ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ መሞታቸው ሁሉም ሰው ያሳዘነ ጉዳይ ነው፡፡ ለምን ከተባለ ሁሉም ሰው ከመሞት የሚያመልጥ ባይኖርም የአሟሟታቸው ሁኔታ ግን ለየት ባለ ሁኔታ ስለተፈፀመ በጣም ያሳዝናል፡፡
መጀመሪያ በሪፖርተር ጋዜጣ አንድ የመንግሥት ቃለ-አቀባይ መነሻ በሌለው ሁኔታ ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ የጤና ችግር የለባቸውም የሚል መግለጫ ሰጠ፡፡ ሰዉየው ይህ ያሉበት ምክንያት ምንድነው? ስለጤናቸው ምን ተብሎ እና ነው ይህን መግለጫ የሰጡ ማለት ጀመረ፡፡ በስተጀርባ አንድ ነገር እንዳለ ጥርጣሬ ውስጥ ገባ፡፡
ቆየት ብለው ጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ታመው ህክምና እንደገቡና ህመሙም የሚያሰጋ እንዳልሆነ መግለጫ ተሰጠ፡፡ ቆየት ብለውም በተለይ አቶ በረከት ስምዖን በዕረፍት ላይ መሆናቸው በቅርብ ግዜ ሥራቸው እንደሚጀምሩ መግለጫ ሰጡ፡፡
ይህ ሁላ ሲሆን ግን አንድ ደ/ር እንኳ ስለየጤንነታቸው ጉዳይ መግለጫ የሰጠ አልነበረም፡፡ ይህ ህዝቡ በበለጠ ጥርጣሬ ውስጥ ከተተው፡፡ የታመመ ሰው ስለህመሙ የሚያቅና ሁኔታውን ማብራራት የሚችል ሃኪም ነው ስለ ጠቅላይ ሚኒስቴር የጤንነት ጉዳይ የሚነገረን ያለ በመንግሥት ሥልጣን ባሉ ሰዎች ነው ይህንን ነገር እንዴት ነው በማለት ራሱ በራሱ መወያየት ጀመረ፡፡ የሃኪም መግለጫ ሳይሰማ ዜና ዕረፍታቸው ተሰማ፡፡ መሞታቸው በጣም አሳዝኖናል፡፡
የጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ባህሪያት
ለተነሱለት ዓላማ በፅናት የሚተገብሩ ሰው ነበሩ፡፡ የሆነ ሐሳብ አቅርበው ተቀባይነት ካላገኘ ሞተው ይገኛሉ፡፡ በሐሳባቸውና በአመለካከታቸው የሚነሱ ልዩነቶች ፍፁም አያስተናግዱም፡፡ ለማስተናገድ ቢሞኩሩም የትም አይደርስም ብለው የገመቱት እንደሆነ ብቻ ነው፡፡
በዓቅም የሚቀናቀናቸው ሰው አይወዱም፡፡ ብዙ አብነቶች ማቅረብ ይቻላል፡፡ አቶ አርከበ ዕቁባይ አቶ መለስ እንደሚጠሩዋቸው “ጅብ” ናቸው፡፡ ጅብነታቸው በሥራ ነው፡፡ የትግራይ ም/ፕሬሲዳንት በነበሩበት ጊዜ አንዳንድ መሰረታዊ ለውጥ ለማምጣት ሲሞኩሩ አዲስ አበባ ወስደው የአዲስ አበባ ከንቲባ ሁነው እንዲሾሙ አደረጉ፡፡ በዚ ጊዜ በተለይ በነጋዴው የአገልግሎት አሰጣጥ ለውጥ ሲያስመዘግቡ ቀለም ከመቀባት የማያልፍ ሥራ ነው የሠራኸው ብለው መዓት ወረዱባቸው፡፡ ከዛ በኋላ የማዕድንና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስቴር ድኤታ ሁነው እንዲሠሩ ተደረገ፡፡ ከዛ በማንሳት ደግሞ አማካሪ ብለው ሰው በማያያቸው (አቅማቸው ህዝቡ በማያየው ዋሻ) እንዲገቡ አደረጉ፡፡ይህ ሁሉ መነሻው ስጋት ነው፡፡ አቶ አርከባ በግልፅ መቃወም አልደፈሩም እንጂ ውስጣቸው ከኛ በላይ የአቶ መለስ በላያቸው ላይ ያደረጉት ዘመቻ ያውቁታል፡፡ በዚህ ቅሬታ ነበር በህወሐት ማእከላዊ ኮሚቴ ለፖሊት ቢሮ ምርጫ አልፈልግም ብለው ራሳቸው ያገለሉት፡፡
አቶ መለስ በተለይ “ከተሃድሶ” በኋላ እሳቸው እንደአስተማሪ የቀረው ማእከላዊ ኮሚቴ የህወሐት/ኢህአዴግ እንደተማሪ ወንበር ላይ ቁጭ ብሎ የሚማርበት ሁኔታ ነው የነበረ፡፡
የዚህ ጉዳት በጣም ብዙ ነው፡፡ አቶ መለስ ብቁ ሰው ማፍራት አልቻሉም፡፡ በተለይ በትግራይ፡፡ ወጣቱ ትውልድ ሥልጣን ላይ እንዲወጣ አይፈለግም ለምን አይታመንማ፡፡ ነባሩ ታጋይ ደግሞ እሳቸውን በዓቅም የሚወዳደር አጥላልተው ሞራሉ እንዲነካ ያደርጉታል፡፡ እነ አባይ ፀሃዬ፣ሥዩም መስፍንና አርከበ ዕቁባይ የዚህ አብነቶች ናቸው፡፡
አቶ መለስ ስልጣን ሙሉ በሙሉ ሳይቆጣጠሩ ጊዜ ያሳዩት የነበረ በህሪ ብዙም አይስተዋልም ነበር፡፡ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራሮች ለነበሩ ሰዎች የሚያሳዩትን ስህተቶች ማረም፣ ለህዝብ ተብሎ ሐቅም ቢሆን ህዝቡ ካልተቀበለው ድርጅቱ ተቀብሎ ተግባራዊ ማድረግ ይጠበቅብናል ሲሉ ይስተዋሉ ነበር፡፡ ስልጣን ሙሉ በሙሉ በተቆጣጠሩበት ጊዜ ጀምሮ ግን አንድ ቀንም ህዝቡን ያነሳው ጥያቄ ወይም አንፈልገውም ያለውን ነገር ተቀብለው አያውቁም፡፡ ለምሳሌ፡ የሊዝ አዋጅ መጥቀስ ይቻላል፡፡ ህዝብ ሲቃወም የተቃዋሚ ድርጅቶች ሐሳብ ነው ተብሎ ይፈረጃል፡፡ ያነሳ ሰውም እንዲሁ፡፡
ለስልጣን ብለው ዲሞክራሲ ያፍናሉ፡፡ እስከአሁን የተካሄዱ ምርጫዎች ህያው አብነቶች ናቸው፡፡ የተካሄዱ ምርጫዎች ሁሉም በማጭበርበር እንጂ ህዝቡ በነጻነት ያካሄደው ምርጫ አይደለም፡፡ ህዝቡ የፈለገው ፖለቲካዊ ፓርቲ መርጧል ማለት ፍፁም አይቻልም፡፡
እርግጥ ነው በ1997 ዓ.ም ዲሞክራሲ ባልገመቱት ሁኔታ ህዝቡ ተነሳስቶ እነሱን ገፍትሮ የመሰለውን የፖለቲካ ፓርቲ መምረጥ በቅቶ ነበር፡፡ በተለይ የአዲስ አበባ ህዝብ በድፍን ቅንጅትን መርጦ ነበር፡፡ ቅንጅት መከራን ተቀብሎ ህዝብን ለማገልገል ስላልተነሳ የህዝብን ድምጽ መንገድ ላይ ጥሎት ሄደ፡፡ የዚሁ ጠባሳ አሁን የምናየው ያለን ዓይነት ምርጫ እንድናስተናግድ ተገደናል፡፡ ይህም ሆኖ ቅንጅት ሥልጣን ይይዛል ከሚል ፍራቻ ምርጫው ከተካሄደ በነገታው አዲስ አበባ ለኦሮምያ ክልል ተሰጥታለች ብሎ በፓርላማ እንዲታወጅ አገረጉ አቶ መለስ፡፡ ይህ የልጆች ጨዋታ ግን ደግሞ ይቅር የማይባል የታሪክ ስህተት ለምን ተደረገ ብለን ካልን የቅንጅትን ዓቅም ለማዳከም ተብሎ ነበር፡፡ ለዚህ ነው አቶ መለስ ለሥልጣን ብለው የማያደርጉት ነገር የለም ያልነው፡፡
በፍትሕ በኩል ስንሄድ፤ ዳኛችና ዓቃቢያነ-ህግ በሙያቸው ባላቸው ብቃት ሳይሆን በፖለቲካ ተአማኒነታቸው ብቻ ነው ዳኛችና ዓቃቢያነ ህግ ሊሾሙ የቻሉት፡፡ ይህ በህዝብ ላይ ከፍተኛ የፍትሕ ዕጦት ፈጥሮ ህዝቡ ዕሪ እያለ ይገኛል፡፡ ሁሉም ነገር አሁን በጉቦ ነው የሚፈፀመው፡፡ ከቀበሌ እስከ ከፍተኛ ፍርድ ቤትና የፍትሕ አካላት፡፡ መሬት በካድሬዎች ስለሚስተዳደር እንደፈለጉት እያደረጉት ይገኛል፡፡
በሌሎች የመንግሥት ሥራዎችም ኃላፊነት የሚሰጣቸው በፖለቲካ አባልነታቸው ነው ብቃት፣ትምህርት፣ስራ ልምድ አይሰራም፡፡ ይህ ማንን እየጎዳ ይገኛል ? ህዝብ ነዋ፡፡ ታድያ ህዝብ የሚጎዳ ከሆነ ለምን ተመረጠ ? ለስልጣን ተብሎ፡፡ ስልጣንን ከህዝብ ማስቀደም ማለት ነው? በትክክል፡፡
ሙስናን በሚመለከት፡- ጠ/ሚኒስቴር መለስ ሙስና መዋጋት አይፈልጉም፡፡ ለምን ? በሥልጣን ላይ ያሉ ሰዎች በፈፀሙት ህግ ፊት በማቅረብ ፍርድ እንዲገኙ አይፈልጉም፡፡ ምክንያት፡-
1ኛ. የቀኝ እጃቸው የሆኑ በሙስና የተዘፈቁ በመሆናቸው አሳልፈው መስጠት አይደፍሩም፡፡
2ኛ. ለቅርብ ወዳጆቻቸው ካላጋለጡ ሌለሎች ማጋለጥ ድፍረት አያገኙም፡፡ በዚህ ምክንያት ከድሃው ህዝብ ብዙ ሚሊዮን የአገሪቱ ሃብት ጥቂት ባለሥልጣናት እያግበሰበሰት ይገኛል፡፡
አድልዎ ወገናዊነት በሰፊው ይስተዋላል፡፡ ከዩኒቨርስቲ ተመርቆ የሚወጣው ወጣት በመንግሥትም ይሁን በፖለቲካ ድርጅቶቻቸው ስም የተቋቋሙ የኢኮኖሚ ካምፓኒዎቻቸው ለመቅጠር አንችልም ራስህ ተደራጅተው ሥራ ፍጠር ይሉታል፡፡ ወጣቱም ሌላ አማራጭ ስለሌለው በድንጋይ ጠረባ፣በኮብል ስቶን ሥራ፣በብሎኬት፣በልስን እና በሌሎች የሥራ ዘርፎች ሳይወድ በግድ ያልፍልኝ ይሆናል በሚል ተስፋ ሲንቀሳቀስ ይገኛል፡፡ የባለሥልጣኖች ልጆች ግን በነዚህ የወጣቶች የኢኮኖሚ ድርጅቶች ብለው በሚጠሩዋቸው ድርጅቶች አንድም የለም፡፡ የሚበዙ ውጭ አገር ተምረው በዛው የቀሩ ናቸው ሌሎች ደግሞ ትእምት በሚባል የህወሐት ካምኒ ተቀጥረውና ሃላፊ በመሆን ወፈር ያለ ደመወዝ እየተከፈላቸው የተንደላቀቀ ኑሮ ይኖራሉ፡፡
በመንግሥት ሥራ የሚገቡ የባለ ሥልጣናት ልጆች በባለሥላናት ግምገማ ወላጆቻቸው ብዙም ተሰሚነት የሌላቸው የማእከላይ ኮሚቴ ኣብል ልጆች ናቸው፡፡ አብነት የአቶ ጎበዛይ ወ/አረጋይ ልጅ የመጀመሪያ ድግሪ እንደያዘ ወድያው በፖስታ ቤት አዲስ አበባ ያለውድድር በቀጥታ እንዲቀጠር ተደርጓል፡፡ የሳቸው ልጅ ብቻ ነው በመንግሥት ሥራ ያለው፡፡ ምክንያቱም ቀደም ብለን የዘረዘርነው ነው፡፡
ሌላው የሙስናና የአድልዎ መግለጫም አለ፡-
በተለያየ የሥልጣን እርከን ሲሠሩ የቆዩ ካድሬዎች በህዝብ ግምገማ ከስልጣናቸው በግድ እንዲወገዱ ይደረጋል፡፡ ይህ ህዝብ ገምግሞ ያስወገዳቸው ሳይሆን በህዝብ የተጠሉ መሆናቸው ሲታወቅ ድርጅቱ ከነበሩበት የሥልጣን ቦታ ቶሎ በማንሳት በፈፀሙት በደል ከመቅጣት ፈንታ የተሻለ ቦታ ተፈልጎላቸው እንዲመደቡ ይደረጋል፡፡ በዚህ ላይ ብዙ አብነቶች መጥቀስ ይቻላል፡-
የዓድዋ ከተማ ከንቲባ የነበሩ አቶ አርአያ መርአድ በሙስና ተዘፍቀው ህዝቡ ከፍተኛ እሮሮ ሲያሰማ ከሳቸው በታች የነበሩ በማሰር እሳቸው ግን በወ/ሮ አዜብ መስፍን ውቅሮ በሚገኘው የቀዳ ፋብሪካ ከ10000.00ነ ብር ለወር እየተከፈላቸው እዛው እንዲውሉ ተደርገዋል፡፡ አቶ ንጉስ የተባሉ የማቸው ከንተባ የነበሩም እንዲሁ በዚህ የቆዳ ፋብሪካ በተመሳሳይ ደመወዝ ተከፍለዋቸው ዕረፍት እንዲወስዱ ተደርገዋል፡፡ አተ ጉዕሽ ሊላይ የተባሉም የአላማጣ ከተማ ከንቲባ የነበሩ ተገምግመው ከወረዱ ኋላ ወ/አዜብ መስፍን በፌደራል በጉምርክ ተመድበው ማን ወጣ ማን ገባ እየመዘገቡ ከፍ ያለን ደመወዝ አየተከፈላቸው ይገኛል፡፡
አቶ መርሃ ገ/ሚካኤል የትግራይ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ከሞሽን ኮሚሽነር የነበሩም፡፡ ከነበሩበት ቦታ በማንሳት የትግራይ በወ/አዜብ መስፍን ጉምርክ ኃላፊ ሁነው ተሹመዋል፡፡ ይህ ለኮሚሽነር ዘአማኑኤል በጣም ያበሳጨ ተግባር ሁኖ ተገኝተዋል፡፡ እኔ ሳሎሁ እንዴት ምክትሌ ይህ መዓት ገንዘብ እንዲያገኝ ይደረጋል ከሚል ፡፡
ዳርድንበርን ማስከበር በሚመለከት፡- የባድመ ጉዳይ አንድ ጉልህ አብነት ነው፡፡ ውሳኔው ለኤርትራ ነው ከተባለ በኋላ እንቀበለው ብለው ካድሬዎቻቸውን በሙሉ አሜን ብሎ እንዲቀበሉት አደረጉ፡፡ አንድ ሁለት የሚሆኑ ካድሬዎች ተቃውሞአቸውን አቀረቡ፡፡ በዚህ ምክንያት ከማእከላይ ኮሚቴ እንዲወገዱ ተደረገ፡፡ ቀጥለው ከሥራም ተባርረዋል፡፡የህዝብ ተቃውሞ እያየለ ከመጣ በኋላ ባለ5 የሰላም እማመ በሚል የህዝቡን ተቃውሞ ለማከሰም ድርሰት ደርሰው ባመቅረብ አንቀበለውም በማለት የተለየ ሐሳብ በባድመ እንደሌላቸው መስለው ብቅ አሉ፡፡
ኢትዮጵያ ወደብ እያላት ወደብ አልባ መሆን የለባትም፤በህጋዊ መንገድ ወደባችንን ማግኘት እንችላለን ላለ ሁሉ የጦርነት አቀንቃኝ ተባለ፡፡ የኢትዮጵያ ወጣት በረንዳ ላይ እያደረ ከኤርትራ የመጡ ወጣቶች ዩኒቨርስቲ ገብተው በሃብታችን የመማር መብት አረጋገጡላቸው፡፡
ይህ ከሆነ ሐቁ የጠቅላይ ሚኒስቴር መለስ ወጣቱ መውረስ ያለበት የቱ ነው ?
አፋኝነታቸው?ለሥልጣን ተብሎ ፀረ-ዲመክራሲ መሆን? ለሥልጣን ተብሎ ብቃት የሌላቸው ሥልጣን ላይ በማምጣት ህዝቡን መጉዳት? ምኑን እንማር?
ከጠቅላይ መኒስቴር መማር ያለብን፡- ለሥራቸው ጥብቅ መሆናቸው፣የማንበብ ልምዳቸው፣ያነበቡት ወደተግባር መተርጎማቸው ነው፡፡ ይህንን ስንወርስ ግን ለህዝብ ባለው ፋይዳ ብቻ እንጂ ስለዕውቀትና ስለማንበብ ወይም ህዝብን በሚጎዳ መንገድ መውሰድ የለብንም፡፡ ሌላው ግን ቢቀርብን ይሻላል፡፡ሠ
ከማርታ መቐለ
ኢትዮሚድያ - Ethiomedia.com
October 2, 2012

No comments:
Post a Comment