Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Monday, 4 June 2012

በአፋር ክልል በተነሳ ግጭት ከ10 ያላነሱ ሰዎች ተገደሉ

ግንቦት ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የአካባቢው ተወላጆች ለኢሳት እንደተናገሩት ጥቃቱን የፈጸሙት በሶማሊ ክልል በሚደገፉ የኢሳ የልዩ ሀይል አባላት ናቸው። ትናንት ከጧቱ 12 ሰአት ላይ በመደበኛ ሁኔታ የታጠቁ ልዩ ሀይሎች 10 ሰዎችን መግደላቸውን ነዋሪዎች ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ  እንደሚሉት መንግስት ጥቃቱ ሲፈጸም ሊታደጋቸው አልቻለም (2፡45-03፡08)። ጥቃቱን የፈጸሙት ሀይሎች በሶማሊ ክልል እና በጂቡቲ መንግስት የሚደገፉ ልዩ የኢሳ  ሀይል ታጣቂዎች መሆናቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች አሁንም በከፍተኛ ፍርሀት ውስጥ መውደቃቸውን እና ፌደራል ፖሊስ አባላት ሊከላከሉላቸው አለመቻላቸውን  ይናገራሉ::
በጥቃቱ 5 ሰዎች ቆስለዋል፣ አንደኛው በከባድ ሁኔታ በመቁሰሉ ራሱን እንደማያውቅ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
የአፋር ሂውማን ራይትስ ድርጅት በክልሉ እየተፈጸመ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በማውገዝ መግለጫ አውጥቷል። የድርጅቱ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ጋአስ አህመድ  በተለያዩ ዞኖች የሚፈጸሙት የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ከስኳር ልማትና ከማእድን ጋር የተያያዙ መሆኑን ጠቅሰው፣ በትናንትናው እለት ብቻ 21 ሰዎች መገደላቸውን ገልጠዋል ።
አቶ ገአስ የኢትዮጵያ መንግስት ታጣቂዎች ግድያዎች ሲፈጸሙ ቆመው መመልከታቸው አገዛዙ ከድርጊቱ ጀርባ እጁ እንዳለበት የሚያመለክት ነው::
አቶ ገአስ እንደሚሉት ከጨው ምርት ጋር በተያያዘ በተነሳ ውዝግብም ሁለት ወረዳዎች ተፋጠው ይገኛሉ።
በአፋር ጉዳይ ስለተገደሉት ሰዎች የክልሉም ሆነ የፌደራል መንግስት ባለስልጣናት የሰጡት አስተያየት የለም።

No comments:

Post a Comment