Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Sunday, 7 October 2012

የወደፊቱ፡ የዓለም ስጋትና የሀገራችን ሁኔታ፡

ማተቤ መለስ
የሰውን ልጅ ታሪክ ወደኋላ መለሥ ብለን ሥንመረምር፡ ከፍጡራን ሁሉ በተሻለ ሁኔ ዓለምንና ተፈጥሮን አጣጥሞ በመግራት እየተጠቀመባት እንዳለ ለመረዳት አያዳግተንም፡፡ በዚያው ልክ ደግሞ አንዱ ሌላውን የበታች አድርጎ ለመግዛትና ለመበዝበዝ ሌላው ላለ መገዛትና ላለመበዝበዝ በሚደረጉ ፍልሚያዎች መነሻ ነት ለጥፋትም እያዘጋጃት መሆኑን እናያለን፡፡ በእነዚህ ትንቅንቆች ሂደት መጠነ ሰፊ የህይወትና የንብረት ውድመቶች የደረሱና እየደረሱም ያሉ ወደፊትም በዳይና ተበዳይ በዝባዢና ተበዝባዥ በአንድ ቃል አምባ ገነኖች፡ ከምድራችን እስካለተወገዱ ደረስ እንደማያቆሙ የታወቀ ነው። ለሰው ልጅ ደመኛ ጠላት የሆኑት አምባገነንነት፣ የግልጥቅም አሳደጅነት፣ ተስፋፊነት ወ.ዘ.ተ. ጨርሰው ተወግደው የሁሉም ሰባዊ ፍጡር ሰላም ዲሞክራሴና ነጻነት በውል እሰካልተከበሩ ድረስ የጥፋቱ መጠንና አይነት ይለያይ እንጅ ጦርነት የማይቆም ቀጣይ ሂደት ነው የሚሆነው። ከዚህ አንጻር ፈጣሪያችን በስልጣኑ ካወረዳቸው ማታት ባሻገር የእውቀት አድማሳችን የፈቀደለንን ያህል ርቀን የዓለምን እውነታ በአይነሕሌናችን ብንዳስስከ20ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ እስካሁን ድረስ እንዳለው ጊዜ ሰብዓዊ ፍጡር ለጦርነት አደጋ የተጋለጠበት ወቅት ከዚያ በፊት የለም፡፡ ለተከሰተው ሁሉ ጥፋት ደግሞ መነሻዎቹም ሆነ መድረሻዎቹ እኛው እራሳችን ሰዎች ነን፡ ከፍጥረታት ሁሉ መጥፊያውን የሚሰራ ቢኖር ሰው ብቻ ነው ይባል የለ።

አዎ! እንደ ጀርመኑ አዶልፍ ሂትለር፣ እንደ ኢጣሊያው ዶቸ ሞሶሌኒ፣ እንደ እስፔኑ
ፍራንኮና፣ እንደ ፖርቱጋሉ ሳለዘር፣ እንደ ዩጋንዳው ኢዲያሚን ዳዳ፣ እንደ ማህከላዊ
አፍሬካው ቦካሳ፣ እንደ ሰሜን ኮርያው ኪምኡል ሱንግ፣ እንደ ኢራቁ ሳዳም ኡሴን፣ እንደ
ኮንጎው ሙቡቱ ሴሴሴኮ፣ እንደ ቻይናው ማኦ ሴቱንግ፣ እንደ ቱኒዚያው ዜን ቤናሊ፣ እንደ
ግብጹ ሙባረክ፣ እንደ የመኑ አብደላ ሳላሀ፣ እንደ ሊቢያው ሙሀመድ ጋዳፊ፣ እንደ ኢራኑ
ሙሀሙድ ነጃድ፣ እንደ ሶርያው አሳድ፣ እንደ ሱዳኑ አልበሽር፣ እንደ ዙባቤው ሙጋቤ፣
እንደ ኢትዮጵያው መለስ ዜናዊ ወ.ዘ.ተ. ባሉ አምባገነንና ሰግብግብ መሬዎች መነሻነት፣
አሁን ድረሥ በምድራችን ላይ በእኛ በሰዎች መካከል ከ14 ሺ ያላነሱ ጦርነቶች
እንደተካሄዱ የታሪክ ምሁራን ይገምታሉ።
ቀደም ያሉትን ትተን በቅርብ ታሪክ የመዘገባቸውን ጦርነቶች ብቻ ብናይ እንኳን
የህይወትና የንብረት ጥፋት ከጊዜ ወደጊዜ እያደገ መምጣቱን እንረዳለን፡፡ ሻለቃ አባይነህ
አበራ ካዝና በሚል እርዕስ አዘጋጅተው ለንባብ ባበቁት መጽሀፋቸው ያካተቱት ጥናታዌ
ዘገባ እንደሚያስረዳን፡
1ኛ/በ17ኛውክፍለዘመን በተካሄዱትጦርነቶች የ3ሚሊዮን ሕዝብ ህይወት ተቀስፏል።
2ኛ/ በ18ኛው ክፍለዘመን በተካሄዱት ጦርነቶች 5.5 ሚሊዮን ሰው አልቋል።
3ኛ/ በ19ኛው ክፍለዘመን፡ 16 ሚሊዮን ሕዝብ ህይወቱን አጥቷል።
4ኛ/ በ20ኛው ክፍለዘመን በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት 10 ሚሊዮን በሁለተኛው
የዓለም ጦርነት፡ ደግሞ 55 ሚሊዮን ሕዝብ አልቋል።
ከላይ በተዘረዘሩት ጦርነቶች በድምሩ 89.5 ሚልዮን ህዝብ እንደቅጠል እረግፏል።
በሁለቱ የዓለማችን ታላላቅ ጦርነቶች ማለትም በ1ኛውና በ2ኛው የዓለም ጦርነቶች
ከሞተው ሌላ 110 ሚሊዮን ሕዝብ አካለጎዶሎ ሆኗል። በገንዘብ በኩልም፡ የአንደኛው
የዓለም ጦርነት ያስከተለው ኪሣራ ከ260 እስከ 360 ቢሊዮን ዶላር እንደሚደርሥ
ሲገመት።
በሁለተኛው ደግሞ ከሦስት እስከ አራት ትሪሊዮን ዶላር የሚገመት ንብረት ወድሟል።
እልቂቱ በ20ኛው ክፍለዘመን ጦርነት ብቻ ያከተመ አይደለም። ከሁለተኛው የዓለም
ጦርነት በኋላ በምንኖርባት ዓለም ውሥጥ 150 ያህል ጦርነቶች ተካሂደዋል፡ በእነዚህ
ጦርነቶች ከ10 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አልቀዋል፡ በዚህ ስሌት የእኛዋ ሀገርም ከሱማሌ
ወራሪ ከሻብያና ከወያኔ ጋር ባካሄደችው ጦርነት ያለቀውን ወገናችንን ታሳቢ ማድርግ
እንችላለን። ለእነዚሁ ጦርነቶችና ለመሣሪያ እሽቅድምድም የሰው ልጅ 10 ትሪሊዮን ዶላር
ወጭ አድርጓል። በጦርነት ሳቢያ ከሚደርሰው የሕይወት እልቂትና የንብረት ጥፋት ባሻገር
በየጊዜው አይነቱና ጥራቱ እያደገ የሚሄደው የጦር መሣሪያ ጋጋታ ሌላው የወደፊቷ
ዓለማችን አሣሣቢ ጉዳይ ነው።
የ17ኛው ክፍለዘመን ወደር የለሽ መሣሪያዎች ጠብመንጃና ሽጉጥ ነበሩ። በ18 እና 19ኛው
ክፍለዘመን መድፍ በጦር ሜዳው አውድ የአንበሣ ድርሻውን ተረከበ። በ20ኛው
ክፍለዘመን በተካሄዱት ሁለት የዓለም ጦርነትች ደግሞ ታንክና ጀት ተካፋይ ለመሆን
በቁ። እንሆ! ዛሬ ደግሞ የኑክሌር መሣሪያዎች ጥፋት በዓለም ላይ ሲያንጃብብ ይታያል።
ዛሬ በምድራችን ላይ ርሀብ እርዛት የተፈጥሮ አድጋ በሽታና ማይምነት አልተወገዱም።
በልጽገዋል በሚባሉ ሀገሮችም ቢሆን የሰውልጅ በቴክኖሎጅ ድጋፍ ከተፈጥሮ ጋር
የሚያደርገው ግብግብ ገና አላከተመም።
ሆኖም ግን በአምባገነንነት መንስኤ ለዕድገትና ለብልጽግና ከሚደረገው ትግል ይልቅ በጦር
መሣሪያዎች ምርት እረገድ የሚደረገው እሽቅድምድም እየተጧጧፈ ይገኛል። በአለንበት
ወቅት በታዳጊ ሀግሮች ብቻ አንድ ቢሊዮን ሕዝብ በችግር ይኖራል። 800 ሚሊዮን
ጎልማሦች በማይምነት ቀንበር ታንቀው ይማቅቃሉ። 250 ሚሊዮን ሕፃናት የትምህርት
ዕድል ተነፍገዋል። በሌላ በኩል በእያንዳንዱ ደቂቃ 3 ሚሊዮን ዶላር ለጦር መሣርያ
እሽቅድምድም ይባክናል እንደ ሻለቃ አባይነህ ጥናት።
መንበሩን ሲዩድን እስቶኮልም ያደረገና ሲፒ የተባለው የአለም ሰላም ምርምር ተቋም 19.
3.2012 በሰጠው መግለጫ ባለፉት 5 አመታት ጊዜ ውስጥ የጦር መሳሪያ ሽያጭ 24
በመቶ እንደጨመረ ሲያረጋግጥ፡ ግንባር ቀደም ሻጭ የሆኑ ሀገራት አሜሬካና እሩሲያ
ሲሆኑ፡ ተከታዮች ጀርመን እንግሊዝና ፈረንሳይ ናቸው ካለ በሗላ በግዥው የተሰማሩት
ደግሞ ከኢሲያ አህጉር ህንድ፣ ደቡብ ኮርያ፣ ቻይና እና ሲንጋፖር ሲሆኑ ከአፍሪካ
አህጉርም ጥቂት የማይባሉ ሀገራት፡ በመሳሪያ ሸመታው እንደ ተሰማሩ ገልጿል፡፡ ከዚህ
ውስጥ የእኛዋ ሀገር ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ ግንባር ቀደም መሆኗ የማይቀር ነው።
እንግዲህ የደቂቃውን ኪሣራ ወደ ሰአትና ቀን፣ ቀጥሎም ወደ ወራትና አመት አጠቃለን
ብናሰላው፡ ምድራችን የምትገሰግሥበትን የጥፋት አዘቅት አሸጋግረን ለመመልከት
አንቸገርም።
በአሁኑ ወቅት ለአንድ የጥፋት መሣሪያ ምርትና ግዥ የሚባክነው እልቆ፡ መሣፍርት
የሌለው ገንዘብና የሰው ጉልበት፡ ለኢኮኖሚና የማህበራዊ ተቋሞች ግንባታ ቢውል ኖሮ፡
ጠቀሜታውን መገመት አያዳግትም፡ ለአብነት ታክል ለመጥቀስ ይለናል ሻለቃው፡
v ትራይዴንት በተባለው የአቶሚክ ባህር ሰርጓጅ መርከብ መግዣ ፋንታ ለ2 ሚሊዮን
ሰዎች፡ የሚሆኑ የመኖሪያ ቤቶች።
v ቶርናዶ በተባለው አንድ አውሮፕላን ፋንታ 5 ሆስፒታሎች።
v ሊኦፓርድ በተባለው ታንክ ፋንታ 36 በአለ 3 ክፍል አፓርትመንቶች።
v በሰለጠነው ዓለም፡ ለአንድ ሻለቃ ጦር መለማመጃ፡ በሚመደበው ወጭ ፋንታ፡ 28
መዋለ ሕፃናት ለመገንባት ይቻል ነበር።
እጅግ የሚገርመው፡ ነገር ደግሞ በጦር መሣሪያው ሽቅድምድም ውስጥ ሕዝባቸው በጠኔ
እየረገፈ ያለው ታዳጊ ሀገሮችም ተሣታፊዎች መሆናቸው ነው። ከላይ ለመግለጽ
እንደሞከርሁት የእኛዋን ሀገር ጨምሮ እንደታዳጊ ከተቆጠረች ማለት ነው፡ በእኔ እምነት
ግን ቁልቁል የምታድግ ቢባል ነው የምስማማው። ከ1960-2012 ድረስ በአለው ጊዜ
የታዳጊ ሐገሮች ብሔራዊ የሀገር ውሥጥ ምርት በአማካይ በሶሥት እጅ ሲያድግ የጦር
በጀታቸው በሰባት እጅ ያህል ክፍ ብሏል። በዚህ የታዳጊ ሀገሮች የመከላከያ በጀት
ከመላው ዓለም የጦር ወጭ ውሥጥ አንድ አራተኛውን እጅ ይዟል።
v እነዚሁ ታዳጊ ሀገሮች ለጦር እሽቅድምድም፡ በሚመድቡት ወጭ፡ እያንዳንዳቸው
120 ሺ ኪሎዋት ሃይል ያላቸው 300 በእንፋሎት የሚሰሩ፡ የኤሌክትሪክ ሃይል
ማመንጫ ጣቢያዎ ችን።
v በአመት አንድ ሚሊዮን፡ ቶን ያህል ነዳጅ ዘይት፡ ለማምረት የሚችሉ 300 የነዳጅ
ዘይት ማጣሪያ፡ ፋብሪካዎችን።
v አንድሺ የመሬት ማዳበሪያ ኬሚካል፡ ፋብሪካዎችን፣
v 600 የስኳር ፋብሪካዎችን ለማቋቋም ይችሉ ነበር።
ወደኛ ሀገር ሰንመጣ ደግሞ ለጦር መሳሬያ ግዢ ከሚውለው በተጨማሪ ወያኔ እየዘረፈ
በውጭ ሀገራት ባንኮች ያሸገው ሲታሰብ የእትዬለሌ ነው። በአጠቃላይ በአሁኑ ወቅት
ያለው የዓለም የሕዝብ ሥጋት በመንግሥታት ወታደራዊ በጀት እድገት፣ በመሣሪያ
ክምችትና በጠረፍ ጦርነት ላይ ብቻ የተመረኮዘ አይደለም እንደ ላይኛው። ይልቁንም
የባሰው ደግሞ የኑክሌር መሣሪያዎች ይዞታ እያደር መስፋፋት፡ እጅግ በጣም አሣሣቢ
ጉዳይ ሆኗል።
በአለንበት ዘመን አንድ የኑክሌር ፈንጅን ዒላማው ላይ ለማሣርፍ፡ ተውንጫፊ
ሚሣይሎችን፡ ወይንም ስትራትጂካዊ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖችን፡ የማምረቱ
አስፈላጊነት፡ በጥያቄ ምልክት ውሥጥ የገባ ይመስላል። የዚህም መንሥኤው በኑክሌር
መሣሪያዎች ምርት እርገድ የተደረገው ለውጥ፡ የአንድን የኑክሌር ፈንጅ መጠን እያደር
ለማሣነሥ፡ መቻሉ ነው። ለአያያዝ በጣም ቀላል የሆኑ ነገር ግን ከፍተኛ የፍንዳታ ሃይል
ያላቸው የኑክሌር ፈንጂዎች ከተመረቱ አመታት ተቆጥረዋል። እነዚህን ቀላል የኑክሌር
ፈንጂዎች በመድፍ በመተኮስ ተፈላጊውን ጉዳት ማድረሥ ይቻላል። የዘመኑ ቴክኖለጂ፡
ከዚህም በቀለለ ዘዴ የሚተኮሱ የኑክሌር ፈንጂዎችንም አምርቷል። ለምሣሌ የአሜሬካ
ወታደር የታጠቃቸው ኤኮ እና ዴልታ የተሰኙትን የኑክሌር ፈንጂዎች፡ በቀላል ተሽከርካሪ
ወይንም በሰው ጀርባ፡ ከአንድ ቦታ ወደሌላ ማንቀሣቀሥና በቀጥታ በዒላማቸው ላይ
ማጥመድ ይቻላል።
ምንም እንኳን ከእነዚህ መሣሪያዎች ውሥጥ በፍንዳታ ወቅት የሚፈተለከውን፡ ሬዲዮ
አክቲቭ፡ መርዛማ አየርን በቀላሉ ለመጠቆም ቢቻልም፡ ከፍንዳታ በፊት ግን የኑክሌር
መሣሪያዎቹ፡ የተጠመዱበትን ሥፍራ፡ በዘመናዊዎቹ ሳተላይቶች እንኳን ለማግኘት
አልተቻለም። ይህም ኑክሌርን የታጠቁ መንግስታት በማነኛውም ወቅትና ቦታ ፈንጂዎቹን
ጥቅም ላይ እንዲያውሉ ያስችላቸዋል።
በአሁኑ ወቅት፡ የኑክሌር ቦምብ ሥራ የአደባባይ ሚስጢር እየሆነ የመጣ ይመሰላል።
ምክናያቱም አንድን የኑክሌር ቦምብ ለመስራት፡ ተፈላጊውን ቀመርና ንድፉንም ከመፃፍት
ማግኘት የሚቻልበት ሁኔታ መፈጠሩ ነው። በኑክሌር ምረት ረገድ ከባዱ ችግር፡ ዩራኒየም
የተባለውን ማዕድን ማግኘቱ ነው። ማዕድኑ ቢገኝም ተፈላጊውን ንጥረ ነገር በጥራት
ለማውጣት የረቀቀ ቴክኖሎጂና ከፍተኛ የማምረቻ ተቋም ያስፈልጋል። ይህም ሆኖ ግን
መሣሪያው፡ በግለስቦችም ሆነ በመንግሥታት እጂ ከመግባት አላገደውም። በሃብት
በበለጸጉ ሀገራት በዩራኒየም ፋብሪካዎች ሥርቆት እየተጧጧፈ ነው።
በአለፉት 20 አመታት ውሥጥ አፖሎ፡ ከተባለው የኑክሌር መሣሪያዎች፡ ማምረቻ፡
ኮርፖሬሽን 342 ኪሎግራም፡ ምርጥ ዩራኒይም መሰረቁ ተዘግቧል። ይህ መጠን ብቻውን
በ2ኛው የዓለም ጦርነት፡ መገባደጃ ሂሮሽማ ላይ የተጣለውን ቦምብ አይነት በቁጥር 38
ማምረት ያስችላል። በኑክሌር መሣሪያዎች ምርት ረገድ፡ ሌላው አሳሳቢ ወቅት እየተቃረበ
ይመስላል። ምንም እንኳን እስካሁን ከፋብሪካ ወጥተው የጠፉት የኑክሌር ንጥረነገሮች፡
ለክፋት ከዎሉ ከ 15 ጊዜ በላይ፡ ምድራችንን ለማውደም ቢችሉም፣ ጠበብቱ ሌላ ረቂቅ
ዘዴ ከመፈለግ አልቦዘኑም። የዩራኒየም ማዕድን በብዛት አለመገኘት፡ ብቻ ሣይሆን ለአንድ
ፈንጅ የሚውለው፡ ክብደት ለመሣሪያው አጠቃቅም፡ አመች አለመሆኑም ጠበብቱን፡
ያሳሰባቸው ይመስላል።
ስለዚህም ነው፡ ሊቃውንቱ ለኑክሌር መሣሪያዎች ምርት የሚበጂ ሌላ ንጥረ ነገር፡ ፍለጋ
ጉድ፣ ጉድ የሚሉት። ሳይንቲስቶች የኑክሌር፡ መሣሪያዎችን፡ አይዞቶፕስ፣ ኦፍ፣
ትራንስራንየም፣ አሜሪሲየምና፣ ካሊፎርንየም፡ ከተባሉት ንጥረ ነገሮች ማምረት
እንደሚቻል፡ አረጋግጠዋል። ከእነዚህ ንጥረ ነገሮች፡ የሚመረቱት፡ የኑክሌር መሣሪያዎች
ክብደታቸው፡ በግራም የሚመጠን በመሆኑ እንደ ብዕር ኪስ ውስጥም ይሽወጣሉ፡ ተብሎ
ተገምቷል። እነዚሁ የመጭው ዘመን የኑክሌር፡ መሣርያዎች በመጠናቸው ጥቃቅን ይሁኑ
እንጂ የጥፋት ሀይላቸው ግን ከግዙፎቹ፡ የዩራኒየም ፈንጅዎች የሚያንሱ አይሆኑም።
በአሁኑ ወቅት ከ5 በላይ ሀገሮች፡ የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት እንደሆኑ በይፋ ይታውቃል።
የአሜሪካን የህዋው ጦርነት ፕሮግራም፡ የሚሣካ ከሆነ ደግሞ የኑክሌር መሣሪያ ባለቤት
ሀገሮች ቁጥር በግሃድ ከ15 እስከ 20 እንደሚያሻቅብ፡ ይገመታል።
የዓለም ህዝብ ሥጋት ግን በእነዚህ ሀገሮች፡ ቁጥር መጨመር ላይ ሣይሆን በኑክሌር
መሣሪያ ባለቤትነት፡ ዝርዝር ውስጥ የግለሰቦች፣ የቡድኖች፣ ወይንም፡ የዓለም አቀፍ
ውንብድና ድርጂቶች፡ ስም መታከሉ አይቀርም የሚል ነው። በተለይ የማፍያ ድርጂቶች፣
የኑክሌርን የጥበብ ውጤት በእጅ ለማሥገባት፡ የሚያመነቱ አይደሉም ያከሆነ እንግዴህ
በመጭው ዘመን የኑክሌር መሣሪያ ጠቀሜታ ዛቻ በሀገሮችና መንግስታት፡ መካከል ብቻ
ሣይሆን፡ በግለሰቦችና በቡድኖችም መካከል፡ ሊከናወን ነው። ወደፊት አንዱ የከፋው፡
ሚሊዮን ህዝብ የሚኖርበትን ከተማ በአንዲት ቀን ጀንበር አጥፍቷት መዋሉ ነው።
በአንድ ወቅት፡ ታዋቂው ሣይንቲስት፡ አልቭርት አንስታይን በ3ኛው የዓለም ጦርነት
ስለሚካፈሉ መሣሪያዎች ተጠይቆ በሰጠው ምላሽ፣ በ3ኛው የዓለም ጦርነት፡ ተካፋይ
ሥለሚሆኑት፡ መሣሪያዎች፡ የማውቀው ነገር የለም። በ4ኛው የዓለም ጦርነት ግን፡ የሰው
ልጅ የሚጠቀምበት፡ መሣሪያ፡ ቀስት እንደሚሆን፡ እርግጠኛ ነኝ በማለት ተንብዮ ነበር።
የአንስታይል፡ አባባል ሁለት እውነታን ታሳቢ ያደረገ ይመስለኛል። እነሱም በአንድ በኩል፡
የ3ኛው ዓለም ጦርነት፡ ከተነሣ አሁን ያለው የሰው ልጅ፡ በሙሉ፡ ከነሥልጣኔው ፡
ተድምስሶ፡ ምድር ባዶዋን፡ እንደምትቀርና በታምር፡ የሚተርፍ የሰው ዘር ቢገኝም፡
እንኳን፡ በአካልም ሆነ፣ በአእምሮ፡ የደቀቀ፣ ከስልጣኔ፣ የራቀና፡የጦር መሳሪያ ማምረት
የማይችል፡ እንደሚሆን፡ የሚያስገነዝብ ሲሆን።
በሌላ በኩል ደግሞ፡ ለዓለም ሠላም ፡የሚደረገው ጥረት ሰምሮ ከምድራችን ላይ፡አምባገነን
መሪ በጠቅላላው ተደመስሶ፡እውነተኛ፡ ዲሞክራሲ፡ ሰፍኖ ጥልና ክርክር፡ ጠፍቶ፡
የሰውልጅ፡ በመፈቃቀር፣ በመከባበር፣ በመደጋገፍ፡ ለብዙ ዘመናት፡ ከመኖር የተነሳ የጦር
መሣሪያ፡ የሚባል ነገር በመጥፋቱ፡ በአጋጣሚ ጥል ቢከሰትና፡የ4ኛው የዓለም፡ ጦርነት
ቢነሳ፡እንኳን፡ በቀሥት እስከመዋጋት፡ እንደሚደርሥ ነው፡ ትንቢታዊ መልሱን የሠጠው፡
ብዬ እገምታለሁ። ወደ እኛዋና፡ መከረኛዋ ሐገር፡ ወደ ኢትዮጰያ፡ ስንመጣ፡ በሁሉም
ዘርፍ፡ እንደካሮት ቁልቁል፡ በማደጉና በባለ ስልጣናቱ፡ ብልግና እረገድ፡ በአለም ከሚገኙ
አምባገነን መንግስታት፡ ሁሉ፡ በከፋ ብቻ ሳይሆን፡ በሚዘገንን ሁኔታ፡ ግንባር ቀደሙን
መድረክ፡ይዛው፡ እናገኛታለን።
የህዝብን፡ ሰላምና ዲሞክራሴ መብት፡ መረገጥን፣ የፍትህ፣ እኩልነትና፣ ነጻነት፡ እነዲሁም
መልካም አስተዳድር፡ ወ.ዘ.ተ. ሞቶ መቀበርን እንዳለ፡ ትተን፡ በገንዘብ በኩል ያለውን፡
አይን ያወጣ፡ ዘረፋና ገፈፋ፡ በተመለከተ፡ በማስረጃ፡ የተደገፈውን፡ አንድ ነጥብ ብቻ፡
ለአብነት ብናነሳ። ግሎባል ፋይናንሻል፡ ኢንቴግሪት በመባል፡ የሚታወቀውና፡ በዓለም
የገንዘብ ፍሰትን፡ የሚቆጣጠረው፡ ዓለም አቀፍ ተቋም፡ ዋና ዳሬክተር፡ የሆኑት፡ ሎሜል፡
ቤልካል፡ የተባሉት ሰው፡ በአውሮፓ አቆጣጥረ 27.12.11 በእኛ አቆጣጥር ደገሞ በ17.4.
2004 ዓ.ም ፡ ከአሜሬካን፡ ሬዲዮ ጋር፡ ባደረጉት፡ ቃለ ምልልስ፡ የተናገሩት፡
ያረጋገጠልን፡ እውነት፡ በአፍሪካ፡ በብድርም ሆነ በእርዳታ፡ ወደ እየ ሀገራቸው፡ ከውጭ
ከሚገባው፡ ገንዘብ 2 እጥፍ የበለጠ፡ ባለስልጣናቱ፡ ወደ ውጭ ሀገር፡ ያስኮበልሉታል፡
በማለት። በተለይ፡ የኢትዮጵያው፡ መንግስት፡ደግሞ ከምህራቡ ዓለም፡ በብድርም ሆነ
በእርዳታ፡ከሚያገኜው፡ ገቢው፡ ከ3 እጥፍ የሚበልጠውን፡ ገንዘብ የሀገሪቱ፡ ባለስልጣናት
ወደውጭ፡ በመላክ ላይ ናቸው።
በትንሹ ለመጠቀሰም፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ፡ከ 12 ቢሊዮን ዶላር በላይ ከሀገር ወጥቷል፡
ሲሉ በአገራሞትና፡ በአዘኔታ ገልጸውታል። ያሳያችሁ እንግዲህ፡ የኢትዮጵያ፡ ህዝብ
ይልሰውና ይቀምሰው፡ በማጣቱ፣ ሕጻናት እና አረጋወያን፡ በርሀብ እንደቅጠል፡
በሚረገፉበት፣ አቅም ያለው ለስደት፡ ከሀገሩ እየጎረፈ፡ በመውጣት፡ በበርሀ፣ የአውሬ
በእውቅያኖስ፡ የአሳነባሪ፡ ቀለብ ፡እየሆነ ባለበት፡ ሴት እህቶቻችን በአረብ ሀገራት
እየተሰቃዩና እያለቁ ባለበት፡ ዛሬ የዚህ ወሮበላ ስርአት መሪዎች፡ ከ12 ቢሊዮን ዶላር፡
በላይ ከሀገር በማስኮብለል፡ የውጭ ሀገራት ባንኮችን፡ በማጨናነቅ ላይ ናቸው።
ይህ ገንዘብ፡ ለሀገር ውስጥ ፍጆታ ቢውል፡ የስንት ወገናችንን ህይወት፡ ከሞት ባተረፈ፣
የስንት ወገናችንን፡ ኖሮ ባደላደለ ነበር። እነዚህ አረመኔዎች የቻሉትን በመዝረፍ፡ ከሀገር
ካስወጡ በሗላ፡ የሚተርፍ ከተገኘ ደግሞ፡ የሚውለው፡ ለሀገር ልማት፣ ለትምህርትና
ለጤና ወ.ዘ.ተ. ሳይሆን ፡ ለስልጣን መደላድል፡ ጠባቂው፡ ለመከላከያ፣ ለፖሊስና
ደህንነት፡ ነው። ለምሳሌ 12.06. 2012 ለፓርላማው የቀረበው፡ የ2005 ዓ.ም. የበጀት
አመት የገንዘብ አመዳድብን፡ ለአብነት ወስደን፡ ብናይ፡
1. ለትምህርት፣
2. ለጤና፣
3. ለግብርና ልማት፣
4. ለኢንዱስትሬና ከተማ፡ልማት፡
ድምር፡ 2 ቢሊዮን የማይሞላ ገነዘብ ሲመደብ።
ለመከላከያና፡ ደሕንነት፡ ለፓሊስ ወ.ዘ.ተ ለአፋኝ ተቋሞች የተመደበው ግን 10.ቢሊዮን 112
ሚሊዮን ብር ነው። ያሳያችሁ ወገን ለ4 ታላላቅና ዋና ዋና ለሚባሉ ተቋማት 2 ቢሊዮን
ያልሞላ ገንዘብ ሲመደብ ለ1 የጥፋት ተቋም ደግሞ 10. ቢሊዮን 112 ሚሊዮን ብር ነው
የተበጀተው፡፡ ይህ እንግዴህ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ፡ የሚፈጸምበትን የግፍ ግፍ በቀላሉ
የሚያሳየን ይመስለኛል። ይህብቻ አይደለም፡ ወያኔ ሀገራችነን ወደብ አልባ አድርጎ፡
ሲያበቃ ለጅቡቲ የወደብ ኪራይ፡ በቀን 3 ሚሊዩን ዶላር ይከፍላል፡ ጅቡቲ በዚህ
አታቆምም በእየጊዜው ትጨምራለች ባለፈው አመት በአንድጊዜ 25 በመቶ ጨምራለችና
በዚህ ትረጋለች ብለን ብናሰብ እንኳን ለወደብ ኪራይ በወር 90 ሚሊዮን ዶላር ይወጣል
ማለት ነው፡ ይህ በአመት ሲሰላ 1.08 ቢሊዮን ዶላር ይሆናል።
የኢትዮጵያ ህዝብ ግን በቀን አንድ ዳቦ አጥቶ፡ በእራብ እየርገፈ ነው። ወያኔ ሀገራችነን
ወደብ አልባ አድርጎ፡ በሌሎች ወደቦች መጠቀም እችላለሁ የሚለውን ቅዠት ስናየው
ደግሞ የእብዶች ጭዋታ አይነት ነው። ምክናያቱም ከሌሎች ሀገራት ወደብ በነጻ ሊገኝ
ካለመቻሉም በላይ። በትራንሰፖርት ረገድ የሚወጣውን ገንዘብ ግምት ውስጥ ያላስገባ
ነውና ነው፡የወያኔ ስሌት። ለምሳሌ መንግስት ተብዬው፡ እጠቀምባቸዋለሁ የሚላችውን
ወደቦች እርቀት በኪሎሜትር እንደሚከተለው እንይ።
1. ከአዲስ አበባ፡ እስከ ኬንያ ሞብአሳ ድርስ 1804 ኪሎ ሜትር፡
2. ከአዲስ አበባ፡ እስከ ፖርት ሱዳን ድርስ 1696 ኪሎ ሜትር፡
3. ከአዲስ አበባ፡ እስከ ፖርት ሞቃድሾ ድርስ 1520 ኪሎ ሜትር፡
4. ከአዲስ አበባ፡ እስከ ፖርት በርበራ ድርስ 943 ኪሎ ሜትር፡
5. ከአዲስ አበባ፡ እስከ ፖርት ጅቡቲ ድርስ 910 ኪሎ ሜትር፡ ሲሆኑ
ከአዲስአበባ አሰብ ድርስ ግን 624 ኪሎ ሜትር ብቻ ነው እርቀቱ። እንግዴህ ወያኔ
አሰብን ለኤርትራ ባይሰጥ ኖሮ ከወደብ ኪራይ ነጻ ከመሆናችንም በላይ የጊዜና የሰው
ጉልበት ብክነትን መከላከል ብቻ ሳይሆን ለነደጅ የሚወጣውን፡ ገንዘብ በመቆጠቡ
እረገድም ቀላል የሚባል አልነበረም። በአንድ ወቅት ነፍሱን አይማረውና አቶ መለስ
ዜናዌ፡ ለኢትዮጵያ ወደብ እንደማያስፈልጋት ሲገልጽ በንጽጽር የጠቀሳቸው ያለወደብ
የሚኖሩ ሀገራት፡ ከዚህ የሚከተሉት ነበሩ።
1. 10,500,000 ህዝብ ያላትን ቼክ ሪፑፕሊክን፡
2. 10,000,000 ህዝብ ያላትን ሀንጋሪ
3. 15,263,417 ህዝብ ያላትን ማላዊን
4. 2,670,966 ህዝብ ያላትን ሞንጎሊያን
5. 9,997,614 ህዝብ ያላትን ሩዋንዳን
6. 7,344,847 ህዝብ ያላትን ሰርቢያን
7. 1,184,936 ህዝብ ያላትን ስዊዘር ላንድን
ወ.ዘ.ተ. ነበር በምሳሌነት ያስቀመጣቸው ያሳያችሁ ወገኖቼ በ90 ሚሊዮን የሚገመተውን፡
የኢትዮጵያን ህዝብ ያወዳደረው 20 ሚሊዮን እንኳን የማይሞላ ህዝብ ካላቸው ሀገራት
ጋር ነው። ለዚያውም እነዚህ ከላይ የተጠቀሱ ሃአገራት ከጎረቤት ሀገር ተኮናትረው
በሚጠቀሙበት ወደብ የሚከፍሉት ገንዘብ ተመጣጣኝ ከመሆኑም በላይ እርቀቱም በጣም
እረጅም የተባለው ከ2 እስከ3 መቶ ኪሎ ሜትር ብቻነው። እዚህ ላይ እንግዴህ እኔን
እንደሚገባኝ በአቶ መለስ እምነት የኢትዮጰያ ህዝብ ማለት፡ የትግራይን ህዝብ ብቻ ነው
ማለት ነው። ምክናያቱም ከላይ ከተዘረዘሩ ሃገራት የህዝብ ቁጥር በታች ያለው የትግራይ
ህዝብ ከመሆኑም በላይ እሱም እንኳንም ካንተ ተወለድሁ ያለው የኢትዮጵያን ህዝብ
ሳይሆን የትግራይን ሕዝብ ነበርና ነው።
ለማጠቃለል
ጠቅለል ለማድረግ ያህል ከላይ እያየነው የመጣነው በዓለማችን ላይ እስካሁን የደረሰውን
የሰውና የንብረት ውድመትና ለወደፊትም ዓለም እየገሰገሰችበት ያለውን የጥፋት መንገድ
እንዲሁም የሃገራችንን ሁኔታም ነው። የዓለምን ስጋት ከዓለም ህብረተስብ ጋር
የምንጋራው ጉዳይ ስለሆነ አጠቃለይ ግንዛቤ ከጨበጥንበት በቂ ስለሚሆን እንተወውና
ወደሀገራችን እናተኩር።
በበኩሌ ዛሪ ኢትዮጵያ ከመቸውም ጊዜ በበለጠ ከድጡ ወደማጡ እያመራች ይመስለኛል፡
ወደብ አልባ ያደረጋት፣ ለዘመናት በደሙ ፍሳሽና ባጥንቱ ክስካሽ ታፍራና ተከብራ
እንድትኖር ያደረጋትን የመከላከያ ሰራዊቷን በመበተን ሰራዊት አልባ ያደረጋት፣በሀገሪቷ
ላይ ተፈጥሮም ሆነ ሰው ስራሽ፡ ችግሮች ቢከሰቱ ለተወሰነ አመት ለመላው ህዝባችን
ልብስና ቀለብ እንዲሆን ታስቦ ከምኒልክ ጀምሮ በጠቅላይ ግምጃቤት ሲጠራቀም
የኖረውን፡ ወርቅ፣ አልማዝ፣ እንቁና ልዩ ልዩ ማህድናትና የከበሩ ድንጋዮችን ወደ
አልታወቀ ቦታ ያስጋዘው፣ ዙሪያዋን እንደዳቦ እየቆረሰ ለጎረቤት ሃገራት ሲያድላት
የኖረው፣ እንደ ጭድና ጭቃ ተዋህዶ የኖረውን ህዝብ በዘርና በሀይማኖት ከፋፍሎ
ሲያፋጀው የኖረው፣ በአማራ፣ በአኝዋክ፣ በሱማሌ፣ በሲዳማ፣ በኦሮሞ ወ.ዘ.ተ. ወገናችን
ላይ ለ21 አመት የዘር ማጥፋት ዘመቻ ያካሄደው፡ በኢንቨስትመንት ስም ነዋሬውን
አስገድዶ ከቀየው በማፈናቀል መሪቱን ለባዳን በማደል ህዝባችንንና ሀገራችንን በእጅ አዙር
ቅኝ ግዛት ስር የጣለው፣ በሙስሊሙ ማህበረሰብ እምነት ጣልቃ በመግባት ህዝብን
የሚገድለውና የሚያስረው፣ አድባራትና ገዳማትን ያስቃጠለው፣ ያስፈረሰው፣ ታቦታትና
ነዋየ ቅድሳትን ያዘረፈው፣ የእሱ ደጋፊዎች በቁንጣን ሲጨነቁ ሌላውን ህዝብ በእራብ
እንዲረግፍ ያደረገው፡ ተተኪው ትውልድ በአካልም በአምሮም የወደቀ እንዲሆን በገዳይ
የትምህርት ፖሊሲው ያሸመደመደውና በጫትና በአሽሽ እነዲደነዝዝ ያደረገው፣እረ ስንቱ
ተቆጥሮና ተዘርዝሮ ያልቃል በአጠቃላይ ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር ከዓለም ካርታ
እንድትፋቅና እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ በማለት አፍ ሞልቶ ደረት ነፍቶ የሚናገር ዜጋ ጨርሶ
እንዳይኖር ለ21 አመት ሌት እንቅልፍ ቀን እረፍት በማጣት ሲሰራ የኖረው ከሃዲው፣
ባንዳው፣ ነፍሰ ገዳዩና የጥፋት መልዕክተኛው መለስ ዜናዊ ፈጣሪ ነፍሱን ለገሃነመእሳት
ይዳርጋትና ሲሞት፡ ትናንትም ለመለስ ባሽከርነት ሲያገለግል የነበረው ሃይለማርያም
ደሳለኝ ያለምንም ወሳኝነት ሚና ስሙን ይዞ እንዲቀመጥ በማድረግ በጀርባ 4 የህዋሃት
ጉምቱ ጉምቱ ሰዎች ማለትም ስዩም መስፍን፣ ብርሃኔ ገ.ክርስቶስ፣ ጌታቸው አሰፋና ሳሞራ
ዩኑስ የመንግስትነቱን ስልጣን ተቆጣጥረውታል።
ለዚህም ነው ሃገራችን ከድጡ ወደማጡ እየሄደች ነው ያልሁት፡ አንድ አምባገነን፣ አንድ
ዘራፊና ገፋፊ አንድ ጨካኝ አረመኔ ቢሞት 4 ምናልባትም ከእሱ ቢከፉ እንጅ የማይሻሉ
ተተክተዋልና ነው፡፡ መፍትሄው አምርሮ በመታገል የወያኔን ስራት ማስወገድ እንጅ
የመለስ ሞትና የሃይለማርያም ተተካ መባል የሚያመጣው ለውጥ የለም። ጠቅላይ
ሚኒስተርም ሆነ ምክትል ተብለው የተቀመጡ ሰዎች ከመናገራቸው በቀር ለብሶ
ከተቀመጠ የወግ ዕቃ የሚለዩበት መንም ነገር የለም። ትናንትም ለምን ማለትን
ሰለማያውቁና እንደሰው የህሌና እና የመንፈስ ጉልበቶቻቸው ተጋግዘዉ ያዘዟቸውን
ሳይሆን እንደቴፕ ካሴት በመለስ የተሞሉትን የሚናገሩ፣ የሚሰሩ በመሆናቸው ነው
ለነበሩበት ቦታ የበቁት ዛሪም አዲስ ወኔና በራስ መተማመን የሚባል ነገር ድንገት
ስለማይመጣ በእነ ስዩም መስፍን እየተዘወሩና እየተሞሉ በበቀቀን እነታቸው ይቀጥላሉ።
በበኩሌ በዚህ ከይሲ ሰው ሞት ስደሰት አሟሟቱ ግን አናዶኛል፡ ምክናያቱም መለስ
መሞት የነበረበት እንደተግባር አምሳያወቹ ማለትም እንደ ናፖሊዮን በእስር ማቅቆ፣ እንደ
ቄሳር ኔሮ በጩቤ ተወግቶ፣ እንደ ሂትለር በገዛ ሽጉጡ ተመትቶ፣ እንደ ሞሶለኒ እንደ
እብድ ውሻ በዱላ ተደብድቦና ተዘቅዝቆ ተሰቅሎ፣ እንደ ሳዳም ኡሴን የሰራውን ግፍ ሁሉ
ለምን እንደፈጸመው ከተናዘዘ በሗላ ተሰቅሎ፡ እንደ ጋዳፊ በጥይት ጭንቅላቱን ተበርቅሶ፡
መሞትና በመጨረሻም እንደ ጆሴፍ ስታሊን መቀበሪያ እንኳን አጥቶ በውርደት ነበር
ማለፍ የነበረበት። አሁን ግን ባሳረፈበት የግፍ አገዛዝ ለ21 አመት ሲያለቅስ የኖረው ህዝብ፡
በካድሬ ተገድዶ ዛሬም እንዲያለቅስ ከመደረጉም በላይ ጨርቅ እያለ ያጣጣለዉ
የኢትዮጵያ ባንዲራ ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ተደርጎ፡ አምርሮ ይጠላትና ለጥፋቷም
አጠንክሮ ሲስራባት የኖራትን ሀገር አፈር በክብር ቀምሷል። መለስ በህይወት እያለ
ኢትዮጵያውያንን በጥይት በማስጨፈጨፍ የዘር ማጥፋት ወንጀል ሲፈጽም ኖሮ ሲሞት
ደግሞ ህዝብ ተገድዶ እንዲያለቅስ በመደረጉ በሕይወት ያሉ ባለስለጣኖቹ የአእምሮ
ጀኖሳይድ እንደፈጸሙና በህግ ፊትም ከፍተኛ ወንጀል እንደሆነ ነሀሴ ወር 2012 መጨረሻ
አካባቢ የስነ ልቦና ተመራማሪዋ ዶክተር አበባ ፈቃደ ከአንድ ሪዲዮ ጣቢያ ጋር ባደረጉት
ቃለምልልስ አስረግጠው ነግረውናልና ቀኑ ሲደርስ በህዝብ ላይ የአእምሮ ጆኖሳይድ
ወንጀል የፈጸሙት የስርአቱ ካድሬዎች ይጠየቁበታል።
እዚያ ለመድረስ ግን ከዚህ በሗላ ከፍሲል በዘርና በሀይማኖት፡ ዝቅ ሲል በደርጀት
እየተቧደን እንደ ሰናኦር ግንበኞች፡ በአመለካከት ተለያይተን፣ በሀሳብ ተራርቀን እንደ
ዳይኖሰር እርስ በረስ መባለቱን በማቆም በአንድነት፣ ለአንድነት ተሰልፈን የወያኔን የጥፋት
መልክተኛ ቡድን ሞት የውሻ ሞት የምናደርግበት ቀኑ ዛሬ ሰአቱም አሁን ነው።
ሞት ለወያኔ!!!!!
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!!!
ማተቤ መለሰ ተሰማ

No comments:

Post a Comment