Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Wednesday, 16 January 2013

ኢትዮጵያ፤የመዳኛወቅትና፤የዕረቀሰላምጊዜ

ከፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም
ትርጉም ከነጻነት ለሃገሬ
      የረፖርተር ድሕረ ገፅ ሲዘግብ:
‹‹በጎሳ ላይ የተመሰረተ ግጭት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሃል በመጸዳጃ ቤቶች፤ በቤተመጻህፍትና በመኝታ ቤት  ግድግዳ ላይ፤የተጻፉ አስፀያፊ ክብረነክ ጸሁፎች ከስድስት በላይ የሆኑ ተማሪዎችን ለከፍተኛ የመቁሰል አደጋ ተጠቂ ዳርጓቸዋል:: በርካታዎችንም ለእስር አብቅቷል፡፡ ለላለፉት አሰርት ዓመታት፤በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሃል ግጭቶችን ሲያስነሱ ከርመዋል፡፡ ይህም መሰረታዊ ችግሩና መንስኤው አስተዳደራዊ ድክመት ነው፡፡ ከዚሁ ጋር በተመሳሳይ ባለፈው በእለተ ዕረቡ ጃንዋሪ 2 2013 የተቀሰቀሰው ግጭትም በተለይ በሁለት ጎሳዎች በኦሮሞና በትግራይ ተማሪዎች መሃል የተከሰተ ነበር፡፡ ምስክሮች እንደሚሉት፤ግጭቱ የተቀሰቀሰው የትግራይ ተወላጅ የሆነው ተማሪ፤ በመጸዳጃ ቤት፤ በቤተመጻህፍትና በተማሪዎች መኝታ ቤቶች  ግድግዳዎች ላይ የጎሳን ክብር የሚነካ ጽሁፍ በመጻፉ ነበር፡፡››
እንደ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባለስልጣን አባባል ‹‹ግጭቱ የተቀሰቀሰው ያንን የጎሣ ክብር የሚነካ ክብረነክ ጽሁፍ በተመለከቱት ተማሪዎች  መሆኑን ነው::›› በዚህም የተነሳ 20 ተማሪዎች መቁሰላችውንና 3ቱ የጠናባቸው ወደ ሆስፒታ፤ል መወሰዳቸውን በተጨማሪ ሁለቱ የቀዶ ጥገና እንደተደረገላቸው ታውቋል፡፡ ሌሎች 20ዎችም በፖሊስ ባልለየለት ውንጀላ ለእስር ተዳርገዋል፡፡
ስለኢትዮጵያ ‹‹የብልሆች መፍለቂያ ከነበረው ዩኒቨርሲቲ›› ይህን ሁኔታ ሳነበው ያደረብኝ ግብታዊ አስተያየት፤ ማመን እስኪያቅተኝ ነበር፡፡ ሳስበዉም ‹‹ይህ ፈጽሞ ሊታመን የሚችል ጉዳይ አይደልም፡፡ ይህ ከኢትዮጵያ አነሮች ትውልድ (ወጣቱ ትውልድ) በዚህ ፈሪነትና የማያስፈራራ አስከፊ ሁኔታ ውስጥ መግባት ተግባራቸው አይደለም፡፡ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በዚህ ቆሻሻ እና እጣቢ አተላ የጎሳ ፖለቲካ ውስጥ ከመንደፋደፍ የተሸለና የበለጠ ተግባር ማከናውን ይችላሉ›› አልኩኝ :: ይህን የመሰለ የረከሰ የጥላቻ ምግባር፤የወዲፊቶቹ ኢትዮጵያዊያን ምሁራን፤የቀጣዩ ትውልድ መምህራን፤ ሳይንቲስቶች፤ እና የፈጠራ ሰዎች ምግባር እንዳልሆነ ነበር እራሴን ማሳመን የሞከርኩት፡፡
ነገሩን የበለጠ ሳጤነው አምአሮ የሚነካና የሚአስቀፍፍ ሆኖ አገኘሁት፡፡ እራሴንም ጠየቅሁ፡፡ ምናልባትስ ይህ የጎሳ ክብር የሚነካ ጽሁፍ በሌሎች የአ አ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች  የተፈጠረ ቢሆንስ? ይህን የመሰለው ዝቃጭ፤ወኔቢስ፤ባለጌ ተግባር ስለነዚህ ተማሪዎች ምን ይላል? ስለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችስ? ስለአጠቃላዮቹ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችስ? ስለ መላው የኢትዮጵያ ወጣቶችስ?

ከዚህ ጥየቄ ጋር በመታገል ላይ እንዳለሁ፤ ሊገታ የማይችል ሃፍረትና ውርደት ሰሜት ወረረኝ፡፡ እራሴን ደጋግሜ መረመርኩት፡፡ ‹‹የኢትዮጵያ ምርጥና ብሩህ አእምሮ ያለቸው ተማሪዎች—- የኢዮጵያ አነሮች —- ይህን በመሰል ኋላ ቀር፤ አረመኔያዊ፤ ጨካኝና አሰቃቂ፤ ተናካሽ፤ ተንኮል የተመላበት፤ተግባር አንዴት ሊሰሩ ይችላሉ?  በምን መንስኤ ነው፤ አንድ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ስብስብ ሌላውን ወገን ስብእና ለመድፈር፤ የጋኔን ተግባር ለመፈጸም፤ ዝቅ አድርጎ ለመመልከት፤ አውሬ በማስመሰል፤ አካሄድና ተግባር የሚሰማሩት? ለምን? እኮ ለምን? ለነዚህ ጥያቄዎች አንዳችም ምክንያታዊ ምላሽ ላገኝ አልቻልኩም፡፡
ይህ የ ጎሳ  ጥላቻ ወንጀል የተፈጸመው ባለፈው ሳምንት ሰለ አትዮጴያ ወጣቶች ክብርና ወደፊት ላገራቸው ሰለምተበቀባቸው ግዴታ በመፅፈበት ወቅት ነበር :: ሆነ በተባለው የጎሳ ጥላቻ ወንጀል የበለጠ ግራ እየተጋባሁ ሄድኩ፡፡ ይህን አስጠያፊና አስፈሪ፤ ቀፋፊ ሁኔታ በምክንያታዊነት በጥልቀት ለመረዳትና በዚህ አስገራሚ ትርኢት ውስጥ አንዳንድ የኢትዮጵያ አነሮች እንደ ጉማሬዎቹ በመንቀሳቀስ እንደጅቦቹ ለመሆን መከጀላቸው አስገረመኝ፡፡ አሳፈረኝ፡፡ አሳዘነኝ፡፡
ያን ግልብ ስሜቴን ወደ ጎን አልኩና ረጋ ብዬ ማሰብ ጀመርኩ:: ከምር ጠንክሬ አሰብኩ፡፡ ይህ በዩኒቨርሲቲው የተከናወነው ‹‹በጎሳ ላይ የተመሰረተውን አልመግባባት›› ድርጊት ከጥሩ እምነት ካላቸው ሁነኛ መደበኛ ተማሪዎች ተጠንስሶ በስራ ላይ የዋለ ነው  ለማለት ምን ማስረጃ ሊቀርብ ይችላል? በእውነትስ  የተባለውና በዚህ በየግድግዳው ላይ የሰፈሩትን ክብረ ነክ ጽሁፎች የጻፈው ‹‹ተማሪ›› ማነው?  በዚህ ዩኒቨርሲቲ የሙዚቃ ሸክላ አጫዋች መሰል የህዝብ ግንኙነት ጽህፈት ቤት ተቀምሞ የተበተነውን መሸንገያ አባባል ማመን አለብን? እንዴት ነው የዩኒቨርሲቲ አስተዳዳሪዎች  ‹‹ለአሰርት ዓመታት በዩኒቨርሲቲዎች ሲከናወኑ የነበሩትን የጎሳ ግጭቶች” ያሳለፏቸውና አሁንም ሲቀጥሉ  አጃቸዉን አጣጥፈው  መመልከት የቻሉት? በዩኒቨርሲቲውስ ውስጥ ምራቃቸውን የዋጡና የበሰሉ፤ችግሮችን ለማክሸፍና ለማግባባት ፈቃደኛ የሆኑ አመራሮች የሉም?
ጥርጣሬ ቀስ እያለ፤ድንጋጤዬንና ሃፍረቴ  መተካት ስለጀመረ፤ የዚህ ‹‹በጎሳ ላይ የተመሰረተ ብጥብጥ›› በገዢው መንግስት ጀብደኛ ባለማዕረግ የተዋቀረና፤ የተተለመ እንደሆነስ የሚለው ጥያቄ አያፈጠጠ ያየኝ ጀመር፡፡ በኋላም የወንጀል መመርመርያ ማስረጃ ማፈላለጊያ “መነጽሬን” ሳደርገው፤ እንደገና በመሹለክለክ ድምጽዋን አጥፍታ ጨለማና ወቅትን መከለያ በማድረግ አንዲት መናጢና ቆሻሻ አይጥ ተንኮሏን ከፈጸመችና ተልእኮዋን ከፈጸመች በኋላ ሳትታይ ጥላው  የሄደችውን የእጇንና የእግሯን አሸራ በግድገዳ ላይ ከተጻፈው አስጠያፊ ጥሁፍ አግርጌ ታትሞ አየሁት፡፡
በሜይ 2010 ጃዋር ሲራጅ ሞሃመድ ወጣቱ ኢትዮጵያዊ የፖለቲካ ሐተታ ሰጪ እንዲሁም የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ተመራቂ ተማሪ እንደዘገበው  በዩኒ ቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ከተማሪዎች ጋር በርካታ ውይይት ካካሄደ በኋላ እንዲሁም በሁለት ክፍል በሃራማያና፤በአዳማ  ዩኒ ቨርሲቲ በ2006 የተከናወነውን ድርጊት  ሰበቡን የአካዳሚክ ነጻነት ማጣትና በኢትዮጵያ የደህንነት ሚስጥራዊ ተቀጣሪዎች ተማሪ በመምሰል ሰርገው በመግባት የግጭቱ መሰሪ ጠንሳሾች መሆናቸውን ለማመን በቅቷል፡፡
ደግሞም በሴፕቴምበር 2011 ላይ በይፋ የዎጣው ማስረጃ አንዳሳየው በሴፕቴምበር 16 2006 “ የኢትዮጵያ የደህንነት ሃይሎች በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ 3 ፈንጂዎች መቅበራቸውንና በመፈንዳቱና፤ በወቅቱም የአፍሪካ ሕብረት ስብሰባ የሚካሄድበት ስለነበረ ከረር ያለ ጥያቄ ያስነሳውን  ፍንዳታም ኤርትራንና የኦሮሞ ነጻ አውጪ ግንባርን ተጠያቂ እንዳደረጉ ነበር::” በአዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካን መንግስት ኤምባሲ ባካሄደው ‹‹የሚስጢር ዘገባ›› በጉዳዩ ላይ የመርማሪዎቹ ጣት  ወደ ኢትዮጵያ ገዢ መንግስት የደህንነት አባላትን በመጠቆም ለዚህ የወንጀል ድርጊት ተጠያቂ አድርጓቸዋል፡፡
በሌላም በኩል በ2006 የተገኘው ሚስጥራዊው ባለ 52 ገጽ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የተዘጋጀው ሰነድ፤ የዲያስፖራው ዳይሬክቶሬት በዲያስፖራው ያሉትን የተቃዋሚ ሃይላትና አባሎቻቸውን የሚነዘንዝ፤ በሃይማኖት፤ በዘር፤ በፖለቲካ ጥላቻ የሚከፋፍልና ማንኛቸውንም ገዢውን ፓርቲ የሚቃወሙትን ለመከፋፈልና በመሃላቸው መግባባት እንዲጠፋ ያደረገው ጥረትና ዝግጅት ተጋልጦ ነበር ፡፡ ስለ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አጋጣሚ በይበልጥ ባሰብኩ ቁጥር፤የገዢው መንግስት ተቃዋሚዎችን ለማስጠላት ለመከፋፈል ለመበታተን ለማክሸፍ ብሎ የሚዘራውን ቆሻሻና የብልግና ባህሪ ያጋልጡት ጀምረዋል፡፡
በተጨባጭ ምርምሬ አንደተርዳሁት ‹‹በጎሳ ላይ ለተመሰረተው ግጭት›› ወንጀል በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ  ተጠያቂው ማን እንደሆነ ግልጽ የሆነው ማስረጃ  የሚጠቆመው ወደ ተለመዱት ወንጀል ፈጻሚ የገዢው መንገስት ወንጀለኞች ነው፡፡
ሊታለፍ የማይችለው መደምደሚያም፤ (ሌላ ተቃራኒ  ማስረጃ  እስካልቀረበ ድረስ) በጃንዋሪ 2 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለተፈጸመው ወንጀላዊ  ተግባር ተጠያቂዎቹ፤ በግቢው ውስጥ በድብቅ የተቀመጡት መዘዝ ፈጣሪዎችና ምግባረ ብልሹ ሕሊና ቢስ  ወኪል ተንኳሾችና ደባ ፈጻሚዎች እንጂ ጨርሶ ለጥሩ ዕምነት የተፈጠሩት ወጣት አቦሸማኔዎቹ የነገ የሃገር አለኝተ ዎች ሊሆኑ አይችሉም፡፡
የማጠቃለያው ግምገማም ይህንን መደምደሚያ የማያጠያይቅ ማስረጃ በመሆን ያረጋግጠዋል፡፡ ያለዉን ማስረጃ በጥቂቱ ብንመለከተው: በመጀመርያ እንድ ብቸኛ “ተማሪ”ብቻ ነው ድርጊቱን በመተንኮሱ  የተወነጀለው፡፡ ይህ ደግሞ ተማሪዎች በአንድ ጎሳ ስር ተቧድነው ለዚህ ድርጊት መንቀሳቀሳቸውንና በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ ሰላም ለማጥፋት ወንጀል ለመፈጸም፤ መደራጀታቸውን ተአማኒነት ያሳጣዋል፡፡  ይህን እንቅሳቃሴ ለመጀመርና መነሻ ሆነ የተባለውም ብቸኛ “ተማሪ” የየት ጎሳ አባል እንደሆነ በግልጽ አልተረጋገጠም፡፡ የዩኒቨርሲቲው ባለስልጣናት: ስምና መለያው ያልታወቀ፤ አንድ ተማሪ በማለት ወንጀለኛ ብለውታል፡፡ ይሁንና ይህ ‹‹ተማሪ›› ዓላማ ያለው እርገግጠኛ  መደበኛ “ተማሪስ” ነው? ወይስ ተቀጣሪ ነገር ቆስቋሽ የስለላ ድርጅት ወኪል ግን እንደተማሪ ተመሳስሎ ተወሻቂ አባል (የቀበሮ መንኩሴ በግ መሃል ይጸለያል አንደሚባለው ሁሉ ) ነው? ይህስ ተማሪ በዘር ላይ የተመሰረተ የጥላቻ ባሕሪ ግለ ታሪክስ ያለው ነው?
ሶስተኛ፤ በሶስት ቦታዎች ማለትም በላይብረሪ፤ በመጻሕፍት ቤትና በተማሪ  መኝታ ቤት ይህን መሰሉን የጎሳን ክብር የሚያዋርድና የሚያንቋሽሽ ጽሁፍ ለመጻፉ ምንም የተጠቀሰ ማስረጃ የለም፡፡ በጥላቻ ወንጀል ድርጊት፤ እንዲህ መሰሎች የጥላቻና የማዋረድ ተግባር ያለባቸው ጽሁፎች ሲጻፉ ዓላማቸው አንድን የጎሳ አባል የሚመለከቱ ሲሆኑ፤ ኢላማ የተደረጉት ግለሰብም ይሁን ቡድኖች ሊደርሱበትና ሊያዩት በሚችሉት ስፍራ ይሆናል እንጂ የግል ጥላቻውንና ብሶት ጣውን  ከተለያዩ ብዙ ጎሳዎች የመጡ በሚገኙበት ግቢ ውስጥ የማይመለከታቸውም እንዲመለከቱት ለምን ይደረጋል?
አራተኛ፤ ከዚህ አስቀያሚ  የግድግዳ ጽሁፍ ሌላ ማስረጃ ሊሆን የሚችል አንዳችም ነገር ከዚህ የችግሩ ጠንሳሽ በተባለው ‹‹ተማሪ›› ላይ አልተገኘም፡፡
አምስተኛ፤ በጃንዋሪ 2 በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተፈጸመው ደባ የተለየ ሁኔታ ሆኖ ሊታይ አይችልም፡፡ ላለፉት በርካታ አሰርት ዓመታት ይህን መሰል በጎሳ ላይ ተመሰረተ አምባጓሮ ይነሳ እንደነበር የማያጠያይቅ ነው፡፡ ለምንስ የዩኒቨርሲቲው ባለስልጣናት ጉዳዩ ሲያቆጠቁጥ አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ ለዚህ ከመብቃቱ ቀደም ብለው አላከሸፉትም፡፡ ድርጊቱ በአስከፊና ሊቀለበስ ወደማይችልበት ሁኔታ ከደረሰና አዳገው ሁሉ ከተከናወነም በኋላ በሌሎች ተማሪዎች ላይ አመጹ ተስፋፍቶ እንዳይቀጥልም ባለስላጣናቱ የወሰዱት እርምጃ የለም፡፡
ስድስተኛ፤ በነጻ አካላት ጉዳዩ ሙሉ በሙሉ ከመጣራቱስ አስቀድመው የዩኒቨርሲቲው ባለስልጣናት “አመጹ የተጀመረው በግድግዳዎች ላይ የተጻፈውን ምግባረ ብልሹና ጎሳን የሚያንኳስስ ጥሁፍ ያዩት ተማሪዎች ነው በማለት ለምነስ መግለጫ አወጡ? ጉዳዩን ከመሰረቱ አንስተው የሚያጣሩ ገለልተኛ ወገኖች በማዋቀርና በመመርመር ለወዲቱ ይህን መሰል ድርጊት በድጋሚ እንዳይከሰት ማድረግ የሚቻልበትን ዘዴ ለምን አልቀያሱም? የዩኒቬርሲቲው ባለስልጣናት ጉዳዩን እራሳቸውን ከተጠያቂነትና ከሃላፊነት በማግለል ለፖሊስ ሙሉ በሙሉ ለምን አስረከቡት? ምናልባት በዩኒቨርሲቲው የሚከሰተውን የጎሳ ጥላቻ ወንጀል ቸል ያሉት አይታችሁ እንዳላየ ሁኑ የሚል መመርያ ስለተሰጣቸው ይሆን?
ሰባተኛ፤ የዚህ የጥላቻ ብጥብጥ ወንጀል ተጠቂ የሆኑትስ በፖሊስ ለመደብደብ ለመያዝና ለመታሰር ለጉዳት ለምን ተዳረጉ?
በአጭሩ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተፈጸመው የጥላቻ ወንጀል የቀረበው ሁኔታና ማስረጃ ጨርሶ ወደ ተከሳሾቹ ተማሪዎች ጣት አያመላክትም፡፡ ይልቁንስ ያአመልካች ጣት በወንጀለከኝነት የሚጠቁመው ወደ ከሳሾቹ ነው፡፡ የዚህን የጥላቻ ወንጀል ፈጻሚዎች ለማጣራትና ለመያዝ የሚያስፈልገው፤ ያንን የግድግዳ ላይ ጽሁፍ የከተቡትን የማይታዩ ጣቶች ብቻ ሳይሆን  እነዚያን ተማሪዎቹን እስኪጠወልጉ ድረስ የቀጠቀጡና ያሰቃዩ፤ ከዚያም በረጩት የአመጽ ነዳጅ ላይ እንዳይጠፋና የበለጥ እንዲቀጣጠል ንዳድ የረጩበትንና የጎሳ ግጭቱን ያቀጣጠሉትን፤በተማሪዎች መሃል ጥላቻ  ንትረክና ዉዝግብ አንድፈጠር የሚዶልቱ ወንጀል ጠንሳሶች ነው፡፡
ያም እንዳለ ሆኖ፤አሁን ወቅቱ ነው፤ አስፈላጊው ወቅት ነው፤ትክክለኛው ጊዜ ……..
የማገገሚያጊዜ፤የመቀበያውየመተቃቀፊያ  የእርቀሠላምጊዜ አሁን ነው
በክዱስ ጽሁፍ እንደሰፈረው፤ ‹‹ለማንኛውም ሁኔታ ወቅት አለው፤ከሰማይ በታች ላሉት ነገሮች ሁሉ  ለየምክንያቱ ጊዜ አለው::›› ለማልቀስ ጊዜ አለው፤ ለሃዘንም ወቅት አለው፤ ድንጋይ ለመወርወርም ጊዜ አለው፡፡ ለመገንባትም ጊዜ አለው፤ ለመናገርም ጊዜ አለው፡፡ እንዲሁም ለመተቃቀፍም ጊዜ አለው ለሠላምና ለማገገምም ጊዜ አለው፡፡ ለእርቀሰላምም  የራሱ ጊዜ አለው፡፡
አሁን ነው ጊዜው፤ — ትክለኛው ጊዜ– ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች በትምህርት ቤቶች፤ በዩኒቬርስቲዎች፤ በስራ ቦታዎች፤ በአጎራባች መንደሮችና በመንገድም ላይ  የማገገሚያው ወቅት፡፡ ጊዜው—– ትክክለኛው ጊዜ—- የኢትዮጵያ ወጣቶች በወንድማማችነት በአህትማማችነት ስሜት መተቃቀፍ  መተሳሰብ እጅ ለእጅ በመያያዝና አንድ በመሆን ብዛታቸውን  ለቅድመአያቶቻቸው ክብርና ለታሪካቸው መከበርያ ማድረግ የሚገባቸው፡፡
ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች የጎሳ ጥላቻን  የብጥብጥን አዙሪት የመበጠሻ ጊዜው አሁንነው:: አላስፈላጊውን የቅሬታ ልምድ የማክተሚያ፤ የፍርሃትን ባህል፤ ጥላቻን፤ አውልቆ የመጣያው ትክክለኛው ጊዜው አሁን ነው፡፡
ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች ጣቶቻቸውን በማቆላለፍ እጅ ለእጅ በመያያዝ የፍርሃትን እከክ ማራገፊያቸው፤ ጥላቻን፤ግጭትን፤ከልባቸው ፤ ከሕሊናቸው፤ ከመንፈሳቸው አውጥተው መጣያ ጊዜያቸው አሁን ነው፡፡ ጓደኞቻቸውንና የትምህርት ባልደረቦቻቸውን እንደጠላትና  ባላጋራ መመልከትን ማቆሚያቸው ጊዜ አሁን ነው፡፡
ሰላም ፈጥረው እርስ በርሳቸው እንደወንድምና እህት የሚተቃቀፉበት ጊዜ አሁን ነው፡፡ የኢትዮጵያ ብልህና ምርጦች አንድ ላይ በመስራትና በመተጋገዝ የተሸለን ነገ ለመፍጠር የሚችሉበት፤በረጋና ጠንካራ በሆነ የሕግ የበላይነት ላይ፤ ሰብአዊ መብትና ዴሞክራሲ የተከበሩበት አማራጭ ሂደቶች ያሉበት መትለሚያው ጊዜ አሁን ነው፡፡ ኔልሰን ማንዴላ እንዳስተማሩት ‹‹ከጠላት ጋር ሠላምን መፍጠር ካስፈለገህ፤ከጠላትህ ጋር ተጓድነህ መስራት አለብህ፤ ያን ጊዜ ጠላትህ ወዳጅህ ይሆናል::›› እነዚያን ጠላት የምንላቸውን ወንድምና አህት አብሮ ተማሪዎች  ና ወዳጅ ማድረጊያ ጊዜው አሁን ነው፡፡
በዩኒቨርሲቲ ግቢያችን ውስጥና ከግቢያችንም ውጪ ጥላቻንና የጥላቻ ወንጀልን ለማጥፋት መተባበርያው ጊዜ አሁን ነው፡፡
ከሕሊናችንና ከመንፈሳችን ውስጥ የጥላቻ ቋጠሯችንን ማጥፊያው፤ የፍርሃትን ሰንሰለትና ካቴና መበጠሸውጊዜ አሁን ነው፡፡ የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች ካለፈው ጫና እራሳቸውን ለማላቀቅና ነጻ ለማድረግ ጊዜው አሁን ነው፡፡
ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ወጣቶች ቆንጨራውን በመቅበር ለአንድዬና ለመጨረሻው ጊዜ ‹‹አሻፈረን! አንዳችን ሌላውን የዚህ ወይም የዚያ ጎሳ ስለሆንን ለመጠላላት አሻፈረን፤ እምቢ! መባያችን ጊዜው አሁን ነው፡፡ አሻፈረን! ምክንያቱም ሁላችንም በተለያየ ስም በምንጠራው የጋራችን በሆነው አምላክ ስር አለያም የሁላችን በሆነችው ሀጋራችን የተለያየ ማእዘን ነዋሪዎች ነንና፡፡ እምቢ! በምንም መልኩ ለመጠቀሚያነትና እንደ አሻንጉሊትነት ሆነን በሚጠቀሙብን ለጥላቻ ለእርስ በርስ መቆራቆስ መጠቀሚያ አንሆንም፤ እምቢኝ! የሠለጠንን ነንና ለጥላቻ አንሰለፍም፡፡ አዳኝ እንደሚያሳድደው የሚታደን አውሬ ለመሆን እምቢኝ!
ከአንድጉማሬጥቂትቃላትለበርካታዎቹአቦሸማኔዎች
በርካታ አቦሸማኔዎች ምናልባትም ጉማሬውን ትውልድ ማዳመጡ ያስገርማቸው ይሆናል፡፡
እኛ ጉማሬዎች ‹‹በዕውቀት የተጋረድን›› ‹‹ራዕይ የጎደለን››  ‹‹የራሳችን ምንጭ እስካልደረቀብን ድረስ ጠቅላላው ሃገር ቢደረማመስ ደንታ የሌለን ›› ነን ተበለን አነታወቃለን:: ያም ሆኖ ወጣቱን ትውልድ  በአክብሮት እባካችሁ ጆሯችሁን አውሱኝና ለመደመጥ እድል ስጡኝ እላለሁ፡፡
ጀግኑ!
የመጀመርያው የኢትዮጵያ ትውልድ በመሆን፤ እራሳችሁን ከሰንሰለቱ ነጻ በማድረግ ካለፈው የጫና ሰቆቃ እኛንም አራሳችህሁንም ለማላቀቅ ብቁ፡፡
የመጀመርያው የኢትዮጵያ ትውልድ በመሆን፤ ታሪካዊ ጥላቻን፤ ቅሬታን በማጥፋት፤ መግባባትንና መቻቻልን በማምጣት አዲስ እርቀሰላም በኢትዮጵያ ታሪክ ጀምሩ፡፡
የጥላቻን ቁስል ለማዳን የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን ለዘመናት ያመረቀዘውን በማጥፋት ለመጪው ትውልድ ያለፈው ትውልድ ስህተትና ጥፋት እስረኞች እንደማይሆኑ አረጋግጡላቸው፡፡
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን ሁላችንም በእኩልነት የሰው ዘር አባላት በመሆናችን ይህንንም በጎሰኝነት ለማቀደም ብለን አዘቅት አንውረድ ::
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን አንደኛችን ለሌላው ይቅርታን በመቸር ለአንድዬና ለመጨረሻ ጊዜ ቆንጨራውን በመቅበር፤ ጣቶቻችንም የጠመንጃ  ቃታና ምላጭ ለመሳብ፤ጣቶቻችን የጥላቻ መነሾ የሆኑ ቃላትን በየግድግዳው ላይ ለመለቅለቅ ሳይሆን እጆቻችን የሚዘረጉት የመግባባት የመተሳሰብ ሰላምታ ለመለዋወጥና ለችግርም ይሁን ለደስታ እጅ ለመዋዋስ ብቻ አንድሆን ማረግ ያሻል፡፡
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን የተለያዩት እምነቶቻችን መለኮታዊነታቸውን ማረጋገጥ እንቻል::
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን አሻፈረኝ! አምቢ! በማለት ውስጥ ውስጡን ከሚበላን የጎሳ የሃይሞነት የጻታ ልዩነት በተቃርኖ እንቁም::
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን በመኝታ ቤቶች፤ በቤተመጻህፍት፤በመጸዳጃ ቤቶችም ያሉትን አስነዋሪና በታታኝ፤ ጎሰኝነትን የሚያቅራሩ ቃላታን በእርቀሰላም፤ በመግባባት፤ በውህደት፤ በፍቅር አሰባሳቢ ቃላቶች እንሸፍናቸው፡፡
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን የወደፊቷ ሃገራችን መሪ ሻምበሎች እናንት ኩሩ አቦሸማኔዎችእንጂ፤ የደከሙት፤ሙሰኞቹ፤ ምግባረብልሹዎቹ፤ እራሳቸውን የሚያስተናግዱ ጉማሬዎች ሊሆኑ አይችሉም፡፡
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን  ለመሆን የምትመኘውን ሁሉ በመሆን፤ለመሆንም ለማሰብ ቀደምት አንሁን፡፡
የመጀመርያዎቹ ትውልዶች በመሆን  የትላንቱን የመረረ ስሜት በዛሬውና በነገው ጣፋጭ እርቀሰላም፤ መግባባት፤ አንድነት፤ መሰረት ላይ መልሳችሁ አዋቅሩት፡፡
የሃቅ ወቅቱ ደርሷል፡ አቦሸማኔዎቹ እራሳቸውን በማዳን ለእኛም መድህን ይሆኑን ይሆን ?
ለኢትዮጵያ ምርጡና ብሩሁ የሃቅ ወቅት ደርሷል!
የኢትዮጵያ ምርጥና ብሩህ አቦሸማኔዎች ካለፈው ጫናና መከራ እራሳቸውን በማዳንና የጎሳ መጎጃጃ፤ የሃይሞነት አክራሪነትን  የጨቋኝ ስጦታ በመጣል እራሳቸውን ማዳን ይችሉ ይሆን?
እነዚህ አቦሸማኔዎች ተጠራጣሪዎቹን፤ የመሸጉትን ምስኪን ጉማሬዎች ከራሳቸው ነጻ ያወጧቸው ይሆን?
ከጎሳ መቆራቆስ ወደ ጎሳ ፍቅር፤መቻቻል አንድነት፤ መግባባትን ያበቁን ይሆን?
አቦሸማኔዎቹ ስብእናችንን ከጎግፍ ማነቆና ከአውሬ አስተሳሰብ ያላቅቁን ይሆን?
አቦሸማኔዎች የእርቀ ሰላምን ጥበብ ያስተምሩን ይሆን? በእርቀሰላም ቋንቋ ያናግሩን ይሆን?
የኢትዮጵያ ብልህና ብሩሆች አንድ የወጣት ግብረሃይል በመሆን 2013ን የአቦሸማኔዎች ዓመት ያደርጉት ይሆን? አንድ ላይ በመቆም የጎሳ ጥላቻን ቆንጨራ በመስበር የወገንተኛነትን ጎራዴ በማቅለጥ የእርቀሰላምን ሙሉነት ያስመርቱን ይሆን?
የአላንዳች ጥርጥር አዎን ይቻላቸዋል!
ባለፈው ሳምንት 2013 የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች ዓመት ብዬ ስተነብይ፤  የኢትዮጵያን ወጣቶች ለማስተማር፤ ለማዳረስ፤ለማሳመን ቃል ገብቼ ነበር፡፡ አኛ ጉማሬዎች አቦሸማነዎችን አናስተመራለን የሚል አምነትም ነበረኝ:: ጉማሬዎችን አቦሸማኔዎችን ያስተምራሉ ብዬ አልገመትኩም ነበር::  ለዚህ ነው እኛ ጉማሬዎች ግራ የተጋባ ሸውራራ (የተዛባ አመለካከት) ቅርብ አዳሪነት፤ጠባብ አስተሳሰብ፤ የምያጠቃን::  ለአቦሸማኔዎች የማስተማርያ ወቅት ሊኖር ስለመቻሉ ጥርጣሬዬ የመጣው::
ስለዚህም የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎችና ጉማሬዎች በርካታ ግብግቦች የሚገጥሟቸው፡፡ የአቦሸማኔዎቹ ፈታና ጉማሬዎቹን የእርቀሰላምን ጥበብ ማስተማሩ ላይ ነው፡፡ የጉማሬዎቹ ፈተና ደግሞ ከአቦሸማኔዎች የእርቀሰላምን ጥበብ መማሩ ላይ ነው፡፡
አቦሸማኔዎች ታሪካዊ ገድል የመፈጸም እድል ቀርቦላቸዋል፡- ይሄዉም በምሳሌነት ማስተማር፡፡
በአዲስ አበባው ዩኒቨርሲቲ አጋጣሚ የተሳተፉትን፤ ወዳዳጆቻቸውንና ሌሎቹም ጭምር በግቢያቸው የተፈጸመውን አስጸያፊ የግጭት ሁኔታና ሁከት አስመልክቼ የማቀርበው ጥሪ ሁኔታውን ወደ ውብና ያማረ ፍቅርና ሰላም የሞላበት ፍሬያማ ውጤት ለማምጣት የአንድነት አውድማ ላይ እንዲሰባሰቡ ነው፡፡ እያንዳንዳቸው ወደ ሌላው በመቅረብ ይቅርታን እንዲጠይቁና እንዲቀባበሉ እጠይቃለሁ፡፡ አንዲት በጣም ትንሽ የሆነችውን ‹‹ይቅርታ›› የምትለውን ቃል ለመተንፈስ ወኔ ይጠይቃል፡፡
በራሳቸው ውህደት እንዲፈጥሩ እጠይቃለሁ—-አንድ ለአንድ፤ በትንሹና በበርካታው ስብስብ—–ልዩነታቸውን ይወያዩበት ይነጋገሩበት ይምከሩበት፡፡ አንደኛቸው የሌላው ጉዳትና ግፍ ይሰማው፡፡ አንዱ የሌላው ፍርሃትና ጥርጣሬ ይሰማው:: አንዱ ለሌላው እንባ ንቀት አይኑረው፡፡

በብሩህ ህሊና፤ በንጹህ ልቦና፤ አእምሮና መንፈስ ሊነጋገሩ ግድ ነውና ይህንንም እጠይቃለሁ፡፡
እያንዳንዳቸው የሌላውን ስሜትና ጥርጣሬ እንዲረዱ እጠይቃለሁ፡፡ በጓደኞቻቸው ጫማ ውስጥ ሆነው ለኪሎሜትር  እንዲራመዱ እጠይቃለሁ:: በመጫሚያም ይሁን በባዶ እግራቸው ፈገግ ሊያሰኛቸው የሚችል ሁኔታ ያጋጥማቸዋል፡፡
የኢትጵያ አቦሸማኔዎችን 2013ን የእርቀሰላምና የሰላም ዓመት እንዲያደርጉት እጠይቃለሁ፡፡
ጃንዋሪ 2 1013 በታሪክ የኢትዮጵያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች  የጎሳ ጥላቻን ቆንጨራ፤የሃይሞነት ወገንተኝነት፤ የጾታ ልዩነት የተቀበሩበት ዕለት ሆኖ ዘወትር አንድታሰብ ይሁን፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተከሰተው አስጸያፊ ሁኔታ ለሕዝብ ማስተማሪያነት ያገልግል፡፡
ጥንካሬን ከችግር ወልዳችሁ፤ አንድነትን ከከፋፋይ ተምራችሁ፤ ከጓደኞቻችሁ ተማሪዎች ጋር ለመደማመጥና የመግባባትን፤ የመቻቻልን፤ የውህደትን ዘር ለማፈስ እንድትበቁ እማጸናችኋለሁ፡፡
የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች ጉማሬዎችን እንደመሩ እጠይቃለሁ፡፡ እኛን አትከተሉን፤መሄጃችንን አናውቀውምና፡፡እኛ የጠፋው የጉማሬ ትውልዶች ነን፡፡
ይህን ግብግብ በመቀበል፤ትክክለኛውን እንደትክክል፤ስህተቱንም ወደ ትክክለኛነት ካልለወጣችሁት፤ አቦሸማኔዎች በስልጠና ላይ ያሉ ደካማ ጉማሬዎች ናቸው የሚል ትችት ላይ መውደቅ ይመጣል::
ለሁሉም ጊዜ አለው::   ለኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች፤ ለማገገምና ለእርቀሰላም ሰዓቱ አሁን ነው፡፡
የኔ ጥያቄ ለእዮጵያ ወጣቶች  ይህ ነው:-  አሁን ስንት ሰአት ነው!?!
የተባበሩት የኢትዮጵያ አቦሸማኔዎች ፈጽሞ ለውድቀትና ለሽንፈት አይዳረጉም!
*የተቶረገመው ጽሁፍ (translated from):
(ይህን ጦማር ለሌሎችም ያካፍሉ::) ካሁን በፊት የቀረቡ የጸሃፊው ጦማሮችን  ለማግኘት እዚህ ይጫኑ::

No comments:

Post a Comment