Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Saturday 15 December 2012

ባዶ ሥልጣን ይዞ ውሸት ለመሳቂያነት

ዳኛቸው ቢያድግልኝ
ፈጽሞ ለማጅ የማያሰኝ ዋሾነት በአቶ ኃይለማርያም ሲተወን አልጀዚራ ላይ ተመልክተናል። እርግጥ ነው እንደ ‘ባለ ራዕዩ’ ጮሌነትና አራዳዊ መገለባበጥ ቢያንሰውም ለመዋሸት ግንባራቸውን እንደማያጥፉ ግን አረጋግጠውልናል። አቶ ኃይለማርያም ምናልባት እየተቆጡ ሲዋሹ፣ እያስፈራሩ ሲቀጥፉ ስለኖሩ እንጂ እንደዚህ በአንድ ጊዜ የላቀ የዋሾነት ሜዳልያ የሚያሰጥ አቅም ሊኖራቸው ባልቻለ ነበር። ብዙ ሰባኪዎችን የተመለከቱ ግን አይመስለኝም። ቢሆን ኖሮ ቴክኒክ ተውሰው ትንሽ እውነት እያስደገፉ ግዙፍ ውሸት በመዋሸት ማደናቆር በቻሉ ነበር እንደ ታምራት ላይኔ። ግን ይዋሻሉ፣ አረ የምን ሰው ምን ይለኛል ነው፣ እግዜር ምን ይለኛልም አይሉም እኮ። አቤት መለስ እንዴት አድርጎ ጠፍጥፎ ሰራቸው እባካችሁ? ግን አላማረባቸውም ምክንያቱም ባዶስልጣን ይዞ ውሸት መሳቂያነት መሆኑን ሊያውቁ በተገባ ነበርና። ለዚህም ነው አስፎጋሪ ውሸት የዋሹት። ስለመሬት ነጠቃው ቀባጠሩ፣ ስለ ታሰሩት ወገኖችም ዋሹ። አዎ ኳስ ጨዋታዋ ላይም ሳቱ። ለመታጠፍ ደግሞ ዘገዩ ኳሱን ተዉትና መለስ እኮ ሃምሳ ጊዜ ኤርትራ እሄዳለሁ ብሎ ነበር አሉና መታጠፍ ጀመሩ። እናቴ ትሙት እጅሽን ልምታ እያለ የሚማጸን ልጅ መሰሉ። አባቱን ድረስልኝ የሚል ልጅ ይመስል ሮጠው መለስ መለስ ሲሉ ያሳዝናሉ። ጋዜጠኛይቱ በሆድዋ ምስኪን የምትል ይመስል ነበር።

ምላስ አጥንት ቢኖረው ታድያ ቀጨ..ጨ..ጨ ሲል በሰማነው ነበር ሲዋሹ። አቤት ባለቤታቸው እንዴት ይሳቀቁ ይሆን? እሳቸውም ከአንድ ውሀ ካልተቀዱ እና ቀዳማይቱን መምሰል ካልፈለጉ ተሳቅቀው ማለቃቸው ነው። ውይ …. የሰው ዐይንስ እንዴት አያለሁ ይሉ ነበር። ደግነቱ ቤተመንግሥት ነው ያሉት ማየትም መስማትም ከማይችሉበት ድብቅ ስፍራ ብለን እንለፈውና ነጥቦቹን እንመልከት። አለዚያማ መጻፋችንስ ምን ዋጋ አለው። ክቡርነትዎ ግን ድንገት ተፈቅዶልዎ ይህንን ካነበቡ የፕሮፌሰር አልማርያምን ምክር አይርሱ። አለም እንደትስቅሎት እየሳቁ ይዋሹ እንጂ አለም እንዲስቅቦት እየሟሸሹ አይዋሹ ቂ..ቂ….ቂ……

የአስመራ ጉዳይ ላይ የሰጡት አስተያየት ትንሽ ብልጠት ነበረው ምክንያቱም በመጨረሻ የኤርትራ ክሊክ አሸናፊ ሆኖ ኢትዮጵያን ለመጠቅለል መውጣቱን ልብ በማለታቸው ሊሆን ይችላል ብሎ መጠርጠር አስፈላጊ ነው። አለበለዚያም የሳቸው ‘ኤክሰለንሲ’ ያደርጉ እንደነበረው መተጣጠፍ ፈልገው ነበር። ይሁን እንጂ እንኳን በሀገር ጉዳይ ሊወያዩ ስለ ኳስ ጨዋታ እንኳን ያለማወቃቸው አሳፋሪና ከታማኝ ተላላኪም በታች ያደርጋቸዋል። አቶ ኃይለማርያም እንደ ሰው ተፈጥረው እንደ መቶ አለቃ ግርማ ሲሆኑ ያሳዝናሉ። እንደዚህ መሳቂያ እናደርግሀለን አርፈህ እንደ እሱ ቁጭ በል የሚሏቸው ይመስላል። ግን እንዲያው ምን አለበት ባያዋርዱዋቸው እሳቸውም እንዲህ ባይወርዱ።


ግን ከዚህ በላይ ዋሽተዋል መዋሸት አይደለም አቶ ኃይለማርያም ደመኛችን ናቸው። አቶ ኃይለማርያም መዋሸት ከጀመሩ ቆይተዋል። አታስታውሱም ብዬ አልልም ከወይዘሮ ገነት ዘውዴ ጋር በመሆን ኢትዮጵያን ለህንዶች ሲደልሉ ኖረዋል፡ አሻሽጠዋል እየዋሹ ሕዝብ አስለቅሰዋል። ይህንን ስትመለከቱ ሰውየው እንደ መግቢያ ያጠኑት ትንሽ አረፍተ ነገር እንዳለና እንደ ትወና በዚያችው እንደሚንደረደሩ ማየት ትችላላችሁ http://www.youtube.com/watch?v=zJ9Lnm7ODjE ይህ ቃልምልልስ ሕንድ አገር ሄደው የሰጡት ነው። ‘Savana land’ ላይ አበሻ አይኖርም ወባ ስለሚፈሩ እዚያ ሰዎች የሉም ይላሉ የአራተኛ ክፍል ጂኦግራፊ እያስታወሱ፣ ሁለት አመት ቆይተውም የተሻለ መከራከሪያ ይዘው አይመጡም አሁንም ‘Savana land’ ውሀው እንደልብ ነው መሬቱ ባዶ ነው ስለዚህ ለውጭ ንግድ የተመቸ ነው ይሉታል ለጠያቂው። ሰው እንዴት እንደዚህ ፈዛዛ ይሆናል ስንት ጽሁፎች ፊልሞች ተሰርተው ከተበተኑ በሁዋላ እንኳን ትንሽ ውሸታቸውን አይቀባቡትም እንዴ? ምንም የተፈናቀለ ሰው የለም ከሚሉ መሰረታዊ ልማት አሟልተን ዘመናዊ የገጠር ቴክኖሎጂ አቅርበን ድሀ ገበሬዎች መካከለኛ ገቢ እንዲያገኙ ጅምራችንን አጠናክረናል አይሉም ነበር? አቤት መሌ ቢሆን ያልገባው ነገር ሲሆን አንጠልጥሎ ነበር የሚሸውደው አንዳንዶች እንደዚህ ሌሎች ደግሞ እንደዚህ ሊሉ ይችላሉ እኛ ግን አማራጫችንን በጊዜው እንወስዳለን ያንን ደግሞ አሁን መናገር አስፈላጊ አይደለም ይሉና ኳስ ከጎላቸው ራቅ ያደርጋሉ ቂ ቂ ቂ ቂ። አቶ ኃይለማርያም ግን እንዲህ እያሉ ይቀጥላሉ…..

የመሬት ነጠቃ የሚባለው ነገር ኢትዮጵያን አይመለከትም ምክንያቱም የምንሰጠው አገልግሎት ላይ ያልዋለ ባዶ መሬት ነው። በሀገር ውስጥ የፖለቲካ ቀውስ ያስከትላል የሚባለው ውሸት ነው። ይሄ የዳያስፖራው ግፊት እንጂ በሀገር ውስጥ ችግር የለብንም ይሉታል ለጠያቂያቸው ለቪክራም ባሂ። ባልደረባቸው ወይዘሮ ገነትም ለዚህ ጋዜጠኛ እንዲህ ነበር ያሉት። “… Our government is giving land to investors with almost negligible price for about 25 to 50 years…” ይላሉ ፈገግ ብለው ። እድሜአቸው እንዲህ ከብዶ ሀሳባቸው እንዲህ መቅለሉ ያሳፍራል። እዚህ ላይ ያገኙዋቸዋል http://www.youtube.com/watch?v=gsFyIeVD108

መቼም ወያኔ በአንድ ነገር ጎበዝ ነው። ከሀዲና ውሸታሞች ፈልፍሎ ያገኛል። እኒህ ሴት እንደተማረ ሰው ሳይሆን የወሬ ወሬ ሰምቶ የሚያወሩ ነው የሚመስለው። እናም እንዲህ አሉ አገራችን ድርቅ ያጠቃታል እናም በረሀብ ትታወቃለች ሕንዶች ደግሞ ጥጥ ይዘራሉ፣ የዘይት እህሎችን ያመርታሉ ስንዴና ሩዝም። ስለዚህ በምግብ ራስን እንድንችል ያደርጉናል ይላሉ። የጥጥ ፍሬ እንኳን ገበሬው

ይተርፈው ይመስል። የአነጋገራቸው መንቀርፈፍና የእውቀታቸው አናሳነት ጎልቶ እንደሚታይ ያውቁት ይሆን? ግን ማን ይነግራቸዋል? እስቲ የትኛው ምርት ነው ለአገር ውስጥ ገበያ የዋለው ብሎስ ማን ይጠይቃቸዋል?

አቶ ኃይለማርያም የፖለቲካ እስረኛ በሀገራችን ውስጥ የለም ይላሉ። ያሉት አሸባሪዎች ናቸው እነሱንም ህግ ይዳኛቸዋል አሉ። ትንሽ መለሳለስና አንዳንድ ችግሮችም ካሉ በጥንቃቄ በመመልከት መፍትሄ እንፈልጋለን፣ ታዳጊ ዲሞክራሲ ስለሆነ እየወደቁ መነሳት ያለ ነው የታሰሩት አሸባሪዎች ናቸው ይሁን እንጂ በምክር፣ በመለስተኛ ቅጣትና በማስጠንቀቂያ ውደ ልማታዊነት እንዲመጡ የማድረግ ሂደትም አለ እያሉ ትንሽ ቢያለሰልሱት የፖለቲካ ሀ ሁ ቆጥርዋል ያሰኛቸው ነበር። ግን በጣም ጭፍንና ደካማ ግን ታማኝና ታዛዥ በመሆን ብቻ ነበርና መለስ አጠገብ መሆን የሚቻለውና ደህና ሰነበቱ። ጠቅላይ አስለቃሹ ሲሰናበቱ ሳያስቡት ስልጣን ላይ ራሳቸውን አግኝተዋል ብሎ ማለፍ ይሻላል። ግን እንጠብቃቸው ለሚሉት ምንም ነገር ከርሳቸው መጠበቅ ሞኝነትም መሆኑን ማሳሰብ አስፈላጊ ነው።

ምንም እንኳን አቶ ኃይለማርያም ዳይቨርሲቲ እያሉ የሚደጋግሟት ነገር ብትኖርም ለርሳቸው አኝዋኮች ዳይቨርሲቲ ውስጥ አይገቡም? አፋሮች ሰዎች አይደሉም፣ የተፈናቀሉት አማራዎች የውጭ ዜጎች ናቸው። የራሳቸው ሚዲያ ላይ እንኳን መሰረተ ልማት ምናምን የሚሉትን ለምን አያነቡም። ውሸት አገርቤት ውስጥ እንጃልህ እያሉ እንደሚደነፉት ይመስላቸዋል እንዴ? ወይ ፋታ እንስጣቸው ብሎ ነገር? በሉ ፋታ ወደ ድንፋታ ዞሮ የመከራ ዘመን ሳይበዛ ጠንከር ብላችሁ ታገሉ። ሰውየው ለራሳቸውም ፋታ አላገኙም። ያለው የትግራይ ተገንጣይ ቡድን ነው። አዘናጊ አስተያየት ይቅርና ሕዝቡ ለነፃነቱ ይታገል።
biyadegelgne@hotmail.com

No comments:

Post a Comment