Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Tuesday, 17 April 2012

የኑሮ ውድነቱ አንገብጋቢው የአገሪቱ ችግር መሆኑን አቶ መለስ ተናገሩ

ሚያዚያ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ላለፉት 8 አመታት የ11 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገባቸውን በተደጋጋሚ ሲናገሩ ይሰሙ የነበሩት አቶ መለስ፣ ዛሬ 99 ነጥብ ስድስት በመቶ የአንድ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎቻቸው በተገኙበት የፓርላማ ውሎ የአገሪቱ ፈታኝ እና ዋነኛው ችግር የኑሮ ውድነቱ መሆኑን ተናግረዋል።
አቶ መለስ ይህን የተናገሩት “መንግስት የኑሮ ውድነቱን ለመቆጣጠር የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰድኩ ነው ቢልም የኑሮ ውድነቱ ግን እየባሰ፣ የምግብ ዋጋ እየጨመረ እና ዝቅተኛው የህብረተሰብ ክፍል እየተጎዳ ነው” የሚል ጥያቄ ከቀረበላቸው በሁዋላ ነው። አቶ መለስ የኑሮ ውድነቱ የአገሪቱ አንገብጋቢው ችግር መሆኑን አምነው፣ ችግሩ የተፈጠረው በአለም ገበያ መዋዠቅ ፣ የጅምላ ንግድ ስርጭቱ በሞኖፖል መያዝ፣  የገንዘብ አቅርቦት መጨመርና የዋጋ ትንበያ በመበራከቱ መሆኑን ገልጠዋል። መንግስት እነዚህን ችግሮች ለመቅረፍ ገንዘብ ከብሄራዊ ባንክ እንዳይበደር ማድረጉን፣ ከጅምላ ነጋዴዎች ጋር በመነጋጋርና ስርጭቱ እንዲስተካከል ለማድረግ ጥረት ማድረጉን፣ የውጭ ምንዛሬ ክምችቱን ለመቀነስ መወሰኑን እና ሌሎች እርምጃዎች መወሰዳቸውን ተናግረዋል።
የስርጭት ስርአቱን ለማስተካካል ከነጋዴዎች ጋር ለመነጋጋር ጥረት ቢደረግም ነጋዴዎች ግን የመንግስትን አማራጭ ለመቀበልና ለመተባባር ፈቃደኛ ባለመሆናቸው፣ መንግስት ስኳርና ዘይት የመሳሰሉትን ገዝቶ ለማከፋፈል ተገዷል ብለዋል። በአሁኑ ጊዜ በቂ የሚባል ስኳርና ዘይት ከውጭ አገር ተገዝቶ መምጣቱንም አቶ መለስ አስረድተዋል። በአለፈው የካቲት ወር የእህል ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩን የገለጡት አቶ መለስ ይህም የሆነበት ምክንያት የበልግ ዝናብ ስላልነበረ ነው ሲሉ አክለዋል። ከ8 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ስንዴ ከውጭ ተገዝቶ ለህዝቡ እየተከፋፋለ መሆኑንም ገልጠዋል። አቶ መለስ የዋጋ ግሽበቱ በሰኔ ወር ወደ አንድ አሀዝ ይገባል ብለው የተነጋሩት ስህተት እንደነበርና አሁን በሚታየው ሁኔታ በሰኔ ወር ወደ አንድ ዲጂት ለማውረድ እንደማይቻል ገልጠዋል።
አቶ መለስ የአለምን የገበያ መዋዠቅ ለመቆጣጠር ሸቀጦች በአገር ውስጥ   የሚመረቱበትን መንገድ ማፈላላግ ተመራጭ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ አስተያየታቸውን የጠየቅናቸው አንድ በአገር ውስጥ የሚኖሩ የኢኮኖሚ ባለሙያ አቶ መለስ ከዚህ ቀደም እንደሚያደርጉት አገሪቱ በዚህን ያክል መጠን አድጋለች እያሉ ቢናገሩ አሁን ከሚታየው የኑሮ ውድነት ጋር  ህዝቡ የሚቀበለው አለመሆኑን በመረዳታቸው በችግሮቹ ዙሪያ ላይ ትኩረት አድርገው ለመናገር መምረጣቸውን ገልጠዋል። የኑሮ ውድነቱ መንስኤ በዋናነት በአገሪቱ ውስጥ ከፍላጎት ጋር ሊመጥን የሚችል በተለይም በቂ የግብርና  ምርት ሊመረት ባለመቻሉ ነው ያሉት ባለሙያው፣ ስንዴ ከውጭ ገዝቶ ማስገባት በቂ ምርት በአገር ውስጥ አለመመረቱን የሚያሳይ እንጅ ከአለም ገበያ መዋዠቅ ወይም ከስርጭት ጋር የሚያያዝነው ነገር የለም ሲሉ አክለዋል። ነጋዴዎች በቂ የእህል ክምችት ቢናራቸው ኖሮ መንግስት አስገድዶ ወደ ገበያ እንዲያቀርቡት ለማድረግ የሚሳነው አልነበረም በማለት የሚገልጡት ባለሙያው የኑሮ ውድነቱ መንስኤ በአገር ውስጥ በቂ ምርት ባለመኖሩ  የተፈጠረ ነው ሲሉ ገልጠዋል።
በአገር ውስጥ በቂ ምርት አለመመረቱ በገሀድ እየታየ ኢኮኖሚው 11 በመቶ አደገ ብሎ ለመናገር መሞከር አስጋሪ መሆኑንና ኢህአዴግ እስከ ዛሬ ሲያቀርበው የነበረው ፐሮፓጋንዳ መልሶ እየመታው መሆኑን ገልጧል። ህዝቡ ” ኢኮኖሚው ካደገ ለምን ዋጋ ይጨምራል፣ ዋጋ እንኳ ቢጨምር የሰዎች የገቢ መጠን ለምን አልጨመረም? በማለት   መጠየቅ መጀመሩ የአቶ መለስ የ11 በመቶ ፕሮፓጋንዳ ውጤት አልባ እየሆነ መምጣቱን እንደሚያሳይ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው እውነታና ኢህአዴግ የሚያስወራው ፐሮፓጋንዳ ህዝቡ ኑሮአችን መሻሻሉን የምናየው  በጓዳችን ሳይሆን በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ነው እንደሚል አስታውሰዋል።
በሌላ ዜና ደግሞ አቶ መለስ ዜናዊ 99 ነጥብ ዘጠኝ የሚሆኑ መምህራን በተደረገላቸው የእርከን ጭማሪ መርካታቸውን፣ ጥቂት ከ500 የማይበልጡ መምህራን ጭማሪውን የተቃወሙት አንድም ጭማሪው የእርከን ጭማሪ መሆኑን ሳያውቁ የደሞዝ ጭማሪ ስለመሰላቸው፣ ሌላም በአስተማሪነት ያልተዋጣላቸው የአስተማሪነት ችግር ያለባቸው ምግባረ ብልሹዎች አጋጣሚውን ተጠቅመው ችግራቸውን ለመሸፋፋን መሞከራቸው እንዲሁም አንዳንዶች ከሻእቢያ፣ ግንቦት 7 እና ኦነግ የተሰጣቸውን የማተራመስ እና ብጥብጥ የማስነሳት ስትራቴጄ ተግባራዊ ለማድረግ ነው ብለዋል። አቶ መለስ የተወሰኑ መምህራን በአማራ እና በአዲስ አበባ መባረራቸው እንዳላሳዘናቸው ይልቁንም ቀደም ብለው መባባረር እንደነበረባቸው ገልጠዋል፣ የአመጽ ሀይሎች መምህራን ተቃውሞአቸውን ወደ አመጽ እንዲቀይሩ ከፍተኛ ግፊት ሲያደርጉ ቆይተዋል ብለዋል።
የአቶ መለስ ንግግር መምህራንን ማሳዘኑን ኢሳት የነጋጋራቸው መምህራን ገልጠዋል። በምእራብ ጎጃም በዳንግላ ወረዳ የሚያስተምሩት መምህር ሰው አገኝ አለሙ በተደረገው የደሞዝ ጭማሪ እንኳን የኢህአዴግ አባል ያልሆኑት ቀርቶ አባል የሆኑትም ማዘናቸውን ገልጠዋል::
መምህር ሰዋ አገኝ እንዳሉት አገዛዙ ወደ ለየለት አምባገነንነት በመግባቱ በመምህራን እና በአገዛዙ መካከል ያለው ቅራኔ የሚታረቅ አይደለም::
አቶ መለስ በንግግራቸው በደቡብ ክልል ስለተፋነቀሉት የአማራ ተወላጆች እና ስለ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ እንቅስቃሴም ገለጣ ሰጥተዋል። የተለያዩ አስተያየቶችን አሰባስበን በነገው ዘገባ እናቀርባለን።

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን በወያኔ አገዛዝ ላይ አለማቀፍ የኢኮኖሚ ማዕቀብ ጥሪ አቀረቡ

የጋራ መግለጫ
boycott woyaneስማቸው ከዚህ በታች የተዘረዘረው በስደት ላይ ያሉ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ቅዳሜ ሚያዝያ 7 ቀን 2004 (April 14, 2012) በአንድ ላይ መጥተው በመለስ ዜናዊ አገዛዝ ላይ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ማዕቅብ ጥሪ አሰተላልፈዋል።
መገናኛ ብዙሃኑ ህዝባዊ ጥሪውን ለማቅረብ የጠሩትን ስብሰባ ከ600 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በኢንተርኔት ተከታትለውታል።
የኢኮኖሚ ማዕቀብ ህዝባዊ ጥሪው የሚከተሉትን ያጠቃልላል፤
1. በአሁኑ ወቅት ከዋና አስተዳደሩ ጀምሮ በጠቅላላ በህወሃት አባላት ቁጥጥር ስር የወደቀው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በብዙ ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ትርፍ ለመለስ ዜናዊና ግብረአበሮቹ እያስገኘላቸው ይገኛል። ይህ ድርጅት ከስሙ በስተቀር ኢትዮጵያዊነት ባህሪይ የሌለው፥ ለኢትዮጵያ  ህዝብ ምንም አይነት ጥቅም የማያስገኝ ሆኖ ስለተገኘ ይህ ህዝባዊ ጥሪ ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ ማንኛውም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ አየር መንገዱን እንዳይጠቀም፥
2. አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ማንኛውንም አይነት ማህበረሰባዊ ግንኙነት ከወያኔ አባላትና ደጋፊዎች ጋር ማቆም፥
3. ከኢትዮጵያ የሚመጣ እንጀራ፤ ቢራዎችና ሌሎችንም ወያኔ የሚቆጣረሯቸው ድርጅቶች የሚያመርቷቸውን ምርቶች አለመጠቀም፥
ይህን የኢኮኖሚ ማዕቀብ ጥሪ ተግባራዊ ለማድረግ ኢትዮጵያን ከህወሃት አገዛዝ ነጻ ለማውጣት የሚታገሉ ግለሰቦችና ድርጅቶች ሁሉ የበኩላቸውን ዝግጅትና ጥረት እንዲያደርጉ እንማጸናለን።
የሀይማኖት አባቶች፥ አርቲስቶች፥ ምሁራን፥ ስፖርተኞች፥ ነጋዴዎች፥ የሀገር ሽማግሌዎችና ማንኛውም ለሀገርና ለህዝብ የሚቆረቆር ኢትዮጵያዊ ይህን የኢኮኖሚ ማዕቀብ ጥሪ እንዲያስተጋቡልንና ተፈጻሚ ለማድረግ እንዲተባበሩ እንጠይቃለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ።
አዲስ ድምጽ ራዲዮ
ዳላስ የኢትዮጵያ ድምጽ ራዲዮ
ኢትዮሜዲያ (Ethiomedia.com)
ኢትዮጵያ ዶት ኦርግ (Ethiopia.org)
የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች የውይይት መድረክ (Ethiopian Current Affairs Discussion Forum)
ኢትዮጵያን ሪቪው (EthiopianReview.com)
ህሊና ራዲዮ
ህብር ራዲዮ
ቃሌ የውይይት መድረክ (Qale Ethiopian Discussion Forum)
ማህደረአንድነት ራዲዮ
ዘሀብሻ ጋዜጣ

ጠቅላይ ሚኒስተሩ ስለመምህራኑን ማብራሪያ ተጠይቀው ማረሪያ ሰጡ!

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በተወካዮች ምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄዎች ዛሬ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።
ብቸኛው የተቀናቃኝ ፓርቲ ተወካይ አቶ ግርማ ሰይፉ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በርካታ ጥያቄዎችን አንስተውላቸው ነበር።
ከጥያቄዎቹ መካከልም ስለ ፖለቲካ ምህዳሩ፤
ፓርቲያቸው በይፋ ስብሰባ ባደረገበት ወቅት ኢቲቪ የቀረፀውን ዋቢ በማድረግ “በህቡዕ በማሴር” ተብለው አባላቶቻችን እና ደጋፊዎቻችን ተከሰውበት እስር ቤት ይገኛሉ፣
ስብሰባ ለማድረግ አዳራሽ አከራዮች “ለሰርግ ካልሆነ በስተቀረ አታከራዩ ተብለናል” ብለው ከልክለውናል።
በዚህ ላይ ማብራሪያ ይሰጠኝ ያሉ ሲሆን በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ደግሞ፤
ከደቡብ ክልል ስለተፈናቀሉ ዜጎች የክልሉ ፕረዘዳንት “አንድም ሰው አልተፈናቀለም” ብለው ተናግረዋል በአይናችን ያየናቸው እርስዎ ፅ/ቤት አቤት ለማለት መጥተው ፀሀይ ተንቃቅተው በኋላም በመኪና ተጭነው የተወሰዱ ዜጎች “አንድም ሰው” አይደሉም ወይ?
ከደምወዝ ጋር በተያያዘ መምህራን ተቃውሞ ሲያሰሙ ገሚሱ ከስራ ተግዷል ገሚሱ ማስፈራሪያ ደርሶበታል። እንደዚህ አይነት “ሆድ የባሰው” መምህር ይዘን ስለ ትምህርት ጥራት ማውራት እንችላለን ወይ?
የሚሉ ጥያቄዎችን ጠይቀዋለው።፡
ጠቅላይ ሚኒስትሩም አብዛኛዎቹን የአቶ ግርማ ሰይፉን ጥያቄዎች በመላ በመላ አልፈዋቸዋል። (የእድሜ እና የስልጣን እኩያዬ ቢሆኑ ኖሮ አጭበርብረው አልፈዋቸዋል እል ነበር)
መምህራኑን በሚመለከት በሰጡት ምላሽ ግን “የማስተማር ስራው በተቋረጠ ወቅት ከወላጆች እና ከተማሪዎች ጋር ውይይት አድርገን ነበር። “በዛን ግዜም መምህራኑ ቀድሞውንም እንዲባረሩልን አቤት ስንል ነበር” የሚል አስተያየት ከወላጆች እና ተማሪዎች አግኝተናል።” ብለዋል። በዚሀም አላበቁም “እነዚህ ከአምስት መቶ እስከ አንድ ሺህ የሚደርሱት መምህራን በመምህርነት አልሳካ ሲላቸው ሌላ አማራጭ ለመሞከር ያሰቡ ናቸው” ሲሉ አብጠልጥለዋቸዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ግርማ ሰይፉን እንዲሁም መመህራኑን “ጭማሪው የደሞዝ ጭማሪ ሳይሆን የእርከን ማሻሻያ መሆኑ ስላልገባችሁ ነው” ሲሉም ተችተዋል።
በዚህም አንዳንድ አስተያየታቸውን የሰጡ መምህራን ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ጠብቀን ማረሪያ አግኝተናል ብለዋል።
በነገራችን ላይ (አዲስ ነገር ጋዜጣ ናፈቀችኝ መስፍኔ በሚፅፋቸው ፅሁፎች ጣልቃ አነስ ያለች በነገራችን ላይ የምትል የጨዋታ “ቦነስ” ነበረችው። ሰላም መስፍኔ! ሰላም አዲስ ነገሮች)
ስቀጥልም በነገራችን ላይ
የመምህራኑ ጥያቄ ባለፉት ግዚያት በተደጋጋሚ እንደገፁልን የኢቲቪ የተጋነነ ዘገባ እንጂ የደሞዝ ማሻሻያው አነሰ አላነሰ አይደለም። ኢቲቪ ሆዬ “መምህራኑ ህይወታቸውን የሚቀይር ገንዘብ ተጨመረላቸው” ብሎ በዘገበ በነጋታው አካራዮች አከርካሪ የሚሰብር ጭማሪ አደረጉብን እናም ዘገባው ይስተካከል ነው ያሉት። ካላመናችሁኝ ድጋሚ አንዱን የአዲሳባ ወይም የአማራ ክልል መምህር ጠይቁት።
በመጨረሻም 1
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዛሬው የፓርላማ ስብሰባቸው በማሳቁ በኩል ብዙም አልተሳካላቸውም። በዚህም ሳቅ ጨዋታ ጠብቀው የሄዱ የፓርላማ አባላት እጅጉን ተከፍተዋል አሉ። እንደውም አንዳንዶች “ካላሳቁ ይልቀቁ” ሲሉ አጉረምርመዋል ሲል ታማኝ ያልሆነ ምንጭ ሹክ ብሎኛል። እዝችው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ሶማሊያ ሲናገሩ “እኛ ሶማሊያ  እንደገባን የሶማሊያ ህዝብ ጫት መቃም ጀምሯል።” በማለት በኩራት ሲናገሩ የሰማ አንድ ወዳጃችን “እንዴት ነው ነገሩ ለማቃቃም ነበር እንዴ የሄዳችሁት?” ሲል የማይመለስ ጥያቄ ጠይቋል።
በመጨረሻም 2
“የግድብ ስራው ተቋረጠ” በሚል አጭር መረጃ አድርሻችሁ ነበር። እኔማ “እስቲ አንዳንዴ እንኳ ጥሩ ወሬ አውራ መንግስታችንን አመስግንልን” ለሚሉ ወዳጆች ጥሩ አጋጣሚ አገኘሁ ብዬ ተደስቼ ነበር። ምን ዋጋ አለው ዌብ ሳይቶቹ ለሶስት ቀናት ተከፍተው የነበረ ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ደግመው ተከርችመዋል። አሉ! በቀደመው ጨዋታዬ ላይ
“…ስለ ኢትዮጵያ የሚያወሩ ድረ ገፆች እንደ ምንጬ አባባል “ፏ” ብለው ይታዩ ነበር። እንዴት ነው ነገሩ መንግስት ተቀየረ… ወይስ ዌብሳይቶችን ሲገድብ የነበረው ሰውዬ ደህና አይደለም?    እነዚህን ጥያቄዎች እርሱ ባለቤቱ ይመልሳቸው።” ብዬ ነበር?
አዎ መልሱን እርሱ ባለቤቱ መልሶልናል። ለሶስት ቀናት ድረ ገፆቹ “ፏ” ብለው የመታየታቸው ምስጢር ገዳቢው ከአመት በዓል ጋር በተያያዘ ጥቂት ጉዳት ደርሶበት ስራውን በአግባቡ ባለመስራቱ ነበር። (ጉዳት የሚለውን ሞቅታ ብሎ መተርጎም አግባብ አይደለም) እናም እንደምንጠረጥረው ልክ  በአሁኑ ሰዓት በ”ኢንሳ” መስሪያቤት  “የዌብሳይት ግደባ እና ቁለፋ ዋና የስራ ሂደት ባለቤት” የሆነው ግለሰብ በግምገማ ቁም ስቅሉን እያየ እንደሚሆን ይገመታል።
እኔ የምለው ግን ምናለ ምስጋናችን እንኳ ጠፈፍ እስኪል ጠብቃችሁ ብትቆልፉት!?

የኢትዮጵያ እስር ቤቶች በጋዜጠኞችና በተቃዋሚ ድርጅት አባላት ተሞልተዋል ተባለ

ሚያዚያ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ይህን ያስታወቁት የአፍሪካ የሲፒጄ አስተባባሪ የሆኑት ሙሀመድ ኬይታ በኒውዮርክ ታይምስ ላይ ባወጡት ጽሁፍ ነው።  ሙሀመድ ኬይታ የአፍሪካ ነጻ ሚዲያ ችገሮች በሚል ርእስ ባወጡት ጽሁፍ ፣ የአፍሪካ ኢኮኖሚ እያደገ ሲሄድ ፣ በነጻው ፕሬስ ላይ የሚደርሰው አፈናም በዚያው ልክ እያደገ ነው ብለዋል። በአፍሪካ ውስጥ የሚካሄደውን ልማት የሚዘግቡ ጋዜጠኖች ፣ ስለ ሙስና፣ እና የውጭ አገር ባለሀብቶች ስለሚፈጽሙት አስነዋሪ ተግባር ሲዘግቡ ይዋከባሉ የሚሉት ኬይታ፣ ምእራባዊያን በአፍሪካ ዲሞክራሲ ተስፋ በመቁረጣቸው የልማት እርዳታቸውን ድህነትን በመቅረፍና በመረጋጋት ላይ ብቻ ትኩረት እንዲሰጡ እንዳደረጋቸው ገልጠዋል።
ትናንት ይላሉ ኬይታ ትናንት ምእራባዊያን የሩዋንዳውን ፖል ካጋሜና የኢትዮጵያውን መለስ ዜናዊ የፖለቲካና የማህበራዊ ታሀድሶ አራማጅ በማለት ያሞካሹዋቸው ነበር፣ ዛሬ ደግሞ እነዚህን መሪዎች የኢኮኖሚ እድገት ያመጡና ሰላምና መረጋጋትን ያሰፈኑ በማለት ያደንቋቸዋል፤ ይሁን እንጅ እነዚህ መሪዎች የተባሉትን ውጤቶች ያስመዘገቡት በአገራቸው ውስጥ ያሉትን ብሄራዊ ተቋማትና ነጻውን ፕሬስ በቁጥጥርራቸው ስር አድርገው መሆኑን ይዘነጉታል ብለዋል።
በአፍሪካ ውስጥ ሊመታየው የፕሬስ አፈና በአንድ በኩል ቻይናን ተጠያቂ ያደረጉት ኬይታ ፣ ከሶስት አመታት በፊት ቻይና እና የአፍሪካ መንግስታት ሚዲያዎች ሁሉ ህዝብ ከመንግስት ጎን እንዲሰለፍና አዎንታዊ ነገሮች ብቻ እንዲዘገቡ መስማማታቸውን ገልጠዋል። ይህ እይነቱ አቋም ከአፍሪካ አገሮች በደንብ የሚንጸባረቀው የምእራባዊያንን እርዳታ በገፍ በምታገኘው እና የቻይና ዋነኛ የንግድ ሸሪክ በሆነችው ኢትዮጵያ ላይ ያሉት ሞሀመድ ኬይታ፣ በኢትዮጵያ የሚገኙ እስር ቤቶች ልክ እንደ ቻይና እስር ቤቶች ሁሉ የተሞሉት በጋዜጠኞችና በተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅት አባላት ነው ሲሉ አክለዋል።
ጻሀፊው በኢትዮጵያ ውስጥ የሚታየው  የፖለቲካ አየር  እጅግ የሚረብሽ መሆኑን አውስተዋል። በ19 80ዎቹ የመንግስቱ ሀይለማርያም አምባገነን መንግስት በአገሪቱ ውስጥ ረሀብ ሲከሰት ለመደበቅ ቢሞክርም አለማቀፍ ጋዜጠኞች በስፍራው በመገኘት እውነታውን በማጋለጣቸው እርዳታ ሊደርስ ቻለ፣ ከሶስት አስርት በሁዋላ ደግሞ ኢትዮጵያ አሁንም በማህበራዊ ቀውስ እና በግጭት እየታመሰች ነው፣ ይሁን እንጅ ዛሬም ጋዜጠኞች ወደ እነዚህ ቦታዎች ገብተው እንዳይዘግቡ እገዳ ተጥሎባቸዋል፤ ይህን ቢያደርጉ በመንግስት አሸባሪ ጋዜጠኞች ተብለው ለእስር ይዳረጋሉ ሲሉ አትተዋል። የእርዳታ ድርጅቶች በኢትዮጵያ አለውን እውነታ ለመግለጽ እንደተሳናቸው የገለጡት ኬይታ፣ የሲቪል ሶሳይቲው፣ ነጻው ፕሬስና ተቃዋሚው በተዳከመበት ሁኔታ ለኢትዮጵያ የሚሰጠው የውጭ እርዳታ ለበጎ ምግባር መዋሉን እና አለመዋሉን  ለማረጋገጥ አይቻልም ያሉት ኬይታ፣ በሩዋንዳ ያለው ሁኔታም ተመሳሳይ መሆኑን ገልጠዋል።
የቻይና ኢንቨስትመንት በአፍሪካ ምንም አይነት ነጻ የሚባል ጋዜጣ እንዳይኖር እያደረገ በመሆኑ፣ በአሁኑ ጊዜ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በአፍሪካ ውስጥ ተገኘ ስለሚባለው የኢኮኖሚ እድገት አሀዝ፣  ስለ ስራ አጥነት፣ የገንዘብ ግሽበት፣ ስለማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች ሚዛናዊና ገለልተኛ ሪፖርት የሚያቀረቡ የአፍሪካ ፕሬሶች ከመቼውም ጊዜ በላይ ያስፈልጋሉ የሚሉት ኬይታ፣ ለአፍሪካ ፕሬስ እድገት የፖለቲካ እና ማህበራዊ ለውጦች ያስፈልጋሉ ሲሉ ደምድመዋል።
ሲፒጄ በኢትዮጵያ ያለውን የፕሬስ አፈና በተደጋጋሚ የሚያጋልጥ ድርጅት ነው።

Monday, 16 April 2012

Feeding Death Squads; UN’s World Food Program in Ethiopia

by IndepthAfrica | Posted on Sunday, April 15th, 2012


While southern Ethiopia and the Ogaden continues to suffer from the worst drought and famine in 60 years the UN’s World Food Program (WFP) has been turning over all its food aid for the region to the Ethiopian military which uses it to feed the paramilitary death squads conducting a counterinsurgency in the region.
The crimes committed by the UN in the Horn of Africa are legion and the WFP is not new to using its aid as a weapon against the people of our region (see WFP; Angel of Mercy or Angel of Death).
Over the past decade this writer has interviewed several UN workers who described how the UN through the WFP has been secretly turning over thousands of tons of food aid directly to the Ethiopian military instead of distributing it to the millions of starving Ethiopians and Ogadenis it was meant for.
The Ethiopian generals in turn use it as payment for the para-militaries, the “Liyu-police” they use as cover to do their dirty work, carrying out ethnic cleansing, mass murder and an ongoing scorched earth program in southern Ethiopia and in the south east in the Ogaden against the population in areas where the insurgency is raging against the Ethiopian regime.

What food is left over is sold by the Ethiopian generals on the black market with the proceeds pocketed, all the while millions are left to starve.

And what is the UN doing about this crime? Their motto seems to be “silence is golden” and silent they remain since they last sent teams to investigate the region in 2007, the reports of which have remained under lock and key in UN headquarters in Addis Ababa.
With the Red Cross (ICRC) and Doctors Without Borders (MSF) both expelled from southern Ethiopia and the Ogaden since 2007 there is no one other than the resistance movement to protest these crimes. Two Swedish journalist who attempted to enter the region in 2011 paid dearly, almost murdered by the Ethiopian death squads and now rotting in an Ethiopian dungeon convicted as “terrorists”.
All the while the real terrorists, the mafia calling itself the Government of Ethiopia headed by its godfather Meles Zenawi is free to carry out it’s crimes aided and abetted by the UN’s WFP, amongst others.
WFP, angel of mercy or devil in disguise? You be the judge.



Thomas C. Mountain is the only independent western journalist in the Horn of Africa living and reporting from Eritrea since 2006. He can be reached at thomascmountain at yahoo dot com.