Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Wednesday 24 April 2013

ኮሎኔል መንግስቱ ኃይለማርያም አልሞቱም

First, his death reported on April fool, now the news spreading again. Col. Mengistu is not dead!
(EMF) የቀድሞው የኢትዮጵያ መንግስት ፕሬዘዳንት የነበሩት ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያም እንደሞቱ ተደርጎ በኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ውጪ ብእሚገኙ ሚዲያዎች ሲወራ ሰንብቷል። ኢ.ኤም.ኤፍ. ከኮ/ል መንግስቱ የቅርብ ቤተሰብ እንዳረጋገጠው ከሆነ፤ ወሬው ከወሬ ያላለፈ የውሸት ዜና ነው ብለዋል። ከዚህ በፊት ከኮሎኔል መንግስቱ ጋር ባደረግነው ቃለ ምልልስ፤ “ወያኔ እንኳንስ በህይወት እያለሁ፤ ሞቼ አስከረኔንም አያገኘውም።” የሚል ምላሽ መስጠታቸው ይታወሳል። እስካሁን የዜና ምንጭ ተብሎ የሚጠቀሰው የዙምባብዌ ቴሌቪዥን ነው። ሆኖም ቴሌቪዥኑ ይን በተመለከተ ምንም ነገር አላለም። ነገር ግን ቴሌቪዥኑን ጠቅሶ ሌላ ድረ ገፅ ባለፈው ኤፕሪል ፉል April Fool እለት ህዝቡን ለማሞኘት ይህን ዜና ሰርቶት ነበር። የሚገርመው ነገር April fool ካለፈ 3 ሳምንታት ተቆጥረዋል።
First, his death reported on April fool, now the news spreading again. Col. Mengistu is not dead!
ጊዜው ቢዘገይም  ይህንን ዜና ይዘው ወሬውን የሚያባዙት ሰዎች በራሳቸው ተሞኝተዋል ማለት ነው። 3 ሳምንታት ቢቆጠሩም… 



እነዚህን የሞኝ ወሬ ሳያረጋግጡ የሚነዙትን ሰዎች April Fool እንበላቸው (ከፈገግታ ጋር)።
ማጠቃለያችን የሚሆነው… “ኮሎኔል መንግስቱ አልሞቱም።” የሚለው ርእሳችን ነው።

No comments:

Post a Comment