Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Tuesday, 27 November 2012

ራስ አሉላ ስም የተሰየመው ት/ቤት በመለስ ተቀየረ

በደርግ ዘመን የተሰራውና በራስ አሉላ ስም ተሰይሞ የ 9 – 10ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ሲያስተምር ከቆየ በሑላ ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ የት/ቤቱን አቅም ለማሳደግ በሚል የ11-12ኛ መመሪያ ክፍሎችን ለመገንባት በአገር ውስጥና በውጭ አገራት የሚገኙ የአካባቢው ተወላጆች ገንዘብ አዋጥተው ስራው መከናወኑን ምንጮቹ ጠቁመዋል። ግንባታው ተጠናቆ ባለፈው ነሃሴ ወር ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ እንዳለ አቶ መለስ በማለፋቸው ፕሮግራሙ መሰረዙን ሲታወቅ; ከሁለት ሳምንት በፊት በተከናወነው የምረቃ ስነ-ስርአት የክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት በስፍራው እንደተገኙ ማወቅ ተችሎዋል።
ከኢየሩሳሌም አርአያ
በትግራይ ተምቤን – አብዪአዲ የሚገኘውና በጀግናው ራስ አሉላ አባነጋ ስም ተሰይሞ የቆየው የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ስያሜው ተቀይሮ በመለስ ዜናዊ ስም እንዲሰየም መወሰኑን ታማኝ ምንጮች አስታወቁ።


ከምረቃው ጋር በተያያዘ የራስ አሉላ ስም ተሰርዞ « መለስ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት » ተብሎ መሰየሙን ባለስልጣናቱ በይፋ እንደገለጹ ምንጮች አረጋግጠዋል። በት/ቤቱ በይፋ የመለስ ስም ተፅፎ መለጠፉ ተጠቁሞዋል። በህዝብ ገንዘብ መዋጮ የተገነባን ት/ቤት በጡንቻና በማን አለብኝነት ህዝብን በመናቅ የተፈጸመ ተግባር ነው ሲሉ የአካባቢው ተወላጆች ማውገዛቸው ታውቁዋል።

በተለይ በአውስትራሊያ፡ ጀርመን፡ ኖርዌይ፡ አሜሪካ፡ ካናዳና… ሌሎች አገራት የሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች ባካሄዱት ቴሌ ኮንፈረንስ ከፍተኛ ተቃውሞ ማሰማታቸውን ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል። ተሳታፊዎቹ እንዳሉት « የአፄ ምንሊክን፡ የሰማዕቱ አቡነ ጴጥሮስን ሃውልት ለማፍረስ የተጀመረው አፍራሽ እንቅስቃሴ ወደ ራስ አሉላ ተሻግሮዋል። ይህ የሚያመለክተው የቆየውን የኢትዮጲያን ታሪክ ለማጥፋት ቆርጠው መነሳታቸውን ነው። ይህ ትውልድ ታሪኩን አስጠብቆ የማቆየትና የተጀመረው አደገኛ አፍራሽ እንቅስቃሴ ከማውገዝ ባለፈ ለትግል መነሳሳት አለበት።ኢትዮጲያዊያን እጅ ለእጅ መያያዝ አለብን፤» ብለዋል። አክለውም « የኢትዮጲያዊነት ጉልህ መታወቂያና መገለጫ የሆኑ አኩሪ ታሪኰችንና ታሪክ ሰሪ ጀግኖችን ለማጥፋት ኤርትራዊው ቴውድሮስ ሃጎስ፡ በረከት ስሞንና ስብሃት ነጋ የሚመሩት አካል በአገራችን ላይ የጥፋት ዘመቻ ከፍተዋል» ሲሉ አንድ ተሳታፊ ተናግረዋል። « የዶጋሊ ዘመቻ » በሚል በየአመቱ ራስ አሉላ የሚዘከሩበት ታሪካዊ ቀን እንደነበረና ሕወሓት ወደ ስልጣን ከመጣ በሑዋላ ግን ይህ እንዲቀር መደረጉን እነዚሁ ወገኖች ያስታውሳሉ።

Monday, 26 November 2012

መቀሌ ዩኒቨርሲቲ እየታመሰ ይገኛል

መቀሌ ዩኒቨርሲቲ በተወሳሰበ ሙስና ውስጥ በመሆኑና የሙስናው ዋና ተዋናዮች ዶ/ር ክንደያ ገብረህይወት እና ዶ/ር ኣብዱልቃድር ከድር የተባሉ ምክትል ፕረዚደንቶች ይውረዱልኝ ብለው ከሶስት ወር በላይ የጠበቁት ጀርመናዊ ፕረዚደንት ችግር ላይ ናቸው።
የቦርድ ሰብሳቢው ኤርትራዊው ኣቶ ቴድሮስ ሓጎስ (የኢፈርት ቦርድ ሰብሳቢም ናቸው) ጀርመናዊውን በአካል እንዳስፈራሩዋቸው ታውቋል! ይህ የሆነው ደግሞ ለትምህርት ሚንስትር ሳይቀር ግልባጭ ባደረጉት የአዲስ ምክትል ፕረዚደንቶች ሹመት የተነሳ ነው።

ጀርመናዊው ፕረዚደንት ከሶስት ወር በላይ/August-November/ የጠየቁትን ጥያቄ ሳይመልሱ ተኝተው የከረሙት ኣቶ ቴድሮስ ሓጎስ አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት ይማታል የሚል አዲስ ዓይነት ቢሂል ፈጥረዋል! ከ300 million ብር በላይ ያባከኑን ሰዎች ገለል እንዲሉ መጠየቃቸው ሊመሰግኑ ሲገባ እንግዳውን German ሰውዬ እንደዚህ እንደውሻ የሚያስፈራሩዋቸው እነ ቴድሮስ ሓጎስ ወደ ማፍያነት መቀየራቸው ጉልህ ማሳያ ነው። ይህን ህዝብ ከመጤፍ እንደማይቆጥሩትና እንዳሻቸው መኖር እንደሚችሉ ግልፅ ማሳያ ነው። ይህ ህዝብ በሚከፍለው ግብርና በደሙ እየነገዱ የሚኖሩት እስከ መቼ ነው? ትግራይ ተማርሯል በማስፈራራት ና በጉልበት ልክ እንደ ትግራይ ህዝብ ደመኛው ለገሰ አስፋው ትግራይን ኤርትራዊው ቴድሮስ ሓጎስ እየገዙዋት ነው። የሚሰርቅን ሰው መጠየቅ ሲገባቸው ኣብሮዋቸው እንደሚሰርቅ በግልፅ በሚያሳይ መልኩ መከላከላቸው ይህ ስርዓት ምን ያህል እንደዘቀጠ፣ ወድቀቱም እንደቀረበ ያሳያል።

የዓረና የፖለቲካ ጉዳይ ተጠሪ ዓምዶም ገ/ስላሴ ታሰረ
አምዶም ገ/ስላሲ
የዓረና የፕሮፓጋንዳና የፖለቲካ ጉዳይ ተጠሪ የሆነው ወጣት ዓምዶም ገ/ስላሴ ከፓርቲ ዶክሜንቶቹ ጋር ታስሯል። ስራ ውሎ፣ አገር አማን ነው ብሎ ወደማረፍያ ቤቱ ሲገባ፣ በተከራየው ግቢ ውስጥ ነዋሪ የሆነችው የህወሓት ካድሬ ከነ ባለቤትዋ በር ላይ ጠብቀው ስርዓት ኣድርግ፤ "በግቢያችን ፖለቲካ እያሳመንክ ሌሎች ሰዎች ወደ ዓረና ትግራይ ልትወስድ ነው በማለት ባነሱት ኣታካራ እሱም ሕግ ባለበት ሃገር ለምን ወደ ሕግ ኣንሄድም ሲላቸው፣ መጀመርውንም የህወሓት ካድሬዎቹ ተዘጋጅተውበት ስለነበሩ ያለ መጥሪያና ያለ ምንም ግጭት በቅርብ ይጠባበቁ የነበሩ ፖሊሶች ሁሉንም ወደ ዓዲ ሓቂ ፓሊስ ጣብያ እስር ቤት ከወሰድዋቸው በኋላ፣ ባልና ሚስት ካድሬዎቹ እናንተ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፣ አንተ ግን ታስረህ ታድራለህ ብለው አስረውታል።

Sunday, 25 November 2012

The Tall Tale of Susan Rice

by Alemayehu G. Mariam
Susan Rice, the U.S. Ambassador to the U.N., Addis Ababa speechOn September 2, 2012, Susan Rice, the U.S. Ambassador to the U.N., delivered a nauseatingly sentimental oration at the funeral of Ethiopian dictator Meles Zenawi. She called Meles “selfless and tireless” and “totally dedicated to his work and family.” She said he was “tough, unsentimental and sometimes unyielding. And, of course, he had little patience for fools, or idiots, as he liked to call them.”  The “fools” and “idiots” that Rice caricatured with rhetorical gusto and flair are Ethiopia’s  independent  journalists, opposition leaders, dissidents, political prisoners, civil society leaders and human rights advocates.Watching the video of her eulogy, one could easily say she “had gone native” completely. But it was clear that her aim was to deliver the last punch to the gut of Meles’ opponents as a sendoff present.

As the old saying goes, “birds of a feather flock together”. Rice, like Meles, likes to insult and humiliate those who disagree with her. She had a reputation in the State Department as boor and a bit of a bully; or as those who knew her say, she was a “bull-in-a-china-shop”. She is known for verbal pyrotechnics, shouting matches and finger wagging at meetings. On one occasion, she is reported to have flipped her middle finger at the late Richard Holbrooke, the dean of American diplomats, at a senior State Department staff meeting. Prior to the onset of the air campaign in Libya in March 2012, France’s U.N. ambassador, Gerard Araud, advised Rice that the European Union would seek a no-fly zone resolution from the Security Council regardless of U.S. support. She gave Araud the verbal equivalent of a kick in the rear end: “You’re not going to drag us into your shitty war.” She later tried to claim full credit for the effort: “We need to be prepared to contemplate steps that include, but perhaps go beyond, a no-fly zone at this point, as the situation on the ground has evolved, and as a no-fly zone has inherent limitations in terms of protection of civilians at immediate risk.” This past July when China and Russia at the U.N. blocked adoption of language linking climate change to international security, she lambasted them as “pathetic” and “shortsighted” and accused them of “dereliction of duty.

‹‹መለሲዝም›› እየመጣ ነው!

(ከተመስገን ደሳለኝ)

22 አካባቢ በሚገኘው አክሱም ሆቴል ፊት ለፊት ከተሰቀለው ግዙፉ የቀድሞ ጠቅላይ ሚንስትር ምስል ስር ‹‹መለስ ኩለ መንኡ ንህዝቢ ዘወፈየ ጂግና ወዲ ህዝብ ኢዩ›› (መለስ ሁለመናውን ለህዝብ የሰጠ ጀግና የህዝብ ልጅ ነው) የሚል የትግርኛ መፈክር ይታያል፡፡ በመላ ሀገሪቱ ከተሞችና ገጠሮች የመለስ ፎቶ ያልተሰቀለበት ጉራንጉር ማግኘት የማይታሰብ ነው፡፡ የምንዱባኖች ጠላና ጠጅ ቤቶች እንኳ ሳይቀሩ ‹‹የመለስ ራዕይን እናሳካለን›› የሚል መፈክር ሊወድቅ ባንጋደደ በራቸው ላይ እንዲለጥፉ ተገደዋል፡፡ የሰውየው ሞት በይፋ ከተነገረ ወዲህ የኢህአዴግ አመራርና ካድሬዎች ከፖለቲከኛነት ወደ ‹‹ሀዋርያነት›› ተቀይረዋል፡፡ በየደረሱበት ስለ‹‹መለስ ራዕይ›› ሲቃ እየተናነቃቸው ይሰብካሉ፡፡ ያነበሩት መንግስት የመቀጠሉን አስፈላጊነት በእርሳቸው ስም ለማሳመን ቀን ከሌት እየባተቱ ነው፡፡

አዳዲስ ምእመናኖችንም እያጠመቁ ደቀ-መዛሙርታትን በማብዛቱ ላይ ተጠምደዋል፡፡ ሰው ዝር በማይልበት ጭው ባለ ምድረ በዳ ሳይቀር ይጮኻሉ ‹‹የመለስን ራዕይ እናሳካለን!››… ከብሔራዊ ቲያትር እስከ ታላቁ ሩጫ ድረስ ያሉ ህዝባዊ መድረኮች የታላቁ መሪ ራዕይ ይዘከርባቸዋል፡፡ በዚሁ መድረክ ስለራዕዩ ቀጣይነት ተተኪዎቻቸው ቃል ይገቡበታል፡፡ ከወረዳ ካድሬ አንስቶ በተለያዩ ሀገራት አምባሳደርነት እስከ ተሾሙ ዲፕሎማቶች ድረስ ‹‹መለስ በስጋ እንጂ በመንፈስ የማይሞቱ›› ዘላለማዊ ህያው ስለመሆናቸው ይሰብኩ ዘንድ ድርጅታቸው ተልዕኮ ሰጥቷቸዋል፡፡ መለስን በማምለክ አቅላቸውን የሳቱት በተባበሩት መንግስታት ጽ/ቤት የአሜሪካ ‹‹ቋሚ መልዕክተኛ›› ሱዛን ራይስ በስርአተ ቀብራቸው ላይ ‹‹ …it’s deeply unfair to lose such a talented and vital leader so soon, when he still had so much more to give. He was an uncommon leader, a rare visionary… world-class mind›› (ብዙ ነገር ሊሰጠን በሚችልበት ወቅት እንዲህ አይነቱ አስፈላጊ መሪ በአጭር መቀጨቱ እጅግ ያስቆጫል፡፡

ለመሆኑ አባ ገብርኤል ስንት ምላስ አላቸው?

ዘመነ ካሳ ፍራንክፈርት ጀርመን
His Grace Abune Gebrielበቀደመ ስማቸው ኢያሱ ተፈሪ ተብለው ይጠሩ የነበሩት አባ ገብርኤል በቀድሞው ፓትርያርክ በብጹእ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ፈቃድ አባ ገብርኤል በመባል የዽዽስና ማእረግ ተቀበሉ ከዚያም በተለያዩ የኢትዮዽያ አሕጉረ ስብከቶች በሊቀ ጳጳስነት አገልግለዋል በተለይም የቀደመችው የኢትዮጵያ አካል የነበረችው የኤርትራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በነበሩበት ጊዜ ከተዋሕዶ ትምህርት የወጣ የምስጢረ ሥላሴን ትምሕርት የሚያፋለስ  መጽሐፍ በመጻፋቸው ምክንያት ተወግዘውና ተሽረው በቀደመው አለማዊ ሥማቸው አቶ ኢያሱ ተፈሪ ተብለው በቅዱስ ሲኖዶስ ተለይተው እንደነበር ታሪክ መዝግቦት የተቀመጠ መሆኑ የታወቀ ጉዳይ ነው
አባ ገብርኤል በአቋማቸው ወላዋይነት በተናገሩበት የማይጸኑእንደ ገበታ ውኃ የሚዋልሉ ይህን ብየ ነበር ብለው ይሉታና ትዝብት የሌላቸው እና ጠንካራ ነው ብሎ ያመኑበትን ክፍል በመጠጋት በሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሚታወቁት እኚህ ግለሰብ ከአባ ጳውሎስም ጋር በፈጠሩት ጠብ አስመልክተው በአንድ ወቅት እንዲህ ብለው ተናግረው ነበር ”አባ ጳውሎስ እንዲመረጡ ለዚህ ፕትርክና እንዲበቁ ባደረግሁት አስተዋጽኦ እጅግ ይጸጽተኛል”በማለት ከሀገር ወጥተው መንግሥትንና ፐትረያርኩን ሲቃወሙ የነበሩ በመንግሥትም የሰላ ሂስ ሲሰነዝሩ የታወቁ ግለሰብ መሆናቸው የአደባባይ ምሥጢር ነው
በምድረ አሜሪካ በነበሩበት ጊዜም ትክክለኛውና ሕጋዊው ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ ናቸው እያሉ ሲናገሩ የነበሩት እኒህ አባት
የሰላማዊ ሰልፍ መሪ በየቲቪው መስኮትና በየሬዴዎው ጣቢያው የኢትዮጵያን ችግር ተንታኝ የነበሩ ግለሰብ ባልታወቀ ምክንያት እንደ አክሮባቲስት ተገልብጠው አዲስ አበባ በመግባት የሆነውን ያልሆነውን በመዘላበድ  እነደገና ተቀይረውና ሌላ ሰው ሆነው ትናትና ደግሞ በአሜሪካ ሬዲዮ ጣቢያ የሰጡትን አስተያየት የሰማ ሰው እጅግ የሚያሳዝን ሆኖ እናገኘዋለን
ታዲያ እነዚህን ከመሰሉ አባቶች የቤተ ክርስቲያን አንድነት ይመጣል ብሎ መጠበቅ ከዝንብ ማር እንደመጠበቅ ያህል ነው አኒህ አባት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ተጣቂ እንደሆኑና ይታጠቁት የነበረው የጦር መሳሪያ እንደጠፋባቸው  በዚህ ጦስ ምክንያት አንድ ግለሰብ ተጠርጥሮ ሥራውን እንዲያጣ ምክንያት አንደተደረገ በአንድ ኢንተርኔት ድህረገጽ  እንዲህ ይነበባል

የሱሉልታ ከተማ ኢንቨስትመንት ባለሥልጣናት ጉቦ ሲቀበሉ ተያዙ

-    የወረዳው ሥራ አስኪያጅ በእስራትና በገንዘብ ተቀጡ
በታምሩ ጽጌ
በኦሮሚያ ልዩ ዞን የሱሉልታ ከተማ ኢንቨስትመንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዮሴፍ ጌታቸውና የከተማው ማዘጋጃ ቤት ሥራ አስኪያጅ አቶ መሸሻ ዘውዴ፣ 200 ሺሕ ብር ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ በኮሚሽኑ የክትትል ሠራተኞች በቁጥጥር ሥር የዋሉት አቶ ዮሴፍና አቶ መሸሻ፣ በሱሉልታ ከተማ የኢንቨስትመንት ቦታ የተረከቡ አንድ ባለሀብት ግንባታ ለመጀመር የግንባታ ፈቃድ ለማውጣት ላቀረቡት ጥያቄ የጠየቁትን ጉቦ ሲቀበሉ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

ባለሀብቱ በ2000 ዓ.ም. የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ቦታው ተለክቶ ሳይሰጣቸው የ2,500 ካሬ ሜትር ቦታ ካርታ ተሠርቶ በቅድሚያ እንደተሰጣቸው የሚያብራራው የኮሚሽኑ መግለጫ፣ መሬቱ በመሐንዲስ ተለክቶ እንዲሰጣቸው ለሦስት ዓመታት ምልልስ ካደረጉ በኋላ ግንቦት 13 ቀን 2004 ዓ.ም. ተሸንሽኖና ተለይቶ እንደተሰጣቸው ኮሚሽኑ አስረድቷል፡፡

ባለሀብቱ ግንባታውን ለመጀመር በጥቅምት ወር 2005 ዓ.ም. ቦታውን ሲያጥሩ ሁለቱ ኃላፊዎች በቦታው በመገኘትና ሕገወጥ መሆኑን በመግለጽ እንዳያጥሩ ማገዳቸውን ኮሚሽኑ ገልጾ፣ ባለሀብቱ ከሥራ አጋራቸው ጋር በመሆን የቦታ ባለቤትነት ማረጋገጫና የግንባታ ፈቃድ ሰነዳቸውን ይዘው ወደ ማዘጋጃ ቤቱ ማምራታቸውን ኮሚሽኑ አስታውሷል፡፡

ማዘጋጃ ቤቱ አቤቱታቸውን ተቀብሎ መልስ ለመስጠት ለጥቅምት 12 ቀን 2005 ዓ.ም. የቀጠራቸው ቢሆንም፣ ባለሀብቱ በቦታው ላይ ግንባታ ለማካሄድ ከፈለጉ 200 ሺሕ ብር ጉቦ መስጠት ከቻሉ ብቻ መሆኑን ኃላፊዎቹ በሌላ ግለሰብ በኩል መልዕክት እንዳላኩባቸው ኮሚሽኑ አስረድቷል፡፡

ባለሀብቱ ጉቦ እንዲሰጡ የተላከባቸውን መልዕክት በመቀበል፣ ጉዳዩን ለፌዴራል የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን በማሳወቃቸው፣ ኮሚሽኑ ክትትል አድርጐ ባለሀብቱ ጉቦውን በኢንቨስትመንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊው አቶ ዮሴፍ ባለቤት በወ/ሮ አቦነሽ በንቲ አማካይነት፣ ሰሜን ሆቴል ውስጥ ሲቀባበሉ እጅ ከፍንጅ መያዛቸውን አስታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ በወንጀሉ አፈጻጸም ዙሪያ የጀመረውን ምርመራ አጠናቅቆ መዝገቡን ሥልጣን ላለው የኦሮሚያ የሥነ ምግባርና የፀረ ሙስና ኮሚሽን ማስተላለፉን አስታውቋል፡፡