ባሳለፍነው ሳምንት የህይወት እልፈታቸውን የሰማነው የህወሃት ኢህአዴግ ከፍተኛ አመራር እና የኢትዮጵያ የቁጭ
በሉ ጠቅላይ ሚንስትር የሆኑትን የአቶ መለስ ዜናዊን ሞት አስመልክቶ ከፍተኛ እና ሳዛኝ ዜና ከሃገራችን የደረሰን
ሲሆን በደጋፊዎች እና በተቃዋሚዎች መካከልም ከፍተኛ ቅራኔን እየፈጠረ ነው ። በተለይም የጠቅላይ ሚንስትሩን ሞት
የዜናን እወጃ ስመልክቶ እንኳን ሞተ ጨካኝ ነበር በማለት የውስጥ ፍላጎቷን በድንገተኛ ሰሜት የገለጸችውን ወጣት
ከሜሪካ ለጉብኝት የሄደው የወያኔ ቀንደኛ ደጋፊ እየተዝናኑ ባሉበት ካፍቴሪያ ውስጥ በጠርሙስ ጭንቅላቷ ላይ
በመምታት የገደላት መሆኑን ከስፍራው የደረሰን ዘገባ ያመለክታል ።በ21ኛው ክፍለ ዘመን የፖለቲካ ልዩነታቸውን
አቻችለው መኖር ሲገባቸው በግልፍተኝነት እና በማን አለብኝነት የሚደረገው የግፍ አስተዳደር ህዝብን ከጭቆና የማያወጣ
መሆኑ ይታወቃል። ስለሆነም በዚህች ንጹህ ወጣት ላይ የተደረገውን ግፋዊ ግድያ ማንኛውም ሰው በህግ ፊት ማቆም
የህዝቡ ግዴታ ነው ሲሉ ከኢትዮጵያ ይህንን ዜና ያደረሰን ሪፖርተራችን ጠቁሞአል ፣በሌላም በኩል ለማጣራት ባደረግነው
መሰረት ገዳዩ ጉዳዩ በፍርድ ቤት እየታየ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ፣የዋስትና መብቱም ተከልክሎ ጉዳዩን በማረሚያ ቤት
እንዲከታተል የሚል መረጃ ደርሶናል ሆኖም ግን ይህንን ፣የቅርብ ደጋፊ የሆነ ወዳጃቸውን በነጻ ሊያሰናብቱት እና
በሚስጥር ወደ መጣበት አሜሪካ ሊመልሱት ይችላሉ እና ጥንቃቄ መውሰድ ይገባል ሲሉ አክለው ገልጸዋል ። በሌላም በኩል
በሃገሪቱ የመንግስት መስሪያ ቤቶችም ሆኑ የግል ድርጅቶች በግዳጅ ከመዘጋታቸውም በላይ የከተማዋ ጸጥ እረጭ ማለት
ይበልጥ በህብረተሰቡ ላይ የፍርሃት ድባብ አጥልቷል ።እስካሁንም ምንም አይነት የገበያ እንቅስቃሴ አይታይም ።
የመንግስት ባልሰልጣናት በተለያዩ አካባቢዎች የለቅሶ ድረሱ ጥሪአቸውን እያቀረቡ ነው ።
No comments:
Post a Comment