Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Sunday 3 February 2013

ኤርትራ Eንደ Eናት Aገር ፣ ችግሮችና ፈተናዎች ትናንትም ዛሬም

የመወያያ ሰነድ
Discussion Paper
ኤርትራ Eንደ Eናት Aገር፤
ችግሮችና ፈተናዎች ትናንትም ዛሬም
ተስፋጽዮን መድሃኔ (ፕሮፈሰር)
ብረመን ዩኒቨርሲቲ፣ ጀርመን
ብረመን፡ ጀኑዋሪ፡ 2013
ኤርትራ Eንደ Eናት Aገር ፣ ችግሮችና ፈተናዎች ትናንትም ዛሬም
ማብራሪያ Eና ምስጋና
ይህ ጽሑፍ ከጥቅምት (Oክቶበር) 5 Eስከ 7፡ 2012 በጀርመን Aገር፡ ካስል ከተማ፡ የኤርትራ ነፃ Aውጪ የEናት Aገር ግምባር ምስረታን በሚመለከት የሚካሄደውን ጉባኤ ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ የምርምር ሰነድ ነው። የዚህ ጽሑፍ ዓላማ በተጠቀሰው ጉባኤ ላይ ይሁን በሌላ ጊዜና ቦታ ስለ ኤርትራ Eንደ Eናት Aገር የሚካሄዱ ውይይቶች Eንዲዳብሩ በመጠኑም ቢሆን AስተዋጽO ለማድረግ ነው። ስለሆነም ይህ “የመወያያ ሰነድ” ጉባኤው ከመካሄዱ በፊት Aስቀድሞ Eንዲሰራጭ ተደርጓል።
ይህ ጥናት Eኔ በግል ተነሳሽነት ያዘጋጀሁት ነው፡፡ በስተጀርባ ሆኖ የገፋፋው ወይም ያሰማራው ድርጅት ይሁን ንቅናቄ Aንድም የለም። የዚህን ጽሑፍ ይዘትም ሆነ ስርጭት በሚመለከት ሃላፊነቱ ሙሉ በሙሉ የኔ መሆኑን ለማስገንዘብ Eወዳለሁ።
ይህንን ጽሑፍ ሳዘጋጅ ስማቸውን መጥቀስ የማያስፈልገኝ ወዳጆቼ በቀጥታም ሆነ በተለያዩ መንገዶች ትብብሮች Aድርገውልኛል። Aንዳንዶቹ ጠቃሚ ሰነዶችን በመላክ፣ Aንዳንዱ ደግሞ መረጃዎችን በማቀበል፤ ሌሎችም Eንዲሁ ይህ ጽሑፉ ንድፍ በነበረበት ጊዜ Aስተያየታቸውን ጠይቄ፡ ጠቀሜታ ያላቸው ጥያቄዎች Aቅርበዉልኛል፤ Aስተያየቶችም ለግሰውልኛል።
ይህ መልEክት በስEለ ድምጽ፡ ማለት በAውዲዩ ቪዲዩ፡ የተቀረጸ ሲሆን በጽሑፍ ደረጃም በትግርኛ፤ በAማርኛ Eና በዓረብኛ ይኸው ተሰራጭቷል፡፡ ጽሑፉ ከትግርኛ ወደ ዓረብኛና ወደ Aማርኛ ሲተረጐም ለኤርትራና ለIትዮጵያ በጎ Aመለካከት ያላቸው ወዳጆቼ በተለያየ መልኩ ትልቅ AስተዋጽO Aበርክተዋል፡፡
ለተባበሩኝ ሁሉ ልባዊ ምስጋና Aቀርባለሁ።
ተስፋጽዮን መድሃኔ
ብረመን፣ ጀኑዋሪ፡ 2013

1
የመወያያ ሰነድ (Discussion paper)፣ ጀኑዋሪ 2013
ኤርትራ Eንደ Eናት Aገር፤
ችግሮችና ፈተናዎች ትናትም ዛሬም
ተስፋጽዮን መድሃኔ (ፕሮፈሰር)
ብረመን፣ ጀርመን
ዛሬ ስለ Aገር-ቤት ወሬ ለመስማት የሚጓጓ ኤርትራዊ ቁጥሩ Aነስተኛ ነው፣ ወይም ከጊዜ ወደ ጊዜ Eየመነመነ መጥቷል። ኤርትራን Aስመልክቶ የሚተላለፉት ዜናዎች የሚያሳዝኑና የሚዘገንኑ ብቻ ናቸው። በታወቁ ዓለም Aቀፍ የዜና Aውታሮች ሳይቀር በሚተላለፉ ዜናዎች፡ ሁሌም ማለት ይቻላል፡ Aገሪቱ ከውድቀት፡ ከመከራና ከስቃይ ጋር በተያያዙ ርEሶች ብቻ ነው የምትጠቀሰው። በዚህ ሁኔታ ላለችው ኤርትራ Eርካታና Eፎይታ የሚባሉ ፅንሰ-ሃሳቦች ባEድ ሆነዋል።
ሕዝባችን ሊገመት በማይቻል የከፋ የመከራ ህይወት ውስጥ Eንዳለ Eውነተኛ የሆነ ታዛቢ ሁሉ የሚመሰክረው ሃቅ ነው። መላ ሕብረተሰባችን በማንኛውንም የህይወት ገጽታዎች በታሪከ ታይቶ በማይታወቅ መጠን Eየተጨቆነ፡ Eየተሰቃየና Eየተረገጠ ይገኛል። ኤርትራ Aጣዳፊ Eርዳታ Eየጠየቀች ነው። ህዝብዋ በEናት-Aገር ግምባር መልክ ተደራጅቶ ህልውናዋን ያድን ዘንድ Aብቱታዋን Eያቀረበች ነው።
ይህ ሁኔታ ስለ ኤርትራ Eንደ Eናት Aገር Eንድንመራመርና Eንድንወያይ Eየጋበዘን ብቻ ሳይሆን በAጽንOት “Eየገዘተን” ነው”። Eኔም ለዚሁ ጥሪ መልስ በAቅሜ ይህንን “ኤርትራ Eንደ Eናት Aገር፤ ችግሮችና ፈተናዎች ትናትም ዛሬም” የተሰኘ ሰነድ ለውይይት ይረዳ ዘንድ Eነሆ Aሰራጫለሁ፡፡
መልEክቴን ማስተላለፍ ከመጀመሬ በፊት ግን የIትዮጵያ መንግሥት መሪ የነበረው የAቶ መለስ ዜናዊን ሕለፈተ-ህይወት በሚመለከት Aጠር ያለ መልEክት ማስተላለፍ Aስፈላጊ ይመስለኛል።
ሰሞኑን የAፍሪካ ቀንድ ፖለቲካን የሚከታተሉ ታዛቢዎች የAቶ መለስን Eረፍት Aስመልከቶ ግምገማ Eና ምስክርነት Eየሰጡ ያሉበት ወቅት ነው። Iትዮጵያዊያን Eና ኤርትራዊያን ብቻ ሳይሆኑ የታወቁ የውጭ Aገር ተንታኞችና መሪዎችም የተሰማቸውን ሀዘን፡ የመራራነቱ መጠን በሚለያይ ቋንቋ፡ ሲገልጹ ሰንብተዋል።
በዚህ Aጋጣሚ Eኔም ባንዳንድ Aቶ መለስ ሲከተላቸው በነበሩት የፖለቲካ ዓላማዎችና ሲያካሂዳቸው በነበሩት Eንቅስቃሴዎች ላይ የነበሩኝ ያለመርካትና ነቀፌታዎች Eንደተጠበቁ ሆነው፡ ወጣት በሚያስብል Eድሜው ከዚህ ዓለም በመለየቱ የተሰማኝን ሐዘን ለመግለጽ Eሻለሁ። ለቤተሰቡና ለወገኖቹም Eንዲሁ ጽናቱን Eመኝላቸዋለሁ።
Aቶ መለስ በወጣትነት Eድሜው በመቀጨቱ ያዘንኩበት የተለያዩ ምከንያቶች Aሉኝ። ከምክንያቶቼ Aንዱ የሚከተለው ነው፡፡ Aቶ መለስ ኤርትራን በሚመለከት የተከተለው ፖሊሲና ያስከተለው ውጤት Aከራካሪ ነው። Aሁን ይህንን Aስመልከቶ Eዚህ ውስጥ 2
ኤርትራ Eንደ Eናት Aገር ፣ ችግሮችና ፈተናዎች ትናንትም ዛሬም
ዝርዝር ትንተና ልገባ Aልፈልግም። ለኤርትራ ተቆርቋሪ በመምሰል በተግባር ግን ጐጂ የሆኑ Eርምጃዎች ሲፈጽም Eንደነበር ግልጽ ነው። ሆኖም ግን፡ ቂም ባልይዝበትም ድርጊቱን ልረሳው Aልችልም። ረዢም Eድሜና ጤና ሰጥቶት ቢቆይ ኖሮ፡ ከጥቂት ዓመታት በሁዋላ፡ ሰፋ ያል ተሞክሮና የላቀ ብስለት Aግኝቶ፡ ሁላችንም ማድረግ Eንደሚገባን፡ ያለፈው Aካሄዱን መልሶ በመመርመር ተምሮ፡ ከበደላቸው ክፍሎች ጋር መረዳዳት ምናልባት ይችል ነበር ብዬ Eገምታለሁ። ይህን ለማድረግ Eድል ባለማግኘቱ በጣም Aዝናለሁ።
Aቶ መለስ Aከራካሪ የሆኑ ቅርሶች ለውርስ ትቶ Aልፈዋል። Aንዳንዶቹ Eያሞጐሱትና Eየመረቁት ናቸው፣ ሌሎች ደግሞ Eየወቀሱትና Eየረገሙት ናቸው። ብዙ ጊዜ መሪዎች በሞት ሲለዩ ስለነሱ የሚሰጡት ሚዛኖች የተለያዩ ናቸው። የAንዳንዱ ወደ Aዎንታ፡ ያንዳንዱ ደግሞ ወደ Aሉታ ያደላ ይሆናል። ይህ Eውነት ነው። ሆኖም Aቶ መለስን በሚመለከት ያለው ያስተያየት ልዩነት በጣም ሰፊና ጥብቅ ወይም ስለታም በመሆኑ፡ Aስገራሚ ባይሆንም፡ ጠለቅ ያለ ትርጉም ያለው ነው።
በተቃዋሚ ካምፕ ያሉ ኤርትራውያንም ለሟቹ ከፍተኛ ምስጋና የተላበሱ Aስተያየቶች ሰንዝረዋል። በባህላችን ሞት ለህሊና ወይም ለስሜት የሚከብድ Aጋጣሚ ነው። በዚህ ምክንያት ይመስለኛል Aንድ ሰው በሞት ሲለይ በታቸለ መጠን የህይወቱን Aዎንታዊ ጐኖችን ብቻ በማጉላት መሸኘት የነበረና Aሁንም ያለ ባህላዊ ስነ ስርAት ነው። ይህ Eውነት ይሁን Eንጂ፡ Aንዳንድ ኤርትራውያን Aቶ መለስን በሚመለከት ያቀረቧቸው ጽሑፎች ይዘቶች የሚስተዛዝብ ወይም የሚያስጨንቅ ገጽታዎች ነበሯቸው። በተለይም ደግሞ በAብዮታችን (ማለት በኤርትራ Aብዮት) ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎችን ቸላ ብለው ወደ ጐን ያስወገዱ፡ በይዘታቸው ደግሞ ‘ከኤርትራ Eናት-Aገርነት’ ጋር የማይጣጣሙ የሚመስሉ መግለጫዎች ትንሽ Aሳስበውኛል።
ይህንን ሁኔታ ለመታዘብ የቻልኩበት Aንደ Aጋጣሚ ነው። Eነኚህ የኤርትራ ተቃዋሚዎች ያስተላለፏቸውን የጽሑፍ መግለጫዎች ያነበብኩት ይህንን ጽሑፍ (‘ኤርትራ Eንደ Eናት Aገር’ ችግሮችና ፈተናዎች ትናንትም ዛሬም) ሳዘጋጅ በነበርኩበት ወቅት ነው። መግለጫዎቻቸው ሳነባቸው፡ ሳዘጋጀው ከነበርኩት ከዚህ ጽሑፍ ጋር የሚጋጭ ሃሳብ ያዘሉ መሆናቸውን ተገነዘብኩኝ፣ ስለዚህም ይበልጥ ሰፋ ያለ ጥናት ለማድረግ ተገደድኩ። ይህ ተያያዥ ሁኔታ ባጋጣሚ ለዚህ AርEስት ጉዳይ በጥልቀት Eንድመረምረውና በበለጠ ግልጽነት Eንዳቀርበው በር ከፋች Eንደሆነኝ ሳልገልጽ Aላልፍም።
- ፩ -
ወደ Aብዩ ርEሳችን Eንግባ። በEናት Aገር መልክ የተዋቀረ፡ መድኅን የሆነ ሃይል ቶሎ Eንዲደርስላት ኤርትራ ትጣራለች! የEናት Aገር ግምባር Aስፈላጊ የሚሆነው ለምንድ ነው? Eናት Aገር (የትግርኛው “ዓዲ Aቦ”) ሲባል፡ ይዘቱ (ትርጉሙ) ቆየት ብለን በሰፊው የምናየው ቢሆንም፡ “መሬቱ”ና ”ሕዝቡ” ብቻ ሳይሆን የህዝቡን ባህልና Eሴቶች፡ ባጭሩ ስልጣኔንና ታሪክን በሙሉ የሚያጠቃልል ነው። Eነዚህ ሁሉ በAሁኗ ኤርትራ Aደጋ ላይ ናቸው። Eንዲያውም፡ በAሁኑ ሁኔታ Aገሪቷ Eንዳትፈርስና ሕዝቡም Eንዳይጠፋ የሚያሰጋ ነው። በEንደዚህ ያለ Aስጊ የታሪክ መድረክ ከተገኘን ዘንድ፤ ኤርትራ “Aገሬ” ነች የሚል ሁሉ በAገር Aድን ዘመቻ Eንዲሰለፍ Eየተጋበዘ ነው።
ኤርትራ ሦስተኛ ዓለም ተብለው ከተመደቡት Aገሮች Aንዷ ነች። ይህች Aገር በውስጣዊ የታሪክ ሂደት የተገነባች ሳይሆን ጣሊያን ከውጭ መጥቶ ለጣጥፎ ያቆማት ሰው-ሰራሽ 3
የመወያያ ሰነድ (Discussion paper)፣ ጀኑዋሪ 2013
Aካል ናት። ከጣሊያን ቅኝ Aገዛዝ በፊት ኤርትራ ለብቻዋ Eንደ Aንድ Aካል የቆመች Aልነበረችም። Eንዳውም ደጋማው ክፍል የሰሜን Iትዮጵያ (Aቢሲኒያ) Aካል ነበረ።ምEራባዊው ቆላማው ክፍልም Eንደዚሁ በባህላዊ ራስ ገዝ Aስተዳደር ህይወታቸው ሲመሩ የነበሩ Aብዛኛው ጊዜ ከማEከላዊና ምስራቃዊ ሱዳን ብለን ከምንጠራቸው Aካባቢዎች ጋር፡ “ስናርን” ጨምሮ፡ ከጊዜ ወደ ጊዜ ሲከሰት የነበረ ግንኙነት ነበራቸው።
በ1941 የጣሊያን ቅኝ ግዛትነት ካበቃ በኋላ የታሪክ ድጋፍ Aለን በማለት Eንደ Iትዮጵያ Eና ግብጽ የመሳሰሉ መንግሥቶች ኤርትራ በመላ ወይንም የኤርትራ ክፍል የሆኑት Aካባቢዎች Eንዲሰጣቸው ጠየቁ። Eንግሊዝና Iጣሊያም Eንዲሁ የየራሳቸው ጥቅምና ስትራተጂ ነበራቸው። Eንግዳውስ ኤርትራ ሉUላዊት Eናት Aገር ለመሆን ብቃት Aላት ወይስ የላትም የሚል ፈታኝ ጥያቄ ወደ ግልጽ መድረክ ብቅ ማለት የጀመረው በዚህ ወቅት Aካባቢ ነው።
የወቅቱን ሁኔታ ለመረዳት የያኔው ፖለቲካ Aዝማሚያ (ሁኔታ) ማስታወስ Aስፈላጊ ነው። ጣሊያን ከተሸነፈ በኋላ Eንግሊዝ የቃል ኪዳን መንግስታትን በመወከል ኤርትራን ተቆጣጠረ። ረዢም ጊዜ ሳይቆይም ወታደራዊ Aስተዳደሩን መሠረተ። ያ Aስተዳደር Eንግሊዞች የኤርትራን የወደፊት Eድል Aካባቢውን በAዲስ የቅኝ-ግዛት መልክ ለመቆጣጠር የነበራቸውን ምኞት በሚያገለግል መንገድ Eንዲወሰን የሚቻለውን Aደረገ።
የEንግሊዞችን ዘዴ ለመረዳት Iትዮጵያን Aስመልክቶ የጣሊያኖች የፖለቲካ መሃንዲሶች ከድሮ ጀምረው የነደፏቸውን ሁለት መመሪያዎችን ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት Aስፈላጊ ነው። Eነዚህ መመሪያዎችም “ፖለቲካ ሸዋና” Eና “ፖለቲካ ትግርኛ” የሚባሉት ናቸው። “ፓለቲካ ሸዋና” የሚባለው በIጣሊያ የውጭ ጉዳይ ጽ/ቤት ይበልጥኑ Aትኩሮት ተሰጥቶት የተመረጠ ሲሆን፡ ይዘቱም የIጣሊያ ጥቅም የሚጠበቀው በIትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት Eና በIጣሊያ Aስተዳዳር ሥር በነበሩት የIትዮጵያ Aጐራባች Aገሮች መካካል መልካም ግንኙነት ሲኖር ነው የሚል ነበር። ይህ Eንዲፈጸም የIጣሊያ ፖሊሲ ስልጣን “በAዲስ Aበባና በሸዋ መኳንንት ዙርያ” መጠቃለል Aለበት የሚል ነበር1።
“ፖለቲካ ትግርኛ” ግን በጣሊያን የኮሎኒ ጉዳዮች ጽ/ቤት የሚደገፍ ሆኖ የ “ፖለቲካ ሸዋና” ተጻራሪ ነበር፡፡ የዚህ መመርያ ትርጉም ወይም ይዘት Iትዮጵያን ለመቆጣጠር የሚያገለግለው ዘዴ “የሸዋን ማEከልነት” ለሚቃወሙ ክፍሎችን መደገፍና ማበረታታት ነው የሚል ነበር። ትግራይን በሚመለከት፡ በተለምዶ በAካባቢው ሲገዙ የነበሩት ሥልጣናቸው Eንዳለ Eንዲቀጥሉ Eና ሃይላቸውም Eንዲበራታ በማድረግ ማEከላዊው የሸዋ መንግሥት ቁጥጥሩ Eንዲላላ Eና Eንዲዳከም ለማድረግ ነበር የፖለቲካ ትግርኛ ፖሊሲ Aቋም።
Eንግሊዞች በኤርትራ ራስ ገዝ ወታደራዊ Aስተዳዳር Aቋቁመው በነበሩበት ወቅት በ1941 ዓ.ም ከጣሊያን መንግሥት ቁጥጥር ነፃ የሆነችውን Iትዮጵያንም በAዲስ የቅኝ ግዛት መልክ ለመቆጣጠር ይሞክሩ ነበር። ይህ Eቅድ ተግባራዊ ለማድረግ Eንዲቻላቸው ከላይ ከተገለጹት ሁለት ንድፎች “ፖለቲካ ትግርኛ” የተባለችውን መርጠው መመሪያቸው Aደረጓት። የኤርትራን ጉዳይም ”ፖለቲካ ትግርኛ” ለሚለው ፖሊሲያቸው Aመች ሆኖ በሚያገለግል መንገድ ተያያዙት።
የEንግዚዝ ወታደራዊ Aስተዳዳር በኤርትራ የተከተለው መመሪያ “ፖለቲካ ትግርኛ’ የምትለዋን ፖሊሲ ሲሆን፡ በዋናነት ትኩረቱ “ትግራይን ከIትዮጵያ ነጥሎ ከኤርትራ ጋር
1 . ሃጋይ ኤርሊክ፡ ገፅ 195
4
ኤርትራ Eንደ Eናት Aገር ፣ ችግሮችና ፈተናዎች ትናንትም ዛሬም
ለማዋሃድ ነበር”። ትግራይ ከIትዮጵያ በተግባር ተነጥላ ከኤርትራ ጋር ከተዋሃደች በኋላ ሁለቱን ያጣመረ “ሃገረ-ትግራይ” የሚባል Aገር ይቋቋማል። ይህ Aገር በEንግዚዞች ቁጥጥር ሥር Eንዲዋቀር ሆኖ ማEከላዊነቷ ከተናጋው Iትዮጵያ ጋር የላላ ግንኙነት ይኖረዋል፡፡ በተጓዳኙም ኤርትራንም ለመገነጣጠል የወጠነ Eቅድ ነበር። በዚህ Eቅድ (ፕሮጀክት) መሰረት ኤርትራ ወደ ሁለት ወይም ሶስት ልትከፋፈል ነበር፡፡ ምEራባዊው ቆላማ Aከባቢ ወደ ሱዳን Eንዲጠቃለል ታስቦ ነበር፤ Eዚህ ላይ መገንዘብ ያለብን በወቅቱ ሱዳን የEንግሊዝ ቅኝ ግዛት መሆኗን፡ Eና Eንደ Aስተማማኝ ደጀን ትታይ Eንደነበረች ነው2።በተጨማሪ፡ ከምጽዋ ወደ ደቡብ በኩል ያለው የባሕር ዳር በሙሉ ወደ Iትዮጵያ Eንዲጠቃለል ታቅዶ ነበር3። ደጋማው የኤርትራ ክፍል - Eስከ ምጽዋ ያለውን Aከባቢ ጨምሮ - በሙሉ ወደ ትግራይ ተጠቃልሎ ነው “ሃገረ-ትግራይ” የሚባለውን Aገር ለመመሥረት ታልሞ የነበረው።
ይህንን Eቅድ ሥራ ላይ ለማዋል የኤርትራ ወታደራዊ Aስተዳደሪ የነበረው ስተፈን ሎንግሪግ” ‘ትግራይ ብሔረተኝነት’ (Tigrean nationalism) የሚለውን ፅንሰ-ሃሳብ በሰፊው ለማራገብ ተንቀሳቀሰ፣ በኤርትራ ፖለቲካም Eንዲስተጋባ Aደረገ። ይበልጥኑ ደግሞ Eንግሊዞቹ የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ በሆነ በደጋማው የኤርትራ ክፍል በሚኖረው ትግርኛ ተናጋሪ የታቀደው የብሔረተኝነት ስሜት Eንዲስፋፋ በከፍተኛ ጥረት ተንቀሳቀሱ4።
ዓላማው Eንዲሳካም የኤርትራ ሕዝብ በፖለቲካ መስክ ገብቶ Eርስ በEርሱ መከራከርና መነታረክ ነበረበት። ለዚህ ዓላማ ነው Eንግሊዞች የፕረስ ነፃነትና የፖለቲካ ማሕበሮች በAስቸኳይ Eንዲቋቋሙ ያደረጉት5። በEርግጥ Eነኚህ ነገሮች ሁሉ ለራሳቸው ተፈላጊ ናቸው፣ ለሕብረተስብ Eድገትም ቢሆን የሚረዱ ናቸው። ቢሆንም Eንግሊዞች ይህንን ሲያቋቁሙ ለራሳቸው ጥቅም - ማለት ሕዝባችን Eርስ በEርሱ Eንዲባላ - መኖሩን ግንዛቤ ውስጥ ማስገባት Aለብን።
የኤርትራ የፖለቲካ ሁኔታ በEንግሊዞች ሴራ ተነድፎ በነበረበት ፈታኝ ወቅት ነበር ወላጆቻችን መጪው የAገራቸውን Eድል ለመወሰን በንቃት የተሳተፉት፡፡ ኤርትራ ምን ትሁን በሚለው ጥያቄ በAመለካከት Eንደሚለያዩ Aይቀሬ ነበር። ስለሆነም ተለያዩ። Aንዳንንዱ ሙሉ በሙሉ ከIትዮጵያ ጋር በAንድነት የመዋሃድ ፍላጐት ሲያስተጋቡ፡ Aንዳንዶቹም ሙሉ ነፃነት የሚለውን Aቋም ሲያራምዱ፡ ሌሎችም ‘ፕሮተክቶረት’ - ማለትም በተባበሩት መንግሥታት ወይንም በEንግሊዝ ጥበቃና ቁጥጥር ሥር - ይሻላል ሲሉ ነበር። ኤርትራን ከፋፍለህ ወደ ሱዳን Eና ወደ Iትዮጵያ ማዋሃድ የሚለው Aገር የሚያጠፋ ሃሳብ በተግባር Eንዲውልም ቀያሾቹ ባለ በሌለ ሃይላቸው በሰፊው ተንቀሳቀሱ።
- ፪ -
የኤርትራን ነጻነት ከሚፈልጉት የፖለቲካ ማሕበሮች መካካል Aንዱ በይፋ የሚታወቅበት ስሙ „የኤርትራ ነፃነትና የEድገት ማሕበር- ኤርትራ ለኤርትራውያን“ (ምህጻረ- ስሙም “ኤርትራ ንኤርትራውያን“) ሆኖ፡ Eንግሊዞች ደግሞ ሊበራል ፕሮግረሲቭ ፓርቲ በማለት ሲጠሩት የነበረው ነው። ይህ ማሕበር፤ በተለይ ወደ መጀመሪያው ወቅት ኤርትራ ወደ
2 . ዝኒ ከማሁ
3 . ዝኒ ከማሁ ገፅ 222
4 . ዝኒ ከማሁ ገፅ 225
5 . ዝኒ ከማሁ ገፅ 225-226
5
የመወያያ ሰነድ (Discussion paper)፣ ጀኑዋሪ 2013
ደቡብ ከመረብ ወንዝ ወዲያ ካሉት Aገሮች (Aካባቢዎች)፡ ማለትም ከትግራይ Eና ከትግራይ ወዲያ ካሉት ትግርኛ ከሚናገሩ Aካባቢዎች፡ ጋር ተዋህዳ ‚ከEንግሊዝ ሞግዚትነት በኋላ ሉዓላዊት Aገር Eንደትሆን የሚል Aቋም ነበረው6። ይህ Aቋም “ትግራይ- ትግርኚ” ተብሎ የሚታወቀው መመሪያ (ፕላትፎርም) ነው።
Eንግዲህ “ኤርትራ ንኤርትራውያን“ የሚለው ሀረግ የ“ትግራይ-ትግርኚ” መፎክር ብቻ ነበር7። ታስባ፡ “ብሔረ AግAዚ” ወይም “”ምድረ AግAዚ” Eየተባለች ስትጠቀስ የነበረችው Aካል የምናውቃት ከመረብ ወዲያ ያለቺው Aገር ሳትሆን በምስራቅ Aለውሃ-ምላሽ” በምEራብ ደግሞ “ተከዜ- ምላሽ” በመላ ያጠቃለለች ነበረች። ኋላ ግን፡ ቆየት ብለን Eንደምናየው፡ በAንዳንድ Aዳዲስ ክስተቶች ምክንያት ኤርትራ ለኤርትራዊያን በሚለው ማሕበር ውስጥ የAመለካከት ልዩነት በመነሳቱ “Aለውሃ-ምላሽ” የሚለው Aቋም (ወይም ጥያቄ) Eየደበዘዘ መጣ።
የትግራይ-ትግርኚ ዓላማና ፍላጐት በመንፈሱ ምን Aንደነበረ ጠለቅ ብለን ማወቅ ሊኖርብን ነው። ምናልባትም ታሪክ Eራሱ Eየደገመ Aንዳይሆን!!
Aንደ ፕሮፈሰር Aለም-ሰገድ Aባይ Aገላለጽ፡ ትግራይ-ትግርኚ Aንድ የሪሶረጂሜንቶ ናሺናሊዝም፡ ማለት የማነሳሳት ወይንም በተዳከመ የማንነት መንፈስ ላይ ‘ትንፋሽን የመዝራት’ ብሄርተኝነት፡ ምሳሌ ወይም ዓይነት ነው8። ሪሶርጂሜንቶ በ19ኛው ክ/ዘመን ዛሬ Iጣሊያ ተብሎ በሚታወቀው Aከባቢ የተካሄደ Aንቅስቃሴ ነው። Eስከ 1870 ዓ.ም በዛው ወቅት የነበሩ ጣሊያንኛ የሚናገሩ Aህዛብ በተለያዩ ግዛቶች ተበታትነው ሲኖሩ ነበር። ያ ሪሶረጂሜንቶ የተባለው Eንቅስቃሴ Eንግዲህ Eነዚያን ተለያይተው ይኖሩ የነበሩትን ጣልያንኛ ተናጋሪዎች በሙሉ ከያሉበት Aሰባስቦ “Aንዲት Iጣሊያ” የምትባል Aገር ለመመስረት ሲካሄድ የነበረው የባህልና የፖለቲካ Aነሳሽ Eንቅስቃሴ ነው።
ኤርትራን፡ ማለት የትግራይ ትግርኚን Eንቅስቃሴ፡ በሚመለከት ይህ የሚሰጠው ትርጉም ምንድ ነው? ይህ ማለት ከAክሱም ሥልጣኔ ጀምሮ ትግርኛ የሚናገር ሕዝብ የራሱ የሆነ ባህል፡ ሃይማኖትና የማንነት ስሜት የነበረውና Aሁንም ያለው፡ ሲቀላቀልም የነበረና ያለም በመሆኑ Aንድ Aገር መሆን Aለበት የሚል ነው። Aለምሰገድ Aባይ Eንደሚለው የትግራይ-ትግርኚ መሠረታዊ Eምነት “በጥንታዊነት ላይ የተመረኰዘ ሆኖ ትግርኛ ተናጋሪው ሁሉ በAንድ የፖለቲካ ጥላ ሥር”፡ ማለት በAንድ Aገራዊ ክልል ውስጥ፡ የመሰባሰቡ ፍልስፍና ነበር9።
ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ፍጻሜ በኋላ “ፎር -ፓወር ኮሚሽን” ማለትም Aራቱ ሃያላን መንግሥታት የተባሉት፡ ማለት የAሜሪካ፡ የሩሲያ፡ የፈረንሳይ Eና የEንግሊዝ ተወካዮች የኤርትራን ሕዝብ ፍላጐት ለማጥናትና ለማረጋገጥ ወደ ኤርትራ በሄዱ ጊዜ “ኤርትራ ለኤርትራዊያን” ይባል የነበረው ማሕበር የማሳሰቢያ ጽሁፍ Aቀረበላቸው። ባቀረበው ጽሁፍ መሰረት ትግራይ በጂOግራፊያዊ Aቀማመጥ፡ በባህል፡ በታሪክና በንግድ ግንኙነት” ጥንት Aንደነበረችው “የኤርትራ Aካል ነች” በማለት ቀደም ብሎ “ትግራይ-ከኤርትራ ጋር
6 . ኣለምሰገድ ተስፋይ፡ ገፅ 225
7 . ኣለምሰገድ ኣባይ፣ (1997) ገፅ 325
8 . ዝኒ ከማሁ(1998)፡ ገፅ 153
9 . ዝኒ ከማሁ፡ ገፅ 163
6
ኤርትራ Eንደ Eናት Aገር ፣ ችግሮችና ፈተናዎች ትናንትም ዛሬም
ማዋሃድ” ከሚለው የEንግሊዝ Eቅድ ጋር ሠምሮ የሚሄድ Aቋም Aሰማ። በማያሻማ Aገላለጽ የትግራይ-ትግርኚን መሠረታዊ-Eምነት Eንደሚከተለው Aንፀባረቀ10።
“በሰሜን Iትዮጵያ የተካሄዱ ጦርነቶች በሙሉ፤ ማለትም ጸረ- ጣሊያን፡ ግብጽ Eና Eንዲሁም መተማ ላይም ከድርቡሽ ጋር የተካሄደ ጦርነት በኤርትራና በትግራይ ሕዝብና መኳንንት Eንጂ በሸዋዊያን Aልነበረም። ይህም የሚያመላክተው፡ የዚያ ትግርኛ ተናጋሪ ሕዝብ የAካባቢ ጂOግራፊያዊ ጐሳዊ Eና ታሪካዊ ሥር-መሠረት ከሸዋ ጋር የሚያገናኝ ወይም የሚያጋራ Eንደሌለው ነው። ስለ ጥንት ዘመን ስናወሳም ቢሆን የIትዮጵያ ሥልጣኔ ከኤርትራና ትግራይ (ከAክሱም) ነው የመነጨው Eንጂ ከሸዋ ተነስቶ ወደ ሰሜን Aልመጣም። በዛኛው ወቅት ሸዋዊያን ያልሰለጠኑ ዘላኖች (ኖማድስ) ነው የነበሩት። Eንዳውም በዛው ጊዜ ሸዋ የነዚያ የትግርኛ ተናጋሪ ሕዝቦች ቀኝ ግዛት (ኮሎኒ) Eንደነበረች በEርግጠኛነት መጥቀስ ይገባል”11።
ይህ Aባባል የሚያብራራው ነጥብ ቢኖር የኤርትራ ለኤርትራውያን መሪ ሃሳብ፡ በፕሮፈሰር ተኸስተ ነጋሽ Aገላለጽ፡ ”በትግራይ ሕዝብ ጥንታዊ ሞገስና ክብር፡ Eና ይህ ህዝብ ከድሮ ጀምሮ በIትዮጵያ በነበረው የልEልና Eና የመሪነት ቦታ ትዝታ ላይ የተመሰረተ መኖሩን ነው12።” ይህ Aቋም የበላይነትን የሚያንጸባርቅ የትምክሕት መንፈስ የቃኘው Eንደነበር ግልጽ ነው። በተጨማሪም የሽዋን መንግሥትነት የማይቀበል የፖለቲካ ትግርኛ ጉልህ መግለጫ ነበር።
Aብሮ ከዚህ ጋር በተያያዘ መጠቀስ ያለበት Aንድ ነጥብ Aለ። ይኸውም “ኤርትራ ለኤርትራዊያን” ሲሉ ከነበሩት Aንዳንድ Aባቶች መሃል Aባባላቸው የ“Iሪደንቲዝም” - ማለት፡ በሌላ Aገር (Aካባቢ) Aስተዳዳር ሥር የሚገኝ መሬት “የኔ ነው” ብለህ ወደ ግዛትህ የማጠቃለል - ገጽታ Eንደነበረው ነው። የተፈለገው መሬትም ዛሬ በምስራቅ ሱዳን የሚገኝ፡ ከሰላንም ጨምሮ፡ ያጠቃለለ ነበር።
ከጥንት ጀምሮ ኤርትራ ወይንም ትግራይ ትግርኚን በሚመለከት በቅጡ ያላስተዋልነው Aንድ Aሳሳቢ ጥያቄ Aለ። ይኸውም “ትግራይ -ትግርኚ” ሲባል ለነበረው ውጥን “Aገር” ማን Aንዲመራው ነበር የታሰበው? የሚል ነው። ለዚህም ጥያቄ መልሱ፡ ባለፉት በርካታ Aመታት ልብ Aላልነውም Eንጂ፡ ግልጽ ነው የነበረው። ብያንስ የAብዛኛዎቹ ‘የ‘ኤርትራ ለኤርትራውያን’ ማሕበር Aባሎች ሃሳብ ያ ትግራይ-ትግርኚ የተባለው Aገር በትግራይ መኳንንት (ትግሪያን Aሪስቶክራሲ) ሥር Eንዲመራ ነበር። ይህንን Aስመልክተው Aንዳንድ በወቅቱ የነበሩ የደጋማው ኤርትራ ክፍል ሊሂቃን (ኤሊቶች) የትግራይ መኳንንት ህጋውያን መሪዎቻችን ናቸው የሚል Eምነት ነበራቸው። ስለሆነም Eቅዱ ቢሳካ “ራስ ስዩም መንገሻ (የAጼ ዮሃንስ የልጅ ልጅ) የትግራይ-ትግርኚ መሪ መሆን ይችሉ ነበር የሚል ሀሳብ ነበራቸው13።
የትግራይ-ትግርኚ Aገራዊ (ብሔራዊ) Eንቅስቃሴ ከመረብ ወንዝ ባሻገር (ወዲያ)፡ ማለትም ትግራይ ውስጥ፡ የጐላ Aልነበረም። በሌላ Aነጋገር፡ ያ ትግራይ-ትግርኚ የሚል ሃሳብ የትግራይን ሕዝብ ቀልብ Aልሳበም ነበር14። ነገር ግን Aንዳንድ ከትግራይ መኳንንት
10 . ኣለምሰገድ ኣባይ፣ (1997) ገፅ 325
11 . ተኸስተ ነጋሽ በገፅ 170 ላይ Eንደጠቀሰው
12 . ዝኒ ከማሁ ገፅ 161
13 . ኣለምሰገድ ኣባይ (1998): ገጽ 43፣ Eንዲሁም ሪቻርድ ገሪንፊልድ ገጽ 26
14. መድሃኔ ታደሰ፡ ገጽ 34
7
የመወያያ ሰነድ (Discussion paper)፣ ጀኑዋሪ 2013
ውስጥ ቢያንስ ለተወሰነ ጊዜ ትግራይ-ትግርኚ የሚለውን ሃሳብ Aስተናግደውት Eንደነበር Aንዳንድ ታዛቢዎች ይገልጻሉ። ለምሳሌ Eነ ራስ ሥዩም መንገሻ Eና ኃይለስላሴ ጉግሳ ትግራይ ከIትዮጵያ Eንድትገነጠል የደገፉበት ወቅት (Aዝማሚያ) የነበረ ይመስላል15፣ ሁለቱም ባንዳንድ መድረኮች ለጊዜው በታላቋ ብሪታኒያ ወይንም በሌላ የውጭ ሃይል Eንክብካቤ ሥር የሆነ የኤርትራና የትግራይ Aንድነት Aንዲመሠረት ፍላጐት ነበራቸው ይባላል16።
የትግራይ ትግርኚ Aንቅስቃሴ ከትግራይ ይልቅ ኤርትራ ውስጥ የበለጠ ህላዌ ነበረው። Eሱም ቢሆን በተወሰኑ የኤርትራ የደጋማው ክፍሎች ብቻ ነበር17፡፡ ባጠቃላይ Aንግሊዞች የትግራይ ትግርኚ ስሜት በክርስትያኑ ደጋማው ክፍል ተቀባይነት Aንዲኖረው ያደረጉት ሙከራ Aልተሳካላቸውም። ፕሮፌሰር ሃጋይ Aርሊክ Eንደገለጸው Eነኚያ መጠነኛ “ዘመናዊ ትምህርት” የቀሰሙ ወይንም ከተሜዎች ሆነው የነበሩ ኤርትራዊያን “ሲነሳሱት የነበረው ዘመናዊነትን በተላበሰ ሃሳብ (ወይም ራEይ)“ ነበር፡፡ ትግራይ ደግሞ የዘመናዊነት ሳይሆን፡ የኋላ ቀርነትና የወግ Aጥባቂነት ተምሳሌት ሆና ትታይ ነበር። Eንግዳውስ Aብዛኛዎቹ የፖለቲካ መሪዎች የነበሩ ወጣት ኤርትራዊያኖች የነበራቸውን “Aዲስ ፖለቲካዊ ራEይ” ከIትዮጵያዊነት ጋር Aያያዙት፣ “Aድናቆታቸውም ለኃይለስላሴ ሆነ”18።
ቀደም ብሎ Eንደተገለፀው፡ Eንግሊዞቹ ራሳቸው የሚቆጣጠሩት የትግራይና የኤርትራ ውህደት ሊመሠረት ፍላጐት ነበራቸው። ቆይተው ግን በፖለቲካ ሁኔታው ለውጥ ሲከሰት፡ ይህንን ሃሳብ ትተው፡ በAሜሪካኖች የቀረበው ፈደራላዊ መፍትሔ፡ ማለትም ከIትዮጵያ ጋር ዋስትና ያለው Aንድነትን ደገፉ። Aንዳንድ የኤርትራ-ለኤርትራዊያን ይባል የነበረው ማሕበር መሪዎችና የታወቁ Aባላትም Aቋማቸውን ለውጠው መካከለኛውን መፍትሄ - ማለት ፈደረሽንን ተቀበሉ። ይህንን ለውጥ ያደረጉትም ብርጋደር ፍራንክ ስታፈርድ የተባለው የታላቋ ብሪታኒያ ወኪል ባከሄደው “ሴራ” ከማሕበሩ ተነጥለው “የነፃነት ሕብረት ከIትዮጵያ ጋር” (“ናጽነታዊ ሕብረት ምስ Iትዮጵያ“) የሚል Aዲስ ማሕበር ካቋቋሙ በኋላ ነው19።
ይህን ‘ፈደረሽን” የተባለውን Aማራጭ ሁሉም የፖለቲካ ማሕበሮች ነበር የተቀበሉት። ሲቀበሉትም ምክንያታቸው የወደዱት ምርጫቸው ሆኖ ሳይሆን፡ Eነሱ Aንደሚሉት ኤርትራ Eንደ Aንድ ወጥ Aካል ሆና Aንድትቀጥል Aንድ Eና ብቸኛው መንገድ ፈደረሽን ብቻ ስለነበረ ነው። ለምሳሌ የዚያ የነፃነት ጐራ (Iንዲፐንደንስ ብሎክ) የተባለው ነፃነት ሲጠይቁ የነበሩት ማህበሮች ቅንጅት ፕረዚደንት፡ ራስ ተሰማ Aስበሮም፡ ቀንደኛው የ“ትግራይ-ትግርኚ” ፖለቲካ Aንቀሳቃሽ የነበሩ ቢሆንም፡ በተባበሩት መንግሥታት የተወሰነውን ፈደረሽን ተቀበሉት፣ Eንደ ድልም ቆጠሩት። ይህ Aቋም በነበረው ሁኔታ ትክክለኛነት Eንዳለው ለመግለጽ የሚከተለውን Aሉ። “Eኛ ….. የታገልንለት …. ሙሉ ነፃነት“ Eንደተመኘነው ባይሳካም፡ “ይህ የተገኘው ድል ሁላችንንም ሊጠቅመን ይገባል። ይህን ድል በመጎናጸፋችን Aገራችን Aልተቆራረጠችም፣ ሕዝባችንም Aልተከፋፈለም“20።
15. ሃጋይ ኤርሊክ፡ ገጽ 201፣ 202
16. ኣለምሰገድ ኣባይ (1998)፤ ገጽ 50
17. ኣለምሰገድ ተስፋይ፡ ገጽ 227-228
18. ሃጋይ ኤርሊክ፡ ገጽ 226
19. ኣለምሰገድ ተስፋይ ገጽ 425-428
20. ኣለምሰገድ ተስፋይ በገጽ 519 ላይ Eንደጠቀሰው
8
ኤርትራ Eንደ Eናት Aገር ፣ ችግሮችና ፈተናዎች ትናንትም ዛሬም
ለነፃነት ሲታገሉ የነበሩት Aባቶቻችን ፌደረሽኑን ሲቀበሉት ከውስጣዊ ስጋት ጋር Eንደነበር መገመት Aያዳግትም። ለምሳሌ Aንጋፋው ታጋይ Aቦይ ወልደAብ ወልደማርያም “ገደል ላለመግባት የEሾህ ቀጋን መታቀፍ” (ከይጸድፉ ቆንጠጠፈ ይሓቑፉ)“21 የሚለውን ተረት በመጥቀስ የሁኔታውን Aስቸጋሪነት ገልፀው ነበር ይባላል። Aንግዲያውስ ‘የኤርትራ Aንድነት’ ለAባቶቻችን የመጨረሻው ‘ክቡር’ ግብ (ስትራተጂካዊ ነገር) ነበር። ፈደረሽኑም በነሱ Aመለካካት ለግባቸው መዳረሻ ዘዴ ነው የነበረው።
የAፄ ኃይለስላሴ መንግሥትም ፈደረሽኑን የተቀበለው ከልብ ረክቶበትና Aምኖበት Aልነበረም። Aማራጭ ስላልነበረው ብቻ ነው። በወቅቱ ከIትዮጵያ ጋር ሙሉ በሙሉ መዋሃድ ሲሉ ከነበሩ ኤርትራውያን ይልቅ በAንጻር የቆሙት ብዛት ነበራቸው። በተባበሩት መንግሥታትም የIትዮጵያ የይገባኛል ጥያቄ በቂ ደገፍ Aልነበረውም። በዚህ ምክንያትም Aፄ ኃይለ ሥላሴ ፈደረሽኑን የተቀበሉት ቀስ Eያሉ Aፍርሰው ኤርትራን መጠቅለል Aንደሚችሉ ተመክረው ስለነበረ መሆኑ ዶ/ር Aማረ ተኽለ በ1964 ባዘጋጀው ሰፊ ጥናት Aመልክቷል22።
ፈደረሽኑ በሕግ የተደነገገ የጊዜ ገደብ Aልነበረውም። ሆኖም ፈደረሽኑ ለ10 Aመታት ነው Eየተባለ በወሬ ደረጃ Aንዲስተጋባ ተደረገ። የዚያ ወሬ ስርጭት ፈደረሽኑን ለማፍረስ የሚያመቻች የስነ-AEምሮ ምንጣፍ ዘረጋ። ያንን ምንጣፍ ዘርግቶ፡ የAፄ ኃይለስላሴ መንግስት ፈደረሽኑን ቀስ በቀስ በመሸርሸር በ1962 ማለት ከ10 Aመት በኋላ በAንዳንድ ኤርትራዊያን ትብብር Aፈረሰው። ፈደረሽን የተባለውን ስርዓት Aንደ መሸጋገሪያ ተጠቀመበት።
Aንግዳውስ ለAጼ ኃይለስላሴ መንግስት ፈደረሽን ዘዴ ብቻ ነበር። ዋናው ግቡ ወይም ስትራተጂው ዞሮ ዞሮ ኤርትራን ጠቅልሎ ማስገባት ነው የነበረው።
የነበረው ፈደረሽን መሸጋገሪያ ብቻ Aንደነበር ልናስታውሰውና ልናሰምርበት የሚገባ ነጥብ ነው። ለምን ቢባል ዛሬም ባለንበት Aዲስ ሁኔታ ታሪክ በሆነ ነገር Eየተደገመ Aንዳይሆን!!
- ፫ -
በ1961 - ፈደረሽኑ በይፋ ሊፈርስ Aጥቢያ - የኤርትራ Aርነት ገድል (ተጋድሎ ሓርነት ኤርትራ - ተ.ሓ.ኤ)፡ በሓሚድ Eድሪስ ዓወተ ወታደራዊ መሪነት የትጥቅ ትግል ይፋ Aደረገ። መግለጫቸው የAገራችን የብሄርና የሃይማኖት Aወቃቀር Eና የቅርብ ታሪካችን ይዘት የሆነ መሰናክሎች ለኤርትራ Aብዮት በትግሉ Aፍላ ወቅት ችግሮች ፈጠሩበት፡፡
Iሳያስ ኣፍወርቂ ከ1970 ዓ. ም. Aንስቶ የራሱን ድርጅት ለመመስረት በተንቀሳቀሰበት ወቅት ከላይ የተጠቀሰው የኤርትራ ሕብረተሰብ Aደረጃጀት Eና በተ.ሐ.ኤ የታየውን ውስጣዊ መንገራገጭ ያለ ምንም ምሕረት መዘመዘው። Iሳያስ “ንሕናን Eላማናን” (Eኛ Eና Aላማችን) በሚለው Aዋጁ ሕዝብን ለማታለል ለመላ ኤርትራ “በAገራዊ የAንድነት ልሳን” Aለዝቦ በተቀመረ ቋንቋ ያስተላልፍ Aንጂ ሕዝበ ክርስትያን የሆነ ኤርትራዊ ሁሉ Aንዲከተለው ነው ጮክ ብሎ የተማጠነው። Eኛ Eና Aላማችን (ንሕናን Eላማናን) የምትለዋ ሰነድ የሕዝብ ሁኔታ ያስጨነቃት ወይንም የሕዝብ መብት ጉዳይ ያሳሰባት ሰነድ Aልነበረችም። ይልቁንስ ሰነድዋ Iሳያስ ስስታም (የስልጣን) ሕልሙን ለማርካት መነሻ
21. ኣለምሰገድ ኣባይ (1998): ገጽ 72
22. ኣማረ ተኽለ፡ ገጽ 353
9
የመወያያ ሰነድ (Discussion paper)፣ ጀኑዋሪ 2013
ያደረገ ክፋት ያጠነጠነች Aዋጅ ነበረች። ታጋይ ረድI መሓሪ ባሁኑ ወቅት ታዋቂነትን ባገኘው Aዲሱ መጽሐፍ Aንዳመለከተው፡ Iሳያስ ሕዝባችንን ለማሞኘት ሲል ነው “Eኛና Aላማችን” (ንሕናን Eላማናን) ያላት Eንጂ AርEስተዋስ “Eኔ Eና Aላማዬ” (ኣነን Eላማይን) ነው መሆን የነበረበት23።
Iሳያስ ኣፍወርቂ ወደ ትግሉ ሲቀላቀል Eውነተኛ Aላማውና ፍላጐቱ የኤርትራ ሉዓላዊ ነጻነት Aልነበረም። በታላቅ ጥንቃቄ ደብቆ ሲንቀሳቀስባት የነበረችው Aላማ “ትግራይ-ትግርኚ” Aንደነበረች ረድI መሓሪ፤ ተስፋይ ተምነዎ፡ Aንዲሁም ሌሎች የሕዝባዊ ግምባር ታጋዮች የነበሩ ደጋግመው ነግረውናል።
በትግሉ ወቅትም ቢሆን Iሳያስ Eና ተባባሪዎቹ ዋናው ግባቸው “ትግራይ ትግርኚ” Aንደነበረ፡ ሆን ብለው ይሁን ወይንም ሳይታወቃቸው፡ በግልጽ ያመለከቱበት ጊዜ ነበር። ለምሳሌ በብሩህነቱና በጥልቅ Aዋቂነቱ የሚመሰገን ረነ ሌፎርት የተባለው የፈረንሳይ ጋዜጠኛ በወቅቱ ሕዝባዊ ግምባር ተቆጣጥሮ ወታደራዊ ትግል ሲያካሂድበት ወደ ነበረው የኤርትራ በረሃ በመዝለቅ ጉብኘት ባደረገበት ጊዜ የታዘባት ነገር Aለች፡፡ በ1983 ዓ. ም. ባሳተመው መጽሃፉ ከመሪዎቹ Aንዱ ስለ ድርጅቱ ረዢም መግለጫ ሲያደርግ ሰማሁት ይላል። መሪው በማግለጫው “የኤርትራ ትግል ዓላማ” ምን Eንደሆነ Aስረድቶ ሲደመድም “Eኛ የAክሱም ንጉሥነት ወራሾች ነን፤ ከዚህ የሸዋ መንግስት ጋር የሚያገናኘን Aንዳችም ነገር Aይኖርም!” Aለ። ብልህ ታዘቢው ረነ ለፎርት Aንዲህ ያለ ጀሮ የሚስብ ንግግር በቀላሉ የተሠነዘረ Aንዳልሆነና ከበድ ያለ ይዘት የነበረው መሆኑን በመጽሐፉ ዘገበ24።
Iሳያስ Aፈወርቂ በህዝባዊ ግንባር ድርጅት ጉልበት ያዳበረው ወደ 70ኛው ግማሽ Aካባቢ የAፄ ኃይለስላሴን መንግስት Eና ዘውዳዊ ስርዓቱን ከነጭራሹ Iትዮጵያ ውስጥ መንግሎ የጣለው Aብዮት ከተከሰተ በኋላ ነው። በተካሄደው የIትዮጵያ Aብዮት ውስጥ ደርግ ጠቅልሎ ስልጣን ያዘ፣ ብዙም ሳይቆይ የሕብረተ-ሰብAዊነትን Aቅጣጫ Eንከተላለን ብሎ ከሶቪየት ሕብረት ጋር ተዛመደ። ወቅቱ ቀዝቃዛ ጦርነት ተብሎ የሚታወቀው ሆኖ በሶቭየት ሕብረት በሚመራው ምስራቃዊ ጎራ Eና በAሜሪካኖች ሲመራ በነበረው ምEራባዊ ጐራ መካከል የስነ ሓሳብና ስተራተጂ ፍክክር ሲካሄድበት የነበረ ነው።
የደርግ ከምስራቃዊው ጐራ መጐዳኘት ለAሜሪካኖቹና ለምEራባዊያን የሕሊና Eረፍት ነሳቸው። ስለሆነም ደርግን Aንዴት Aንደሚጥሉት ጥናት Aደረጉ። ይኸውም ንድፍ የኤርትራን Aብዮት ደርግን ለመጣል መጠቀም ሆኖ፡ በሚከተለው ትንታኔ ላይ የተንተራሰ ነበር።
በትጥቅ ትግል ደርግን ሲፋለሙ ከነበሩት ንቅናቄዎች ሁሉ የጠነከረው ያ ጀብሃንና ሻEቢያን ያቀፈ የኤርትራ Aብዮት ነበር። ችግሩ፡ በAመሪካኖቹ የፖለቲካና ስትራተጂ ቀያሾች Aባባል፡ የኤርትራ ድርጅቶች ዓላማ ሙሉ ነፃነት፡ ማለት ከIትዮጵያ መገንጠል መሆኑ ነበር። ይህ ዓላማ ከAሜሪካኖቹ ስትራተጂ ጋር የሚጣጣም Aይደለም፣ ምክንያቱም ኤርትራ ለብቻዋ ከሆነች ለEስራኤል ጠንቅ መሆኗን ስለማይቀር። ስለዚህም፡ የAሜሪካኖቹ ሃሳብ የኤርትራን Aብዮት Eንጠቀምበት፣ ስንጠቀምበት ግን የኤርትራ ነፃ መውጣት ለEስራኤል Aደጋ በማይሆንበት መንገድ ወይም Aኳሃን መሆን Aለበት የሚል ነበር።
23. ረድI መሓሪ፤ ገጽ፡ 114
24. ረነ ለፎርት፡ ገጽ 268
10
ኤርትራ Eንደ Eናት Aገር ፣ ችግሮችና ፈተናዎች ትናንትም ዛሬም
የኤርትራን ጥያቄ በዚህ Aገባብ ለመፍታት የተለያዩ ሃሳቦች በAሜሪካውያን ጠበብት ቀረቡ። ከነሱም Aስፈላጊ የሆኑት የሚከተሉት ሁለት ሃሳቦች ናቸው፡፡
Aንደኛው ሃሳብ፡ የተ.ሓ.ህ.ት (የዛሬው ሕዝባዊ ወያኔ) መመስረት ከግምት በማስገባት፡ ትግራይ ውስጥ የመገንጠል ንቅናቄ ስላለ የኤርትራ ከIትዮጵያ መለየት ለEስራኤል ጠንቅ Aይሆንም የሚል ነበር፡፡ ትግራይ ከተገነጠለች በኋላ በሆነ መልክ ከኤርትራ ጋር መዋሃዷ የማይቀር ነው፣ የተባበረው Aገር Aብዛኛው ሕዝብ ደግሞ ክርስትያን ነው የሚሆነው፡፡ ክርስትያን የበዙበት የተባበረው Aገር ለEስራል ጠንቅ ሊሆን Aይችልም። ይህንን ሃሳብ ፕሮፈሰር ቶም ፈረር የተባለ ሊቅ ለAሜሪካ የሕግ Aውጪ ሰኔት በነሐሴ 1975 Aቀረበ25።
ሁለተኛው ሃሳብ ወይም Eቅድ ደግሞ ጆን ስፐንሰር በተባለው ሊቅ የቀረበ ነበር። ይዘቱም የሚከተለው ነበር። ደርግን በመጣል ሶቭየቶችን ከAፍሪቃ ቀንድ ማስወጣት የሚችሉት የኤርትራ ነፃ Aውጪ ድርጅቶች ናቸው፤ የነዚህ ድርጅቶች ግብ ግን ኤርትራን ከIትዮጵያ ለመነጠል - ማለት ነፃነት ለማወጅ - ነው። የኤርትራ ነፃነት ግን Eኛ Aሜሪካዊያን የምንፈልገው ነገር Aይደለም። ታዲያ ይህ ከሆነ ምን መደረግ Aለበት? በሚለው ጥያቄ የሚከተለውን Eቅድ ነድፎ Aቀረበ። ይኸውም ነፃነት የሚለው Aንቅስቃሴ ደርግ Eስኪወድቅ ድረስ Eና ሶቭየት ሕብርትም ከAፍሪቃ ቀንድ Eስኪወጣ ድረስ ይቀጥል፡ ደርግ ተወግዶ ከAሜሪካ ፖሊሲ ጋር በሚጣጣም መንግሥት ሲተካ፡ ኤርትራ ነፃ ትሁን የሚል ነው።
የተባለው የኤርትራ ነፃነት ግን ዘላቂ ሳይሆን ላጭር ጊዜ ብቻ Eንዲቀጥል ነበር ሃሳቡ። ነፃነቱ፡ በጆን ስፐንሰር Aባባል “ፍሊቲንግ ኤክስፐሪየንስ“ - ዘለቄታነት የሌለው፤ ላጭር ጊዜ ብቻ የሚኖር ተሞክሮ (ልምድ) ነው የሚሆነው። በዚህ መሠረት Eንግዳውስ ኤርትራ ላጭር ጊዜ ብቻ ነው ነፃ Aገር የምትሆነው ማለት ነው። ታዲያ Aገሪቱ ምን ልትሆን ነው? በጆን ስፐንሰር ንድፍ ኤርትራ ሄዳ ሄዳ Eንደሚከተለው ተመታትራ ትጠፋለች። ይኼውም፦ ደጋማው ክፍልና ደንካልያ፡ Eንዲሁም ከምጽዋ ወደ ደቡብ በኩል Eስከ ባብ Aልመንደብ ድረስ ያለው የቀይ ባሕር ደንደስ Aካባቢ ወደ Iትዮጵያ ይገባል፤ ወደ Iትዮጵያ ገብቶ ግን የውስጥ Aስተዳደር ይኖረዋል፡፡ (መገንዘብ ያለብን ከIትዮጵያ ጋር ይዋሃዳል ሲባል Aብዛኛው ከትግራይ ጋር ማለት Eንደሆነ ነው፡ ምክንያቱም ኤርትራ Eና ትግራይ በድምብር በቀጥታ ይገናኛሉና)። ሌላው የኤርትራ ክፍል ደግሞ -ማለት ሳሕል Eና የተቀረው የEስልምና ሃይማኖት ተከታይ የሆኑት የሚኖሩበት የኤርትራ ምEራባዊ ቆላ ደግሞ ከሱዳን ጋር ይጠቃለላል። Aንግዲህ ኤርትራ በEንደዚህ ያለ ንድፍ ተመታትራ ትበታተናለች። ይኼ ነበር የስፐንሰር ንድፍ26።
ይህንን በሚመለከት ካሁን በፊት ደጋግሜ Aንደገለጽኩት የኤሜሪካ መንግሥት የፈረርን Eና የጆን ስፐንሰርን ንድፍ ግምት ውስጥ በማስገባት የፖሊሲው መሰረት ያደረገው ይመስላል።
ኤርትራ ተሰነጣጥቃ ህላዌዋ Eንዲጠፋ ባነጣጠረ ረጂም የምEራባውያን ስትራተጂ፡ ጀብሃ (ማለት ተ. ሓ. ኤ.) በህ. ግንባር (ሻEቢያ) Eና ወያኔ ጥምረት ተጠቅቶ፡ Aሁን Eንደሚመስለውም በራሱ በጀብሃ ውስጥ በነበሩት የሻEቢያ Aገልጋዮችና የውጭ Aካላት ቅጥረኞች ተቦርቡሮና ተሰናክሎ ሰፊ Aካሉ ተገፍቶ ከትግል ሜዳ ወጣ፡፡ ቀስ በቀስም የኤርትራ Aብዮት በIሳያስ ፖለቲካ መዳፍ ገባ። ስለዚህ ከ1980-81 ጀምሮ የተካሄደው
25. ዩ.ኤስ ኮንግረስ፡ ገጽ 106
26. ጆን ስፐንሰር፡ ገጽ 63-67
11
የመወያያ ሰነድ (Discussion paper)፣ ጀኑዋሪ 2013
ወታደራዊ ንቅናቄ “የኤርትራ Aብዮት“ የሚል ስያሜ ቢሰጠውም፡ ለሌላ ዓላማ - ማለት ለIሳያስ Eና ምEራባውያን Aጋሮቹ Eና Eንዲሁም ለሌሎች ተባባሪዎቹ ዓላማ - ነበር ያገለገለው። በሌላ Aነጋገር፡ከዚያን ጊዜ Aንስቶ “የኤርትራ Aብዮት” በEርግጥ በህልውና ያለ ወይም Eውነተኛ ነገር ሳይሆን ሕሊናን ለመጥለፍ የሚያገለግል Aጭበርባሪ “ምስል (Aስመሳይ)” ብቻ ነበር። ከረድI መሓሪ መጽሃፍ Aንዲት ውብ ሃረግ ተውሼ ይህንን Eውነታ በበለጠ ላብራራው Eሞክራለሁ። “ላም ልጇ ሞታባት፤ በጥጃ ምስል ለወራት ያክል ትታለባለች”27፡፡ Aንዲሁም የኤርትራ ወጣት Aብዮቱ ተጠልፎ Eያለ በAስመሳይ የኤርትራ Aብዮት ለAመታት ደሙ ሲታለብ ህይወቱም ሲፈጅ ኖሯል፡፡
ቀደም ብሎ Aንደተገለጸው የIሳያስ ፖለቲካ በ“ትግራይ-ትግርኚ” የተመሠረተ ነበር። በስነ ሞገት Aነጋገር (ሎጂክ) የትግሉ ወታደራዊ ፍልምያ ለትግራይ ትግርኚ ዓላማ በረዢሙ ያለመ Eንጂ፡ ሉዓላዊነቷና Aንድነቷ የተጠበቀ ኤርትራን መመስረት Aልነበረም። የኤርትራ ነፃነት መፈክር ወይም ስልት ነው የነበረው፡ Aሁንም ያለው።
Aሁን ያለው የኤርትራ ሁኔታ በጣም ያሳዘነው፡ Aባቱ በትግሉ ፍልምያዎች የተሰዋ፡ Eርሱም ወጣት Eድሜውን በትጥቅ ትግል ያሳለፈ፡ “ፓይሎት” በሚል የቅጽል ስሙ የሚታወቀው በፓል ቶክ ውስጥ Eንዲህ ሲል የሰማሁት መሰለኝ። “Aኔ የታገልኩት ለከንቱ ነበር፤ Aባቴም ለብላሽ ነበር የተሰዋው!”። ይህ Aባባል ንፁህና ትክክለኛ ነው። በሌላ Aነጋገር፡ Eሱ Eያለ ያለው “Eኔ ለኤርትራ ጥቅም Aይደለም የታገልኩት፣ Aባቴም ለኤርትራ ጥቅም Aይደለም ህይወቱን የሰጠው” ነው።
ይህ ታጋይ Eንዳለው፡ Eነ Iሳያስ ነፃነት ብለው ከሚጠሩት ሁኔታ የኤርትራ ሕዝብ Aልተጠቀመም። ያ ሁሉ ህይወቱን የሰጠና Aካላቱ ለጉዳት የተዳረገ ብቻ ሳይሆን፡ በትግሉ የተካፈለው ዜጋ በሙሉ ለሕዝቤና ለAገሬ ልለፍ በሚል ሕሊና ነበር። ስለዚህም ሁሉም ሱታፌ ሊከበር የሚገባ መሆኑን ላሰምርበት Eሻለሁ።
የኤርትራ ሕዝብ Aልተጠቀመም ቢባልም ያልተጠቀመ ክፍል ፈጽሞ የለም ማለት Aይደለም። ሁልጊዜ ማለት ይቻላል፡ መስዋEት ይሁን ስራ ወይም Aብዮታዊ ጥረት፡ ‘ፍሬ-Aልባ’ ሆኖ Aይቀርም። የሚጠቀም Aካል Aለ። ጥያቄው ተጠቃሚው Aካል ማነው? የሚል ነው። ከኤርትራ ልጆች መስዋEት፡ ከኤርትራ ሕዝብ የገድል ስቃይ የተጠቀሙ Aካላት Aሉ። ደርግን ለማውደቅ Eና ለሕብረተሰብAዊነት ጐራ ተደማጭነት Eንቅፋት ለመፍጠር የተንቀሳቀሱ ምEራባዊያን ሃይሎች ግባቸው ሰምሮላቸዋል፣ ሕዝባዊ ወያኔም Iትዮጵያ ውስጥ የሥልጣን ወንበር መያዝ ችለዋል፣ Iሳያስ Aፈወርቂ Eና ቡዱኑ ደግሞ ኤርትራ ውስጥ ነግሠው Eቅዳቸውን Eየተገበሩ ናቸው። ሌሎች Aካላትም - ኤርትራውያን ግለ-ሰቦች ጨምሮ - ተጠቃሚ Eንደሆኑ መገመት ይቻላል!!
- ፬ -
ኤርትራ በዚህ ዘመን ውስጥ በጥፋት ሂደትና በሞት ጐዳና ትገኛለች። በAገራችን ያለው መከራ ዝርዝር Aስቀድሞ ተጠቅሷል። በጣም ከሚያሳዝኑትና የሚያሳስቡት ነገሮች Aንዱ ያሁኑ ሁኔታ ኤርትራ ውስጥ ሊከሰት የማይገባው መኖሩን ነው።
ዛሬ ኤርትራ ያለው ሁኔታ ቭላዲሚር ፖዝነር የተባለ ሩስያዊ (ሶቭየት) ታዛቢ (ዘጋቢ) ወደ 80ኛው መጨረሻ ጊዜ Aካባቢ የተናገረው Aንድ ነገር ያስታውሰኛል። ይኼውም ፊል
27 . ረድI መሓሪ፡ ገጽ 254
12
ኤርትራ Eንደ Eናት Aገር ፣ ችግሮችና ፈተናዎች ትናንትም ዛሬም
ዶነሂው የተባለው Aሜሪካዊ ጋዜጠኛ “ስለ Aገርህ የሚያሳዝንህ ነገር ቢኖር ምንድ ነው?” ብሎ ሲጠይቀው “Aገሬ የት ለመድረስ ትችል Eንደነበር ግምት Aለኝ፣ በEውነት ወይም በተጨባጭ የት Aንዳለች ደግሞ Aውቃለሁ፣ ልትደርስበት ትችል በነበረችው Eና Aሁን ባለችበት ሁኔታ ያለውን ሰፊ ልዩነት ሳገናዝበው ያሳዝነኛል።” ሲል ገለጸ። ይህ Aባባል የኤርትራን ሁኔታ በትከክል የሚገልጽ ነው።
ኤርትራ ምን ያህል ልትራመድ ትችል Eንደነበር Eናውቃለን። በተለይም Eኛ የወጣትነት ጊዜያችንን ኤርትራ ውስጥ ያሳለፍን፡ ባሁኑ ጊዜ EድሜAችን በማምሺያው ገደማ ላይ የምንገኝ ዜጎች ሙሉ ግንዛቤ Aለን!! ኤርትራዊያን በሃይለኛ ታታሪነታችን ነበር የምንታወቀው፣ Eውነትም ታታሪ ነበርን፡፡ በሁኔታችንና ባለን Aነስተኛ የተፈጥሮ ጸጋ ምክንያት ለመኖር ብለን Eንሰራለን፡ Eንጥራለን፡፡ በጐረቤት Aገሮች - ለምሳሌ Iትዮጵያ Eና ሱዳን ውስጥ ስንኖር - Aንደ ታታሪዎች፡ ምርታማዎች፡ ብቃት ያላቸው፡ ባለሞያዎችና ታማኞች ታውቀን ተከብረን የነበርን ነን፡፡ በEርግጥ ተፈላጊነት ነበረን፡፡
ነፃ Aገር ሆነን ችሎታችንንና የAቅማችንን ክምችት ጥቅም ላይ Aውለን Eንደ ሕብረተ-ሰብ Aብበን፡ Aድገን፡ ደምቀን Eና ተኳኩለን ልንታይ ነበር የሚገባው። Aለመታደል ሆኖ ግን ኤርትራ ያለው ሁኔታ የዚሁ ተቃራኒ ነው!!
ኤርትራ ዛሬ በሁሉም መስፈርት Aስጠሊና የተገለለች Aገር ሆናለች። ሕዝባችን ባሁኗ ወቅት ደቃቃዋ የፖለቲካ መብት Eንኳ የሌለው፡ ሰብAዊ መብቱ ፈጽሞ ያልተጠበቀ፡ Eጅግ ከባድ ድህነት ያጐሳቈለው፡ ማህበራዊ ኑሮው ሰብAዊነት የራቀው፡ የህላዌው ሁኔታ በፍርሃትና ስጋት ተበክሎ የደህንነትና የዋስትና ጭላንጭል Eንኳን የሌለው ነው፡፡ የወጣቶቹ ሁኔታ በተለይ Eጅግ የሚያሳዝን የከበደ ትራጀዲ ሆኗል፡፡ ወጣቱ ሊደሰትበት በሚገባ Aፍላ Eድሜው በግድ Eየታፈሰ ሳዋ ወይም Aገልግሎት ለሚባለው ባርነት Eየተዳረገ ነው። ወጣቶቹ ከዚያ ገሃነማዊ ሁኔታ ለማማምለጥ ሙከራ ሲያደርጉ፡ ከስደት ወደ ስደት Aገር ለመሸጋገር ሲሞክሩ Aንዳንዱ ባሕር ውስጥ Eየሰጠሙ ለምህረት-የለሽ ዓሳ ሲሳይ Eየሆኑ ነው፣ Aንዳንዱ ደግሞ በAረሜኔዎች ተጠልፈው Eንደ Eንስሳ Eየታረዱ ኩላሊታቸውና Eና ሌላ ውስጣዊ Aካላቸው Eየተነጠቀ ሬሳቸው በሳሃራና በሲናይ ምድረ-በዳዎች Eየበሰበሰ ነው፡፡ ይህ መከራ በጣም የሚዘገነን፡ ስትሰማውም Eጅግ የሚያስደነግጥ ነው።
ለመሆኑ ዜጎች ለዚህ Aሰቃቂ መከራ ሲጋለጡ Aስመራ ውስጥ ያለው መንግሥት ምን Eየሰራ ነው? የሚል የዋህ ጠያቂ Aይታጣም። Aስመራ ውስጥ ያለው Aምባገነን Iሳያስ የሚመራው መንግሥት Eውነትም ኤርትራዊ መንግሥት Aይደለም፣ በኤርትራውያን ላይ የጥላቻና የቂም በቀል ቁርሾ በያዙ፡ ድብቅ ሴራ ባላቸው Aካላት የቆመ ቡድን (ካባል) ነው። Eነኚህ ሴረኞች በትውልድ ትግሬዎች ቢሆኑም ኤርትራዊያን ሊሆኑ የችሉ የነበሩ፡ ሆኖም ግን ምንነቱ ባልተመረመረ ችግር ምክንያት፡ ሕዝባችንን በሚያጠቃ መልኩ የ“ትግራይ-ትግርኚ” ንድፍ Aዝማቾች ለመሆን የመረጡ ናቸው።
ከዚህ ጋር በተዛመደ ሊነሳ የሚገባው Aሳዛኝ ነገር Aለ። ለብዙ Aመታት ከበረሃ ትግል ጀምሮ Eስከ ህግዲፍ መንግሥትነት ድረስ Iሳያስን ያገለገሉ፡ Eንደ Eነ ሃይለ ወልደትንሳኤ፡(ድሩE)፡ማሕሙድ ሸሪፎ፡ Eስጢፋኖስ ስዩም፡ ጴጥሮስ ሰለሞን፡ ጀርማኖ ናቲ፡ ኣስቴር ፍስሓጽዮን፡ በራኺ ገብረስላሴ፡ Uቕበ ኣብርሃ፡ ብርሃነ ገረዝጊሄር የመሳሰሉ፡ በዛ ገሃነማዊ የIራIሮ Eስር ቤት ውስጥ ተቆልፎባቸው Aንዳንዶቹ ሞተው፤Aንዳንዶቹ ደግሞ Eየተሰቃዩ ሞታቸውን ይጠባበቃሉ። Eነኚህ ታጋዮች የፈጸሙት ወንጀል የለም። ኤርትራ ውስጥ ዲሞክራሲ Aንዲጀመር ጥገናዊ የሆነ ለውጥ በመጠየቃቸው ብቻ ነው ለዚሁ 13
የመወያያ ሰነድ (Discussion paper)፣ ጀኑዋሪ 2013
Aበሳ የተዳረጉት። Eነዚህንና ሌሎች የፖለቲካ Eስረኞችን የምትመለከት Aንዲት Aንገብጋቢ ነጥብ Aለች፤ Eርስዋም Aኚህ በIሳያስ የሚታሰሩና በተለያየ ዘዴ Eየተገደሉ ያሉት ዜጎች በሙሉ ንጹሃን “ኤርትራዊያን” መሆናቸው ናት። በተቀረ፡ ብዙ ሰዎች Aንደነገሩኝ ከሆነ፡ በትውልዳቸው ትግሬዎች የሆኑ ኤርትራውያን በIሳያስ መንግስት Aንዲገደሉ ወይንም Eንዲታሰሩ የተደረጉ የሉም። ይህ Aሳሳቢ የሆነ ትዝብት ነው!!
ነፃነት ተብሎ የሚጠራው ሁኔታ ከተከሰተ በኋላ ያለው Eውነታ ኤርትራ ወደ ፊት Aለመራመዷ ብቻ ሳይሆን፡ Aጐራባች Aገሮች በሙሉ ወደ ፊት ሲራመዱ Aርስዋ ግን የኋልዮሽ Eየተጓዘች ከሁሉም ጭራ ረድፍ ተሰልፋ መገኘትዋ ነው። ሌላ ቀርቶ ከነፃነት በፊት በዘመናዊ Eደገት ኋላ ቀር የነበረችው ትግራይ Eንኳን ዛሬ በድርብርብ Eነሆ ኤርትራን Aልፋት ሄዳለች!! ትግራይ ውስጥ ያለው Eድገት በጣም የሚያስደሰት ነው። ትግሬዎች በEውነቱ በርትተዋል። ጥያቄው ኤርትራ Eንዴት ሲሆን ነው ይህን ያህል የሰነፈችው የሚለው ነው። ያውም በትግሬዎች Eየተገዛች!! ትግራይ Eጅግ Eያደገች፡ ኤርትራ ግን በAንጻሩ Eየተዳከመች ወደ ኋሊት ስትጓዝ ማየት Aስገራሚ ትEይንት ነው።
Aገራችን ከነፃነት በኋላ ምን ስለሆነች ነው በዚህ Aዘቅት ውስጥ ልትገባ የቻለችው? የሚል ብዙ ወይንም Aብዛኛው ኤርትራዊ የሚጨነቅበት ጥያቄ ሆኖ መጥቷል። ይህ ጥያቄ ግን ብሩህ መልስ Aለበት።
ሁኔታው Aንዲህ የሆነበት ምክንያት ኤርትራ ለስሙ ብቻ Eንጂ በEውነት ነጻና ሉዓላዊት ስላልሆነች ነው። Aንዲት Aገር ነፃ ወጥታለች ሲባል፤ ነፃነቷና ሉዓላዊነቷ ነባራዊ (ወይም ዘልዓለማዊ) ነው በሚል ትርጉምና ግምት (ወይም ሃሳብ) ነው። ቀደም ብዬ Aንደገለጽኩት ደርግ ከተወገደ በኋላ ኤርትራ ለAጭር ጊዜ ብቻ ነው ነፃና ሉዓላዊት Aገር ሆና የምትቆየው። ከዚያ በኋላ ግን፡ በተጠነሰሰላት ሴራ መሰረት “ብትንትኗ” ትወጣለች። ለተወሰነ ጊዜ ሉዓላዊት Aገር ተብላ በኋላ ግን Aንድተበታተን በሚል ንድፍ የተቀመረ ነፃነት “Eውተኛ” ነፃነት Aይደለም። Eንግድያውስ Aሁን ኤርትራ ያለችባት ሁኔታ የነጻነትና የሉዓላዊነት ሳትሆን የመሸጋገሪያ መድረክ ነች። ያለፈው “ፈደረሽን’ ወደ ፍጹም ውህደት መሸጋገሪያ መድረክ Eንደነበረ ሁሉ፡ የዛሬዋ “ነፃነት” ደግሞ ለAገራችን መበታተንና ለትግራይ-ትግርኚ ምስረታ የምታመቻች መሸጋገሪያ መድረክ ናት።
Aሁን የምናየው ያለን ሁኔታ የኤርትራን ህላዌ ትርጉም-Aልባ የሚያደርግ ነው። ኤርትራዊ የማንነት ስሜትን የሚያዳክም፡ Aገሪቱን ያለወጣቶች Aስቀርቶ መጪ Eድል Eንዳይኖራት የሚያደርግ፣ ኤርትራውያን፡ በተለይ ወጣቶቹ፡ ዓይናቸውን Aሁን የሚመሰገን Eድገት ወደሚታይባት ትግራይ በቅናትና በጉጉት Eንዲያተኩሩ የሚያስገድድ፤ ባጭሩ ኤርትራውያን - በተለይ ትግርኛ ተናጋሪዎች - የትግራይ-ትግርኚን፡ ዓላማ፡ ማለት ከትግራይ ጋር መዋሃድ የሚለውን ንድፍ Eንዲቀበሉ በሕሊናና በስነ-ኣEምሮ የሚያዘጋጅ ነው።
የትግራይ ትግርኚ Aስተሳሰብ (ሎጂክ) Aንግዲያውስ ኤርትራ ሕዝቧን የማታኰራ፡ በገዛ ሕዝቧም የተጠላች Aንድትሆን የሚያስገድድ ነው። የትግራይ ትግርኚ Aራማጆች የነደፉትና የሚጠብቁት፡ የኤርትራ ሁኔታ Eንዲህ መጥፎ ሲሆን ሕዝባችን “Aሁን ትግራይ Aድጋ የትና የት ደርሳ ይኼው Eያያችኋት ነው” ብሎ “ከትግራይ ጋር መዋሃድ” ይሻለናል Eንዲል ነው።
በደቡብም - ማለት በIትዮጵያ በኩልም - Eንዲሁ የትግራይ-ትግርኚን ንድፍ ለመተግበር ዝግጅት የሚመስል ክንዋኔ Eየተፈጸመ ነበር፤ ዛሬም Eየተፈጸመ ነው። የዚህ ዝግጅት ዋና 14
ኤርትራ Eንደ Eናት Aገር ፣ ችግሮችና ፈተናዎች ትናንትም ዛሬም
Aካል ደግሞ ያች “የብሄር ብሔረሰቦች መብት Eስከ መገንጠል” የምትለዋ ሰበበኛ መመሪያ ነች። ስለሆነም ሕዝባዊ ወያኔ የሚቆጣጠረው የIህኣዲግ መንግሥት ያችን የመገንጠል መብት በIትዮጵያ ሕገ መንግሥት ውስጥ Eንድትሰፍር Aድርጓል። በAንቀጽ 39 የIትዮጵያ ሕገ-መንግስት መሠረት ትግራይ ልትገነጠል ትችላለች። በEርግጥም ታዛቢዎች Eንደሚሉት፡ ወያኔዎች ወይንም Aንዳንድ የወያኔ Aካላት ትግራይን ከIትዮጵያ ለመገንጠል Eንደ መጨረሻ Aማራጭ Aድርገው ደብቀዋት ያሉት ካርዳቸው ነች።
ሕዝባዊ ወያኔ ይህችን የብሔሮች መብት Eስከ መገንጠል የምትባለዋ ሰበበኛ ሴራ ኤርትራ ውስጥም Aንድትገባ ለረዢም ጊዜ ያልተቋረጠ ጥረት Aድርጓል። ዛሬም ጥረቱን Eየቀጠለበት ነው። Eነዚያ ከወያኔ ጋር ስትራተጂካዊ (ጥብቅ) ዝምድና Aለን የሚሉ - በብዙ ታዛቢ Aስተያየት ግን የወያኔ የበታች ተባባሪዎች ወይም ታዛዦች - የሆኑት የኤርትራ (ተቃዋሚ) ድርጅቶች፡ የብሔሮች መብት Eስከመገንጠል የምትለውን መመርያ መለያቸው Eና Aቋማቸው Aድረገው Eየተንቀሳቀሱባት ይገኛሉ።
ይህች የብሔሮች መብት Eስከ መገንጠል የምትባል ቋንቋ በቀጥታ ‘ትግራይ-ትግርኚ’ ለሚለው ዓላማ የምታገለግል ነች። ብሔረሰቦቻችን፡ ወይም ከመሃላቸው Aንዳንዶቹ፡ ተለይተናል ሲሉ፤ ያ ትግርኛ ተናጋሪው ደጋማው ክፍል ደግሞ ከትግራይ ጋር ይጠቃለል Eና የትግራይ-ትግርኚ ሕልም Eውን ይሆናል ማለት ነው።
Eኔ በብሔረሰቦቻችን Eኩልነት Aምናለሁ። ብሔረሰቦቻችን የራሳቸውን Eድል በራሳቸው የመወሰን መብት Eንዳላቸውም Aምናለሁ፤ ይህንን ስል ግን የብሔረሰቦቻችን መብት የሚረጋገጠው በAንዲት የተዋሃደች ኤርትራ ሥር ውስጥ መሆኑን ላሰምርበት Eፈልጋለሁ። የብሔሮች መብት Eስከ መገንጠል የሚለውን በስመ “መብት” ተሞርኩዞ የኤርትራን Aንድነት የሚያደፈርስ Aጀንዳ ማካሄድ በAገር ላይ “ክሕደት” መፈጸም” (ትሪዝን) ከመሆን Aያልፍም።
ቀደም ብሎ Eንደተመለከተው ዛሬ ያለው ፈታኝ ውጥረት ኤርትራ ትኑር ወይስ Aትኑር የሚል ነው። Aገር Eንድትኖር ከተፈለገ ኤርትራዊ ሁሉ ለAርነታዊ ትግል የበኩሉን ድርሻ ማወጣት ይኖርበታል። የትግሉ ዘመቻ ደግሞ በ“Eናት Aገር” (ግንባር ዓደ’ቦ) መልክ የተደራጀ መሆን Aለበት።
- ፭ -
በተለምዶ ሲተረጐም የትግርኛው “ዓደ’ቦ” (በAማርኛ “Eናት Aገር”) Aባቶችህ፡ ከነርሱ በፊት ደግሞ Aያቶችህ፡ ሲኖሩበት የነበረው Aገር ወይንም Aከባቢ ማለት ነው። በስነ-ፖለቲካ መስክ ግን ዓደ’ቦ ወይንም Eናት Aገር ጠለቅ ያለ ትርጉም ያዘለ ነው። ለAንድ የተወሰነ ወይም የታወቀ Aካባቢ ወይንም ገጠር፤ ብቻ Aይደለም የሚመለከት፤ የሚመለከተው ለAንድ ባለው የተለየ “ባህላዊ፤ ፖለቲካዊ፤ ማሕበራዊና ስነ ልቦናዊ”’ ይዘት የሚታወቅ ህዝብ ነው። በበሳል ወይም በበሰለ መልኩ ወይም ምንነቱ ከረጅም ትውልዶች Aንስቶ በAንድ የተወሰነ ቦታ የሚኖር በጋራ ቋንቋ ባህልና ክብር የተሳሰረ ሕብረተ-ሰብ ማለት ነው።
የIጣልያን Aገር ለመመስረት፡ ሪሶርጂመንቶ በሚባል ንቅናቄ ከታገሉት Aንዱ ‘ጁዘፐ ማዚኒ’ የተባለው የዓደ’ቦ (Eናት Aገር) ትርጉምን በሚመለከት Aንዲህ Aለ።
15
የመወያያ ሰነድ (Discussion paper)፣ ጀኑዋሪ 2013
“ዓደ’ቦ (Eናት Aገር) ቦታ ወይ ቦታ ብቻ ኣይደለም፤ ቦታ መሰረት ብቻ ነው፤ ዓደ’ቦ (Eናት Aገር) በመሰረቱ ላይ የታነጸ ሐሳብ ነው፤ የፍቅር ሐሳብ፤ የዛ ቦታ Aገር ልጆች የሆኑትን ሁሉ የሚያስተባብር የውህደት መንፈስ ነው“28።
በታሪክ ዓደ’ቦ (Eናት Aገር) የተለያየና ታዳጊ ትርጉም ነበረው፡ Aሁንም Aለው። ለምሳሌ Aውሮፓ ውስጥ ከምEተ ዓመታት በፊት - ማለት በፊዩዳል ስርዓት ዘመን - Eናት Aገር ጠባብ ትርጉም ያቀፈ ሃሳብ ነበር። ሲሰጠው የነበረው ትርጉም Aውራጃን፡ ክልልን፡ ክፍለ-Aስተዳደርን ወይም ወረዳን የመሳሰሉት Aካባቢዎችን ነበር የሚመለከት። ቆየት ብሎ ግን በAውሮፓ ውስጥ የካፒታሊዝም ስርዓት ብቅ ሲል፡ Aገሩ በሙሉ ተገናኝቶና ተያይዞ በማሕበራዊና ምጣኔ ሃብታዊ ፈጣን ሂደት ግንኙነት ሲፈጥር ‘Eናት-Aገር’ የሚለው ሃሳብ የAገሩን በሙሉ ፓለቲካዊ፡ ባህላዊና ህብረተሰባዊ ማሕበረ-ሰብ የሚመለከት ትርጉም ያዘ።
ሦስተኛ ዓለም Aገሮች በAመሰራረታቸውና በEድገታቸው ደረጃ ከAውሮፓ Eና ካደጉት ሌሎች Aገሮች ይለያሉ። በውስጣዊ (ማለት በገዛ ራሳቸው) ታሪክ መሰረት ሳይሆን የተለያዩ ብሔረሰቦች በቅኝ ግዛት ቁጥጥር ስር በመግባታቸው ተዋቅረው የቆሙ Aገሮች ናቸው። Aመጣጣቸውና የEድገታቸው ደረጃ በማያሳስብ ሁሉም Eናት Aገሮች ናቸው። ያ ከቅኝ ግዛትነት ነፃ ለመውጣት ያደረጉት ትግል Eንደ ሕጋዊና ብቁ Eናት Aገርን የመከላከል Aቅዋም ታውቆ በተራማጅነት Aና በሰላም ሃይሎች ተደግፏል።
ከዚህ ጋር የተያያዘ ግልጽ መሆን ያለበት Aንድ ነገር Aለ። ወራሪዎችና Aመጸኞች መንግሥታትም ቢሆኑ ለEናት Aገር ዘብ መቆም ወይንም Eናት Aገር የሚለውን ሐረግ ለብዝበዛና ለጸረ-ሠላም ዘመቻቸው ሲሉ ይጠቅሱታል። በዚህ መልኩ የተነሳሳ የEናት Aገር ግንባር ግን Eውነተኛ Aይደለም።፡ ይህ ሃቀኛ የሕብረተሰብ ፍቅር ያላነገበ፡ መርሆ ነው፣ የጥቂቶች የስስታምነትና የብዝበዛ ጥቅም ብቻ የሚያስጠብቅ Aስመሳይ መፈክር ነው። የEናት Aገር ግንባር ፍትሓዊ ሆኖ ተቀባይነት የሚኖረው ዓላማው መሠረታዊ መብቶችን ለመከላከል ወይም የሌሎችን መብት በማይጋፋ መልኩ የራስን መብት መጠቀም ሲሆን ነው።
ኤርትራ Eናት Aገር ነች? ወይም የኤርትራውያን Eናት Aገር ማን ነች? ይህ ጥያቄ በ40ዎቹ Aካባቢ ብዙ ያነጋግር ነበር። Aነጋጋሪ የሆነበት ምክንያትም ‘ኤርትራ ለኤርትራዊያን’ የሚባል ማሕበር ሲያራምደው የነበረው ‘የትግራይ-ትግርኚ’ ፖለቲካ ነው። በፊት Aንዳብራራሁት፤ የዚያ ማሕበር Aባላት ‘ኤርትራ’ ሲሉ፡ በተለይ ወደ መጀመሪያው Aካባቢ፡ “ትግራይ ትግርኚ” (Aለውሃ ምላሽ) ማለታቸው ነበር። ስለሆነም “Eናት Aገራችን ”(ዓደ’ቦ) ሲሉ በተግባር “ትግራይ ትግርኚ” ይሉ ነበር ማለት ነው።
ዛሬስ ትግርኛ ተናጋሪ የሆነው ኤርትራዊ “Eናት Aገሬ” ሲል ምን ወይም የትኛዋን Aገር ማለቱ ነው? ትግሬዎችሳ ማንን ወይንም የትኛዋን Aገር ነው Eናት Aገራችን የሚሉዋት?29
28. ማውሪዚዮ ቪሮሊ፤ በገጽ 84-85 ላይ Eንደጠቀሰው
29. በEነዚህ ገፆች ውስጥ ያሉት የኤርትራ Eናት-Aገርነትን፡ Eንዲሁም ትግራይንና Eናት-Aገርነትን በሚመለከት የቀረቡ የጥያቄና መልስ ተጨባጭ መረጃዎች Aብዛኛዎቹ - ወይንም ሁሉም ማለት ይቻላል - Aለምሰገድ Aባይ ከጻፈው “Identity Jilted or Re‐imgining Identity“ የሚል መጽሓፍ የተገኙ ናቸው። ፕሮፈሰር ኣለምሰገድ Eንደዚህ ያለ በመረጃ የደለበ መጽሐፍ በማበርከቱ ላመሰግነው Eፈልጋለሁ። Eርግጥ Aንዳንድ የማልስማማባቸው ነጥቦች ቢኖሩም መጽሐፉ ጠቃሚ መሆኑን ሳልገልጽ Aላላፍም። 16
ኤርትራ Eንደ Eናት Aገር ፣ ችግሮችና ፈተናዎች ትናንትም ዛሬም
Eናት-Aገር (ዓደ’ቦ) የሚለውን ቃል ትግርኛ ተናጋሪ ኤርትራዊያን በAንድ ዓይነት Aይረዱትም። ለምሳሌ በደጋማው ኤርትራ ስንመለከት፡ በተራው (ሲቪል) ሕዝብና በፖለቲካ ተዋንያን መካከል የሃሳብ (ወይም የAተረጓጐም) ልዩነት Aለ። የተራው ሕዝብ የማንነት ስሜት ወይም Eምነት ጥንት በቆየው ታሪክ፡ ልማድና ዝምድና ላይ የተመሰረተ ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ መገንዘብ ያለብን Aንድ ነጥብ Aለ፤ ኤርትራ በጣልያን ሥር በነበረችበት ወቅትም ቢሆን፡ ይህ የደጋማው ክፍል ሕዝብና ከመረብ ወንዝ ማዶ የሚገኘው የትግራይ ሕብረተሰብ Eንደጥንቱ Eየተገናኘና Eየተጋባም መኖሩ ነው።
Eናት Aገራችን (ዓደ’ቦና) ማነች ትላላችሁ? ሲል Aለምሰገድ Aባይ በኤርትራ ደጋማው ክፍል ላሉት ተራ ሕዝብ መጠይቅ (ኩወሽነር) Aቅርቦላቸው ነበር። ከተጠየቁት ተራ ሕዝብ 21.4% ብቻ ነበሩ Eናት Aገራችን (ዓደ’ቦና) ኤርትራ ነች ብለው ያሉት። Aብዛኛዎቹ፡ (ማለት 53.6%) Eናት Aገር (ዓደ’ቦና) የሚሏት መንደራቸውን ወይንም Aባቶቻቸው Eና Aያቶቻቸው የተወለዱበት Aካባቢን ነው። ከነዚህም በጣም ጥቂቶች Aገራችን (ዓደ’ቦና) ትግራይ-ትግርኚ ወይንም ትግራይ ነች ያሉም ነበሩባቸው30፡፡
ተራው (ሲቪል) የትግራይ ሕዝብሳ? Aብዛኛዎቹ ሳይሆኑ በርከት ያሉ (39.3%) የትግራይ ሲቪል ሰዎችም Eናት Aገራችን (ዓደቦና) ብለው የሚሏት መንደራቸውን ወይንም የተወሰነ የትውልዳቸው Aከባቢን ነው። ወደ 25% ግን Eናት Aገራችን ትግራይ ነች ብለዋል።
ኤርትራውያንና ትግሬዎች በጣሊያን Aገዛዝ ምክንያት ለ62 ዓመታት ተለያይተው ኖረዋል። ይህ መለያየት ባስከተለው ሰበብ ምክንያት ታሪካዊ ጠላታችሁ ማን ነው ወይንም ታሪካዊ ጠላቶቻችሁ Eነ ማን ናቸው? በሚለው ጥያቄ ይለያያሉ። ኤርትራውያኖች በነዚያ 62 ዓመታት ውስጥ በጣልያን Eንደ ባሮች ይገዙ ነበር። ትግሬዎች ደግሞ የAፄ ዮሃንስ ሥልጣነ-ንግሥና ተነጥቀው በሸዋ Aማራዎች ይገዙ ነበር። ኤርትራውያን ጣልያኖችን Eና ሌሎችን የባሕር ማዶ ባEድ ገዢዎች ጠሉ። ትግሬዎቹ ደግሞ በAማራዎች ላይ - በተለይ ደግሞ በሸዋ Aማራዎች ላይ - ቂም Eና ቅራኔ Aሳደሩ።
ከዚህ ታሪክ የመነጨ ይመስለኛል፡’ታሪካዊ ጠላቶቻችሁ Eነማን ነቸው?’ ለሚለው ጥያቄ ኤርትራዊያን Eና ትግሬዎች የተለያዩ መልሶች Aሏቸው። ከEነኚያ ተራ (ሲቪል) ኤርትራውያን Aብዛኛዎቹ (86%) ታሪካዊ ጠላቶቻቻን ብለው የጠቀሱዋቸው፡ መጀመሪያ ቱርክን፡ ቀጥሎ ደግሞ በቅደም-ተከተል ግብፅ፤ ጣሊያንና Eንግሊዝን ጠቅሰዋል። በመጨረሻ ያስቀመጧቸው ኃይለስላሴን Eና ደርግን ነበር። ትግሬዎቹ ግን ታሪካዊ ጠላቶቻችሁ Eነ ማን ናቸው ሲባሉ Aብዛኛዎቹ (ማለት 82.1%) “Aማራዎች፤ በተለይ የሸዋ Aማራዎች” ብለው ነበር የመለሱት። Aነስተኛ ቀጥር (ማለት 10.7% ብቻ) ቱርክንና ጣልያንን Eንደ ታሪካዊ ጠላቶች ጨመሯቸው።(31)
የኤርትራና የትግራይ ልሂቃን (ኤሊት) - ማለትም የፖለቲካ ተዋንያን - Eናት Aገራችሁ ማነች? ተብለው ሲጠየቁ በሰጡዋቸው መልሶች ልዩነቶች ነበሩ። የሰጡዋቸው መልሶች ምን ነበሩ? በኤርትራውያኖች Eንጀምር። በኤርትራውያን ፖለቲከኞች መሃልም ቢሆን Eናት Aገራችን ማን ነች በሚለው ጥያቄ ላይ Eዚህ ግባ የማይባል ትንሽ ልዩነት ነበር። ከተጠየቁት Aነስተኞቹ ክፍል (ማለት 26.5%) Eናት Aገር ብለው የሚጠሩት Eነሱ ወይንም Aባቶቻቸው የተወለዱበት ቦታ መሆኑን ገለጹ። Aብዛኛዎቹ ግን (ማለት 71.4%)
30. ኣለምሰገድ ኣባይ (1998)፡ ገጽ 160
31. ዝኒ ከማሁ፡ ገጽ 153-154
17
የመወያያ ሰነድ (Discussion paper)፣ ጀኑዋሪ 2013
Eናት Aገራችን ኤርትራ ነች ነበር ያሉት። ለምሳሌ Aምባሳደር ኣድሓኖም ገብረማርያም Eንደሚከተለው ብሏል።
“ለነፃነት በተደረገው ትግል ተሰልፎ ሲታገል የነበረ ማንኛውም ታጋይ ሁሉ ወንድሜ ነው። መሐመድ Oስማንም (ታጋይ የነበረ) ወንድሜ ነው። ለሁለታችን ደግሞ Eናት Aገር ሲባል ቀድማ ወደ ሕሊናችን የምትመጣው ኤርትራ ነች”32.
Eናት Aገሬ ‘ትግራይ-ትግርኚ’ ነች ብሎ የመለሰ በጥያቄው የተሳተፈ ኤርትራዊ የፖለቲካ ተዋናይ የለም።
ኤርትራውያን Eናት Aገራችን ኤርትራ ናት ሲሉ ግን፡ ይህች ኤርትራ Eናት Aገር ከሆነች ረዢም ዘመን Eንዳላስቆጠረ ያምናሉ። Eንዲያውም ኤርትራዊ ብሄርተኝነት ራሱ የተነሳው ወይም የተጀመረው በጣሊያኖች የቅኝግዛትነት መነሻ - ማለት በ19 ክፍለ-ዘመን መጨረሻ Eንደነበር ያሰምሩበታል። ይህ ማለት ደግሞ፡ ቆየት ብየ Eንደምገልጸው፡ የኤርትራ Eናት-Aገርነት በEድገት ሂደት ያለ ነው ማለት ነው።
በጥያቄው የተሳተፉት የዛሬው የትግራይ ፖለቲከኞች (ወይም የፖለቲካ ተዋንያን - ማለት ኤሊት) Eናት Aገራችሁ ማነች ለሚለው ጥያቄ የሰጡት መልስ በመንፈስም በAስተሳሰብም ኤርትራውያን ፖለቲከኞቹ ከሰጡት መልስ Aሳሳቢ በሆነ መጠን ይለያል። ከተሳተፉት የትግራይ ፖለቲከኞች መሃል Eናት Aገራችን Iትዮጵያ ነች ብለው የመለሱ 3.6% ብቻ ናቸው። Aብዛኛዎቹ በጥያቄው የተሳተፉ የትግራይ ፖለቲከኞች ግን Eናት Aገራችን ትግራይ ነች ነበር ያሉት። Iትዮጵያ Aላሉም። Aቶ ስብሓት ነጋ ይህንን ጥያቄ ሲመልስ፡ ላንዳፍታ “ዝግ ካለና ካመነታ በኋላ”፡ Eናት Aገር ሲባል በAEምሮው ውስጥ ድቅን የምትልበት “ትግራይ“ መሆኗን ገልጿል። Aንደዚሁም Aቶ ጸጋይ በርሄ - Eስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የትግራይ ክልል ፕረዚደንት የነበረና፡ ዛሬ ግን የሕዝባዊ ወያነ ማEከላዊ ኮሚቴ ስራ Aስፈጻሚ Aባል የሆነው - ይህ ጥያቄ ቀርቦለት ሲመልስ ሳያመነታ በቀጥታ “Eናት Aገሬ ትግራይ ነች“ ነው ያለው። Iትዮጵያ ነች Aላለም። “ብትግሬነቴ በኩል Aድርጌ ነው Iትዮጵያዊ የምሆነው“ በማለት ግን መልሷን ስስ በሆነች Iትዮጵያዊነት ሸፋፍኗታል።33
ይህ Eናት Aገራችን ትግራይ Aንጂ Iትዮጵያ Aይደለችም የሚል መልስ ከታወቁ የሕዝባዊ ወያኔ Aመራር Aካሎች ሲደመጥ የሚያሳስብ ክስተት ነው። (ለምሳሌ Aንድ በኤርትራዊ የፖለቲካ ድርጅት Aመራር ውስጥ ያለ ሰው Eናት Aገሬ ብሎ ኤርትራን ከመጥቀስ ይልቅ ባርካን ወይም ቢለንን ወይም ኩናማን ቢጠቅስ፡ ወይንም ደግሞ ከደጋማው Aውራጃዎቻችን - ማለትም ሓማሴን፡ Aከለጉዛይ - ብሎ ቢጠቅስ፡ ለኛ ለኤርትራውያን Eጅግ የሚያሳስበን ይመስለኛል!!)
በIትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የIትዮጵያ ነገሥታት “Eናት Aገር” ሲሉ ሃሳቡ Iትዮጵያን የሚያመላክት Eየሆነ ነው የመጣው። Iትዮጵያን’ “Eናት Aገር“ ብለው ነው የሚጠሯት! ለምሳሌ Aጼ ዮሐንስ Eንኳ፡ የተምቤን ተወላጅ የትግራይ ሰው ሆነው፡ Iትዮጵያን ነበር Eናት Aገር የሚሏት። ይህንን በግልጽ የምታመለክት በብዙ የታሪክ ጸሓፍት ዘወትር የምትጠቀስ በጣም ጥልቅ ይዘት ያላት የኚህ Aጼ ንግግር Aለች። ንጉሡ በ1887 ዓ.ም ከጣሊያን ጋር ጦርነት ለመግጠም ወደ ሰሓጢ ዘመቻ ሲነሱ ለመኳንንቶቻቸውና
32. ዝኒ ከማሁ. ገጽ 168
33. ዝኒ ከማሁ፡ ገጽ 169
18
ኤርትራ Eንደ Eናት Aገር ፣ ችግሮችና ፈተናዎች ትናንትም ዛሬም
ለሰራዊታቸው “Eኔም ስለ Eናቴ፡ ስለ Iትዮጵያ ህይወቴን ልሰዋላት ሙሉ ፈቃድ ኣለኝ“ ካሉ በኋላ፡ የሚከተለውን Aወጁ፤
“የIትዮጵያ ልጅ ሆይ! ልብ Aድርገህ ተመልከት! Iትዮጵያ የተባለችው Aንደኛ Eናትህ ናት፤ ሁለተኛ ዘውድህ ናት፤ ሶስተኛ ሚስትህ ናት፤ Aራተኛም ልጅህ ናት፤ Aምስተኛም መቃብርህ ናት፡፡ Eንግዲህ የEናት ፍቅር፤ የዘውድ ክብር፤ የሚስት ደግነት፤ የልጅ ደስታ፤ የመቃብር ካባቲነት (ታቃፊነት) Eንደዚህ መሆኑን Aውቀህ ተነሳ።“34
ለAጼ ዮሃንስ Eናት Aገር ሲባል Iትዮጵያ መሆኗ ግልጽ ነው። Eንግዳውስ የትግራይ ፖለቲከኞች ‘በዚህ ዘመን’ Eናት Aገራችን ‘ትግራይ’ ነች ሲሉ የወደፊቷን Iትዮጵያ በሚመለከት Aመላካች ትርጉሙ ምንድነው? ወይም Aሳሳቢነቱ ምን ያህል ነው? ይህ ሁኔታ ኤርትራንስ Eንዴት ሊመለከታት ይችላል? የሚሉትን ጥያቄዎች ያስነሳል። ቢሆንም ጥያቄው ላሁኑ ወደ ጐን Aስቀምጠን፡ የኤርትራን Eናት-Aገርነት የEድገት (ወይም ጥንካሬ) መጠንና Aይነት ወደሚመለከት ጉዳይ Eናትኩር።
- ፮-
በታሪክ Aይን ሲታይ ኤርትራዊ ብሔራዊ ማንነት ጥንታዊ Aይደለም፣ ገና Aፍላ ነው። ኤርትራ Aገሬ ነች የሚል ስሜት በሰፊው ሕዝብ ማቆጥቆጥ የጀመረው በትግሉ ጉዞ ከነበረው መስዋEትነት ስቃይና የብሔረሰቦች ግንኙነትና ትውውቅ ጋር በተያያዘ ነው። ለምሳሌ Aንድ ኤርትራዊ Aባት Eናት Aገርዎ ማን ናት ተብለው ሲጠየቁ “ኤርትራ፤ ኤርትራ ነች Eናት Aገሬ! ሁለት ልጆቼ ለኤርትራ ነፃነት ታግለው፤ ስለ ኤርትራ መስዋEት ሆነዋል Eኮ!“ Aሉ።35
Eንግዲያውስ ኤርትራ በመሰረቱ ብቻ ነው Eንደ Eናት Aገር ያለችው። ከዚያ በተረፈ መጽናት፡ መብሰልና መጠናከር ያለባት ናት። በሌላ Aነጋገር ኤርትራ Eንደ Eናት Aገር ገና በሂደት ላይ ነች፤ መጠናቀቅ ያለባት ስራ ወይም ግብ (ፕሮጀክት) ነች።
Eናት-Aገርነት በንግግር ምሳሌዎች፤ ባህላዊ ምልክቶች፤ ተረቶች፤ Aባባሎች የተሸኘ የብዙ ግኝቶ ድምር መንፈስና ባህርይ ያለው ነው። የኤርትራ Aገርነት Eምቡጥ ስለሆነ Eነኚህ ግኝቶችን በቂ በሆነ መጠን Aላዳበረም። ስለሆነም የኤርትራ Eናት-Aገርነት (ዓደቦነት ኤርትራ) ብዙ ጥበቃ፤ ክንክንና ድጋፍ የሚያስፈልገው ነው። በሁሉም ዘርፎች -ማለትም በባህላዊ Eንቅስቃሴዎች፡ በምጣኔ ሃብታዊ Eድገት፡ በዜናና መረጃ ስርጭት፡ በብሔረሶቦቻችን ወንድማዊ Eና Eህትማማዊ ዝምድና፡ Eንዲሁም ብቃትና ጠቃሜታ ባለው ስርAተ-ትምህርት፡ የኤርትራን Eናት-Aገርነት የሚያደምቅና የሚያጐለብት ጥንቁቅ በሆነ ጥናት ላይ የተሞረኰዘ ፖሊሲ ተነድፎ ስራ ላይ መዋል Aለበት። ህፃናት Eናት Aገራቸው ኤርትራ መሆኗን በሚያመለክት ትምህርት መኰትኮት Aለባቸው። ደራሲያን በጽሁፎቻቸው፡ የስነ-ጥበብ ሰዎች በተለያዩ የፈጠራ ስራዎቻቸው የኤርትራ Eናት-Aገርነትን Eንደ ሃሳብ በሚያጐላና በሚደግፍ መልኩ ለመንቀሳቀስ Eንዲፈቀድላቸውና Eንዲበረታቱ ያስፈልጋል።
34. ተክለጻድቅ መኩርያ፡ ገጽ 471
35. ኣለምሰገድ ኣባይ (1998): ገጽ 170
19
የመወያያ ሰነድ (Discussion paper)፣ ጀኑዋሪ 2013
ታሪካችንን በትክክል መረዳት ለኤርትራ Eናት-Aገርነት Eድገትና መጠናከር ማEከላዊ Aስፈላጊነት Aለው። Eንግዲህ ከገጠሙን Aበይት ችግሮች Aንዱ ይህ ነው። Iሳያስ፡ የIሳያስ ተባባሪዎችና ተላላኪዎች ከድሮ ጀምሮ የሕብረተሰባችንን የሩቅና የቅርብ ታሪክ ጠምዝዞ ተረት-ተረት የሚመስል ፈጠራ ለሰራዊታቸውና ለAባሎቻቸው፡ ለሕዝባችንና Eንዲሁም ለመላ ዓለም ሳይታክቱ Aሰራጭተዋል። በውሸት ታሪክ የታጠበው ሰራዊታቸውና ተከታዮቻቸው (በኤርትራ Aብዮት ውስጥ) ለጸረ Aንድነት ውግያ ታዛዥ ሆኖ ሳይታወቀው የኤርትራን Aፈራርሶ ‘ትግራይ-ትግርኚ’ን የመመስረት የIሳያስ ግብ መገልገያ ሆነዋል።
Eንግዲያውስ ሕዝባችን የEውነተኛ ታሪኩ ግንዛቤ Eንዲኖረው መከናወን ያለባቸው ብዙ ነገሮች Aሉ። ግቡ Eጅግ ውስብስብ ነው። Eንዲህ የሆነበት ምክንያትም ሕዝቡ - በተለይ ወጣቱ - ትክክለኛ ታሪኩ ማወቅ ይኖርበታል ብቻ ሳይሆን በመጀመርያ ያ Eስካሁን Aውነተኛ የታሪክ Eውቀት ብሎ የተቀበለው ውሸት ካስተሳሰቡ መደምሰስ ስለሚኖርበት ነው። ወጣቶቹ ያላቸው ታሪክን የሚመለከት ሐሳብ ስሕተተኛና ውሸት መሆኑን Eንዲያምኑና Eንዲቀበሉ መደረግ Aለበት።
Eንደሚመስለኝ፡ Aንዳንዶቻችን ሓቀኛ ታሪካችንን ለማወቅ Eንፈራለን። Eውነተኛ ታሪካችንን ካወቅንና ካመንን ነፃነታችንና ሉዓላዊነታችን Aደጋ ውስጥ የሚገባ ይመስለናል። ይህ ግን ከየዋህነት የመነጨ ፍርሃት ነው። በታሪክ ከመላ ጐረቤቶቻችን ጋር Eንዛመዳለን። ይህንን Eውነተኛ ታረክ መቀበል ነፃነታችንና ሉUላዊነታችንን የሚጻረር Aይደለም።
በምEራባዊ ቆላ የሚኖሩት ሕዝቦቻችን በታሪክ ከምስራቃዊና ማEከላዊ ሱዳን ጋር ይዛመዳሉ። Eንዳውም የጋራ ታሪክ ነው ያላቸው። ትግርኛ ተናጋሪው የደጋው ሕዝባችን ደግሞ በታሪኩ ከሰሜን Iትዮጵያ ሕብረተሰቦች ጋር የሚዛመድ ነው። Eንዲያውም የጣሊያን ቅኝ ግዛትነት Eስከ ጀመረ ድረስ ወደ ኋላ ያለው ታሪክ ሁሉ የጋራ ታሪካችን ነው።
ታሪክ ሲባል ቀላል ነገር Aይደለም። በዚህ ዘመን፡ በዚያ ዘመን Eንዲህ ሆነላችሁ Eያለ የፍጻሜ ድርጊቶች የሚያወሳ Aፈ ታሪክ ወይም ተረት ብቻ Aይደለም። ታሪክ በAንድ ሕዝብ Aካሄድ ላይ ተጽEኖ የሚያሳድር ብቻ ሳይሆን፡ የAካሄዱን ቅርጽ የሚሰጥ፡ የAንድን ሕዝብ የሥልጣኔ ሂደት Aቅጣጫ የሚያስይዝ፡ የማንነት ስሜትን፡ ባህልን፡ ሃይማኖትን፡ ቋንቋን፡ ወግንና ክብረትን (ወይም ጨዋነትን) ሁሉ ያቀፈ፡ ከትውልድ ወደ ትውልድ Eየተላለፈ በቅርስ መልክ የሚኖር ህያው ነገር ነው። Eውነተኛ ታሪኩን የሚክድ ሕዝብ የማንንት ቀውስ Aጥቅቶት፡ በተምታታ ባህል Eየተደናበረ በመዳከር ላይ ገብቶ ወንድሞቹ በሆኑት በጐረቤት ሕብረተሰቦች ላይ የተሳሳተ Aፍራሽ Eይታ ሊኖሮው የግድ ነው።
ታሪክን በሚመለከት Eንግዲህ Eኛ ኤርትራውያን ልንገነዘበው የሚገባን Aሳሳቢ ነጥብ Aለ።የምስራቃዊና ማEከላዊ ሱዳን ታሪክ በውንድሞቻችን በኒ-ዓምር Eና በሌሎቹ የምEራባዊ ቆላ ሕብረተሰቦቻችን በኩል ይደርሰናል። የIትዮጵያ ታሪክም ቢያንስ በትግርኛ ተናጋሪው የደጋው ሕብረተስብ Aድርጐ ይደርሰናል። ይህንን ታሪክ ማወቅ Aለብን ብቻ ሳይሆን፡ Aሁን ላሉን የሃይማኖት፡ የባህል፡ የወግ፡ የማEረግና የስነምግባር ሕጐችን ቅርጽ ያስያዘ - ባጭሩ ጠቅላላ ማንነታችን የገነባ - መሆኑን በማመን የኛ የራሳችን ነው ብለን መቀበል ይገባናል። ታሪካችንን ማወቅ፡ ደካማና Aሉታዊ ጐኖቹን ለይተን Eንድንጠነቀቅባቸው፤ገምቢና Aዎንታዊ ጐኑንም ልናከብረው፡ ልንኰራበትና ልንንከባከበው Eጅግ Aስፈላጊ ነው። Eንዲህ ስናደርግ ብቻ ነው፡ በAካሄዳችን በAላማችንና በAመለካከታችን ኤርትራ Eናት Aገራችን መሆኗን በተግባር ልናስመሰክር የምንችለው። 20
ኤርትራ Eንደ Eናት Aገር ፣ ችግሮችና ፈተናዎች ትናንትም ዛሬም
- ፯ -
Aስቀድሜ Eንደጠቀስኩት የኤርትራ Eናት-Aገርነት በ40ዎቹ በትግራይ-ትግርኚ መርሆ ፈተና ውስጥ ነበር። Eንዲያውም በዚህ መርሆ መሰረት የተጠየቀው ተሟልቶ ትግራይና ኤርትራ Aንድ Aገር ቢሆኑ ኖሮ፡ በቁጥር Eኩል የሆኑት Eስላሞችና ክርስትያኖች የሚኖሩባት ኤርትራ ዞራ ዞራ መበታተኗ Aይቀርም ነበር። ለምን? ትግራይ-ትግርኚ ተብሎ ሊቆም በታሰበው Aገር፡ ያ ክርስትያናዊ Aካል ከEስላሙ ክፍል በቁጥር የበላይነት ስለሚኖሮው፡ የብዛተ-ህዝብ ሚዛን (ደሞግራፊክ ባላንስ) በደፈረሰ ነበር። Eንዲያ ሲሆን፡ Eንዳልጨፈለቅ በሚል ስጋት ምEራባዊ ቆላ ውስጥ የሚኖሮው ህዝባችን ወደ ሱዳን መጠቃለል ይሻለናል በማለት Eንቅስቃሴ መፍጠሩ Aይቀርም ነበር። Eንግሊዞቹም ያ ነበር Eቅዳቸው።
የሆኖ ሆኖ የትግራይ-ትግርኚ ንድፈ ሃሳብ ግቡን Aልመታም። Aባቶቻችን Aገር Eንዳትገነጣጠል በማሰብ፡ ፈደረሽንን Eንደ ማEከላዊ መፍትሔ ተቀብለው የኤርትራ Aንድነት Eንዲረጋገጥ Aደረጉ። Eንግዳውስ ያ ፈደረሽን የኤርትራ Eናት-Aገርነት መሠረት Eንዲቀጥል AስተዋጽO Aድርጓል ማለት ይቻላል።
ዛሬም የኤርትራ Eናት-Aገርነት በAንዲት መጥፎና Aስጊ የሆነች መፈክር Eየተፈተነ ወይም ለAደጋ Eየተጋለጠ ነው። ያች መፈክርም Aስቀድሜ የጠቀስኩዋት “የብሔሮች መብት Eስከ መገንጠል” የምትለዋ ናት። ይህች መፈክር ብላ-ብላ ከላይ ከተመለከተው ከEነ Aቶ ስብሃት ነጋና Aቶ ጸጋይ በርሀ Aስተሳሰብ ጋር ነው የምትያያዘው። Eነዚህ ሁለት የወያኔ መሪዎች “Eናት Aገራችን ትግራይ ናት” (Iትዮጵያ ሳትሆን ትግራይ ናት) Eንዳሉት ሁሉ፡ Aንዳንድ የብሔሮች መብት Aስጠባቂዎች ነን የሚሉት ፖለቲከኞቻችንም Eናት Aገራችን ኤርትራ ሳትሆን ከብሔሮቻችን Aንድዋ (ለምሳሌ “ኩናማ፡ ብሌን፡ ትግረ ወይም ከደጋው Aውራጃዎቻችን Aንድዋ ለምሳሌ Aከለ-ጉዛይ ወይንም ሐማሴን) ናት ሊሉ ነው ማለት ነው። ይህ Aቋም የኤርትራን Eናት-Aገርነት ያለ ምሕረት የሚፈታተን ነው።
ለኤርትራ የመሬት ወይም የግዛት ሙሉነትና Eናት-Aገርነት ቆሞ መከላከል ትግራይን ማስወገድ Aይደለም፣ Eንደዚያ ተብሎም መተርጐም የለበትም። ይህችን ነጥብ ላሰምርባት Eፈልጋለሁ። ኤርትራና Iትዮጵያ ሁለት የተለያዩ፡ የየራሳቸው ሉዓላዊነት ያላቸው Aገሮች Eንኳ ቢሆኑም በሁለቱ መካከል በሁሉም መስኮች ወንድማዊ ዝምድናዎች የማይኖሩበትና የማያድጉበት ምክንያት የለም። ኤርትራና ትግራይማ በቀጥታ በድምበር የሚገናኙ ስለሆኑ ዝምድናቸው የጐላ ነው። በተለይ ደግሞ በድምበር Aካባቢ ያሉት የኤርትራ Eና የትግራይ ማሕበረሰቦች ለዘመናት ሲቀላቀሉና ሲዋሃዱ የነበሩ ናቸው። Eንዲያውም ለነዚህ ሕዝቦች የድምበሩ መስመር ተግባራዊ ወይም Eውነተኛ ትርጉም የለውም፡ Aይታያቸውምም። ስለዚህ ከትግራይ ሕዝብ ጋር የነበረ ጥንታዊ ዝምድናችን Eንዳይቀጥል የሚያግደው Aንዳችም ነገር የለም።
Iትዮጵያዊያን የትግራይ ወንድሞቻችን ይህችን የብሄሮች መብትንና የኤርትራን Aንድነት ጉዳይ የምትመለከተውን Aስተያየቴ፡ በዛው ባቀረብኳት የወዳጅነትና የሰላም መንፈስ Eንዲያጣጥሟት ለማሳሰብ Eሻለሁ።
ለኤርትራ Eናት-Aገርነት ገጥሞት የሚገኝ Aስገራሚ ችግርና ከባድ ፈተና ባጭሩ ከዳሰስኩ በኋላ የተማጽኖ መንፈስ ባዘለ ቃና መልEክቴን በማስተላለፍ ሃሳቤን Eደመድማለሁ።
21
የመወያያ ሰነድ (Discussion paper)፣ ጀኑዋሪ 2013
በመክፈቻ ንግግሬ Eንዳስቀመጥኩት ዛሬ Iትዮጵያ በድህረ-መለስ ዘመን ውስጥ ትገኛለች። Aገርን በመምራት ትልቅ ሚናና ተሰሚነት ወይም ተጽEኖ የነበረው ሰው በሞት መለየት Aንድ Aሰሳቢ ምEራፍ ነው። Aሳሳቢ የሚሆንበት ምክንያትም የሚያስከትላቸው ነገሮች ወይም Aደጋዎች ስላሉ ወይም ሊኖሩ ስለሚችሉ ነው።
ሕዝባዊ ወያኔ ከበረሃ ትግል ወቅት ጀምሮ Eስካሁኗ ደቂቃ ድረስ ኤርትራን በሚመለከት ጉዳይ ትልቅ ሚና ነበራቸው፡ ዛሬም ቢሆን ገና Aላቸው። በመለስ ዜናዊ Aመራር የተከተሉት ስትራተጂና መላ Aምባገነኑን Iሳያስ Eና ወደር የሌለው Aራዊታዊ ስርዓቱን በመሰረቱ ጠቅሞታል Eንጂ Aልጐዳውም። የኤርትራን ሕዝብ ግን በEርግጥ ጐዳው፣ Aገራችን የምድር ገሃነብ Aንድትሆን AስተዋጽO Aድርጓል።
Aቶ መለስ Eንደ ግለሰብ የሚደነቅ ችሎታ Eንደነበረው ብዙ ታዛቢዎች የሚመሰክሩት ነው። Eኔም በብቃቱና በብርታቱ Eጅግ ከሚያደንቁት Aንዱ ነኝ። ኤርትራን በሚመለከት በተከተለው ፖሊሲ ግን ድሮ Aላመሰገንኩትም፣ Aሁንም Aላመሰግነውም። Aሁን-Aሁን ሟቹ መለስ የፖሊሲ ለውጥ ለማድረግ Eቅድ ነበረው፣ ሊተገብረውም ጀምሮ ነበር የሚል ነገር ይሰማል። ሊተገበር የታሰበው ለውጥ - Eውነት ከሆነ - Eዚህ መልEክት ሠፍረው ያሉትን ጉዳዮች ምን ያህል ሊመለከታቸው ይችል Eንደነበር የማረጋግጥበት መንገድ ባሁኑ ጊዜ የለኝም።
የሆኖ ሆኖ Aሁን Aዲስ ሁኔታ ተከስቷል። ይህ ሁኔታ ደግሞ ለሕዝባዊ ወያኔ Aመራሮች በAካሄዳቸው ለውጥ Eንዲያደርጉ በር ከፍቶላቸዋል። ያለፈው Aካሄዳቸውን ያለምንም ማወላወል ገምግመው የኤርትራ ሕዘብ Aሁን ላለበት Aዘቅት Aንዲዳረግ Eነርሱም በምን መልኩ AስተዋጽO Eንዳደረጉ በጥሞና (ከልብ) መመራመር Aለባቸው። ከዚህ ተነስተው የኤርትራ Aንድነት፡ ሉUላዊነትና Eናት-Aገርነት Eንዲጐለብት፡ የኤርትራና Iትዮጵያ መልካም ዝምድና ደግሞ Eንዲጠነክርና Eንዲያድግ የሚያስፈልጉ ጥገናዎች Eንዲያደርጉ Eማጠናለሁ።
_________________________________________________________
22
ኤርትራ Eንደ Eናት Aገር ፣ ችግሮችና ፈተናዎች ትናንትም ዛሬም
23
ማጣቀሻ (Bibliography)
Alemseged Abbay, Identity Jilted or Re-Imagining Ide?, (Lawrenceville, NJ: The Red Sea Press, 1998)
Alemseged Abbay, “The Trans-Mereb Past in the Present”, The Journal of Contemporary African Studies, vol. 35, No. 2, (1997)
Amare Tekle, “The Creation of the Ethio-Eritrean Federation: A Case Study in the Post War International Relations (1945-1950),” PhD dissertation, University of Denver, 1964.
Haggai Erlich, “Tigrean Nationalism, British Involvement and Haile-Sellasse’s Emerging Absolutism – Northern Ethiopia, 1941-1943”, Asian and African Studies, Vol. 15 (1982)
Richard Greenfield, “Pre-colonial and Colonial History”, in Basil Davidson, Lionel Cliffe, and Bereket Habte Selassie, Behind the War in Eritrea, (Notingham: The Spokesman Press 1980)
Rene Lefort, Ethiopia: An Heretical Revolution? (London: Zed Press, 1983)
Medhane Tadesse, The Eritrean-Ethiopian war: Retrospect and Prospects, (Addis Ababa: Mega Printing Enterprise, 1999)
John Spencer, Ethiopia, The Horn of Africa and US Policy (Cambridge, Mass.: Institute for Foreign Policy Analysis, 1977)
Tekeste Negash, Italian Colonialism in Eritrea, 1882-1941: Policies, Praxis and Impact, (Uppsala: Acta Universitatis Upsaliens, 1987)
US Congress, Sub Committee on African Affairs, Ethiopia and the Horn of Africa, Hearings, 94th Congress, 2nd Session, Aug. 4, 5, and 6, 1976.(Washington, D. C.)
Maurizio Viroli, Republicanism, (New York: Hill and Wang, 1999)
ኣለምሰገድ ተስፋይ፤ ኣይንፈላለ 1941-1950 (ኣስመራ፤ ሕድሪ፡ 2001)
ረድI መሓሪ፤ ትልሚ ንዘርI ክርዳድ፤ (ኪቸነር፡ Oንታርዮ፤ ኣለና፡ 2012)
ተክለ ጻድቅ መኩርያ፤ Aፄ ዮሃንስ Eና የIትዮጵያ ኣንድነት (ኣዲሰ-Aበባ፤ ኩራዝ ኣሳታሚ ድርጅት፡ 1982)
Copyright © 2012 by Tesfatsion Medhanie.
የደራሲው መብት © 2012 ተስፋጽዮን መድሃኔ፡፡

No comments:

Post a Comment