Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Tuesday 5 June 2012

ግንቦት 20ን ለማክበር 120 ሚሊዮን ብር መውጣቱ ተጠቆመ


ኢህአዴግ 21ኛውን የግንቦት 20 በዓል ለማክበር ከፍተኛ ገንዘብ ማውጣቱን የውስጥ አዋቂ ምንጮች ለዝግጅት ክፍላችን ገለጹ፡፡ ምንጮቹ እንደሚሉት ኢህአዴግ በዓሉን ለማክበር 120 ሚሊዮን ብር በላይ አውጥቷል፡፡ ምንጮቻችን አክለውምበዓሉ በየአባል ድርጅቶቹና በየመሠረታዊ ድርጅቶች እንዲከበር ተደርጓል፡፡ በዝግጅት ላይም የጋባዥና ተጋባዥ ኮሚቴ ተዋቅሮ በጀት ተመድቦ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በዚሁ መሠረት በዓሉ በገንዘብ ብዛትና ለጥቅም ሲባል በተሰበሰቡ ሰዎች እንጂ በዓሉን በእምነት አላከበሩም፡፡ብለዋል፡፡ አያይዘውም በተለይ የኦሮሚያ የግንቦት 20 በዓል የተከበረው በከፍተኛ የገንዘብ ወጪ እንደሆነ ይገልፃሉ፡፡ እነዚህ ታማኝ የዜና ምንጮች እንደሚሉትሰዎችን ጋብዞ ላመጣ አንድ ብር፣ ለፎረም አባል 600 ብር፣ ለቀበሌ ቀስቃሽ 300 ብር፣ ለሰልፈተኛ መቶ ብር እየተከፈለ የተሰበሰበ ነው፡፡ ለዚሁ ማስፈፀሚያ የሚውል ለኦሮሚያ ብቻ 30 ሚሊዮን ብር መመደቡንያስረዳሉ፡፡ እነዚህ የውስጥ አዋቂዎች እንደሚሉትግንቦት 20 እንዲከበር ከፍተኛ ገንዘብ ቢወጣበትም ተሰብሳቢዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ሥርዓት እየሆነ በመጣው ሙስና፣ የመልካም አስተዳደር እጦትና ኦሮሚያ ከሞግዚት አስተዳደር አለመውጣት ቅሬታ ሲያሰሙ ተደምጧል፡፡ እንዲያውም ለሥራ ነው እንጂ ኦሮሚያ መኖሬ፣ የከፋኝ ዕለት እማ ትግራይ ነው አገሬየሚል ግጥም ሲነገር መደመጡን በሥፍራው የነበሩት ምንጮቻችን ገልፀዋል፡፡ በሌላ በኩል ግንቦት 20 በዓል ማለዳ ላይ በመስቀል አደባባይ ለማክበር የተደረገው ጥረት አለመሳካቱን ሪፖርተራችን ዘግቧል፡፡ በዕለቱ እስከ ሦስት ሰዓት ድረስ በመስቀል አደባባይ የነበረው ህዝብ 300 ሰው የማይበልጥ ሲሆን እነሱምአቶ መለስ ይመጣሉ ውጡ ተብለን መተን በፀሐይ ያስደበድቡናልበማለት ተበሳጭተው ተበትነዋል ሲል ዘግቧል፡፡ መንግስት ለቦንድ ግዢ የሰራተኞችን አቅም ያላገናዘበ የግዳጅ ሽያጭ እያደረገ ባለበት ወቅት ስልጣን የያዘበትን ቀን ለማክበር ለአንድ ቀን ይህን የሚያክል ወጪ ማውጣቱ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

No comments:

Post a Comment