Welcome

"The thing that lies at the foundation of positive change, the way I see it, is service to a fellow human being." - Lech Walesa

Saturday 22 September 2012

የብአዴን አባልነትን ያልተቀበሉ ሰራተኛ “ከተማዋን ለቅቀህ ጥፋ” ተባሉ…………..ከፍኖተ ዘመቻ ነጻነት “እናሸንፋለን” we will win (www)




በአማራ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ጐንደር ዞን ምዕራብ አርማጭሆ ወረዳ የአብርሃጅራ ከተማ አስተዳደርና የፀጥታ ቢሮ ኃላፊዎች ከፍተኛ የሆነ የመብት ጥሰት እየፈፀሙ እንደሆነ የዜና ምንጮቻችን ገለፁ፡፡ ምንጮቻችን እንደሚሉት የቢሮው ኃላፊዎች ራሳቸውን ከህግ በላይ አድርገው ስለሚያስቡ የዜጐችን ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን እንዲሁም ሰዎች በዜግነታቸው ያገኙትን ህገ መንግስታዊ መብቶች ይጥሳሉ፡፡ሲሉ ቅሬታቸውን ያቀርባሉ፡፡

ምንጮቻችን እንደሚሉትኃላፊዎች በማን አለብኝነትና በጀብደኝነት ሰዎችን በአመለካከታቸው ብቻ እንደ ወንጀለኛ በመቁጠር ከህግ አግባብውጭ ከሥራ ያግዳሉ ያዋክባሉ፣ ያመናጭቃሉ  ያንጓጥጣሉ . . .” በማለት ያስረዳሉ፡፡ ለነዚሁ የፀጥታ ቢሮ ኃላፊዎች ሰለባ ሆነዋል የተባሉትን የቢሮውን ሠራተኛ አቶ አንጋው ተገኝ ጠይቀን በሰጡን መልስበእርግጥ ከፍተኛ በደል እየተፈፀመብኝ ነው፡፡ እኔ የአስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ሠራተኛ ነኝ፡፡ ከአንድ ዓመት በፊት የብአዴን አባል እንድሆን ተጠየቅኩ፡፡ እኔ እንደ አንድ የመንግስት ሠራተኛ የሞያ ሥራ ከመሥራት ውጪ አባል መሆን እንደማልፈልግ ነገርኳቸው፡፡ አንተ የተቃዋሚ ደጋፊ ስለሆንክ ቢሮ እንዳትመጣ ከሠራተኛ ጋርም እንዳትገናኝ ደሞዝህን ብቻ መጥተህ እንድትወስድ አሉኝ፡፡ እኔ ደሞዝ መውሰድ ያለብኝ ሥራ ሠርቼ ነው፡፡ ሥራዬን ልሥራ ብላቸው ከለከሉኝ፡፡

ምንም ማድረግ ባለመቻሌ አንድ ዓመት ሙሉ ያለ ሥራ ደሞዝ እየተከፈለኝ ቆየሁ፡፡ ተከታትለው ተከታትለው ምንም ጥፋት ሊያገኙብኝ ባለመቻላቸው አሁን ሰሞኑን ደግሞ ሥራውንም ከተማውንም ለቀህ ሂድ የሚል ትዕዛዝ ደረሰኝ፡፡ የተወለድኩትም ሥራዬም ኑሮዬም እዚሁ ነው፡፡  የት ልሂድ ብላቸው ምንም የምናውቀው ነገር የለም ወደ ፈለክበት ሂድ እያሉኝ ነው፡፡ አቤት የምልበት ቦታ አላገኘሁም፡፡ የዜግነት መብቴም ተገፏል፡፡ እባካችሁ የሚሰማ የመንግስት አካል ካለ ጩኽቴን አሰሙልኝሲሉ መልሰውልናል፡፡

በዋናነት የመብት ጥሰቱን እየፈፀሙ ናቸው የተባሉትን የአካባቢውን የአስተዳደር ፀጥታ ሠራተኛ አቶ /መድህን ወንድም እሸትን በስልክ አግኝተን ስለሚባለው ነገር ብንጠይቃቸውም ዝናብ ስለሆነ አይሰማኝም፡፡ ለማላውቀው ሰው መረጃ ለመስጠት ፍቃደኛ አይደለሁምየሚል መልስ የሰጡን ሲሆን የአስተዳደርና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ናቸው የተባሉትን አቶ ፋሲል ሰንደቁን በተመሳሳይ ሁኔታ በተንቀሳቃሽ ስልካቸው ላይ አግኝተን ላቀረብንላቸው ጥያቄ በሰጡን መልስእኔ አሁን ያለሁበት ቦታ በረሃ ውስጥ ስለሆነ መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ አይደለሁምብለዋል፡፡ ባገኘነው መረጃ መሠረት ግን በረሃ ነኝ ያሉት አቶ ፋሲል በወቅቱ ቢሮአቸው እንደነበሩ መረዳት ችለናል፡፡

No comments:

Post a Comment