Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Monday, 9 April 2012

ጭር ሲል አልወድም ያመረቀናቸው መለስ


ከዳዊት ዋስይሁን
April, 09, 2012
ስልዚህ ሰውየ እብደት ብዙ ተጽፎአል፤ አሁን ደግሞ እስቲ እኔ ልሞክር ስንቶቻችን ተመችቶን ዝም እንበል፣ ተንደላቀን በጀርባችን ተኛን፤ ሆዳችንን አሳብጠን ካሳቸው ጋር አደር ሆንን፤ ዛሬ ከኖርን ብለን ዝም አልን፣ ለዚህም ነው ይህንን ችግራችንንና ጉድለታችንን በመገንዘብ በተነጫነጭን ገዜ ሁኑ በአፋችን ጡጦ እየከተቱ እየሳቁብን ይኸው እኛ ሳንፈልጋችው 20 አመታቸው ስልን አሳቸው ከነጋሻ ጃግሬዎቻቸው እምዬን፣ ህዝቧንና መሬቷን በስመ ልማት እያመሱና ለመጪው 40 አመት ለመንገስ ዙፋናቸውን እያጸኑ ይገኛሉ ጥያቄው እስከ መቼ ነው ይህ የሚሆነው፣ በአገር ቤት ያለው ያሚከፍለው መስዋእትነት ከፍተኛ ለመሆኑ ቃሊቲንና ማእከላዊን ከውስጥ ሳይሆን ከውጭ ማየት ማስረጃ ይሆናል፣ ግፉ ከመብዛቱ የተነሳና ሰዎች ከመታጎራቸው ብዛት ማጎርያው አብጦ ሊፈነዳ ደርሷል ጥያቄው መቼነው እኛ በቃ የምንላቸው ሲሆን በውጭ ያለው ይህንን ጉድና ችግር የተገነዘበ አይመስልም እንደውም በስመ ዲያስፖራ ኢንቬስተር ክብሩንና ስብእናውን በማዋረድ ተባባሪ በመሆን የሚይረሳ ከፍተኛ ወንጀል እየፈጸመ ይገኛል።
ድሮ በየመንግዱ የምሰማው አንድ ዘፈን ነበር እሱም ጭር ሲል አልወድም የሚል ሲሆን በርግጥ ድሮ አይገባኝም ነበር አሁን ግን ከመግባትም አልፎ ዘፍኑን በተግባር የሚተሩጉሙ አብዮታዊ ዲሞክራት መሪ አሉኝ በዚህም ደስታ ይሠማኛል ልበል? ሰውየው በውነት ለመናገር ከሆነ ጭር ሲል ውቃቢያቸው እየተነሳ ስለሚጥላቸው የሳቸውን አባዜ ለማስደሰት አገር መታመስ አለበት ጠዋትም ማተም ሌሊትም ሲበሉም ሲጠጡም የሚፈልጉት ሲታመስና ሲበጠበጥ መስማትና ማየት ነው።
ለዚህም ነው ይህ የፈረደበት አገርና ህዝብ እንደፈለጉ ቢያረጉት ቢሰድቡት፣ ቢገሉት የማይረኩት ለመጣቀሻ እንዲሆነኝ ለሳቸው የዛር ማብረጃ ከቀረበላቸው ግብር ጥቂቶቹን ብገልጽ በዚሁ አመት በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ቆመንለታል እንዲሁም መንገድ መርቶ አዲስ አበባ አስገባን የሚሉትን ባለውለታቸው አርሶ አደሩን ከመሬቱና ከርስቱ በማፈናቀል መሬቱን ለህንዶች፣ ለአረቦች ለቱንኩች እንዲሁም ለቻይኖች እያደሉ እርሱን ጭሰኛ ሲያረጉ ገበሬው ከነ ቤተሰቡ ተፈናቅሎ ሲጮህ አገር ስትተራመስ መሬት የወሰዱት ባለሃብት ተብዬዎች በየቴሌቭዥን መስኮት እየቀረቡ በስውየው ደደብነት ሲደንሱ እሳቸው አራት ኪሎ ተቀምጠው ነገ ሊያፈናቅሉት ያለውን የሌላውን ገበሬ ጤፍ እየበሉ የገበሬውን ጫጫታ ጫት እየቃሙ ይዝናኑበታል፣ በነጋዴው መንደር በቀረጥና በማዋከብ ሲያስጮሁትና ከገበያ ውጭ ሲያደርጉት፣ በተማሪውና በወጣቱ ወገን ስራ በማሳጣት፣ በማስፈራራትና ተስፋ በማስቆረጥ ሲያስጮኹት፣ በወታደራዊው እዝ የተወሰኑ ቡድኖች እንደፈለጉ ሲያዙና ሲያስጮኹት በመምህራኑ ሰፈር ሞራልን በመምታት በሙያውና በመምህራኑ ስብና ሲያላግጡበትና ሲያስጮኹት በሃይማኖቱ ጎራ ጣታቸውን አስገብተው የፈልጉትን ሲሾሙ የፈለጉትን የቤተ እምነት ስፍራ ሲወርሱና ሲያርሱ ሲያቃጥሉ ሲበጠብጡና ሲያስጮኹ የርሳቸው ዛር ከመርካት ይልቅ የጭር ሲል አልወድም ከበሮ እየመታ ያቅራራል፣ አንዱን ወገን በገዛ አገሩ እንዳይኖር ከትዳሩ፣ ከወለደበት፣ ካፈራው ሃብት ተደላድሎ ከሚኖርበት ቦታ በብሄሩ ብቻ ኢትዮጵያዊነቱን በመግፈፍ በአገሩ እንደባይተዋር እያፈናቀሉ ሲያስጮኹት ጡት በሚጠቡ ጨቅላ ህጻናት ጩኸት ሲፍነከነኩና እንደተኮረኮረ ሲፍለቀለቁ ይታያል፣ ዜጋው እንደዜጋ ተው ይህ ነገር ላገርም ለትውልድም አይበጅ ብለው ዚናገሩ የእምዬን ወደአብዬ በመወርወር በየማጎሪያው በመክተት ማስጮህ፡ ጩኸት እዚህ ጩኸት እዚያ ጩኸት ……….ጩኸት
ጎበዝ በድሮው ዘመን ያስቸገረ ዛር ካለ መፍትሄው ቀላል ነው ለነፍሱ ያደረ ና ወደአምላኩ የተጠጋ መንፈሳዊ አባት መፍትሄ ያመጣል፣ የሰውየው ዛር ግን በዚህ መንገድ የሚቻል እይደለም ምክንያቱም ዛሩ ወደሳቸው ሳይሆን የመጣው እርሳቸው ናቸው ዛሩላይ የተፈናጠጡት፣ ሳይንስ ቀመስ ዛር ይላሉ ይህ ነው በፍትሄው በያለበት ቁጭ ብሎ መምከር ሲሆን የተበጣጠቀ ጩኸት ለሳቸው እድሜ ከማርዘም ውጭ የፈጠረው የታየ እንደምታ የለም ስለዚህ እሳቸው ሲያስጮኹን እኛ የጯሂውች ህብረት መመስረት ከተለያየ ጩኸት የጠነከረ አንድጩኸት መፍጠር፣ ጠርዝ ተርዝ የያዝን ሁላችን ጉዳዩ ያገባናል ብለን ከእስራኤላውያን ትምህርት ወስድን አንድ ታላቅ ጩኸት ልክ የኢያሪኮን አጥር \ግንብ\ እንደናደ ያለ የተጠራቀመ ቁጭትና የቁጣ ጩኽት ልንጮህበት ይገባል ያኔ የትውልድ ባለውለታ እንሆናለን ካለበለዛ ግን ነገ ጠዋት የኛንም በር ያንኳኳል ባገር ቤት ያለውን ጩኽት ለመድኩ ደግሞ የውጪው አምሮኛል ሊል ይችላል፣ ሞክሯልም! ስለዚህ ጊዜው አሁን የህብረት ሰአት ነው፡
የጭር ሲል አልውድም የአራት ኪሎው ባላባት ጊዜውን እናሳጥር። በቃ!

አስተያየት፡fzdwoslo@gmail.com


No comments:

Post a Comment