Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Thursday 30 August 2012

“ቴዲ ለመለስ ነጠላ ዜማ ለመስራት ሀሳብ የለውም”






ታዋቂው አርቲስት ቴድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የሟቹን /ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት አስመልክቶ ነጠላ ዜማ አዘጋጅቷል መባሉን የድምፃዊው ማናጀርና የአዲካ ኮሙኒኬሽን ሚዲያ ማናጀር ከእውነት የራቀ ነው ሲሉ አስተባበሉ፡፡ ባሳለፍነው ሳምንት ነሐሴ 15 ቀን 2004 . አቶ መለስ ከዚህ አለም በሞት የመለየታቸውን ዜና መንግስት ይፋ ካደረገ በኋላ ላለፉት ሰባት ቀናት ብሔራዊ ሀዘን መታወጁን ተከትሎ ታዋቂው አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) የአቶ መለስ ዜናዊን ሀዘን ምክንያት በማድረግ ነጠላ ዜማ ለቋል የሚሉ መረጃዎች ሲሰራጩ ሰንብተዋል፡፡

ከዚህ ጋር በተያያዘም ድምፃዊው በብሄራዊ ቤተመንግስት በመገኘት ሀዘኑን ለመግለጽ በሞከረበት ወቅት በስፍራው የተገኘው ህዝብ ጩኽት በማሰማቱ ወደ ውስጥ ሳይዘልቅ እንደተመለሰ ተናግሯል፡ ጉዳዩን በማስመልከት ጥያቄ ያቀረብንላቸው የአዲካ ኮሙኒኬሽን ሚዲያ ማኔጀር ሠርካለም ታፈሰ ግን ቴዲ አፍሮ ለአቶ መለስ ምንም አይነት ነጠላ ዜማ አለመስራቱን ተናግረው ከሁለት ዓመት በፊት የሰራውን ሙዚቃ በአቶ መለስ እና በቴዲ ፎቶዎች በማጀብ የተቀናበረ ምስል በዩቲውብ ተለቆ አይቻለሁካሉ በኋላ ቅንብሩ ከቴዲ እውቅና ውጪ እንደተሰራ ለፍኖተ ነፃነት አረጋግጠዋል፡፡

የቴዲ አፍሮ ማናጀር የሆኑት አቶ ዘካርያስ ጌታቸውም ስለጉዳዩ ማብራሪያ እንዲሰጡ ተጠይቀውቴዲ ምንም አይነት ሙዚቃ አልሰራም፤ ለመለስ ነጠላ ዜማ ለመስራት ሀሳቡም የለውምብለዋል፡፡ ብሔራዊ ቤተመንግስት አጋጠመው የተባለውም ተቃውሞ መሠረት ቢስ መሆኑን አብራርተውአርብ ዕለት ቤተመንግስት ሳንገባ የተመለስነው በተቃውሞ ምክንያት ሳይሆን ለጀነራሎች የተዘጋጀ ልዩ የሀዘን ስነ ሥርዓት በመኖሩ ነውካሉ በኋላ በስፍራው የነበረው ህዝብ የአድናቆት ድምጽ ማሰማቱን ብቻ እንደሚያውቁ አስረድተዋል፡፡ አቶ ዘካሪያስ ጌታቸው ጨምረውም በትላንትናው ዕለት ቴዲ አፍሮ ብሔራዊ ቤተመንግስት በመገኘት ለቅሶው እንደደረሰ የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ አረጋግጠዋል፡፡ ታዋቂው ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ 1997 . ያስተሰርያል በሚል ርዕስ ባወጣው አልበሙ ምክንያት ከመንግስት ጋር እሰጣገባው ውስጥ መግባቱ የሚታወስ ሲሆን፣ ይህን ተከትሎ በአወዛጋቢ ክስ ከሁለት አመት በላይ በቃሊቲ በእስር ማሳለፉም አይዘነጋም፡፡

No comments:

Post a Comment