Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Monday 26 November 2012

መቀሌ ዩኒቨርሲቲ እየታመሰ ይገኛል

መቀሌ ዩኒቨርሲቲ በተወሳሰበ ሙስና ውስጥ በመሆኑና የሙስናው ዋና ተዋናዮች ዶ/ር ክንደያ ገብረህይወት እና ዶ/ር ኣብዱልቃድር ከድር የተባሉ ምክትል ፕረዚደንቶች ይውረዱልኝ ብለው ከሶስት ወር በላይ የጠበቁት ጀርመናዊ ፕረዚደንት ችግር ላይ ናቸው።
የቦርድ ሰብሳቢው ኤርትራዊው ኣቶ ቴድሮስ ሓጎስ (የኢፈርት ቦርድ ሰብሳቢም ናቸው) ጀርመናዊውን በአካል እንዳስፈራሩዋቸው ታውቋል! ይህ የሆነው ደግሞ ለትምህርት ሚንስትር ሳይቀር ግልባጭ ባደረጉት የአዲስ ምክትል ፕረዚደንቶች ሹመት የተነሳ ነው።

ጀርመናዊው ፕረዚደንት ከሶስት ወር በላይ/August-November/ የጠየቁትን ጥያቄ ሳይመልሱ ተኝተው የከረሙት ኣቶ ቴድሮስ ሓጎስ አውቆ የተኛ ቢቀሰቅሱት ይማታል የሚል አዲስ ዓይነት ቢሂል ፈጥረዋል! ከ300 million ብር በላይ ያባከኑን ሰዎች ገለል እንዲሉ መጠየቃቸው ሊመሰግኑ ሲገባ እንግዳውን German ሰውዬ እንደዚህ እንደውሻ የሚያስፈራሩዋቸው እነ ቴድሮስ ሓጎስ ወደ ማፍያነት መቀየራቸው ጉልህ ማሳያ ነው። ይህን ህዝብ ከመጤፍ እንደማይቆጥሩትና እንዳሻቸው መኖር እንደሚችሉ ግልፅ ማሳያ ነው። ይህ ህዝብ በሚከፍለው ግብርና በደሙ እየነገዱ የሚኖሩት እስከ መቼ ነው? ትግራይ ተማርሯል በማስፈራራት ና በጉልበት ልክ እንደ ትግራይ ህዝብ ደመኛው ለገሰ አስፋው ትግራይን ኤርትራዊው ቴድሮስ ሓጎስ እየገዙዋት ነው። የሚሰርቅን ሰው መጠየቅ ሲገባቸው ኣብሮዋቸው እንደሚሰርቅ በግልፅ በሚያሳይ መልኩ መከላከላቸው ይህ ስርዓት ምን ያህል እንደዘቀጠ፣ ወድቀቱም እንደቀረበ ያሳያል።

የዓረና የፖለቲካ ጉዳይ ተጠሪ ዓምዶም ገ/ስላሴ ታሰረ
አምዶም ገ/ስላሲ
የዓረና የፕሮፓጋንዳና የፖለቲካ ጉዳይ ተጠሪ የሆነው ወጣት ዓምዶም ገ/ስላሴ ከፓርቲ ዶክሜንቶቹ ጋር ታስሯል። ስራ ውሎ፣ አገር አማን ነው ብሎ ወደማረፍያ ቤቱ ሲገባ፣ በተከራየው ግቢ ውስጥ ነዋሪ የሆነችው የህወሓት ካድሬ ከነ ባለቤትዋ በር ላይ ጠብቀው ስርዓት ኣድርግ፤ "በግቢያችን ፖለቲካ እያሳመንክ ሌሎች ሰዎች ወደ ዓረና ትግራይ ልትወስድ ነው በማለት ባነሱት ኣታካራ እሱም ሕግ ባለበት ሃገር ለምን ወደ ሕግ ኣንሄድም ሲላቸው፣ መጀመርውንም የህወሓት ካድሬዎቹ ተዘጋጅተውበት ስለነበሩ ያለ መጥሪያና ያለ ምንም ግጭት በቅርብ ይጠባበቁ የነበሩ ፖሊሶች ሁሉንም ወደ ዓዲ ሓቂ ፓሊስ ጣብያ እስር ቤት ከወሰድዋቸው በኋላ፣ ባልና ሚስት ካድሬዎቹ እናንተ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፣ አንተ ግን ታስረህ ታድራለህ ብለው አስረውታል።


አቶ ዓምዶም ስራ ላይ ውሎ ወደ ቤቱ ሲመለስ በእጁ ይዟቸው የነበሩትን በፍላሽ እና በወረቀት ላይ የሰፈሩ የጽ/ቤቱ ዶክሜንቶችና የፅሕፈት ቤቱ ቁልፍ (ሁለት የተለያዩ ቁልፎች) አስረክብ ተብሎ እንደተወሰደበትና የዓረና ትግራይ ዋና ጽ/ቤት አሁን አደጋ ውስጥ እንዳለ ያረጋግጣል።

ከዚህ በተጨማሪ ያሳሰሩት ካድሬዎች ለፖሊስ ጣብያው በሰጡት ቃል ‘ያኔ ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ ሙተው እኛ ስናለቅስ እሱ ዝም ብለዋል”፣ በዚህም ተደስተዋል በማለት እንዳመለከቱ ሲገለፅ በወቅቱ በሚኖሩበት ግቢ ውስጥ የነበሩ ሰዎች እንዳሉት ግን ወጣት ዓምዶም በቤቱ ተኝቶ እያለ ሆን ብለው ዓረና መሆኑን ስለሚያውቁ ‘መለስ ሞተ እኛም ለተቃዋሚዎች ኣጋልጦን ሄደ ‘ እያሉ በማልቀስ እሱን ክፉ ለማናገር እንደ ሞከሩና እስከ መጨረሻም ከግቢው ለቆ እንዲወጣ የተለያዩ ምክንያቶች እያነሱ ይነዘንዙት እንደነበር ይገልፃሉ።

ኣሁን ማለት 07/03/2005 ዓ/ም የዓረና ትግራይ ከፍተኛ ኣመራሮች በፖሊስ ጣብያው ተገኝተው ምንድ ነው ጥፋቱ ሲሉ መጠየቃቸውና የጣብያው ኣዛዥ ፖሊስ ወታሃደር የሀይስ የተባሉ እኔ ቀስ ብየ ነው ጉዳዩን የማየው ለምን ኣቀላጥፈዋሎህ "ተዘጋ ያላችሁት ፅህፈት ቤትና ተዘረፈ ያላችሁት ዶኪመንት እኔ ኣያገባኝም የሚል መልስ እንደሰጡ በቦታው የነበሩ የዓረና ትግራይ ኣባላትና ኣመራሮች ይገልፃሉ።

ወጣት ዓምዶም ገ/ስላሴ 2002ዓ/ም በተካሄደው ሃገራዊ ምርጫ ዓረና ትግራይ ወክሎ በደጉዓ ተምቤን ወረዳ (ሃገረ ሰላም) የተወዳደረ ሲሆን በወቅቱ የዓረና ትግራይ ኣባል በመሆኑ ብቻ ጋዜጠኛ ሁኖ ይሰራበት ከነበረ በህወሓት ንብረትነት ከሚታወቀው ድምፂ ወያነ ትግራይ መባረሩ የሚታወስ ነው።

ከ100 በላይ ማዳበሪያ ያልገዙ ገብሬዎች ታሰሩ

ስማቸው መግለፅ ለደህንነቴ ያሰጋኛል በማለት የደወሉልኝ ኣዛውንት መጀመርያ “ድምፂ ወያነ ነው ወይ?” ሲሉ ጠየቁኝ።፡ኣይደለም ግን ልደርስልዎ እችላሎህ ኣልኳቸው። እንደዛ ያልኳቸው ስማቸው ሳይጠቀስ ግን ከትግራይ ክልል ምስራቃዊ ዞን ሓውዜን ወረዳ ደጋምባ ቀበሌ ብዙ የታሰሩ ሰዎች ስላሉ እንድታውቀው ይደዉልሉሃል ብለው ኣሳውቀውኝ ነበርና ! ‘ ድምፂ ወያኔ ነው ወይ ‘ ሲሉኝ ስጋታቸው ለመቀነስ የተጠቀሙበት ዘዴ መሆኑን ስለገባኝ ያጋጠማቸውን እንዲነግሩኝ ጠየቅኩዋቸው።
በደጋምባ ቀበሌ በገበሬዎች ማሰልጠኛ ማእከል ብዙ ሰዎች ታስረዋል፣ “እጅግም ተከፍተናል፤ ተቸግረናል!” ሲሉ ቁጣ የተሞላበት እረሮ ኣሰሙኝ። በዚህ ግዜ ያሰራችሁ ማን ነው? ለስንት ግዜ ታሰራችሁ? ስንት ሰውስ ታሰራችኋል? ብየ ጠየቅኳዋቸው ስማቸው ለመግለፅ ያልፈለጉት ኣዛውንት ያሰሩን ብርሃነ ሃይለ የሚባል የግብርና ሰራተኛና ሃለቃ ተስፋይ የተባሉ ከወረዳ የመጡ ሰዎች ናቸው። የታሰሩበት ምክንያት ሲገልፁ ደግሞ ማዳበርያ ካልገዛችሁ ተብለን ነው" ካልገዛችሁ ከሴፍትኔት ስራ ትወጣላችሁ እያሉም በመኸር ወቅት ሰብላችን እንዳንሰበስብ ችግር ፈጠሩብን ይላሉ።

በገበሬዎች ማሰልጠኛ ጣብያ ከ100 ሰው በላይ ነው የታሰርነው ስላሉኝ ይህን ሁሉ ሰው በዛው ታስሮ ነው የሚውለውና የሚያድረው? ጠባቂስ ሚሊሻ ነው ወይስ ፖሊስ? ስላቸው ጥዋት በቦታው እንድንገኝ ይደረጋል ማታ 12 ሰዓት ወደ ቤታችን እንድንገባ ይፈቀድልናል። እንደዛ እያልን ማዳበርያ መግዛት ፈቃደኛ ነኝ እስክንል ድረስ "የሚቆጣጠሩን ሚሊሻዎች ናቸው እና እንካችሁ ድምፂ ወያኔዎች ችግራችን በዜና ኣስተላልፉልን ‘ ብለው ተማፀኑኝ። ህዝባችን ያለ ድምፂ  ሬድዮ ሌላ እንዳይሰማ የተነፈገ መሆኑ ህወሓት የፈጠረለትን ችግር መልሶ ለህወሓት ራድዮ ችግራችን ኣስተላልፉልን ማለቱ እና ድምፂ ወያኔም ሰምቶ ለህወሓት ቢሮ በማስረከብ እንደዛ ችግሩን ላካፈለ ወገን ኣድኖ ግፍ ሲፈፅምበት ኖረዋል ኣሁንም ኣለ።

ሰውየው ለደህንነቴ ስል ስሜን ኣልገልፅልህም ሲሉኝ በሌላ ጥያቄ መጣሁባቸው። ከታሰሩት ሰዎች ለምሳሌ ብለው ጥቂት ሰዎች ቢጠቅሱልኝ ኣልኳቸው! ትንሽ ረጋ ብለው ከቆዩ በኋላ ሊጠቃቅሱኝ ገቡ። እነሱም፦

1.ኣቶ መሓሪ ወልደስላሴ
2. ኣቶ ኣረጋዊ ገ/ኣነንያ
3. ወ/ሮ ሂወት ገ/መድህን
4. ወ/ሮ ኣሚት ዘርኡ
5. ወ/ሮ ኣፅበሃ ገ/መስቀል እኚሁ የ70 ዓመት ኣዛውንት ናቸው:: ኣፅበሃ የወንድ ስም ነው? ኣልኳቸው የሴት ነው ብለው ኣረጋገጡልኝ::
6. ኣቶ መስፍን ገ/ገርግስ
7. ኣቶ ገ/መድህን ገ/ሂወት ……ኣሉኝ::

በመጨረሻም ኣደራችሁን ‘ ድምፂ ወያኔዎች ብሶታችን ግለፁልን ኑሮ እየኖርን እንዳይመስላችሁ ‘ ብለው ተለዩኝ::
እኔም እንደነሱ ስሜን መግለፁ ይቅርብኝ$

No comments:

Post a Comment