Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Thursday 4 October 2012

ኦህዴድ ውስጡን እየታመሰ ነው!

ህወሃት እንደበሬ ጠምዶ በኦሮሞ ህዝብ ላይ ለቆበት የነበረው ኦህዴድ፤ “ካሁን በኋላ ህዝቤን ኣላስንቅም፣ ኣላስመዘብርም፣” በማለቱ የምንጠራ ዘመቻ ጀምሮበታል። የኦህዴድ ኣባላት በህወሃት ተደልለው ወይም ፈርተው ወንድሞቻቸውን ይበሉ ይሆን? መቼም ወያኔ ደፍሮ ጦሩን ኣያዘምትም። የሚልከው ያው የኦሮሞ ልጅ የኦሮሞ ልጅን እንዲበላ ነው። ቁርጥ ቀን እየመጣች ነው።
(ሰንደቅ ጋዜጣ)፦ የኢህአዴግ መተካካትን ተከትሎ በኦሮሞ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ድርጅት (ኦህዴድ) ውስጥ አነጋጋሪ ስሜት ፈጥሯል። ድርጅቱ በኢህአዴግ አመራር መተካካት መሠረት ከፊት አለመምጣቱ ድርጅቱ አመራር ባለማብቃቱ ነው የሚሉ ትችቶች እየተሰነዘሩ ነው።
አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈጉ የድርጅቱ ምንጭ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት በኦነግ አስተሳሰብ የተወጠሩ መተካካቱን ባልሆነ መስመር እያራገቡት ነው ብለዋል። አራቱ ድርጅቶች አንድ ግንባር ፈጥረዋል። በብሔራዊ መግባባት የተጀመረውን ልማት በማስቀጠል የሕዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የድርጅቱ ዋነኛ ዓላማ መሆኑን ተናግረዋል።
ይሄንን መተካካት የሚያራግቡ የኦሮሞ ሕዝብ እንዲገነጠል የሚፈልጉ “ጠባቦች” መሆናቸው የጠቀሱት ምንጫችን የኦሮሞ ሕዝብ ከኢትዮጵያውያን ወንድሞቹ የሚገነጠልበት አመለካከት የመሸበት ጊዜ ላይ መድረሱን ገልፀዋል። 8 ነጥብ 9 ሚሊዮን የኦሮሞ ሕዝብ ከትግራይ በስተቀር በሚያዋስኑት ክልሎች ድንበር ላይ እንደሚኖር በማስታወስ የኦሮሞ ሕዝብ ተገንጥሎ እየደማ እንዲኖር የሚፈልጉ ኃይሎች መተካካቱን እያጥላሉ ነው ብለዋል።
መስከረም 5 ቀን 2005 ዓ.ም የኢህአዴግ ም/ቤት የመተካካት ጉባኤ ባካሄደበት ወቅት የህወሓት ሥራ አስፈፃሚ አባል በሆኑት በወ/ሮ አዜብ መስፍን አማካይነት የኦህዴድ ሥራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ ሶፊያን አህመድ ለግንባሩ አመራር መጠቆማቸው ድርጅቱ በኢህአዴግ ውስጥ የእራሱን ዕጩ ማቅረብ አልቻለም የሚሉ ትችቶችን አስከትሏል። የኦህዴድ ሊቀመንበር አቶ አለማየሁ አቶምሳ እና ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ሙክታር ከድር ተዘለው አቶ ሶፊያን መጠቆማቸው ድርጅቱ ብቁ አመራሮችን አላሰለፈም የሚል ጉምጉምታን አስነስቷል።

የድርጅቱ ምንጭ ግን አቶ ሶፊያን በህወሓት ጓዶች ጥቆማ መቅረቡ ምንም አዲስ ነገር እንደሌለውና ይህም ድርጅቱም አመራር አላበቃም የሚል መልዕክት የሚያስተላልፍ እንዳልሆነ ተናግረዋል። አሁንም ቢሆን ኢህአዴግ ትኩረቱ በግለሰቦች ሳይሆን ድርጅቱ በሚመራበት የመስመር ጥራት ላይ ነው ብለዋል። መስመሩ ሕዝቡን ተጠቃሚ ማድረጉ ወይም ከድንቁርና ማላቀቁ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ ነው ብለዋል።
በድርጅቱ ባህል መሠረት የአንዱ ድርጅት አባል የሌላውን መጠቆም የተለመደና ቀላል ተግባር መሆኑ እየታወቀ፤ የኢህአዴግ ድርጅቶችን የዓላማ አንድነት በሚሸረሽር መልኩ “ኦህዴድ ተጎድቷል” የሚሉ አሉባልታዎች መሰንዘራቸው የሚጠበቅ ጉዳይ እንደሆነ ገልፀዋል። ነገር ግን ድርጅቱ ባካሄደው ተደጋጋሚ ግምገማ ይሄንኑ ጉዳይ እያጠራ መሄዱንም አስረድተዋል።
ሌሎች ምንጮች እንደጠቀሱት የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሜቴ ከመስከረም 19 ቀን 2005 ዓ.ም ጀምሮ ስብሰባ ይቀመጣል ተብሏል። የስብሰባው አጀንዳ ለጊዜው ባይገለፅም በቀጣይ ከአመራር መተካካቱና ከክልሉ ልማት ጋር በተያያዙ ጉዳዮች ሊሆን እንደሚችል ይገመታል።

No comments:

Post a Comment