Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Thursday, 12 April 2012

አማራው ተማሯል፣ አማሯል፣ ግን አምርሯል?

ደመቀ ታዬ
  በዚህ አራስት  አጭር አስተያየት  ለመስጠት  ያነሳሳኝ  ሰሞኑን  አማሮች ናችሁና  ከአገራችን ውጡ፣ ወደ አገራችሁ ሂዱ ተብለው የተባሩት  ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ነው። አነዚህ ሰዎች ወይም ኢትዮጵያውያን  መባረራቸው ብቻ ሳይሆን የተባረሩትበት መንገድ ወይም ዘዴ አጂግ የሚዘገንን ነው። ውጡ ሲባሉ አቃቸውን የመሰብሰቢያ፣ የሚሸጠውን የመሸጫ፣ የሚጓዙበትን መንገድ የማዘጋጃ፣ ጎረቤቶቻቸውን የሚሰናበቱበት ጊዜ  አልተሰጣቸውም። አንዳንዶቹ  ውጡ በተባሉበት ወቅት የወለዱ ሚስቶቻቸውን ጥለው አንዲለቁ ተደርገዋል፣ ሕጻናት  ትምህርታቸውን አቋርጠው አንዲነሱ ተደርጓል። ግፋቸው አንዳይታይና አንዳይሰማ ከፍተኛ ጥረት ተደርጓል። ይህን ሰቅጣጭ ድርጊት የጠነጠኑት፣ በተግባር ያዋሉትና ያስዋሉት  ይህን ያክል ወንጀል ሲፈጽሙ በድብቅ ለማካሄድ የሚችሉ መስሏቸው በአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ተጋልጠዋል።ከዚሁ ጋር ተያይዞ ደግሞ በጣም የሚገርመውና የሚያሳዝነው ነገር በአንድ በኩል ስዎችን አያሰቃዩና አያባረሩ በሌላ በኩል ደግሞ አላየነም፣ አልሰማነም በማለት አርሳቸውን ከማታለል የማያልፍ ምጉት መሰንዘራቸው ነው። አቶ ታመነ ተሰማ የተባሉት ባለሥልጣን የተባረሩትን ሰዎች  ጫጫታና ለቅሶ አቶ አዲሱ አበበ አያሰማቸው ጋዜጠኞች ያቀረቡትን ሁሉ ማመን የለብንም፣ ችግር ያጋጠማቸው ሰዎች አሉ ስለተባለ ጉዳዩን ለማጥናት ሰዎች ልከናል ወዘተ ማለታቸው ያጋለጠውና ያሳፈረው አቶ  ታመነ ተሰማን አንደሆነ የተገነቡት አይመስለኝም:: ባጭሩ አቶ  ታመነና አጋሮቻቸው  በ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚኖሩ አይመስሉም።
ከዚህ በላይ በተመለከተው መንገድ ወጡ ቢባልም መውጣት ነበረባቸው ወይም አልነበረባቸውም  የሚለው አብይ ጥያቄ  አልተነካም። አንዚህ ሰዎች አንዲወጡ የተደረገበት ምክኒያት አማራዎች በመሆናቸው ብቻ ነው። ውጡ የተባሉትም ከአንዱ  የኢትዮጵያ ክፍለ-ሃገር  ሲሆን  ሂዱ የተባሉትም  ወድሌላው የአገሪቱ ክፍለ-ሃገር ነው። ውጡ  ወደተባሉበት አካባቢ የሄዱትም ማንኛውም የኢትዮጵያ ክፍል ለሁሉም ክፍት ነው በማለት ነው ።አነዚህ ውጡ የተባሉ ሰዎች ወደባተረሩበት አካባቢ የሄዱት በወራሪነት ተሰልፈው፣ መሳሪያ  ወልውለውና ታጥቀው አይደለም። የሄዱት ኑሯችሁን ታሻሽላላችሁ ተብለው  ከአንዱ የአገራቸው ክፍል ወደሌላው ነው። ይህ ደግሞ የአንድ አገር ዜጎች መሠረታዊ መብት ነው። አነዚህ  የተባረሩ ሰዎች የተባረሩበት አካባቢ  በውጭ ጠላት ተወረረ ቢባል ጥቃቱን ለመከላከል ግዴታ  አልባችሁ ይባሉ ይሆን? ወይም በሌላ አንጋገር አቶ ሺፈራው  ሸጉጤና ተከታዮቻቸው ሌላው የኢትዮጵያ ክፍለ በጠላት ተወረረ ቢባል የአገርን ዳር-ደንበርና ሏላዊነትን ለማስከበር ይሰለፉ ይሆን?።
አቶ ሺፈራው ሸጉጢና ተከታዮቻቸው በአቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝ መሾምና በሌሎችም ምክኒያቶች በሥልጣን  የሰከሩና አርሳቸው የዞረ ይመስላል። ሰዎች መጠጥ አንድሚያሰክርና  አርስ አንደሚያዞረ ያውቃሉ፣ ግን ከሁሉም በላይ የሚያሰክረውና አርስ የሚያዞረው  ሥልጣን  መሆኑን በውል የተገነዘቡ አይመስልም።በሥልጣን በመታወራቸው ምክኒያት በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ አማሮችንና አማርኛ ተናጋሪዎችን በድብቅ ጠራርጎ ለማስወጣት ማቀድና መሞከር የሚያመለክተው አንድም በሥልጣን መታወርን፣ አልበለዚያም ያለንበትን 21ኛ ዘመን በቅጡ አለመረዳትን ነው። ከመሠራታዊዉ የዜጎች መብት አንጻር ሲናየው ድርጊቱ ጥፋት ብቻ ሳይሆን ወንጀል መሆኑን የሕግ ምሁሩና በሩዋንዳ  አልቂት ጠበቃ የነበሩት ፕሮፈሰር ያአቆብ ኃይለማሪያም በማያሻማ መንገድ አስረድተውናል።ድርጊቱ በዓለም ሕግ ተቀባይነት የሌለው፣ በኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥትም የማይፈቀድ መሆኑ ተመልክቷል። ግን ይህ ድርጊት የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት ዓለምን ለማታለል የተጻፈ አንጂ በሥራ ላይ የማይውል መሆኑ በድጋሚ  የተረጋገጠብት  ነው።
የአማራው ሕዝብ  የኢትዮጵያን ሏላዊነት፣ ዳር-ደንበርና፣ ነጻነት በማስከበር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል፣ በዚህም ምክኒያት በውጭና በውስጥ የኢትዮጵያ ጠላቶች ዘንድ ጥርስ ተነክሶበት ኑሯል። በዚች አጭር ጽሑፍ የኢትዮጵያን የውስጥና የውጭ ጠላቶች ዓይነትና ድርጊት መዘርዘር አይቃጣም፣ ግን በተማሪዎች ንቅናቄ ወቅት በአማራው ላይ የተካሄዱትን ዘመቻዎች አጠር አድርጎ መዳሰሱ አቋራች ወይም አማራጭ የማይገኝለት ጉዳይ ነው።በተማሪዎች ንቅናቄ ወቅት የብሔረ-ሰቦች መብትና የአምራው ገዢነት የማይታለፉ የአብዮተኝነት መለኪያዎች ነበሩ። አማራው ተማሪ ከገዢው መደብ የመጣህ ነህ ተብሎ አንዳይፈረጅ በመስጋቱ አብዮተኛነቱን ለማስመስከር ከሁሉም በላይ አብዮተኛ  ሆኖ መገኘት ተገዶ ነበር። ቀደም ሲል ዋለልኝ መኮነን አሁን ደግሞ አንድሪያስ አሸቴና መሰሎቹ በምሳሌ የሚጠቀሱ ናቸው።
የኢትዮጵያ አብዮት ተቀጣጥሎ ተማሪዎች ወደ ገጠር በዘመቱበት ወቅት ብዙ አሳዛኝና አስቂኝ ሥራዎች ተከስተዋል። በአንድ ወቅት አኔ ራሴ አዋሳ አካባቢ በሚገኝ የገበሬ ማሕበር ተገኝቼ ነበር። የሄድሁት ከክፍለ-ሀገሩ አስተዳዳሪ ጋር ሲሆን ዓላምችንም የመሬት ክፍፍልን  ለመመልከት ነበር።በአንድ የገበሬ ማሕበር ውስጥ አንድ ገበሬ ከበርቴ ተብሎ ተከሶ ቀረበ። ነገሩ ሲጣራ የተከሰሰው ገበሬ የነበረው አንድ ጥንድ በሬ፣ በጥንድ በሬ የሚያርሰው አርሻ፣ አንድ የሳር ቤት፣ በቤቱ ውስጥ በተሰቀለና ጢስ በጠገበ ገመድ ላይ የተሰቀሉ ሁለት የደረቁና ጢስ የጠገቡ ቋንጣዎች፣ ቤቱ ለሰውና ለቤት ከብቶች የተከፈለ ነበር።ገበሬው ከበርቴ ነው ተብሎ የተፈረጀው በመጀመሪያ አማራ ተብሎ በመፈረጁ ነበር። ከሳሾቹ ዘማች ተማሪዎች በአብዛኛው አማራዎች ነበሩ። አኛ ተመሳሳይ ገበሬዎች አንዳሉ ነገሩ ይጣራ ብለን ብንመለስም አማራው ገበሬ ታስሮ ንብረቱ አንደተወረሰ ሰማን። ያ ድሃ ገበሬና ቤተሰቡ በዚህ መንገድ ተበታትነው የደረሱበት ሳይታወቅ  ቀረ። ይህን ክስ ያቀረቡትና ለገበሬው መታሰርና ንብረት መዘረፍ በጥብቅና የቆሙት አብዛኛዎቹ አማራዎች ነበሩ።ይህን ሳስታውስና አነ አንድሪያስ አሸቴ የሚያደርጉትን ስመለከት አማራው ተማሯል፣ አማሯል ግን በውነት አምርሯል? የሚለው ጥያቄ ያስጨንቀዋል።
በቅርቡ በደቡብ ክፍለ-ሃገር በተከሰተው አማሮችን የማባረር ተግባር አንጀቱ ያረረ ወጣት አማራ የሚባል የለም አትበሉን አማራ አየተባሉ የሚባረሩ አሉና፣ አማራ የሚባል የኢትዮጵያ ክፍለ-ሃገር  የሉም አትበሉን አማራ አየተባሉ አማራ ወደሚባለው ቦታ የሚባረሩ አሉና ሲል አስጨናቂ ጥያቄዎች አቅርቧል።ወጣቱ የሚለን  አማራ የሚባል ጎሳ አለ፣ አማራ አየተባለ የሚጠራ  ክልል አለ፣ ስለዚህ ተባብረን መብታችንን አናስከብር ነው። ወጣቱን የሚያንገበግበው ንዴት ይገባኛል፣ የአማራው መብትም መጠበቅ አንዳለበት ሙሉ በሙሉ አስማማለሁ። አማራ ማነው በሚለው ላይ ግን ችግር አለኝ። አማራ የሚለው ቃል የሚገልጸው በባህል ተመሳሳይ የሆኑትን ሁሉ አንጂ በደም አንድ የሆኑ ማለት አይደለም።ስለዚህ ለአማራው መብት አንታገል ስንል ለሁሉም ኢትዮጵያውያን አንታገል ማለታችን መሆን አለበት። በዚህ መርህ ከተሰለፍና ከታገልን ትግላችን የሚያነጣጥረው በነጻነት ገፋፊዎች አማሮችና በሌሎች ተመሳሳይ ቡድኖች ላይ ይሆናል፣ መሆንም አልበት።ዓላማችን የሁሉም ኢትዮጵያውያን የዜግነት መብቶች አንዲከበሩ መሆን አልበት።
አቶ መለስ ኢትዮጵያን በአጠቃላይና አማራን በተለይ ቢጠላ አይፈረድበትም፣ ምክኒያቱም በአናቱ የጥቂት ኤርትርውያንን ጥላቻ ባባቱ ደግሞ የጥቂት ትግሬዎችን ጥላቻ ሲጋት ያደገና ለብልግናው ተወዳዳሪ የሌለው ሰው ነው። በአንድ ወቅት ፕሮፈሰር መስፍን ወልደማሪያም አንድ ኤርትራዊ አዛውንት ጋር ሲወያዩ የሚከተለውን ጥያቄ ጠይቀው ነበር።ኤርትራ ለኢትዮጵያ ነጻነት፣ ሏላዊነት፣ አንድነት ወዘት ብዙ ጀግኖችን ያፈራች ናት። ወጣቱ የኤርትራ  ትውልድ ኢትዮጵያን የመጥላት አባዜ ከየት አመጣው ብለው አዛውንቱን ጠይቃዋቸው ነበር?  ኤርትራዊ ሽማግሌ የሚከተለውን መለሱ። ወጣቱ ጥላቻን የተማረው አኛ አዋቂዎች በየቤታችን በየጊዜው ስናማ በመስማቱ ነው ብለው ነበር። መለስ በናቱም ሆነ ባባቱ ሲኮተኮት ያደገው ኢትዮጵያን አንዲጠላ ተደርጎ ነው ።  መለስ በኤርትራውያን ሲናቅ፣ በትግሬዎች ሲሰድብ የኖረ ሰው ነው። ይህን ያስተዳደግ ችግሩን አጥጥ ሙጥት አድርጎ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያውያን ላይ አውሏል።መለስ የአገር መሪ ሳይሆን የአራዳ ሌባ ለመሆን የተፈጠረና የተቀረጸ ሰው ነው። አቶ መለስ በአስተዳደግ የተበደለ መሆኑ የሚታወቀው በጭፍን ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያውያንን በመጥላቱ ነው።መለስ ዜናዊ አነዚህ አማራዎችና አማርኛ ተናጋሪዎች አንዲባረሩ ውስጥ ውስጡን መሥራቱ አሌ የማይባል ነው።
አማራው ተማሯል፣ አማሯል ግን አምሮ ተነስቷል ብሎ በሙሉ አፍ መናገር የሚቸግር ይመስላል።አያንዳንዱ አማራ የያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዜጋ መብት አንዲከበር መታገል አለበት።አማራው በግልም ሆነ በቡድን ቆርጦ ከተነሳ ለሌሎች ግለሰቦችም ሆነ ቡድኖች ጠንካራ አጋር አንጂ አንቅፋት አይሆንም።የየአንዱ ጎሳ ጠላት  ጎሳን ከጎሳ፣ ኃይማኖትን ከኃይማኖት፣ የሚያጋጨው  ስራት ነው። ይህ ስራት የሁሉም ጠላት ስለሆነ ሁሉም ተባብረው ሊነሱበት ይገባል።

No comments:

Post a Comment