Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Friday, 12 June 2015

የጆርጅ ኦርዌል “የእንስሳት አብዮት” (Animal Farm) መጽሃፍ በመስፍን ማሞ ተተርጉሞ ቀርቧል

June 12, 2015
ይህ የትርጉም ሥራ መታሰቢያነቱ
በተስፋይቱ ምድር ኢትዮጵያ ከአለፉት አያሌ ዓመታት ጀምሮ ለፍትህ፣ ለአንድነት፣ ለባንዲራ ክብር፣ ለሀገር ሉዓላዊነት፣ ለሕግ የበላይነት፣ ለሰው ልጆች ሰብዓዊ መብት መከበር፤ ለዜጎች ሁሉ እኩልነት፤ በጥቅሉ ለዲሞክራሲያዊ ስርዓትና ለመልካም አስተዳደር እውን መሆን የሕይወት መስዋዕትነትን ለገበሩት፤ በየወህኒ ቤቶችም በግፍ ለማቀቁት ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይሁን!!
ተርጓሚ – መስፍን ማሞ ተሰማ
ደራሲ – ጆርጅ ኦርዌል

ሙሃመድ ቡአዚዝ ራሱን በማቃጠል በቱኒዚያ የቀሰቀሰው አብዮት እነሆ ሰደድ እሳት ሆኖ በ17 የዓረብ ሀገራት ተቀጣጥሎ፤ የታችኛውንም የአፍሪካ ክፍል መጎብኘት ጀመረ።
በዚህም ወቅት ከ65 ዓመታት በፊት ለንባብ የበቃው የጆርጅ ኦርዌል ‘Animal Farm’ መጽሀፍ በመስፍን ማሞ ‘የእንስሳት አብዮት’ በሚል ወደ አማርኛ ተመልሶ ደረሰኝና አነበብኩት።
ብዙዎች በንግግራቸውና በፅሁፎቻቸው የሚጠቅሱት ይህ ዝነኛ መፅሀፍ ዘመን የማይሽረው መሆኑን ዛሬ በአብዮት በሚናጠው የአፍሪካና የመካከለኛው ምስራቅ ክፍል ተወላጆች የሆንን ይበልጥ ይከሰትልናል።

ፀሀፊው ኤሪክ አርተር (ጆርጅ ኦርዌል) ይህችን ዓለም የተሰናበተው ከዛሬ 60 ዓመት በፊት ቢሆንም፤ የዛሬውን የሚነግረን እንጂ የትናንቱን የሚያስታውሰን አይመስልም። የሁልጊዜም ተወዳጅ እና ተነባቢ መፅሀፍ ቢሆንም፤ ከምን ጊዜውም በላይ ይበልጥ ወቅታዊ ሆኖ አግኝቼዋለሁ። መስፍን ደግሞ ወደ አማርኛ ሲመልሰው ለተነባቢነቱ ብዙ እንደተጨነቀበት ያስታውቃል፤ ተሳክቶለታልም።
ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና
የኢትኦጵ ጋዜጣና መፅሄት አሣታሚ
የፔን ዩ ኤስ ኤ 2010 ተሸላሚ
Animal Farm book in Amharic (Ensisat Abyot)

No comments:

Post a Comment