Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Wednesday 3 June 2015

ፈጣን ሩጫ አይሉት ማራቶን – የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ (The Economist)

Ethiopian unconnected citizens
June 3, 2015
የተርጓሚው ማስታወሻ
ይህ ጽሁፍ ዘኢኮኖሚስት ከሚያወጣቸው ኁሉ ብናየውና ብንወያይበት ይጠቅማል በሚል አሳብ ተተርጉሞ ቀርቧል። እራሱን ሳንሱር እያደረገ እንደጻፈው ማየት አያስቸግርም። ከዚህ ትርጉም እንደምታዩት ምዕራብ፡ ምስራቁ ህወሀት መሩ መንግስት ተብዬ ላይ ሁሉም ተስፋ መቁረጡን በግልጥ ያሳያል። የቻይና አምባሳዶር እቅጩን ይናገራል።ያፈርጠዋል። እዲያው አበዛችሁት ዓይነት ነው።በቻይና የምጣኔ ሃብት ግንባታው ሊሰራ የቻለው የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የህዝቡን ድጋፍ ይዞ ነው።ዛሬ ወያኔ ከህዝብ ተገልሎ ፈርቶ አደር ሆኖ እያነከሰ ነው።ህወሀቶች ቻይና መልሳ ካፒታሊዝምን ተማሩ የምትላቸው ከጊዜው ጋር መራመድ የማይችሉ፤መለስ ከሞተ ወዲያ እንኳን የሰራውን ጥፋት ማየት ያልቻሉ ትቷቸው እንደሄደ ተገትረው የቀሩ ጉዶች ናቸው።ዘኢኮኖሚስት ከመለስ ሞት በኋላ በሰላም በመንግስትነት ተሸጋገሩ ይላል ሌላ ሊሆን እንደሚችል ሁሉ።ዛሬ እየሆነ ያለውን፤የምርጫውን ቧልት፤በሰሜን ኢትዮጵያ ወያኔን ስለሚያጫንቀው ሁኔታ አይተነፍስም።ወያኔ ላይ ያንጃበበው ዳመናም አይታየውም ወይም አይቶት አይናገርም።ለኛ ገሀድ የሆነውን።
የውጭ ተንታኝ ይሳሳታል።እኛ ወያኔ ይወድቃል ህዝብ ተመሯል አይሰነብትም ስንል።በኢትዮጵያ ወያኔን ቀጣይ አድርጎ ያያል። ወያኔዎች ዙሪያው ገደል ሆኖባቸው፤እርስ በርስ እየተወነጃጀሉ ለመሆናቸው ምልክቶች እየታዩ ነው። ወያኔ ዳሩ እየላላበት ነው። መሃሉም ረመጥ እሳት ይሆንበታል። በመጣበት ዘዴ ሊሸኝ። ትርጉሙ እነሆ።

ከቢላል አበጋዝ፡ ዋሽግቶን ዲሲ
——————————-
ፈጣን ሩጫ አይሉት ማራቶን – የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ
ይህ ጽሁፍ ዘ ኢኮኖሚስት May 30th 2015 ያወጣው ጽሁፍ ትርጉም ነው።
ከመላው አፍሪካ በሙሉ እንደ ኢትዮጵያ አድርጎ ቻይና እንደ መራሄ ኮከብ፤ዋና ምሳሌ ተደርጋ የምትወሰድበት የለም።ይሄው ኢትዮጵያ በሜይ 24 እዚህ ግባ የማይባል ውጤቱ ቀድሞ የታወቀ፤ምርጫ አካሂዳለች።ያው ለነባሩ ፓርቲ አዲስ አገዛዝ ዘመን የሚለግስ።ከአሃጉሩ በህዝብ ብዛት ሁለተኛ፤በፍጥነት ታዳጊ ኢኮኖሚ ያላት ኢትዮጵያ ከኮሚኒስት ቻይና ጋር የጠበቀ የአስተሳሰብ ዝምድና አላት።የኢትዮጵያም ባለስልጣናቶችዋን ወደ ቻይና የፓርቲ ትምርት ቤት ትልካለች።ኢትዮጵያኑ በቻይና ኢንዱስትሪ የማስፋፋትን ወንጌልን፤እንዲዋሀዱና ጠንካራ ማከላዊ የማያላውስ ጨቌኝ መንግስትን ባለብዙ ዘውጎች ያውም ያለመስማማትም ታሪክ ያላቸላቸው ህዝቦችን ስለመግዛት፡ያጠናሉ።
ዛሬ ከቻይና ጋር ሁሉም አልጋባልጋ አይደለም። አዲሱ የቻይና አምባሳዶር ያለፈው ፌብሩአሪ አዲስ አበባ ሲደርሱ ለወዳጆቻቸው ያልታሰበ አጉል መልዕክት አድርሰዋል። አምባሳደር ሊ ፋን በዝግ ችሎት የወያኔን ባለስልጣናትን ያለፈው ብቸኝነትን ትታችሁ፤ኢኮኖሚያችሁን ለውድድር ክፈቱት ብለዋል።ንዋይም ዜናም በማዕቀብ መያዙን እያመልከቱ።ባንክና ቴሌ አሰራራቸው የዘመነ ሎጥ ነው።ነጋዴዎች ተመረዋል።ንግድ ወደ ኋላ ቀርቷል።ላመታት ወያኔን ሲያመሰግኑ የኖሩት ቻይኖች ዛሬ ልክ እንደምእራብያውያን ተችዎች ሁሉ ያማርራሉ።
[ሰንጠረጁ የሚያሳየው የኢትዮጵያን በኢንተርኔትና ቴሌ እጅግ ኋላ መቅረትን ነው።] እአአ 2013 የተቀናበረ ሪፖርት የተወሰደ ከመቶ ሰዎች ምን ያህሉ ግለጋሎት ያገኛሉ በሚል የተጠና።
የችግሩ መሰረት ድፍረት የለም።በኢትዮጵያ መንግስት ውስጥ ያሉ፤የገዥው ፓርቲ አባላት የጸጥታ ተቋሙን የሚቆጣጠሩትም መሻሻሎችን ማድረግ ብቻ የኢኮኖሚ እድገትና የፖለቲካ መረጋጋትን እንደሚያመጡ ያምናሉ። ሊተገብሩአቸው ግን ቀርፋፎች ናቸው።

የመንግስቱ ቀዳማይ ፍላጎት ኢንዱስትሪን ማስፋፋት ነው።ነገር ግን ነጋዴዎች በቢሮክራሲ ተተብትበው ከንዋይም ማንቀሳቀስ ታግተዋል።ባለስልጣናት ሁዋጅያንን ያመለክታሉ።ሁዋጅያንን የቻይና በኢትዮጵያ የጫማ ፋብሪካ ነው።በጥቂት አመታት የሰራተኛን ቁጥርን ከ600 መቶ ወደ 3 ሺ 600 ያደረሰ ነው።ኢትዮጵያ ታዲያ መቶዎች ሁዋጅያንን ትፈልጋለች። ኢንዱስትሪ ሳይስፋፋ 80 % ግብርናን ከማሻሻል በኋላ የሚተርፈውን የሰው ሀይል የምታደርስበት መኖር አለበት።
መንግስት ኢንዱስትሪ መስፋፋትን ለመርዳት መንገጎች ይሰራል፤ባቡር ሃዲዶች ይዘረጋል፤የሀይል ማመንጭያ ጣቢያዎችን፤ግድቦችን ልክ ቻይና እዳረገችው ቅጅውን ይተገብራል።እኒህ ተግባሮች በኦፊሴል የሚታወቀውን የአስር እጅ የኢኮኖሚ ዕድገት አስከትለዋል።ምንም እንኳ ዕድገቱ ሰባትና ስምንት እጅ ነው ተብሎ በውጭ ጠበብት ቢነገርም።የዋጋ ግሽበት ወደ አንድ አሃዝ ወርዷል።ሆኖም ባለፉት ሶስት ዓመታት የዓለም የንግድ ድርጅቶችን ለመቀላቀል የሚደረግ ጥረት የለም።ስራ የሚያንቀሳቅስ የውጭ ካፒታል መገኘቱ አስተማማኝ አይደለም።
ያለው መንግስት ቁንጮዎች መንግስታችን ይገለበጣል የሚል ስጋት ለውጦችን ከመግፋት ችላ እንዲሉ አድርጓል።በአንድ በኩል ሲያስቡት የመልካም ውጤታቸው ሰለባ የሆኑ ይመስላል።ዲሲፕሊንና አስተዳደራዊ ረቂቅነት ላለው መንግስት ቁንጮዎች መጨቆኛ መሳሪያዎችን በጃቸው እንዲሆኑ አድርጓል።ይህ ደግሞ በአሃጉሪቱ ያሉ መሰል ጨቋኞቸ ሊመኙት ብቻ የሚችሉት ነወ። አሁን ያለው መንግስት ቁንጮዎች ካልዘረጉት የጭቆና መረብ ተለይተው ለመኖር አይታሰባቸውም።
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከ1974 እስከ 1991 እአአ ከነበረው የስበስ ጦርነት በኋላ አገሪቱን ያደሳት መሃንዲስ በ2012 እአአ ከሞተ ወዲህ ሁኔታው እየባሰ መጣ እንጄ የተሻለ ነገር አልሆነም።መለስ በባህሪው ብርታት፤የአእምሮ ችሎታውና በጦርነት ጊዜ ባፈራቸው ጥብቅ ወዳጅነቶች መሰረት የመንግስቱን ወደፊት እንዲሄድ ያደርገው ነበር።እርግጥ ነው የንግዱ ክፍልና ህዝባዊ ድርጅቶችን ይጠላ ነበር።ቢያስ ግን ጋሬጣ የሆኑ ጉዳዮችን ያስወግድ ነበር።ከሞቱ በኋላ መንግስቱ በሰላም ሽግግር አድርጓል።ረዳትጠ/ሚኒስትሩ እንደታቀደው ስልጣን ይዟል።
አሁን ያለው አመራር የስብስብ ነው።አዲሱ ረዳትጠ/ሚኒስትር መለስ አይደለም።መለስ አንዱ መታሰቢያው የተከፋፈለውን ድርጅት መከፋፈሉን መደበቅ ነበር። ዛሬ ሚኒስትሮች ውሳኔ ከማድረግ በፊት የነባር አመራርን ፈቃድ ማግኘት አለባቸው።የትግራይ ተወላጆች መለስ ወገናቸው የሆኑት ጦሩን፤ጸጥታውን፤ ቴሌን፤የውጭ ጉዳይን ይቆጣጠራሉ።እነርሱ ጡረታ እስቲወጡ ወይ እስቲሞቱ ቢያንስ ሌላ አስር ዓመት ይፈጅ ይሆናል።
አዲሱ ጠ/ሚኒስቴር ለውጥ የሚሻ፤ምክንያታዊ ሰው ነው።በአንጻሩ ደካማ ነው።በመጭው ሴፕቴምበር በኢህአዴግ ጉባኤ የፓርቲው መሪነት እንደገና ይጸድቅለት ይሆናል።ግን መሰንበቱ የተረጋገጠ አይደለም።መለስ ለምን እንዳጨው የረሱት ጥቂቶ ናቸው።ከተበታተነው ደቡብ የአገሪቱ ክፍል በመሆኑ ዋናዎቹን ቡድኖች የማይቀናቀን በመሆኑ ነው።
በኢትዮጵያ የሚገኘው የቻይና ህብረተ ሰብ ከፍተኛ አባል ተስፋ በመቁረጥ የአገሪቱ[ኢትዮጵያ] ትልቁ ችግር በቻይና ማእከላዊው መንግስት የክልሎች የበላይ ነው።በኢትዮጵያ ግን ሁሉም ነገር ፌዴራል ነው። የንግድ ቀዬዎች የሚገነቡት በጥናት በተመረጡ ቦታዎች ሳይሆን በኮታ ነው።ከዚህም በላይ እንደ ማኦ መርህ “ፓርቲው ጠመንጃውን ይቆጣጠራል” የሚለው ተረስቷል።ጸጥታ ጠባቂዎቹ ህጉን ራሱን ሆነዋል።
በመጨረሻም የኢትዮጵያ ከፍተኛ መሪዎች ችሎታ ቢኖራቸውም እንደቻይና ችሎታ ያላቸው የመካከለኛ ደረጃ አስተዳዳሪዎች የላቸውም።ባጠቃላይ ብዙ ቻይኖች ኢትዮጵያ በብዙ በየቦታው ባሉ ጉልበተኞች እደተያዘች ያያሉ።
ቻይኖች የማይተነፍሱት መእራባውያን ግን የሚናገሩት የፖለቲካ ስርዓቱ የሚያደርሰው ጭቆና እንዳዳከመው ነው። ወጣቶች ተቆጥተዋል።ስራ አላገኙም።የብሶት መወጫቸው፤መተንፈሻቸው ቶሎ ተዘግቷል። አስተዋይ የተቃዋሚ መሪዎች ለስደት፡ለእስራት ይዳረላሉ።ይህ ደግሞ ለአክራሪዎች ቦታውን ክፍት ያደርጋል። የዩኒቨርሲቲ ቁጥሮች በርከቷል ግን ለብሩሃኑ ተመራቂዎች የተዘጋጀ ስራ የለም።
ፈርቶ አደርሮች ምክንያት ኢትዮጵያ አጣብቂኝ ውስጥ ትገኛለች።ባላት አስደናቂ እድገት የተነሳ ለጥቂት ጊዜ አንከስ እያለችትሄድ ይሆናል።የሀይል ማመንጫዎችዋም ተጨማሪ ድጋፍ ይሰጥዋት ይሆናል። ኢትዮጵያ ቀርቶባታል መሆን ትችል የነበረውን አስደናቂ መሆን አልሆነችም

No comments:

Post a Comment