Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Sunday 2 June 2013

ሰላማዊ ሰልፉ በሰለም ተጠናቀቀ፡፡ by Abe Tokichaw

ሰላማዊ ሰልፉ በሰለም ተጠናቀቀ፡፡
Photo: picture of the year <3
መንግስት በ3 ወር ውስጥ ጥያቄያችንን ካልመለስ በተጠናከረ መልኩ ድምፃችንን እናሰማለን! (ሰማያዊ ፓርቲ)
ያለ አግባብ የታሰሩ የፖለቲካ የሀይማኖት እና የህሊና እስረኞች እንዲፈቱ፤ ከቀዬአቸው የተፈናቀሉ ዜጎች በአግባቡ እንዲመለሱ እና አፈናቃዮች ለፍርድ እንዲቀርቡ፤ የኑሮ ውድነቱ አስተማማኝ እልባት እንዲሰጠው እና ሌሎችንም ጥያቄዎች አንግበው ዛሬ ኩባ አደባባይ የተገናኙት ኢትዮጵያውን ሰላማዊ ሰልፋቸውን በሰላም አጠናቀቁ!
ሰልፉ ከጠዋቱ አራት ሰዓት ጀምሮ እስከ ስምንት ሰዓት ድረስ እጅግ ደማቅ በሆነ መልኩ የተከናወነ ሲሆን ቀበና ከሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ ፅ/ቤት አንስቶ በአራት ኪሎ በፒያሳ እና በቸርቸር ጎዳና ሄዶ መድረሻውን ኩባ አደባባይ አድርጓል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ በሰልፉ ላይ መንግስት በ3 ወር ጥያቄያችንን ካልመለሰ በተጠናከረ መልኩ ድምፃችንን እናሰማለን ብሏል፡፡
ሰልፉ በሰላም በመጠናቀቁ የተሰማኝን ደስታ በዚህ አአጋጣሚ እገልፃለሁ በሌላ አጋጣሚም እደግመዋለሁ!

No comments:

Post a Comment