Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Saturday, 9 June 2012

ከኣዲ ዳኣሮ በሮ በሮ…

Dawit Abebe - Oslo, Norway
ዳዊት አበበ / ኦስሎ ኖርዌይ
የሚሚ ስብሃቱንና ዉሪዎቿን የጠረቤዛ ዝርጥጫ ዉይይት ካደመጥኩ በኋላ ሁለት ነገሮች ወደ አይምሮዬ  መጡ ፡፡ አንድም የዉሻን ባህሪ መመርመር ፣ በሌላ በኩል ደግሞ የአበበ ገላውን ማንነት መፈተሽ ፡፡
ከውሻ ባህሪ ልነሳ ! ፡፡ ስለዉሻ ባህሪ ይህንን ስፈትሽ አገኘሁ ፡፡
Dogs bond with the person who feeds them & interacts with them most.
“Loyalty” is a human concept. Dogs do not think in terms of “loyalty”….they think in terms of, “Who’s got my food? Who’s going to pet me?” They are opportunistic animals and largely form attachments with people who offer the most “benefit”….be it food, work or attention that they desire.
አዎ ! ታማኝነት ለሰው ልጅ የሚሰጥ ባህሪ ነው ፡፡ ዉሻ ደግሞ ተአማኒነት የሚል የሰው ልጅ ምግባር ሳይሆን ያለው ! የሱ ታማኒነት የሚገለጸው በሆዱ ብቻ ነው ፡፡ ጌታውን የሚያውቀው ፣ ሆዱን እስከሞላለት ድረስ ብቻ ነው ፡፡ ዉሻ የአድርባይነት ባህሪ የተላበሰ ፥ ጥቅሙን እስከ-አሟሉለት ድረስ ብቻ ጭራውን የሚቆላ እንስሣ ነው ፡፡
‘’ ሚሚ ስብሃቱ የማሽላ ሳቅ እየሳቀች ‘’ በዝርጥጫ ጠረቤዛዋ ላይ የሰበሰበቻቸውን  ‘’ችሎ ማደሮች’’ ! ማስለፍለፍ ጀመረች ፡፡የአህያዋ ፍልስፍና እኮ ነው ! እኔ ከሞትኩ… እኔ ! እኔ ! የተስፋ መቁረጥ ! የግባተ መሬት … ቢሞቱ ስልጣን አይዟት አለች እርር እያለች ፡፡
‘’ ቤን ‘’  ጃስ ! ስትለው ! ችሎ ማደር ቀጠለ ! አቶ መለስ ደንግጠው ነበር አሉ ? አቶ መለሰን አያውቋቸውም ነበር ማለት ነው ? መድፍ ሲያገላብጡ የነበሩ ሰውየ ስማቸው ሲጠራ ዞር ስላሉ ! ሚሚ ስብሃቱ በማሽላ ሳቅ ተብሰከሰከች ! በጌታዋ እጢ መውደቅ እያረረች ፡፡ ቤን ቀጠለ ! አንዳንድ ጊዜ ሪያሊቲን እንወቅ ! የመድፍ ጀርባ ተደግፈው መጽሃፍ ያነቡ የነበሩ ሰውን አበበ በሚሉት ሰው ይደነግጣሉ ብሎ ማለት ዘበት ነው ፡፡ ደግሞ ዳግማዊ ቴዎድሮስ እያሉ ሲጠሩት አለ…. ችሎ ማደር አንድ ፡፡ ችሎ ማደሮች ተራ በተራ ቀጠሉ ፡፡
አንድ ጊዜ ስዩም መስፍንን ዲሲ ውስጥ በቦክስ መትቶት የነበረው ሰው ቀጠለ ፡፡ አሁን የክፍያ ረብጣ ስለዘነበለት ፣ ከሰዉነት ወደ ችሎ ማደርነት የተለወጠው ሰው ያቅሙን ተንደፋደፈ ፡፡ ሚሚ ተሳለቀች ! ለወጭቷ አደረች ፡፡ ለተሰፈረላት ድርጎ የውሻ ጩኽቷን ጮኽች ፡፡ ትንሽ የስኒ ማዕበል ፈጥራ ! ለቤተ መንግሥት ለተቀኘችው ቅኔ ፟- የታክስ ማስቀነሻ የከተፎ ሥራ ሠራች ፡፡እንደሠራ አይገድል አሉ እማማ ሸዋረገድ ገድሌ !
የአቶ መለስ ጀግንነት በዶክተር  አረጋዊ በርሄ ሲፈተሽ !
ሲሳይ አጌና እየኮረኮረ ጠየቃቸው ፡፡ ዶክተር አረጋዊ የመለሰን የጦር ሜዳ ውሎ ወደኋላ ሄደው አስታወሱ ፡፡ መለስ ! ‘’ኮዳ ትራሱ ’’ ሳይሆን ጀርባው እንደ-አህያ በሸክምና በጀሪካል ውሃ መላላጡን ነው እኔ የማውቀው እንኳን የጥይት አረር ሊያቆስለው  አሉ ፡፡ ምን ማለት ነው ? አለ ሲሳይ ዝርዝሩን ለማግኘት ፡፡ በተላከበት በጀግንነት ሄዶ የማይመለስ  ! ገላው ያለቀ ነው በቅጣት አሉ፡፡ ቤን ! ይሰማል ?  እሳቸው እንኳን ታንክ ሊደገፉ   ጀሪካል ሲደፉ ነው የኖሩት ሰማህ ! ከአብሮ አደግህ አትሰደድ ነው ፡፡
አድዋ ባንክ እንዲዘርፉ ቢላኩ – በሸሽት ያፈተለኩ ! ሽሬ ኣዲ ዳኣሮ ‘ ላጥ ያሉ  እንደ ዶሮ ! ናቸው እንኳን መድፍ ሊያገላብጡ ፡፡ ይሰማል ሚሚ ስብሃቱ ?
የአበበ ገላውን ጀግንነትና ጋዜጠኝነት ለተጠረጠራችሁ የአቶ መለስ ‘’ ችሎ ማደሮች ‘’ !
ጊዜው የሠለጠነ ነው ! አንድ ጉግል የሚል መስመር አለ ! መጀመርያ የአንችን ስም አስገቢና ጎልጉል በይው፡፡ ሚሚ ሰሞኑን በአንድ ጸሃፊ መከሰስ እንዳለብሽ ከተጻፈ ጽሁፍ በስተቀር ስምሽና ገድልሽ ቢፈለግም አይገኝ፡፡ በየትኛው ሞራልሽ ነው የሚያበላሽን ጌታሽን ስም ለማዳን ስትይ ! የአበበ ገላውን የሙያ ብቃት ልትጠይቂ የቻልሽው ? ፡፡ እርግጠኛ ነኝ አሳዳሪ ጌታሽ እንኳ ሳያፍርብሽ የሚቀር አይመስለኝም ፡፡ አይ ! ቡቺ ! አበዛችው ! ጭራሽ አስፎገረቺኝ ሳይልሽም አይቀር፡፡ሳሙኤል ፍቅሬም ፥ ዮሴፍ ግዛቸውም፥ቢንያም ከበደም እንዲሁ እስቲ ገድላችሁን ዳሽ ውስጥ አስገቡና ፈትሹ ዳሽን ባንክ ውስጥ አላልኩም .. የምታገኙት መልስ -Dogs do not think in terms of “loyalty”….they think in terms of, “Who’s got my food? ነው፡፡

No comments:

Post a Comment