Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Sunday 12 May 2013

የፍትህ ሚንስትር አቶ ብርሃን ሃይሉም ተባረረ!!


Justice Minister Birhan Haile - Fired!
የጉምሩክ ዳይሬክተር እና ምክትሉ መባረራቸው በተሰማ ማግስት ሌላ ዜና ደግሞ ተከትሎ መጥቷል። የኢትዮጵያ ፍትህ ሚንስትር የነበሩት አቶ ብርሃን ሃይሉ ያለምንም ማስጠንቀቂያ ስልጣናቸውን ተነጥቀው ተባረዋል። አቶ ብርሃን ሃይሉ ከስልጣን መነሳታቸውን የሚገልጸው ደብዳቤ የደረሳቸው ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት፤ አዲሱ ጠ/ሚ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በፈረሙበት ደብዳቤ ነው። ሚንስትሩ እ.አ.አ በ2005 ዓ.ም. በማስታወቂያ ሚንስትርነት ሲሰሩ ነበር። ሆኖም ማስታወቂያ ሚንስትር እንዲፈርስ ሲደረግ፤ በቀጥታ ሌላ ሹመት በማግኘት የፍትህ ሚንስትር ሆነው ኢህአዴግን በታማኝነት ሲያገለግሉ ቆይተዋል።



Justice Minister Birhan Haile – Fired!

አቶ ብርሃን ሃይሉ የብአዴን (ብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ) ማዕከላዊ ኮሚቴ እና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ለብዙ አመታት ሲያገለግሉ ቢቆዩም፤ ባለፈው ማርች ወር 2013 ዓ.ም. ብአዴን በባህር ዳር ስብሰባ አድርጎ በነበረበት ወቅት፤ ከፍተኛ ወቀሳ ከተደረገባቸው አባላት መካከል ዋነኛው አቶ ብርሃን ሃይሉ ነበር። “ብቃት እና ችሎታ የሌለው ሚንስትር” ተብሎ በተደጋጋሚ ተገምግሟል። ከዚህ ስብሰባ በኋላ ከብአዴን እና ኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚነት ተነስቷል።
በኢትዮጵያ ውስጥ 1ሺህ 923 የፖለቲካ እስረኞች ቢኖሩም፤ “አሸባሪዎች እንጂ ምንም የፖለቲካ እስረኛ የሉም።” በማለት ሲመጻደቅ የነበረ ሰው ነው። ባለፈው የፓርላማ ስብሰባ፤ ብቸኛው የተቃዋሚ ፓርቲ አቶ ግርማ ሰይፉ ስለ እስረኞች አጠባበቅ ሁኔታ በመረጃ አስደግፈው ላቀረቡት ጥያቄ ጭምር፤ “የለም። እስረኞች መብታቸው ተጠብቆ ነው ያሉት።” በማለት የሃሰት ፖለቲካዊ ምላሽ መስጠቱ ይታወሳል።
እንግዲህ ይህ በዚህ እንዳለ ነው፤ በቅሚያ ከብአዴን፤ ከዚያም ከኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ አባልነት የተባረረው። አሁን ደግሞ ከፍትህ ሚንስትርነት በደብዳቤ ተሰናብቷል። ሰሞኑን በኢህአዴግ መካከል ያለው ሽኩቻ እና የሹም ሽር እንዳለ ሆኖ፤ በቅርቡ በታሰሩት እና በተባረሩት ምትክ ማን ሊቀመጥበት እንደሆነ ህዝቡ በጉጉት የሚጠብቀው ጉዳይ ሆኗል። አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ባለባቸው ጫና እና ፍራቻ የተነሳ፤ በትምህርት ችሎታ ሳይሆን የዘር ፖለቲካን መሰረት በማድረግ… ቀጣዩን የፍትህ ሚንስትር ከህወሃት ሊያደርጉ ይችሉ ይሆናል። ሁሉንም አብረን የምናየው ይሆናል።

No comments:

Post a Comment