያዎችን የመሰረተው ዮሐንስ ፣ ኢህአዴግ ለምርጫ በሚወዳደርበት ጊዜ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ለፓርቲው ለግሷል።
የትኛውም የአገር ውስጥ ባለሀብት ባላደረገው መልኩም፧ ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ በማውጣት ለአባይ ግድብ ማሰሪያ ቦንድ ገዝቷል።
ከኢህአዴግ ባለስልጣናት ጋር እጅና ጓንት በመሆን ቢሊዮነር ደረጃ የደረሰው ዮሀንስ፣ ያሬድ ከሚባለው የንግድ ሸሪኩና ከሌሎችም የኩባንያው ሰራተኞች ጋር በመሆን ያለፈውን አንድ ወር በማእከላዊ እስር ቤት አሳልፎአል።
በዮሀንስ እና በሸሪኮቹ  ላይ የቀረበው ክስ እንደሚያሳየው፧ ግለሰቡ እና ግብረ አበሮቻቸው ከ795 ሚሊዮን ብር በላይ የሚሆን ገንዘብ በታክስ ማጭበርበር ለግል ጥቅማቸው አውለዋል።
የብረታብረት ማቅለጫ ፋብሪካ ባለቤቶች የሆኑት ዮሀንስና ያሬድ፧ ድርጅታቸው በአመት 3 ቢሊዮን የሚጠጋ ገንዘብ የሚያንቀሳቅስ ቢሆንም፣ ለመንግስት ይፋ ያደረጉት ግን 2 ቢሊዮን ብር ገደማ ነው።
የፌደራል አቃቢ ህግ ባቀረበው ክስ፧ የሱ ኩባንያ ከ2000 እስከ 2003 ዓም ያልከፈለው ታክስ 200 ሚሊዮን ብር ይተጋል::
፣ኩባንያው; ከ2004 ዓም ጀምሮ  ከ500 ሚሊዮን ብር በላይ ኪሳራ እንደደረሰበት ለመንግስት ቢያሳውቅም:  አቃቢ ህግ እንደሚለው ግን  በ2004 ዓም ከ450 ሚሊዮን ብር በላይ ትርፍ አግኝቷል።
የ ተ ከሳሾቹን ጉዳይ የያዘው ስምንተኛው ወንጀል ችሎት ፧ተከሳሾች ላቀረቡት የዋስትና ጥያቄ ከአምስት ቀናት በሁዋላ መልስ እንደሚሰጥ ፎርቹን ዘግቧል።
በኢህአዴግ ደጋፊነታቸው የሚታወቁት አቶ ዮሀንስ፧ ለምን ታሰሩ የሚለው ጥያቄ የከተማው መነጋጋሪያ ሆኗል።
ብዙዎች የሚገምቱት ግለሰቡ ለኢህአዴግ መስጠት የሚገባውን ገንዘብ ባለመስጠቱ ነው የሚል ሲሆን፣ ሌሎች ወገኖች ደግሞ ከዚህ ቀደም ህወሀት ስታር ኩባንያንና የኢትዮጵያ  አማልጋሜትድ ሊሚትድን የመሳሰሉ ድርጅቶችን  አጥፍቶ ገበያውን በራሱ ድርጀቶች እንዳስያዘው ሁሉ፣ በአጭር ጊዜ ቢሊየነር የሆኑትን የአቶ ዮሀንስንና ሸሪኮቻቸውን ኩባንያዎች ከውድድር ውጭ በማድረግ ገበያውን ለመቆጣጠር አስቦ ሊሆን ይችላል ይላሉ።

ኢህአዴግ በ አማራ ተወላጆች ላይ እየፈጸመ ያለውን የማፈናቀል ተግባር ቀጥሎበታል

ሚያዚያ ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-እንደ ጋዜጣው ዘገባ፤በደቡብ ክልል በጉራ ፈርዳ ወረዳ ይኖሩ የነበሩ አማሮች ፦”ወደ አገራችሁ ሂዱ” ተብለው መባረራቸው ህዝባዊ ተቃውሞ ባስነሳበት
በሁኑ ጊዜ፤ በቤንሻንጉክ ጉሙዝ ክልል ይኖሩ የነበሩ የ አማራ ተወላጆችም ተመሣሳይ ዕጣ ገጥሟቸዋል።
እንዲሁም  በሰሜን ጎንደር ዞን ሱዳን ድንበር አቅራቢያ በሚገኘው አርማጭሆ ወረዳ ውስጥ በኢብርሀጂራ  አካባቢ በእርሻ ሥራ  ተሰማርተው ይኖሩ የነበሩ የአማራ ተወላጅ አርሶ አደሮች የ እርሻ መሬታቸውን ተነጥቀው ሰሞኑን መባረራቸውን፤ የአካባቢውን አርሶአደሮች ተናግረዋል።
በድርጊቱ የተበሳጩት አርሶ አደሮች፦  ኢህአዴግ በአማራ  ላይ ጣቱን ቀስሯል”ሲሉ በምሬት መናገራቸውን ፍኖት ገልጿል።
ከተለያዩ ቦታዎች ከይዞታቸው እየተፈናቀሉ ያሉት አርሶአደሮች ምንም መቋቋሚያ  ስላልተሰጣቸው የከፋ ችግር ላይ እየወደቁ መሆናቸውም ተመልክቷል።
ከ አርማጭሆ አካባቢ ሰሞኑን የተፈናቀሉት አርሶ አደሮች፤ ከ1998  ዓመተ ምህረት ጀምሮ በስፍራው ሲኖሩ የቆዩ መሆናቸውን ተናግረዋል።
አርሶ አደሮች  ከይዞታቸው በሚነሱበት ጊዜ፦”መሬቱ በብሎክ ስለሚደለደል፤ ያለሰለስኩት ማሳዬ ስለሆነ ለኔ ይገባኛል “የሚል  ጥያቄ እንዳያነሱ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸውም ገልጸዋል።
 አርሶ አደሮቹ  የተፈናቀሉት መንግስት አካባቢውን  ቆርሶ ለሱዳን በመሰጠት በመወሰኑ እንደሆነ ተገልጿል።
ከዚህም ባሻገር፤በታች አርማጭሆ ወረዳ ፤ሳንጃ ውስጥ ለረጂም ዓመታት የቤተ-ክርስቲያን መገልገያ የሆነን ሥፍራ “ለልማት” ተብሎለአንድ ባለሀብት እንዲሰጥ በመወሰኑ ፤በአካባቢው ህብረተሰብ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ መፈጠሩን  ጋዜጣው ጨምሮ ዘግቧል ፡፡
የአካባቢው ህብረተሰብ በውሳኔው መቆጣቱ ያሣሰባቸው  የወረዳው ኃላፊዎች ህዝቡን ሰብስበው ለማግባባት ቢሞክሩም ህዝቡ በተቃውሞው በማምረሩ  በአካባቢው ውጥረት መንገሱን  ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡
ወረዳው፤ በምርጫ 97 ኢህአዴግ አንድም ድምጽ ያላገኘበት አካባቢ በመሆኑ ፤ ነዋሪው በተለይ  ከዚያን ጊዜ ወዲህ ባሉት  ዓመታት ከፍ ያለ አስተዳደራዊ በደል ሲፈጸምበት መቆየቱን የዜናው ምንጮች አስታውሰዋል።
 “በአሁኑ ጊዜ የአካባቢውን ህብረተሰብ ነፃነቱ ሙሉ በሙሉ ተገፏል፤ሁሉም ዜጋ የቁም እስረኛ ተደርጓል፡፡ ከሚኖርበት
ቀበሌ ወደ ሌላ ማናቸውም ቀበሌ ለመሄድ ቢፈልግ እንኳ፤ ለአካባቢው ኃላፊዎች አሳውቆ የይለፍ ወረቀት መያዝ ይጠበቅበታል፡፡
የፍቃድ ወረቀት ሳይኖረው ከሚኖርበት ቀበሌ ተነስቶ ወደ ሌላ ቀበሌ ቢሄድ ይታሰራል” ሲሉም- በ አካባቢው  የሚታየው ውጥረት ምን ያህል የከፋ እንደሆነ ምንጮቹ ለማመልከት ሞክረዋል።
መንግስት በዋልድባ የስኳር ፋብሪካ ለመስራት የጀመረውን እንቅስቃሴ ተከትሎ  ውጥረት ነግሶ መቆየቱ የሚታወቅ ሲሆን፤ ከሰሞኑ ደግሞ  የሰሜን ጎንደር ህዝብ ዶማ፣ አካፋና ጦር እየያዘ ወደ ስፋራው እየተመመ እንደሚገኝ  መዘገቡ ይታወሳል።

ቤንቺ ማጂ ጉራፋርዳ ወረዳ….ፍኖተ ነጻነት


ባለፈው ተከታታይ ሳምንታት በከፍተኛ የክልሉ ባለሥልጣናት ትዕዛዝ ከመኖሪያቸው በመፈናቀል ላይ ያሉት የቤንች ማጂ ዞን ጉራፋርዳ ወረዳ ነዋሪዎች ዛሬም የማፈናቀሉ ሥራ ተጠናክሮ ቀጥሎአል ሲሉ የዜና ምንጮቻችን ገለፁ፡፡ ምንጮቹ እንደሚሉትከዚህ በፊት 2 በላይ አባወራዎች ከመኖሪያቸው የተፈናቀሉ ሲሆን ወደ የተለያየ ቦታ ተበታትነዋል፡፡ መሄጃ የለንም ብለው አዲስ አበባ አዋሬ አካባቢ የነበሩ ወደ ቦታችሁ ትመለሳላችሁ ብለው መልሰው
ቢወሰዷቸውም እስከአሁን ድረስ በሥፍራቸው ላይ አልመለሷቸውም፡፡ በሚዛን ተፈሪ ማዘጋጃ ቤት ፊት ለፊት ሜዳ ላይ ሰፍረው ለሥቃይ ተዳርገዋልይላሉ፡፡ሌሎች ከመኖሪያ ቦታቸው ያልተነሱትን አሁንም ታጣቂዎች በማስገደድ እያፈናቀሉ ይገኛሉ፡፡ የክልሉ ባለሥልጣናትና /ሚኒስትሩ የተፈናቀሉት33 ሰዎች ብቻ ናቸው ቢሉም የማፈናቀል ሥራው ዛሬም ተጠናክሮ ቀጥሎአልይላሉ፡፡

ቤኒሻንጉል ጉምዝ ማቡክ ወረዳ…ፍኖተ ነጻነተ


በተለያዩ ጊዜ ከተለያየ የአገሪቱ ክፍሎች ተንቀሳቅሰው በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልላዊ መንግስት ማቡክ ወረዳ ላይ ሠፍረው በግብርና ይተዳደሩ የነበሩ አማርኛ ተናጋሪ አርሶአደሮች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ በመደረጉ ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠናል ሲሉ አማረሩ፡፡ ከሥፍራው ተባረን ባህርዳር የመጣን ነን የሚሉ አርሶአደሮች ለዝግጅት ክፍላችን እንደገለጹት በአካባቢው ኃላፊዎች አስገዳጅነት 2 በላይ አባውራዎች ከሥፍራው ተፈናቅለናል፡፡ የተሰጠን ትዕዛዝ ወደ ትውልድ ሥፍራችሁ ተመለሱ ብንባልም ትውልድ ሥፍራችን ለመድረስም ከደረስንም በኋላ ቦታ ባለማግኘታችን
ለችግር ተጋልጠናል፡፡ይላሉ፡፡ እነዚህ ተፈናቃዮች ነን የሚሉት ሰባት አባውራ አርሶ አደሮች በትላንትናው እለት ባህርዳር ለምግብ ዋስትና አመልክተው መፍትሔ አለማግኘታቸውን በቅሬታ ገልፀዋል፡፡ አርሶአደሮቹ እንደሚሉት ከመኖሪያ ሥፍራችን ካፈናቀሉን የአካባቢው ባለሥልጣናትና ታጣቂዎች ባልተናነሰ መልኩ በትውልድ ሥፍራችን የሚገኙ የአካባቢው ባለሥልጣናትም በጥላቻ እያመናጨቁን ናቸውይላሉ፡፡ አያይዘውም አቤት የምንልበት ቦታ
አተናል፡፡ ማንም ሊሰማን አልቻለም፡፡ እባካችሁን ለሚመለከተው የመንግሥት አካል አሳውቁልንሲሉ የድረሱልን ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡