Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Sunday 11 November 2012

በሚዛን ተፈሪ አቅራቢያ አንድ ወር ያስቈጠረ ግጭት ሊቆም አልቻለም

ህዳር ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ከሚዛን ተፈሪ 90 ኪሎ ሜትር ርቀት  ላይ በምትገኘውና  ልዩ ስሟ <<ዲማ>> ተብሎ በሚጠራው ቦታ በሱርማ እና በዲዙ ብሔረሰብ መካከል በተፈጠረ ግጭት በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች መጎዳታቸው ተሰማ።
ጉዳዩን አስመልክተው ለኢሳት  ቃለ-ምልልስ የሰጡ የአካባቢው ነዋሪዎች እንዳሉት፤ግጭቱ ከተከሰተ አንድ ወር ያስቆጠረ ቢሆንም፤ እስካሁን ሊበርድ አልቻለም።
የፌዴራል የመከላከያ ሠራዊት ወደ ስፋራው ቢላክም ግጭቱን ብስለት በተሞላበት መንገድ ከማረጋጋት ይልቅ ሀይል ወደ መጠቀም በማዘንበሉ፤ ረብሻውና ትርምሱ ተባብሶ  ሊቀጥል ችሏል-ይላሉ ነዋሪዎቹ።
በደቡብ ሱዳን አቅራቢያ የሚገኙት የሱርማ ብሄረሰብ አባላት በህገ-መንግስቱ የሰፈሩት የፖለቲካ መብቶቻችን አልተከበሩልንም በማለት በተደጋጋሚ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ መሆኑ ይታወሳል።
የብሔረሰቡ አባላት<<የፖለቲካ ጥያቄዎቻችን አልተፈቱም>>እያሉ ባሉበት ሁኔታ  ይባስ ብሎ አካባቢያቸውን ለቅቀው ወደሌላ ቦታ እንዲሰፍሩ መታዘዛቸው፤  የመጠቃት ስሜት እንደፈጠረባቸውና ቁጡ እንዳደረጋቸው ነዋሪዎቹ ይናገራሉ።
<<ዲማ>.የተባለችው ስፍራ በወርቅ ሀብት የበለጸገች በመሆኗ  በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ ክልሎች እየፈለሱ በባህላዊ መንገድ ወርቅ ለማምረት ወደዚያው ማቅናታቸውን የገለጹት ነዋሪዎቹ፤  ወርቅ ለማምረት ብለው የሄዱት እነዚህ ወገኖች በሁለቱ ብሄረሰቦች ሳቢያ  የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት እየደረሰባቸው እንደሚገኙ ተናግረዋል።
ከአንድ ወር በላይ ያስቆጠረውና እስካሁን እልባት ሊያገኝ ያልቻለው የአካባቢው ግጭት በመንግስት ሚዲያ አንድ ጊዜ እንኳ ሊነገር አለመቻሉን የገለጹት ነዋሪዎቹ፦<<ድረሱልን! ሰሚ አላገኘንም፣ እየጠፋን ነው>>ሲሉ ኢሳትን ተማጽነዋል።
እስካሁን በግጭቱ  ከስምንት እስከ ዘጠኝ ሰዎች መሞታቸውን የገለፁት ነዋሪዎቹ ፤የቁስለኞችን ብዛት ግን ለመገመት እንደማይችሉ ተናግረዋል።
ከዚህም በላይ  ከአካባቢው  ወደ ሚዛን ተፈሪ ለመምጣት መሞከር እንደማይቻል የተናገሩት ነዋሪዎቹ ፤ለንግድ የሚንቀሳቀሱ ሰዎች  በመንገድ ላይ በሰፈሩ የመከላከያ ሰራዊት አባላት፦  <<ሰላም የለም የሚል ወሬ ለማቀበል ነው>> እየተባሉ ሰለባ እንደሚሆኑ አብራርተዋል።

No comments:

Post a Comment