
June 3, 2015
የተርጓሚው ማስታወሻ
ይህ ጽሁፍ ዘኢኮኖሚስት ከሚያወጣቸው ኁሉ ብናየውና ብንወያይበት ይጠቅማል በሚል አሳብ ተተርጉሞ ቀርቧል። እራሱን ሳንሱር እያደረገ እንደጻፈው ማየት አያስቸግርም። ከዚህ ትርጉም እንደምታዩት ምዕራብ፡ ምስራቁ ህወሀት መሩ መንግስት ተብዬ ላይ ሁሉም ተስፋ መቁረጡን በግልጥ ያሳያል። የቻይና አምባሳዶር እቅጩን ይናገራል።ያፈርጠዋል። እዲያው አበዛችሁት ዓይነት ነው።በቻይና የምጣኔ ሃብት ግንባታው ሊሰራ የቻለው የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የህዝቡን ድጋፍ ይዞ ነው።ዛሬ ወያኔ ከህዝብ ተገልሎ ፈርቶ አደር ሆኖ እያነከሰ ነው።ህወሀቶች ቻይና መልሳ ካፒታሊዝምን ተማሩ የምትላቸው ከጊዜው ጋር መራመድ የማይችሉ፤መለስ ከሞተ ወዲያ እንኳን የሰራውን ጥፋት ማየት ያልቻሉ ትቷቸው እንደሄደ ተገትረው የቀሩ ጉዶች ናቸው።ዘኢኮኖሚስት ከመለስ ሞት በኋላ በሰላም በመንግስትነት ተሸጋገሩ ይላል ሌላ ሊሆን እንደሚችል ሁሉ።ዛሬ እየሆነ ያለውን፤የምርጫውን ቧልት፤በሰሜን ኢትዮጵያ ወያኔን ስለሚያጫንቀው ሁኔታ አይተነፍስም።ወያኔ ላይ ያንጃበበው ዳመናም አይታየውም ወይም አይቶት አይናገርም።ለኛ ገሀድ የሆነውን።
የውጭ ተንታኝ ይሳሳታል።እኛ ወያኔ ይወድቃል ህዝብ ተመሯል አይሰነብትም ስንል።በኢትዮጵያ ወያኔን ቀጣይ አድርጎ ያያል። ወያኔዎች ዙሪያው ገደል ሆኖባቸው፤እርስ በርስ እየተወነጃጀሉ ለመሆናቸው ምልክቶች እየታዩ ነው። ወያኔ ዳሩ እየላላበት ነው። መሃሉም ረመጥ እሳት ይሆንበታል። በመጣበት ዘዴ ሊሸኝ። ትርጉሙ እነሆ።



