The rumor that has been swirling around has been confirmed by TPLF mouthpiece. How much money did Getachew Belay bring along or has he already stashed away? Is he in the US to help other TPLF heads in case of a meltdown? Can he be investigated by the US for money laundering (stealing aid money, diverting finances gained illegally abroad...) and looting of Ethiopia?
(Reporter) -- የግል ተቋማት ሠራተኞች የማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው በላይ ከአገር እንደወጡ አለመመለሳቸውን ምንጮች ገለጹ፣ ኤጀንሲው በሥራ ገበታቸው ላይ በአጭር ቀን ውስጥ ካልተመለሱ ዕርምጃ እወስዳለሁ ብሏል፡፡
የቀድሞ የገቢዎች ሚኒስትር በመሆን ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ ጌታቸው በላይ፣ በመቀጠልም የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕውሓት) ኢንዶውመንት የሆነው ኤፈርት ምክትል ሥራ አስፈጻሚ በመሆን እስከ ቅርብ ጊዜ አገልግለዋል፡፡ ከዓመት በፊት ደግሞ የግል ተቋማት ሠራተኞች የማኅበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር በመሆን ተሾመው ነበር፡፡
በዚህ መሥሪያ ቤት ባደረጉት የአንድ ዓመት ቆይታ ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ ከግል ተቋማት ሠራተኞች እንዲሰበሰብ ያደረጉ ሲሆን፣ ድርጅቱን በሚገባ በማዋቀርና በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ እንዲሆን በማድረግም ይታወቃሉ፡፡ ይሁን እንጂ ባልታወቀ ወይም ለጊዜው ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ልጆቻቸውንና ባለቤታቸውን ይዘው አሜሪካ መግባታቸውን ምንጮች ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ፍሎሪዳ ውስጥ በመኖር ላይ እንደሚገኙ የሚናገሩት የቅርብ ምንጮች፣ ከዚህ በኋላ ወደ አገር ቤት በመመለስ በሥራ ገበታቸው ላይ የመገኘት ፍላጎት እንደሌላቸው ገልጸዋል፡፡
በጉዳዩ ላይ የሚያውቁትን እንዲገልጹልን ያነጋገርናቸው የኤጀንሲው ምክትል ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ውቤ፣ ‹‹የማውቀው በእረፍት ላይ መሆናቸውን ነው›› ብለዋል፡፡
አቶ ጌታቸው የወሰዱት የዓመት እረፍታቸውን ሲሆን የተሰጣቸው የእረፍት ጊዜ ከተጠናቀቅ ከወር በላይ ሆኖታል፡፡ ይሁን እንጂ ከድርጅቱ ኃላፊነታቸው በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ወይም ወደ ሥራ ገበታቸው ያልተመለሱበት ምክንያት እስካሁን አለመግለጻቸውን ለመረዳት ተችሏል፡፡
‹‹እስካሁን ወደ ሥራ ገበታቸው ያልተመለሱበት ምክንያት ግልጽ ባይሆንም፣ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይመለሳሉ ብለን እናምናለን፡፡ ይህ ካልሆነ ግን አስፈላጊውን አስተዳደራዊ ዕርምጃ ለመውሰድ እንገደዳለን፤›› ሲሉ አቶ ደረጀ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡
ኤጀንሲው ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲሆን፣ በዚህ ጉዳይ ላይ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ወይም ከጽሕፈት ቤታቸው ለኤጀንሲው የተላከ ነገር እንደሌለ አቶ ደረጀ ተናግረዋል፡፡
አቶ ጌታቸው በላይ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመርያ ዲግሪያቸውን ሲያገኙ ከኦስትሪያ ቪዬና በስታትስቲክስና በኢኮኖሚክስ የማስትሬት ዲግሪያቸውን ይዘዋል፡፡
ላለፉት 16 ዓመታትም በተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በማገልገል ልምድ ሲያካብቱ፣ ለአምስት ዓመታት የገቢዎች ሚኒስትር በመሆን ሠርተዋል፡፡
No comments:
Post a Comment