የጋራ መግለጫ
ስማቸው ከዚህ በታች የተዘረዘረው በስደት ላይ ያሉ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ቅዳሜ ሚያዝያ 7 ቀን 2004 (April 14, 2012) በአንድ ላይ መጥተው በመለስ ዜናዊ አገዛዝ ላይ ዓለም አቀፍ የኢኮኖሚ ማዕቅብ ጥሪ አሰተላልፈዋል።
መገናኛ ብዙሃኑ ህዝባዊ ጥሪውን ለማቅረብ የጠሩትን ስብሰባ ከ600 በላይ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በኢንተርኔት ተከታትለውታል።
የኢኮኖሚ ማዕቀብ ህዝባዊ ጥሪው የሚከተሉትን ያጠቃልላል፤
1. በአሁኑ ወቅት ከዋና አስተዳደሩ ጀምሮ በጠቅላላ በህወሃት አባላት ቁጥጥር ስር የወደቀው የኢትዮጵያ አየር
መንገድ በብዙ ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ትርፍ ለመለስ ዜናዊና ግብረአበሮቹ እያስገኘላቸው ይገኛል። ይህ ድርጅት ከስሙ
በስተቀር ኢትዮጵያዊነት ባህሪይ የሌለው፥ ለኢትዮጵያ ህዝብ ምንም አይነት ጥቅም የማያስገኝ ሆኖ ስለተገኘ ይህ
ህዝባዊ ጥሪ ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ ማንኛውም ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ አየር መንገዱን እንዳይጠቀም፥
2. አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ማንኛውንም አይነት ማህበረሰባዊ ግንኙነት ከወያኔ አባላትና ደጋፊዎች ጋር ማቆም፥
3. ከኢትዮጵያ የሚመጣ እንጀራ፤ ቢራዎችና ሌሎችንም ወያኔ የሚቆጣረሯቸው ድርጅቶች የሚያመርቷቸውን ምርቶች አለመጠቀም፥
ይህን የኢኮኖሚ ማዕቀብ ጥሪ ተግባራዊ ለማድረግ ኢትዮጵያን ከህወሃት አገዛዝ ነጻ ለማውጣት የሚታገሉ ግለሰቦችና ድርጅቶች ሁሉ የበኩላቸውን ዝግጅትና ጥረት እንዲያደርጉ እንማጸናለን።
የሀይማኖት አባቶች፥ አርቲስቶች፥ ምሁራን፥ ስፖርተኞች፥ ነጋዴዎች፥ የሀገር ሽማግሌዎችና ማንኛውም ለሀገርና
ለህዝብ የሚቆረቆር ኢትዮጵያዊ ይህን የኢኮኖሚ ማዕቀብ ጥሪ እንዲያስተጋቡልንና ተፈጻሚ ለማድረግ እንዲተባበሩ
እንጠይቃለን።
ፈጣሪ ኢትዮጵያን ይባርክ።
አዲስ ድምጽ ራዲዮ
ዳላስ የኢትዮጵያ ድምጽ ራዲዮ
ኢትዮሜዲያ (Ethiomedia.com)
ኢትዮጵያ ዶት ኦርግ (Ethiopia.org)
የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች የውይይት መድረክ (Ethiopian Current Affairs Discussion Forum)
ኢትዮጵያን ሪቪው (EthiopianReview.com)
ህሊና ራዲዮ
ህብር ራዲዮ
ቃሌ የውይይት መድረክ (Qale Ethiopian Discussion Forum)
ማህደረአንድነት ራዲዮ
ዘሀብሻ ጋዜጣ
ዳላስ የኢትዮጵያ ድምጽ ራዲዮ
ኢትዮሜዲያ (Ethiomedia.com)
ኢትዮጵያ ዶት ኦርግ (Ethiopia.org)
የኢትዮጵያ ወቅታዊ ጉዳዮች የውይይት መድረክ (Ethiopian Current Affairs Discussion Forum)
ኢትዮጵያን ሪቪው (EthiopianReview.com)
ህሊና ራዲዮ
ህብር ራዲዮ
ቃሌ የውይይት መድረክ (Qale Ethiopian Discussion Forum)
ማህደረአንድነት ራዲዮ
ዘሀብሻ ጋዜጣ
No comments:
Post a Comment