Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Tuesday, 21 August 2012

ሰባት አባላት ያሉት ቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ ተዋቀረ እስከቀብሩ ድረስ የሚቆይ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ታወጀ

ሰባት አባላት ያሉት ቀብር አስፈጻሚ ኮሚቴ ተዋቀረ
እስከቀብሩ ድረስ የሚቆይ ብሔራዊ የሐዘን ቀን ታወጀ
የጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት በይፋ ከተነገረ በኃላ የመጀመሪያ በሆነው የመንግስት መግለጫ የቀብር አስፈጻሚ ብሔራዊ ኮሚቴ መቋቋሙን፣ከዛሬ ጀምሮ እስከቀብር ቀን የሚዘልቅ ብሔራዊ የሐዘን ቀን መታወጁን፣የአገሪቱ ባንዲራ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ አቶ በረከት ስምኦን አስታወቁ፡፡
ሚኒስትሩ ዛሬ ጠዋት በሒልተን ሆቴል በሰጡት መግለጫ ብሔራዊ ኮሚቴው የቀብሩን ቀንና ሥነሥርዓት በተመለከተ በቀጣይ መግለጫ እንደሚሰጥ ጠቁመው ጠ/ሚኒስትሩ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ተጠባባቂ ጠ/ሚኒስትር ሆነው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል፡፡
አቶ በረከት ጠ/ሚኒስትሩ የት አገር እንደታከሙ፣የት አገር እንደሞቱ ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡

Monday, 20 August 2012

Ethiopia’s dictator Meles Zenawi is dead – ETV

The state-controlled Ethiopian Television (ETV) has reported that Ethiopia’s dictator Meles Zenawi has died at the age of 57.
After announcing Meles Zenawi’s death, the ETV started showing various photos of the dictator with music on the bacground.
The TPLF junta has been claiming that Meles was recovering for a minor illness and that he would return to his job before September 11, Ethiopian New Year. However, multiple sources have been informing Ethiopian Review and other media that Meles has died several weeks ago. Finally, the regime has admitted this morning (Ethiopian local time) that he is dead.
Obviously, it has been a while since Meles has died. It took this long for the ruling TPLF junta to announce his death because they couldn’t agree on his replacement.
Toward the end of last week, as reported by Ethiopian Review, the U.S. Africa Command led by Gen. Carter F. Ham persuaded the minority tribal junta to appoint Hailemariam Dessalegn as acting prime minister. … stay tuned.

ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዐቃቤ መንበር ፓትርያርክ ሆነው ተመረጡ


 


አዲስ አበባ ነሐሴ 14/2004 የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የአርሲ ሃገረ ሰብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ዐቃቤ መንበር ፓትርያርክ ሆነው እንዲሰሩ መወሰኑ የሲኖዶሱ ዋና ፀሃፊ ገለፁ። 

የሲኖዶሱ ዋና ፀሐፊና የከፋ፣ ሸካና ቤንች ማጂ ዞን አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የፓትርያርኩን ምርጫ አስመልክተው ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የዋና ፓትርያርክ ምርጫ እስከሚካሄድ ድረስ ብፁዕ አቡነ ናትናኤል ዐቃቤ መንበር ፓትርያርክ ሆነው እንዲሰሩ ተወስኗል።

የቤተክርስቲያኒቱ መንፈሳዊም ሆነ ማህበራዊ ተግባራት ዘርፈ ብዙ በመሆናቸው በሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ጳውሎስ ምትክ ጳጳስ መምረጥ ማስፈለጉን ገልጸዋል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ዛሬ ባደረገው ስብሰባ ቀደምትነት ካላቸው ብፁዓን አባቶች መካከል ብፁዕ አቡነ ናትናኤልን ላልተወሰነ ጊዜ ዐቃቤ መንበር ፓትርያርክ ሆነው እንዲሰሩ መወሰኑን አመልክተዋል።

ከዐቃቤ መንበር ፓትርያርክ ምርጫ በተጨማሪ ከቋሚ ሲኖዶሱ ጋር አብረው የሚሰሩ ሰባት አባላት መመረጣቸውን ዋና ፀሃፊው ተናግረዋል።

የተመረጡት አባላትም ብፁዕ አቡነ ጢሞቲዮስ፣ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል፣ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ፣ ብፁዕ አቡነ ሉቃስ፣ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል፣ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስና ብፁዕ አቡነ አብርሃም መሆናቸውን ገልጸዋል።

አላማችን ላይ ሊያደርሱን ያልቻሉ መጣመሮች


ከጌዲዮን ደሳለኝ (ኖርዌይ)
ወደድንም ጠላንም የኢትዮጵያ ሁኔታ ወደአንድ አቅጣጫ እያመራ እንደሆነ እየተከናወነ ያለው እውነታ ይመሰክራል ነገሮች በፍጥነት እየተለወጡ ነው ያለው፣ ትላንት የሰማነውን አዲስ ነገር አጣጥመን ሳንጨርስ ሌላ አዲስ ነገር ይፈጠራል ይህ ደግሞ በአገራችን እየተከናወነ ያለ የለት እለት ክስተት ሆኗል።
የዚህ ጽሁፍ መነሻ የሆነኝ ዋናው ምክንያት እኛ ስንጣመር፤ ስንቀናጅና ስንተባበር ትግሉን በዚህ ብቻ በመጨረስ። የተግባር መግቢያው ወቅት እያለፈን እንዳለ ስለተገነዘብኩ ነው። አንዳንዴ እንደውም እኛ ተቃዋሚ የምንባለው የወያኔ ስርአት ተወደቀ የምንጎዳ ይመስል ወደትግል ከመግባትና ከማስገባት፣ ከመታገልና ከማታገል ይልቅ ስንተባበር፣ ስንቀናጅና ስንጣመር ዘመናትን ያስቆጠርን ይመስላል በዚህም ወሳኝ የሆኑ የለውጥ ወቅቶች እያለፉን ይገኛሉ።

ወ\ሮ አዜብ መስፍን በስማቸው ያለ ማንኛውም አይነት ገንዘብም ሆነ ንብረት የትኛውም ቦታ ሆነው እንዳያንቀሳቅሱ መመሪያ ተላለፈ!!






ከአቶ መለስ መሰወር በኹአላ እየተፍረከረከ የመጣው የህወሐት ጠባብ ቡድን ከተወሰኑ ቀናቶች ጀምሮ ከመሃከላቸው የሆነ አስፈሪ ነገር እየተፈጸመ እንዳለ እየታየ ነው። 

ይህም ክስተት ነባር እና ታማኝ ተብለው በድርጅቱ ተፈርጀው የነበሩ ካድሬዎችንና አባላትን ይበላ ጀምሯል፤ ይህ የሚደንቅ አይደለም ምክንያቱም አብዮት ወልዳ ያሳደገቻቸውን ልጆች እንደምትበላ የታሪክ እውነታ ስለሆነ ይህንን ደግሞ ለመስዋእት የቀረቡ የህውሃት ካድሬዎች ሊገነዘቡት ይጋባል።

 የአቶ መለስ ጥላ ሰብስቦ ይዟቸው የነበር አቅመ ደካማና ልፍስፍስ ቱባ ባለስልጣናት ሁሉ ጥላው ሲነሳ የሚሆኑት ግራ ገብቶአቸው በቀን ቅዠት ውስጥ ነው ያሉት። በደረሰን ትክክለኛ መረጃ መሰረት ከፍተኛ የህወሐት ባለስልጣናት ባለፈውና በአሁኑ ሳምንት የደቡብ አፍሪካንና የሳውዲ ሆስፒታሎችን እያጥለቀለቁ ሲሆን። የበሽታቸውም ዋናው ምንጭ ተደርጎ የተነገራቸው በስርአቱ መዋዠቅ የተፈጠረ የኧምሮ መረበሽ እና ጭንቀት ነው። 

Sunday, 19 August 2012

በዳላስ ግድያ የፈጸመው አብይ ግርማ፤ በዴንቨር ፖሊስ ሲያዝ አስደንጋጭ መረጃዎች ተገኙበት


- በግድያ ወንጀል የተጠረጠረው አብይ ግርማ መያዙን ለማብሰር ኢ.ኤም.ኤፍ የመጀመሪያው ነው።
- በግድያ ወንጀል የተጠረጠረው አብይ ግርማ መያዙን ለማብሰር ኢ.ኤም.ኤፍ የመጀመሪያው ነው።

(ኢ.ኤም.ኤፍ) በዳላስ የደስታ ሬስቶራንት ባለቤት የሆኑትን አቶ ያየህይራድ እና የኒን በማታ ተከትሎ የገደላቸው ኢትዮጵያዊ ዴንቨር ከሚገኘው ዳግማዊት ግሸን ማርያም አጠገብ ከሚገኘው ትምህርት ቤት የ2011 ኒሳን መኪናውን እንዳቆመ ነው በፖሊስ የተደረሰበት። አብይ ግርማ ይባላል። ከዚህ በፊት ዴንቨር ነዋሪ ነበር። አትላንታ ከተማም መምጣትን ያዘወትራል። ዳላስ ከተማ ውስጥ ደግሞ በሊሞዚን መኪና ሹፌርነት ይሰራል። ከዚህ በፊት ዳላስ በሚገኘው ደስታ ሬስቶራንት ውስጥ ከሰዎች ጋር ተጣልቶ ስለተፈነከተ፤ የጉዳት ካሳ በመጠየቅ ጉዳዩ ፍርድ ቤት ድረስ ሄዷል። 

(ከላይ የጠቀስናቸው ጉዳዮች ሰፊ ትንታኔ የሚያስፈልጋቸው ስለሆኑ፤ ያንን ለጊዜው ትተን ዴንቨር ውስጥ በተያዘበት ወቅት የነበረውን ሁኔታ በጥቂቱ እንግለጽላችሁ)
የዴንቨር ፖሊስ ወደ አብይ መኪና በማምራት እንዲከፍትለት ሲጠይቀው፤ ልጁ መኪናውን አስነስቶ ለማምለጥ ቢሞክርም… የዴንቨር ፖሊስ ቀደም ብሎ ተዘጋጅቶ እየጠበቀ ስለነበር ከትንሽ የመኪና ማሯሯጥ በኋላ በቁጥጥር ስር አውሎታል። ከዚያም መኪናው ሲፈተሽ ያልተጠበቀ ነገር ተገኘ። 15 ሽጉጦችን ፖሊስ አገኘበት። ይህ ብቻ አይደለም… ሊገድል ያሰባቸው ናቸው የተባሉ የ15 ሰዎች ዝርዝር አብሮ አለ። ከዚህም በተጨማሪ 20 ሺህ ዶላር በጥሬው በመኪናው ውስጥ ይዞ ነው የተገኘው።

እነዚያ ሊገድላቸው ዝርዝራቸውን ይዞ የነበረው የ 15 ሰዎች ስም በፖሊስ ይፋ አልሆነም። ነገር ግን ይህ ከታወቀ ጊዜ አንስቶ የዴንቨር ነዋሪዎች በተለይም ድሮ አብይ ግርማን ያውቁት የነበሩት ሰዎች በጣም ተረብሸዋል። የዴንቨር ፖሊስ በአብይ ግርማ ላይ ጥብቅ የሆነ ምርመራ እያካሄደ ነው። ምናልባት ከዚህ በፊት የገደላቸው ሰዎች ካሉ፤ በመስቀለኛ ጥያቄዎች እያፋጠጡት ሊሆን እንደሚችል ግምት አለ። በሌላ በኩል ደግሞ የዳላስ ፖሊስ ይህንን ግለሰብ እየፈለገው ነው። ወደ ዳላስ እንዲላክለትም ፈልጓል። የዴንቨር ፖሊስ በበኩሉ ገና የማጣራው ነገር አለ በማለት ጉዳዩን እንደያዘው ይገኛል።
ይህ በ እንዲህ እንዳለ፤ የደስታ ባለቤቶች የአቶ ያየህይራድ እና የወ/ሮ የኔነሽ የቀብር ስነ ስርዓት በከፍተኛ ድምቀት በትላንትናው እለት በዳላስ ከተማ ተፈጽሟል።

ማስታወሻ – በግድያ ወንጀል የተጠረጠረው አብይ ግርማ መያዙን ለማብሰር ኢ.ኤም.ኤፍ የመጀመሪያው ነው። ሌሎች ዜናውን ሲያቀርቡ የነበሩ የአሜሪካ ሚዲያዎች የግለሰቡን በቁጥጥር ስር መዋል ገና ባለመዘገባቸው በኛ ዜና ላይ ጥርጣሬ ያደረባቸው ሰዎች ሊኖሩ ይቻላሉ። በኢ.ኤም.ኤፍ. በኩል ግን አብይ ከመታሰሩ በፊት ስለነበረው ሁኔታ እና እንዴት ሊያዝ እንደቻለ ጭምር ዝርዝር መረጃዎች ቢኖሩንም የግለሰቦችን መብት ለመጠበቅ ዝርዝሩን ከማውጣት ተቆጥበናል። ግለሰቡ እንዲያዝ ለዴንቨር ፖሊስ መረጃ በመስጠት የተባበሩ ኢትዮጵያውያን የፈጸሙትን ተግባር በማመስገን ወደ የዛሬው ዘገባችንን እናበቃለን።